6 months ago
በታዝማ ልዩ የሕክምና ማዕከል ሌላኛው አስደናቂ ስኬት!
በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተከናወነ እጅግ ውስብስብ የቤንታል (Bentall) የልብ ቀዶ ሕክምና!
በሀገራችን እጅግ ውስብስብና የመጀመሪያ የተባሉ የልብ ቀዶ ሕክምናዎችን በማከናወን ግንባር ቀደም የሆነው ታዝማ የውስጥ ደዌ እና የቀዶ ህክምና ልዩ ማዕከል፤ ዛሬም እንደተለመደው በስኬት የታጀበ የምስራች ይዞላችሁ ቀርቧል።
የህክምናው ሂደት በአጭሩ
የ50 ዓመት ጎልማሳ የሆኑት ታካሚው፦
* የልብ ደም ወሳጅ ቧንቧ እብጠት (Aortic Aneurysm) እና
* የደም ቧንቧ መሰንጠቅ (Type A Aortic Dissection) አጋጥሟቸው ለሕይወት አስጊ በሆነ ደረጃ ላይ ነበሩ።
በታዋቂው የልብ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ብርሃኑ ኃይለማርያም በሚመራው የሕክምና ቡድናችን በተደረገ ከፍተኛ ርብርብ፤ እጅግ ውስብስብ የሆነው የቤንታል (Bentall) ቀዶ ሕክምና በጥንቃቄ ተከናውኖ የታካሚውን ሕይወት መታደግ ተችሏል።
በአሁኑ ወቅት ታካሚው ሙሉ በሙሉ አገግመው በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ።
የልብ ህክምና ፍለጋ ወደ ውጭ ሀገር መሄድ የቀረበት ዘመን!
ይህ ስኬት በራሳችን ልጆች፣ በኢትዮጵያውያን ሐኪሞች በአገር ውስጥ መከናወኑ፤ ማዕከላችን ለኢትዮጵያውያን ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሕያው ምስክር ነው።
ታዝማ - የጤናማ ልብ አርማ! 💙
#tazmamedicalcenter #heartsurgery #bentallprocedure #ethiopiandoctors #healthcareethiopia #savinglives

የልብ ሕሙማን ሕፃናት ተስፋ
170 ሕፃናት በ45 ቀናት ውስጥ ነፃ ሕክምና ሊያገኙ ነው
#ethiopia | በኢትዮጵያ በልብ ሕመም ሳቢያ በሕክምና ወረፋ ላይ ላሉና ለከፋ ችግር ለተጋለጡ ሕፃናት ትልቅ የምስራች ተሰምቷል።
የኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ (Heart to Heart Children's Aid) ፋውንዴሽን "በኢትዮጵያውያን የልብ ሐኪሞች - ለኢትዮጵያውያን ሕጻናት ልብ ጤና!!" በሚል መሪ ቃል፣ 170 ሕፃናትን በ45 ቀናት ውስጥ ለማከም የሚያስችል ታሪካዊ ስምምነት መጋቢት 20/2018 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል ፈጽሟል።
የስምምነቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
ሕክምናው ከሚያዝያ 12/2018 (April 20) ጀምሮ ባሉት 45 ቀናት ውስጥ ተጠናቆ ለሕፃናቱ ይደርሳል።
በስምምነቱ ላይ የጤና ሚኒስቴር፣ የጥቁር አንበሳና የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታሎች፣ የኢትዮ ኢስታንቡል፣ ጣዝማና ኤሊዘር የልብ ሕክምና ማዕከላት እንዲሁም የዘርፉ ማህበራት በጋራ ለመሥራት ቃል ገብተዋል።
አቶ ብርሃን ተድላ (የፋውንዴሽኑ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ) እንደገለጹት፣ ፋውንዴሽኑ አስፈላጊውን የሕክምና ግብዓትና ወጪ በመሸፈን ተልዕኮውን ይመራል።
ከጣልያን አገር የሚመጣ የሕክምና ቡድንም የዚሁ ጥረት አካል ሲሆን፣ ለ50 ሕፃናት ሕክምና ይሰጣል።
ይህ ትብብር በሕክምና ወረፋ ብዛት ሕይወታቸው የሚያልፍ ሕፃናትን ለመታደግ ከመጣጣሩም በላይ፣ የሀገር ውስጥ የሕክምና ባለሙያዎችና ተቋማት ተቀናጅተው ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ በተግባር ያሳየ ነው።
#getu #hearttoheart #childrenshealth #cardiacsurgery #ethiopiahealth #humanitarianaid #ethioistanbulhospital #ministryofhealth #savinglives #addisababa #የልብሕክምና #ሕፃናት #በጎአድራጎት #ጤና #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments