10 hours ago
በጡረታ የተገለሉት አመራር ከፍተኛ ስልጣን ተሰጣቸው
*የቀድሞ የባህር ሀይሏ አመራሯ ጥቁር አሜሪካዊት ቁልፉን ተቋም ለመመራት ተሹመዋል።
#ethiopia |የአሜሪካ ሴኔት ባደረገው ምርጫ የቀድሞ የባህር ኃይል አባሏ
ዶ/ር ኤሪካ ሸዋርትዝ የአሜሪካ የበሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አድርጎ መረጠ።
ይህ ሹመት ተቋሙ ላለፈው አንድ አመት ገደማ ያህል ያለ ቋሚ መሪ በጊዜያዊ አመራር ሲመራ ከቆየ በኋላ የተሰጠ ትልቁ ሹመት ነው ተብሏል።
የቀድሞ የባህር ሀይል አባል ዶክተር ኤሪካ በታሪክ ሲ.ዲ.ሲን በመሪነት የሚያገለግሉ የመጀመርያዋ ጥቁር አሜሪካዊት ሴት አድርጓቸዋል።
ዶክተር ኤሪካ በጡረታ የተገለሉ የባህር ኃይል አመራር የነበሩ ሲሆን ቀደም ሲል የአሜሪካ የባህር ሀይል የጤና ስርዓትን በበላይነት የመሩ ብቁ የህክምና እና የአመራር ባለሙያ መሆናቸው ታውቋል።
ላለፉት 12 ወራት ያህል ቋሚ ዳይሬክተር ሳይኖረው የቆየው ሲዲሲ ለተደቀኑበት ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የጤና ስጋቶች አዲስ እና ጠንካራ አመራር ለማግኘት ያደረገው ጥረት በመጨረሻም ውጤት አምጥቶለታል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #usa #cdc #uscoastguard #drericaschwartz

3 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ የራስ ገዝነት መብቱን ለመተግበር ባደረገው የመዋቅር ማስተካከያ ምክንያት ከ500 በላይ አስተዳደራዊ ሰራተኞች እና 50 መምህራን ያለመደብ መቅረታቸውን ኤስቢኤስ ራድዮ ከአውስትራሊያ ዘግበ። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ማንም ሰራተኛ እንዳልተባረረ ገልጸው፤ የተጎዱት በጡረታ፣ በካሳ ወይም በቅርቡ በሚጀመረው የንግድ እንቅስቃሴ እንደሚካተቱ ተናግረዋል።
ፎርቹን ጋዜጣ እንደዘገበው ደግሞ ምደባው ለአስተዳደር ሰራተኞች በፈተና፣ ለመምህራን ደግሞ በትምህርት ዝግጅት አግባብነት ላይ ተመስርቶ እየተከናወነ ነው። በሀገሪቱ ከሚገኙ 46 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የመጀመሪያው ሞዴል የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሪፎርም እርምጃ፣ ቀጣይ ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ ለሚዘጋጁት እንደ ጅማ፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ መቀሌ እና መሰል ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች ማሳያ ይሆናል ተብሏል።

4 days ago
AAU ከ500 በላይ ሰራተኞቹን አሰናበተ‼️
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ የራስ-ገዝነት መብቱን ለመተግበር ባደረገው የመዋቅር ማስተካከያ ምክንያት ከ500 በላይ አስተዳደራዊ ሰራተኞች እና 50 መምህራን ያለ ምደባ ቀርተዋል።
ይሁን እንጂ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ማንም ሰራተኛ እንዳልተባረረ ገልጸው፣ የተጎዱት በጡረታ፣ በካሳ ወይም በቅርቡ በሚጀመሩ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንደሚካተቱ አረጋግጠዋል።
ምደባው ለአስተዳደር ሰራተኞች በፈተና፣ ለመምህራን ደግሞ በትምህርት ዝግጅት አግባብነት ላይ ተመስርቶ የተከናወነ ነው።
በሀገሪቱ ከሚገኙ 46 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የመጀመሪያው ሞዴል የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሪፎርም እርምጃ፣ ቀጣይ ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ ለሚዘጋጁት እንደ ጂማ፣ መቐለ፣ ባህር ዳር እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲዎች ትልቅ ማሳያ እንደሚሆን ተገልጿል።
Seledadotio

12 days ago
በህይወት እያሉ ተመሰገኑ
(በዕዝራ እጅጉ)
.የመዲናዋ ጤና ቢሮ ነፃ ህክምና እንዲያገኙ ወሰነ
#ethiopia | አንጋፋ የሚድያ ባለሙያዎች አዲስ አለም ሓድጉና በልሁ ተረፈ ዛሬ ጋቢ በተደረበላቸው ዕለት ደስታቸውን መቆጣጠር ተስኗቸው ነበር።
በኢትዮጵያ የሚድያ ታሪክ የማይረሳ አሻራ ያኖሩት እነዚህ ጉምቱ ባለሙያዎች ከ 35 አመት በላይ በትጋት ያገለገሉ ሲሆን በሙያ አጋሮቻቸው ተከበው አድናቆት ሲቸራቸው ውለዋል።
ቅዳሜ ሐምሌ 18 2018 ዓ.ም ከ 4 ሰዓት ጀምሮ በወመዘክር መርስኤሀዘን አዳራሽ በተደረገው መርሀ ግብር የሚድያ ባለሙያዎች እና ወዳጆቻቸው ተገኝተው እኛም አመስጋኞቻችሁ ነን በማለት ለመርሀ ግብሩ ድምቀት ሰጥተዋል።
ባለሙያዎቹን ለማመስገን ራሱን የቻለ ኮሚቴ የተዋቀረ ሲሆን ይህም ኮሚቴ ባለሙያዎቹ በዘለቄታዊነት የሚታገዙበት መንገድ ያመቻቸ ነው።
ለዝግጅቱ መሳካት በተከፈተው የwhat is up ገፅ ኮሚቴው ውስጥ ተግባራቸውን የተወጡት ጥላሁን ካሣ ፣ሀብታሙ ድረስ ፣ሰለሞን ሀይለኢየሱስ፣ዕዝራ እጅጉ (ተወዳጅ ሚድያ)፣ አለም ታደሰ፣ሠናይት ሀይሌ፣እሸቱ ገለቱ፣ ጌጡ ተመስገን እና ግደይ ገብረ ሲሆኑ እነርሱም በዕለቱ እንደተናገሩት ሥራው በአጭር ጊዜ ታስቦ ለስኬት መብቃቱ ደስ ያሰኛቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ለአንጋፋ ባለሙያዎቹ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ነፃ ህክምና የሚያገኙበት መንገድ ያመቻቸ ሲሆን ይህ የመረዳዳት ባህል ወደፊትም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተነግሯል።
አዲስ አለም ሓድጉ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በትግርኛ ክፍል በኤዲተርነት እና በጋዜጠኝነት የሠራ ሲሆን ላለፉት 35 አመታትም ሙያውን ወዶና አክብሮ በመሥራት ይታወቃል።
የሚድያ ሰው በልሁ ተረፈ ደግሞ በኢትዮጵያ ሬድዮ ከሳይንስ ማህደር፣ ማንነት ሲፈተሽ እና ዝክረ ሰንበት በተባሉ ፕሮግራሞች ከ30 አመት በላይ የሠራ ሲሆን ሌሎችንም በማብቃት የማይዘነጋ አሻራ ለማኖር የቻለ ነው።
"ሰውን በሕይወት ሳለ እናመስግን "የሚል መርህ ያነገበው ይህ መሰናዶ የሚድያ ባለሙያዎችን በኑሯቸው የማገዝ ፣ በችግራቸው ጊዜ አብሯቸው የመሆን ግብ የሰነቀ ነው። እንዲህ አይነቱ ተግባር ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።
ሁለቱም ባለሙያዎች አገር የጣለችባቸውን አደራ የተወጡ ብርቱ ባለሙያዎች እንደነበሩ በዕለቱ ምስክርነት የሰጡ ባልደረቦቻቸው የተናገሩ ሲሆን የምስጋና ቀን መዘጋጀቱ አዲስ የሚመጣውንም ባለሙያ የሚያበረታታ ነው ሲሉ ሀሣብ ሰንዝረዋል።
በዕለቱ የሚድያ ሥራን ከ1950ዎቹ ጀምሮ ያስቃኘ አጭር የትዝታ ዘጋቢ ፊልም የቀረበ ሲሆን ተመስጋኞቹ ከዚህ ቀደም አየር ላይ ያዋሏቸው ሥራዎችም በዕለቱ ለታደሙት እንግዶች ቀርበዋል።
በባልደረቦቻቸው የምስጋና ዝግጅት የተደረገላቸው አዲስአለም ሓድጉና በልሁ ተረፈ እንደዛሬ ደስ ብሎንም አያውቅ ፣ ይህን መርሀ ግብር በተሳካ መንገድ ዕውን እንዲሆን የጣራችሁ ሁሉ ፈጣሪ መንገዳችሁን ያቃና ሲሉ መርቀዋል።
የአዘጋጅ ኮሚቴው አባል እሸቱ ገለቱ እንዳለው በኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን የሚሠሩ ባልደረቦች የመጠያየቅ ባህልን ከጀመሩ ሁለት አመት እንደሆናቸው ጠቅሰው ይህ የምስጋና መርሀ ግብር የዚያ መጠያየቅ አካል እንደሆነ ጠቁሟል።
ባለሙያዎች ጡረታ ሲወጡ የሚደገፉበት፣ በተለይም በኢኮኖሚ እገዛ የሚያገኙበት ስልት መነደፍ እንዳለበትም ጋዜጠኛ እሸቱ ጥቆማ ሰጥቷል። በተጨማሪም የጤና ሁኔታቸውን፣ የሚከታተሉበት መንገድ መፈጠር እንዳለበትም ተናግሯል።
ከጡረታ በኃላ ምክር በመስጠት ባለሙያዎቹ ልምዳቸውን ማጋራት አለባቸውም ብሏል።ይህንኑ ትልቅ ርዕይ ለማሳካት መንግሥትና የሚመለከታቸው የሚድያ ማህበራት ሊተባበሩ ይገባልም ሲል ሀሣብ አንስቷል።
የእለቱን የምስጋና መሰናዶ እንዲሳካ አቶ ሠርፀፍሬ ስብሓት አዳራሽ በመስጠት ፣ ጋዜጠኛ ማህደረ ታሪኩ ፕሮጀክተር በመለገስ እንዲሁም አልፋ ውሃ፣ ለታዳሚዎች የመስተንግዶ ውሃ በማቅረብ መርሀ ግብሩ የተሳካ እንዲሆን አድርገዋል።

16 days ago
ዕንባ ጠባቂ ተቋም ከቀረቡለት አቤቱታዎች መካከል 84% የሚሆኑት በመንግስታዊ ተቋማት ላይ የቀረቡ እንደሆኑ ገለጸ
የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በተጠናቀቀው የ2018 በጅት ዓመት ከቀረቡለት አቤቱታዎች መካከል 84 በመቶዎቹ በመንግስት ተቋማት ላይ የቀረቡ እንደሆኑ አስታውቋል።
የተቋሙ ዋና ዕንባ ጠባቂ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 1ሺህ 867 አቤቱታዎች በ45 ሺህ 189 ሰዎች ቀርበዋል።
ከእነዚህ አቤቱታዎች መካከል 1ሺህ 571 ወይም 84.5 በመቶ የሚሆኑት በመንግስት ተቋማት ላይ የተመሩ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ 296 አቤቱታዎች በግል ድርጅቶች ላይ የቀረቡ መሆናቸው ተገልጿል።
አቤቱታዎቹ በስራ፣ በጡረታ፣ በይዞታ እና በካሳ ጥያቄዎች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ምሆናቸውንም የተቋሙ ዋና እምባ ጠባቂ አስረድተዋል።
ተቋሙ አቤቱታዎችን መሰረት በማድረግ ምርመራዎች የሚያካሂደው ተቋሙ፤ እስከ አሁን ከ2017 በጀት ዓመት የዞሩ 282 መዝገቦችን ጨምሮ በ1ሺህ 104 መዝገቦች ላይ ምርመራ አከናውኗል።
በዚህም 72 አቤቱታዎች መፍትሄ ማግኘታቸውን፣ በደል መፈጸሙ ተረጋግጦ በድርድር 178 መዝገቦች መፍትሄ ማግኘታቸውን እንዲሁም ለ184 መዝገቦች የመፍትሔ ሃሳብ መሰጠቱን ወይዘሮ ስመኝ ተናግረዋል።
ተቋሙ ልዩ ትኩረት የሚሹ የማኅበረሰብ ክፍሎችን እና የአስተዳደር በደልን መከላከልን በተመለከተ ቁጥጥር እያደረገ ሲሆን፤ በሂደቱም ለሚመለከታቸው አካላት ምክረ-ሃሳብ መስጠቱን ዋና ዕንባ ጠባቂዋ ገልጸዋል።
በተጨማሪም፤ በቀጣይ አስተዳደራዊ በደልን አስመልክቶ በተካሄደ ጥናት ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።
#አሐዱ

24 days ago
