3 months ago
በአይራብ ዶኔሽን እና በጃተኒ አሊ ፋውንዴሽን የተዘጋጀው ይፋዊ የዲጂታል ገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ሊካሄድ ነው
📌ተቋማቱ የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ
#ethiopia | በአይራብ ዶኔሽን እና በጃተኒ አሊ ፋውንዴሽን በጋራ የተዘጋጀው ይፋዊ የገቢ ማሰባሰቢያ የመክፈቻ ፕሮግራም በቅርቡ እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን፣ ሁለቱ ተቋማትም አብረው ለመሥራት የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት በይፋ ተፈራርመዋል።
ይህ ልዩ መርሃ-ግብር ደህንነቱ በተጠበቀ፣ ግልጽነት ባለው እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በተደገፉ ዲጂታል የለጋሽነት መፍትሄዎች አማካኝነት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰብአዊ እና ማህበረሰባዊ እገዛዎችን በዘላቂነት ለመደገፍ ያለመ ስትራቴጂካዊ የገቢ ማሰባሰብ አጋርነት መጀመሩን አብስረዋል።
በዕለቱም አይራብ ዶኔሽን የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ለጋሾች በቴሌብር ሱፐር አፕ እና በአይራብ ዶኔሽን ድረ-ገጽ አማካኝነት በቀላሉና በአስተማማኝ ሁኔታ መዋጮ ማድረግ የሚችሉበትን ምቹ ዲጂታል አሰራር በጉልህ የሚያሳይ ይሆናል።
የአይራብ ቴክ ሶሉሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (AYRAB TECH SOLUTION PLC) መስራች አቶ ቢኒያም ፈቃዱ እና የጃተኒ አሊ ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር መሌቻ ሎጄ ህዝቡ እና የሚመለከተው አካል ሁሉ በዚህ ሰብአዊ ስራ ላይ ከጎናቸው እንዲሆንና አጋርነቱን እንዲያጠናክር ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ጃታኒ አሊ ፋውንዴሽን በአርቆ አሳቢው ሻለቃ ጃታኒ አሊ ማስታወሻነት የተመሰረተ ሲሆን፣ ማህበረሰቡ ራሱን እንዲችል፣ ጠንካራ የሆነ ማህበረሰብ እንዲገነባ እና ዘላቂ ልማት እንዲፈጠር በትምህርት፣ በውሃ፣ በጤና እና በማህበረሰብ አቅም ግንባታ ላይ በትጋት እየሰራ ነው።
ዛሬ የፋውንዴሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚና በተለያዩ ሀገር የሃላፊነት ቦታዎች የሚያገለግሉ ብዙ ግለሰቦች ሻለቃ ጃታኒ አሊ በተቋቋመው ትምህርት ቤት የተማሩ ሲሆን፣ ይህም የፋውንዴሽኑ ትውልድ የሚቀይር ራዕይ ህያው ማስረጃ ነው።
የእርስዎ ድጋፍ አንድ ልጅ እንዲማር፣ አንድ ቤተሰብ ተስፋ እንዲያገኝ እና አንድ ማህበረሰብ በራሱ እግር እንዲቆም ያግዛል።
ዛሬ ይቀላቀሉ ፣ ይደግፉ ፣ዘላቂ ለውጥ ይፍጠሩ። ሲሉ ጥሪያቸውንም አስተላልፈዋል።
እንዲሁም: በቴሌብር ሱፐር አፕ ላይ በሚገኘው አይራብ(AYRAB) አፕ ላይ እና በአይራብ ዶኔሽን ( https://donate.ayrabtech.c... ) ሊንክ በመግባት በቀላሉ በሃገር ውስጥም ይሁን ከሃገር ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮዽያ ወዳጆች በቀላሉ የፈለጉትን እና የቻሉትን ያህል መለገስ የሚችሉ መሆኑን አሳውቀዋል።
ይህንን ትልቅ ሰብአዊ እቅድ በይፋ ለመጀመር በሚሰናዳው በዚሁ ደማቅ መርሃ-ግብር ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ በጎ አድራጊዎች፣ የቢዝነስ መሪዎች፣ የሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ ታዋቂ የኢትዮጵያ ስብዕናዎች እና ከተለያዩ ዘርፎች የተወጣጡ ደጋፊዎች እንደሚገኙ ታውቋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ethiopia #ayrabdonation #jatanialifoundation #digitalfundraising #techforgood #humanitarianaid #telebirr #addisababa #socialimpact #ethiopiannews

5 months ago
ዮዳሄ የበጎ አድራጎት ድርጅት የማዕድ ማጋራት መርሐግብር ድጋፍ አደረገ
#ethiopia | ዮዳሄ የበጎ አድራጎት ድርጅት የ1447 ዓመተ ሂጅራ የረመዷን ጾምን በማስመልከት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ለሚገኙ ወገኖች የማዕድ ማጋራት መርሐግብር በዛሬው ዕለት አከናወነ።
በመርሐግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የዮዳሄ የበጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አቶ ታፈሰ አመንሲሳ እንደገለጹት፤ ድርጅቱ ከተመሠረተ ጥቂት ወራትን ያስቆጠረ ቢሆንም፣ የቆመለትን ዓላማ ለማሳካት ሰፊ ጥረት እያደረገ ይገኛል።
ድርጅቱ ሥራውን ለማከናወን የውጭ ፈንዶችን ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም፣ የታሰበው ድጋፍ ባልተገኘበት ወቅት "ዮዳሄ እጃችን ለድጋፍ፣ ልባችን ለፍቅር " በሚል መሪ ቃል መንፈስ አባላቱን በማስተባበር በወረዳው ለሚገኙ ወገኖች የረመዳንን ጾም በማስመልከት የማዕድ መርሐግብር ማከናወኑን ገልጸዋል።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደህንነት ገብሩ በበኩላቸው፣ ድርጅቱ በዚህ ፈታኝ ወቅት ያሳየው የተራድኦ ተግባር የሚመሰገን መሆኑን ገልጸው፤ መሰል የበጎ አድራጎት ሥራዎች የሕዝቡን የአንድነትና የመረዳዳት እሴት እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ለዝግጅቱ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱ የድርጅቱ አባላት፣ የወረዳው አመራሮችና በጎ ፈቃደኞች ምስጋና ቀርቧል።

በዕለቱ የማዕድ ማጋራት መርሐግብር ላይ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደህንነት ገብሩ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የዮዳሄ የበጎ አድራጎት ድርጅት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1113/2011፣ በምዝገባ ቁጥር 7460 ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ መንቀሳቀስ መጀመሩ ይታወቃል።
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን
#yodahecharity #ramadankareem #iftarsharing #ethiopia #socialimpact #communityservice #charityevent #kirkossubcity #selfreliance

Comments