Logo
Getu Temesgen
በሃዘን ለተጎዱ ቤተሰቦች እንድረስላቸው! 💔🙏

"ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ" (ሮሜ 12:15)
#ethiopia | በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ አካባቢ በሚገኘው የኮየ ፈንታ ደብረ ፀሐይ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን በበዓለ ጥምቀት ዕለት በአሳዛኝ የኤሌክትሪክ አደጋ አራት ወጣት አስተባባሪዎችን ማጣታችን ይታወሳል።

እነዚህ ወጣቶች በበዓሉ ድምቀት ሰረገላ በማዘጋጀት እና በማጓጓዝ ላይ እንዳሉ በኤሌክትሪክ ንኪኪ በተከሰተ አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ማህበረሰቡን በእጅጉ አሳዝኗል።

ይህ ክስተት የወጣቶቹን ቤተሰቦች ለከፍተኛ ችግር ዳርጓቸዋል። በተለይም፦

ከሟቾች መካከል የአቶ አበበ ተፈራ ባለቤት የ9 ወር ነፍሰ ጡር መሆናቸውና ልጆቻቸውም አሁን ካሉበት ቤት በኪራይ ምክንያት እንዲወጡ መደረጋቸው፤

የሟች አቶ ፍቃዱ ተክለየስ ቤተሰቦች የሚመገቡት የሌላቸው 5 ቤተሰቦች በችግር ላይ መውደቃቸው፤

ሌላኛው ሟች አቶ ሄሮጳ ማሞ የቤተሰቡ አስተዳዳሪና ብቸኛ ደጋፊ በመሆኑ ቤተሰቡ በከፍተኛ ሃዘንና ችግር ውስጥ መገኘቱ ሁኔታውን ይበልጥ አሳዛኝ ያደርገዋል።

ስለሆነም እነዚህን የተቸገሩ ቤተሰቦች ለመርዳት ከጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 27 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል።

ለተጎጂ ቤተሰቦች ተብሎ በተከፈተው የጋራ የባንክ አካውንት ድጋፍዎን ማድረግ ይችላሉ፦
💰 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000742754247
💰 አቢሲኒያ ባንክ፦ 249319147

የፊታችን ማክሰኞ የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በሚደረገው የቀጥታ ስርጭት ላይ በመሳተፍና ይህን መልዕክት ለሌሎች በማጋራት የድርሻዎን እንዲወጡ በትህትና እንጠይቃለን።

ፈጣሪ ለሟቾች መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ይስጥልን!
#emergencyappeal #charityethiopia #supportfamilies #humanitarianaid #eotc #communitysupport #ethiopiahelp

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.