Logo
Getu Temesgen
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በጋሞ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለጹ
#ethiopia | የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ማዞ ዶይሳ ቀበሌ በደረሰው ድንገተኛ የመሬት ናዳ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖችና ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን በመግለጽ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን ተመኝተዋል።

በአካባቢው የተከሰተው ይህ አደጋ በርካታ ቤተሰቦችን ለሃዘንና ለችግር የዳረገ ሲሆን፣ ድርጅቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ሰብአዊ ድጋፍ ለማቅረብ ቁርጠኝነቱን አረጋግጧል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #gamozone #landslide #who #drtedrosጸAdhanom #ethiopia #gachobaba #emergencyresponse #staysafe #humanitarianaid

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.