የ69 ዓመታቸው አዛውንት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን ገብተዋል።
በትምህርት ዓለም ውስጥ ዕድሜ ገደብ እንደሌለው በተግባር ያሳዩት የ69 ዓመቱ አዛውንት አባባ ወልደየስ አያና አሻቦ ዘንድሮ በሚሰጠው 4ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ላይ በመቀመጥ አዲስ ታሪክ አስመዝግበዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ልዩ ስሟ ዳንጋራ ሳላጣ በተባለች ቀበሌ ተወልደው ያደጉት አባባ ወልደየስ፣ ቀደም ሲል ማህበረሰባቸውን በቀበሌ አስተዳዳሪነት ከስድስት ዓመታት በላይ በታማኝነት ያገለገሉ የሀገር ሽማግሌ ናቸው።
በደርግ ዘመን በትውልድ አካባቢያቸው እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ ተምረው ቢያጠናቅቁም፣ በወቅቱ በነበረው የትምህርት አደረጃጀት፣ የአገዛዝ ሥርዓትና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአቅራቢያቸው አለመኖር ምክንያት ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደው ነበር።
ይሁን እንጂ ለትምህርት ያላቸው ፍቅርና ቁጭት ሳይቀንስ ከረጅም ዓመታት ቆይታ በኋላ በ2015 ዓ.ም ወደ ገበታ በመመለስ ከ9ኛ ክፍል ጀምረው በመማር ዛሬ ለዚህ ትልቅ ሀገር አቀፍ ፈተና ለመብቃት ችለዋል።
አባባ ወልደየስ የ6 ልጆች አባት ሲሆኑ፣ የቤተሰብ ኃላፊነትንና የማህበረሰብ አገልግሎትን ከትምህርት ጉዟቸው ጋር ጎን ለጎን አስማምተው ማስኬዳቸው ልዩ ያደርጋቸዋል።
ይበልጡኑ ደግሞ ከገዛ ልጆቻቸው ጋር በአንድ የመማሪያ ክፍል ውስጥ ተቀምጠው መማራቸውና ለፈተናውም በጋራ መዘጋጀታቸው ልዩ ደስታ እንደፈጠረላቸው ይናገራሉ።
እኩዮቻቸው ወደ ጡረታ በሚገቡበት ዕድሜ መጽሐፍ አንግበው ወደ ትምህርት ቤት የተመላለሱበት ዋና ዓላማ በመንግሥት ተቀጥሮ ለመሥራት ሳይሆን፣ አሁን የሚሰሩትን የግብርና ሥራ በዘመናዊ መንገድ ለማሻሻልና በተሻለ ሁኔታ ለማምረት የሚያስችላቸውን ሳይንሳዊ ዕውቀት ለማግኘት እንደሆነ ያስረዳሉ።
ይህ አስደናቂ ታሪክ “የተማረ ሰው የሥራ ዕድል ፈጣሪ እንጂ ተቀጣሪ ብቻ መሆን የለበትም” የሚለውን ዘመናዊ ትርክት በተግባር የሚያሳይ ነው።
በትጋትና በጽናት ከተጓዙ ዕድሜ ለማንኛውም ስኬት እንቅፋት ሊሆን እንደማይችል ለሚያነበውና ለወጣቱ ትውልድ ትልቅ መነሳሻ እንደሚሆን ይታመናል።
የዩኒቨርሲቲው ህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኝነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት እንዲሁም መላው የፈተና አስተባባሪ ግብረ-ሃይል ለአባባ ወልደየስ መልካም ምኞቱን እየገለጸ፣ ይህ ፈተና የረጅም ጊዜ ራዕያቸውን የሚያሳኩበት እንዲሆን ተመኝቷል።
Via ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ

25 days ago
ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሐምሌ 7/1940 ዓ.ም በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጨለንቆ አቅራቢያ በምትገኝ ፈንዲዴ በተባለች መንደር ተወለዱ።
እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በትውልድ መንደራቸው ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን በሐረር በሚገኘው የላዛሪስት አባቶች የዘርዐ ክህነት ትምህርት ቤት በመግባት መንፈሳዊ ጥሪያቸውን ጀመሩ።
