Logo
Getu Temesgen
"አቅማችን ተሟጧል!"
— ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አስቸኳይ ጥሪ አቀረበች
#ethiopia | ​ኢትዮጵያ ወደ አገሪቱ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ፣ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለማቅረብ የመንግስት አቅም እየተሟጠጠ መሆኑን በይፋ አስታወቀች።

​በተለይ በትምህርትና በጤና ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶች በስደተኞች ቁጥር መጨመር ምክንያት ከፍተኛ ጫና ወድቆባቸዋል።

በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ጸጋዓብ ክበበው በተመድ ስደተኞች ኮሚሽን ስብሰባ ላይ የሀገሪቱን ስጋት በዝርዝር አቅርበዋል።

​ ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ዘላቂ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግ እና ስደተኞች በሚገኙባቸው አካባቢዎች በኢንቨስትመንት እንዲሳተፍ ተጠይቋል።

​ከገንዘብ ድጋፍ ባለፈ፣ ለስደቱ መሠረት የሆኑ ችግሮችን በመፍታት ረገድ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ አምባሳደሩ አሳስበዋል።
#ethiopia #refugees #humanitarianaid #unhcr #geneva #addisadmas #breakingnews #globalcall #ኢትዮጵያ #ስደተኞች

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.