ታሳ ታሳ ጋሞ
የሲሲአርዲኤ (CCRDA) አመታዊ ጉባኤ ተካሄደ
* ጋሞ በመሬት መንሸራተት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጽሎት ተደርጎ ጉባኤው ተከፍቷልዠ
#ethiopia | የሲሲአርዲኤ (CCRDA) አባላት አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን አካሂደዋል።
በጉባኤው ላይ የድርጅቱ የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ አቶ መላኩ ስብሀት እንደገለጹት፤ ስብሰባው ያለፈውን አመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለመገምገም እና ለማጽደቅ ያለመ ነው። ከዚህ ባለፈም በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶች ላይ ውይይት ተደርጓል።
በዋና ዋና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ያለው ተሳትፎ የሲቪክ ማህበራት በሃገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑ በጉባኤው ተመላክቷል።
በተለይም በሃገራዊ ምክክር ሂደት ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንዲሁም በምርጫ ወቅት መራጮችን በማስተማር ገለልተኛ ሚና ለመወጣት ይተጋል ተብሏል።
ሰብአዊ ድጋፍ እና ልማት🔎
ማህበራቱ በተጠናቀቀው አመት በበርካታ የልማት ስራዎች ላይ የተሳተፉ ሲሆን፣ በተለይም ከግጭት ጋር ተያይዞ ለተፈናቀሉ ወገኖች አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ በማቅረብ ረገድ ከፍተኛ ስራ ሰርተዋል። በጤና፣ በትምህርት እና በመልካም አስተዳደር ረገድም ማህበረሰብ ተኮር ስራዎች መከናወናቸው ተገልጿል።
የጋሞ አደጋ እና ቀጣይ እቅዶች🔎
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ – የሲቪል ማህበረሰብ አስተባባሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማሞ ሞሊሶ በጋሞ ዞን ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ጋጮባባ፣ ከምባ ዙሪያ ወረዳ፣ አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ አርባምንጭ ከተማ፣ ቦንኬ ወረዳ፣ ጨንቻ፣ ገረሴ ዙሪያ እና ገረሴ ከተማ በጎርፍ፣ በናዳ እና አውሎ ንፋስ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰብአዊ እና የንብረት ጉዳት ማድረሱን አብራርተዋል፡፡
አደጋው ጋጮባባ ፣ ከምባ ዙሪያ ወረዳ ፣ አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፣አርባምንጭ ከተማ ፣ ቦንኬ ወረዳ ፣ጨንቻ ፣ ገረሴ ዙሪያ ምእራብ አባያ እና ገረሴ ከተማ ላይ የደረሰ ሲሆን የጉዳቱ መንስኤም በጎርፍ ፣ በናዳ እና አውሎ ንፋስ ሰፊ ሞትና የንብረት ጉዳት ደርሷል ፡፡
በዚህም በአደጋ አባወራ 2644 እማወራ 376 በድምሩ 302ዐ እና ወንድ 8261 ሴት 10310 በድምሩ 18571 ቤተሰብ አባላት ተፈናቅለዋል፡፡
አደጋው በደረሰባቸው ወረዳዎች በተከሰተው አደጋ 1271 ሄር በላይ የሙዝ ፣ የሰብል ጉዳት ደርሷል ፤ 1100 የመኖሪያ ቤቶች የወደሙ ሲሆን በተያያዘም በአርባ ምንጭ ከተማ የኩልፎ ወንዝ በመሙላት ተፈጥሮአዊ አቅጣጫውን ለቆ በመሄድ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ 31 በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ ማህበራት፣ 2 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችና 1 የግብረ ሰናይ ድርጅት ንብረት ወድሟል አቶ ማሞ አስረድተዋል።
አያይዘውም በዞኑ አደጋ በደረሰባቸው ወረዳዎች ከ 125 በላይ ከፍተኛ ሞት የተመዘገበበት ነው፡፡ በዚህም 81 አስክሬን በቁፋሮ ተገኝቶ በክብር እንዲያርፉ መደረጉን አስታውቀዋል።
የሲሲአርዲኤ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ንጉሱ ለገሰ በጋሞ አካባቢ በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ሲሲአርዲኤ (CCRDA) አባላቱን በማስተባበር እና ድጋፎችን በማሰባሰብ በኩል ኃላፊነት ወስዶ እየሠራ መሆኑን አውስተዋል።
የክርስትያን በጎ አድራጎት እና ልማት ማህበራት ኅብረት (CCRDA) ከ500 በላይ አገር በቀልና ዓለም አቀፍ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን አባል ይዟል።
ሲሲአርዲኤ(𝐂𝐂𝐑𝐃𝐀)
LinkedIn: www.linkedin.com/in/ccrda-...
Telegram: https://t.me/ccrda_et
Twitter: https://x.com/CCRDA454972
Website: https://ccrdaeth.org/
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ccrda #civilsociety #ethiopia #humanitarianaid #nationaldialogue #development #civicengagement #etbusinessview

7 months ago