ከዚያም በአዲስ አበባ በሚገኘው የካፑቺን ፍራንቸስካውያን የፍልስፍናና ቲዎሎጂ ኮሌጅ ከፍተኛ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።
ብፁዕ ካርዲናል ወደ እንግሊዝ ሀገር በማምራት በለንደን ዩኒቨርሲቲ በሶሺዎሎጂ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
እ.አ.አ ሰኔ 1976 ምስጢረ ክህነትን የተቀበሉ ሲሆን
የማኅበረ ልዑካን አባቶች ላዛሪስት ገዳም ያፈራቸው ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ጥር 17/1990 ዓ.ም ጵጵስናን ፤ የካቲት 7/2007 ዓ.ም በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አማካኝነት የካርዲናልነት ማዕረግን ያገኙ ሲሆን በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ታሪክ ከብፁዕ ጳውሎስ አድዋ ቀጥሎ ካርዲናል የሆኑ ሁለተኛው ጳጳስ ናቸው።
ብፁዕ ካርዲናል በኢትዮጵያ በሰላም ሚኒስቴር ስር ተቋቁሞ የነበረው የብሔራዊ እርቅና ሰላም ኮሚሽን ውስጥ በሊቀመንበርነት አገልግለዋል።
ብፁዕነታቸው ለቅድስት መንበር ባቀረቡት የጡረታ ጥያቄ መሰረት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ ጥያቄያቸውን መቀበላቸውን በቅድስት መንበር ልዪ መልዕክተኛ ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ ጉጀሮቲ አማካይነት ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ተደርጓል።
ለብፁዕ አባታችን እንኳን ለ50ኛ ዓመት የክህነት በዓልዎ በሰላም አደረስዎት።

26 days ago
የፓኪስታን አየር መንገድ አቶ ተወልደ ገብረማርያምን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ለመሾም ማጨቱ ተሰማ
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዘርፍ ያፈራቸው አንጋፋ መሪዎች በዓለም አቀፍ እና በአህጉራዊ መድረኮች ላይ ያላቸው ተፈላጊነት እና ተፅዕኖ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየጎላ መጥቷል። ከቀናት በፊት የወጡ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት፣ የፓኪስታን ብሔራዊ አየር መንገድን ወደ ግል ይዞታነት ያዛወረው አዲሱ ጥምረት የቀድሞውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያምን አየር መንገዱን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንዲመሩለት በእጩነት መርጧቸዋል።
በጉዳዩ ላይ ቅርበት ያላቸውን ምንጮች ጠቅሶ ብሉምበርግ እንደዘገበው፣ በኪሳራ ውስጥ የቆየውንና በቅርቡ ወደ ግል ይዞታነት የተሸጋገረውን የፓኪስታን አየር መንገድ ሙሉ በሙሉ ለመረከብ የመጨረሻ ሂደቶችን እያጠናቀቀ የሚገኘው የአሪፍ ሀቢብ ኮንሰርቲየም፣ የአቶ ተወልደ ገብረማርያምን ሹመት በይፋ ለማሳወቅ ዝግጅቱን አጠናቋል።
