የልብ ሕሙማን ሕፃናት ተስፋ
170 ሕፃናት በ45 ቀናት ውስጥ ነፃ ሕክምና ሊያገኙ ነው
#ethiopia | በኢትዮጵያ በልብ ሕመም ሳቢያ በሕክምና ወረፋ ላይ ላሉና ለከፋ ችግር ለተጋለጡ ሕፃናት ትልቅ የምስራች ተሰምቷል።
የኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ (Heart to Heart Children's Aid) ፋውንዴሽን "በኢትዮጵያውያን የልብ ሐኪሞች - ለኢትዮጵያውያን ሕጻናት ልብ ጤና!!" በሚል መሪ ቃል፣ 170 ሕፃናትን በ45 ቀናት ውስጥ ለማከም የሚያስችል ታሪካዊ ስምምነት መጋቢት 20/2018 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል ፈጽሟል።
የስምምነቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
ሕክምናው ከሚያዝያ 12/2018 (April 20) ጀምሮ ባሉት 45 ቀናት ውስጥ ተጠናቆ ለሕፃናቱ ይደርሳል።
በስምምነቱ ላይ የጤና ሚኒስቴር፣ የጥቁር አንበሳና የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታሎች፣ የኢትዮ ኢስታንቡል፣ ጣዝማና ኤሊዘር የልብ ሕክምና ማዕከላት እንዲሁም የዘርፉ ማህበራት በጋራ ለመሥራት ቃል ገብተዋል።
አቶ ብርሃን ተድላ (የፋውንዴሽኑ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ) እንደገለጹት፣ ፋውንዴሽኑ አስፈላጊውን የሕክምና ግብዓትና ወጪ በመሸፈን ተልዕኮውን ይመራል።
ከጣልያን አገር የሚመጣ የሕክምና ቡድንም የዚሁ ጥረት አካል ሲሆን፣ ለ50 ሕፃናት ሕክምና ይሰጣል።
ይህ ትብብር በሕክምና ወረፋ ብዛት ሕይወታቸው የሚያልፍ ሕፃናትን ለመታደግ ከመጣጣሩም በላይ፣ የሀገር ውስጥ የሕክምና ባለሙያዎችና ተቋማት ተቀናጅተው ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ በተግባር ያሳየ ነው።
#getu #hearttoheart #childrenshealth #cardiacsurgery #ethiopiahealth #humanitarianaid #ethioistanbulhospital #ministryofhealth #savinglives #addisababa #የልብሕክምና #ሕፃናት #በጎአድራጎት #ጤና #ጌጡተመስገን #getutemesgen

6 months ago