አቶ ተወልደ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በበላይነት በመሩባቸው 11 ዓመታት ውስጥ፣ አየር መንገዱ ከአዲስ አበባ ማዕከል በመነሳት አህጉሪቱን ከዓለም ጋር በማስተሳሰር ወደ አፍሪካ ትልቁና ትርፋማው አየር መንገድነት እንዲያድግ ያደረጉበት ስኬታማ የሥራ ታሪክ፣ ለፓኪስታን አየር መንገድ አዲስ ሕይወት ለመዝራት ለተነሳው አዲሱ ባለቤት ዋነኛ ምርጫ ሊያደርጋቸው ችሏል።
እ.ኤ.አ በ2022 ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት በዩናይትድ ስቴትስ ለሚያደርጉት የሕክምና ክትትል ትኩረት ለመስጠት ሲሉ በቅድሚያ ጡረታ መውጣታቸው የሚነገርላቸው አቶ ተወልደ፣ አሁንም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው የኢንዱስትሪ ተደማጭነት እና ተሰሚነት ከፍተኛ መሆኑን የሚያመለክት እንደሆነ ተጠቁሟል።
የአቶ ተወልደ ወደ ፓኪስታን አየር መንገድ መምራት መነጋገሪያ ከመሆኑ ወራቶች አስቀድሞ ፣ ሌላኛው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ቁንጮና አንጋፋ መሪ አቶ ግርማ ዋቄ በተመሳሳይ መልኩ የኡጋንዳን ብሔራዊ አየር መንገድ ለመታደግ በኃላፊነት ላይ መሾማቸው ይታወሳል።
Via capital

Sponsored by
Surafel
27 days ago
በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የረጅም ዓመት የቆንስላ ሠራተኛ አቶ ግዛቸው ተፈራ አረፉ
#ethiopia | በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቆንስላ አገልግሎት ክፍል ለ30 ዓመታት በታማኝነት ያገለገሉትና በቅርቡ ከሥራ በጡረታ የተሰናበቱት አቶ ግዛቸው ተፈራ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገልጿል።
ቤተሰቦቻቸው እንደገለጹት፣ አቶ ግዛቸው ትናንት ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም አርፈዋል።
አቶ ግዛቸው ተፈራ ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በቅንነት፣ በትህትና እና በወገናዊ ፍቅር ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን፣ በተለይም ለቆንስላ አገልግሎት ወደ ኤምባሲው የሚመጡ ዜጎች በሚያሳዩት አክብሮትና ቀና አገልግሎት በማኅበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ፍቅርና ክብር አትርፈው ነበር።
በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም፣ “ላበረከቱልን ቀና አገልግሎት፣ ድጋፍ እና ወገናዊ ፍቅር ሁሉ እናመሰግናለን” በማለት ለአቶ ግዛቸው ተፈራ ያላቸውን አክብሮትና ሀዘን ገልጸዋል።
ነፍሳቸውን በሰላም ያሳርፍ፤
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው ወዳጆቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።
#getu #ethiopia #rip

በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለ30 ዓመታት ያገለገሉት አቶ ግዛቸው ተፈራ አረፉ
በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የቆንስላ አገልግሎት ክፍል ውስጥ ለሰላሳ ዓመታት ሲሰሩ የቆዩት እና በቅርቡ በጡረታ የተሰናበቱት አቶ ግዛቸው ተፈራ ትናንት ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ማረፋቸውን ቤተሰቦቻቸው ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።
አቶ ግዛቸው በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ለሚገኘው የዲያስፖራ ማህበረሰብ የተለያዩ የቆንስላ አገልግሎቶችን በመስጠት በኤምባሲው ውስጥ ለሶስት አስርት ዓመታት አገልግለዋል። የአካባቢው የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ አባላትም፣ ሟቹ በስራ ዘመናቸው ለሰጡት አገልግሎት እና ድጋፍ እውቅና በመስጠት ሀዘናቸውን ገልጸዋል።
በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ መገኘት ለሚፈልጉ፣ በቀብር አስፈጻሚዎች የተዘጋጀው ዝርዝር ፕሮግራም ከዚህ ዜና ጋር ተያይዟል።

30 days ago
"ከደመወዙ 35% ግብር ፣ 7% ጡረታ በድምሩ 42% ይቆረጣል። ከ58% ደመወዙ ላይ በእያንዳንዱ በሚሸምተው ሸቀጥ 15% ቫት (VAT) ይቆረጣል። ትራንዛክሽን ላይ ንግድ ባንክ ለሰርቪስና ቫት እያለ ሌሎችም የማይታወቁ ተቆራጮችን ይቆርጣል። ሰራተኛው ለውሃ፣ ለመብራት ለሌሎችም አገልግሎቶች ይቆረጥበታል። እነዚህ ሁሉ ተዳምረው ኑሮን መቋቋም አቅቶታልና ለዚህ ታጋሽ ሲቪል ሰርቪስ እና አነስተኛ ኑሮ ላይ ላለው ዜጋ ምን ታስቦለታል ? ከሚመሰርቱት መንግሥት ምን እንጠብቅ? " አቶ ባርጤማ ፍቃዱ በፓርላማ
1 month ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ለበርካታ ትውልዶች በሚቺጋኑ ካላማዙ ኮሌጅ ከኢኮኖሚክስ መምህርነትም የዘለለ አሻራ ያሳረፉት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ አህመድ ሁሴን የህይወት ጉዟቸውን የሚያወሳ አዲስ መጽሐፍ አሳትመዋል። ፕሮፌሰሩ በኮሌጁ የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ፣ የአካባቢ ጥበቃ ትምህርት መስራች፣ እንዲሁም የኮሌጁ ከፍተኛ የማስተማር ክብር የሆነው የፍሎረንስ ጄ. ሉካሴ ሽልማት ተሸላሚ በመሆን ትልቅ ታሪክ ሰርተዋል። ሆኖም ከተማሪዎቻቸው አዕምሮ የማይጠፋው ማዕረጋቸው ሳይሆን፣ ለተማሪዎቻቸው ስኬት የነበራቸው ልባዊ ፍላጎት፣ ያበረከቱት የላቀ የምክር አገልግሎት እና ደግነታቸው ነው።
አሁን ደግሞ "ዘ ዴሴ ኪድ" (The Dessie Kid) በተሰኘው አዲሱ ማስታወሻቸው፣ ከኢትዮጵያ ደሴ ከተማ የልጅነት ጊዜያቸው አንስቶ አህጉራትን እስካቋረጠው የአካዳሚክ የህይወት ጉዟቸው ድረስ ያለውን ታሪክ ወደኋላ መለስ ብለው ዳስሰውታል። መጽሐፉ ፕሮፌሰሩ በጃፓን ዋሴዳ ዩኒቨርሲቲ፣ በዚምባብዌ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ፣ እንዲሁም በቦትስዋና ዩኒቨርሲቲ ያሳለፉትን ጊዜያት ጨምሮ፣ ስለ ጽናት፣ ምስጋና፣ ቤተሰብ እና ህይወታቸውን ስለቀረጹ ሰዎች ጥልቅ የሆነ ግላዊ ምልከታን የያዘ ነው።
ፕሮፌሰሩ ይህንን ማስታወሻ ለመጻፍ ስላነሳሳቸው ምክንያት ሲገልጹ፣ ዓለማዊ ትምህርት ገና ባልተስፋፋበት ወቅት፣ መደበኛ ትምህርት ከሌላቸው ቤተሰቦች የተገኘ አንድ ልጅ እንዴት በአሜሪካ የአካዳሚክ ዓለም ውስጥ ስኬታማ ሊሆን እንደቻለ ለመረዳት መሆኑን ይናገራሉ። በተለይም የመንግስት ትምህርት ቤቶች የክርስትና ትምህርት ተጽዕኖ አለባቸው ተብሎ በሚታሰብበት ማህበረሰብ ውስጥ አድገው ይህንን ደረጃ ላይ መድረሳቸው ታሪካቸውን ልዩ ያደርገዋል።
ጸሃፊው አክለውም ታሪካቸው የተለመደውን የስደተኞች ህይወት የሚያስተጋባ ቢሆንም፣ መጽሐፉን የጻፉት የግል ስኬታቸውን ለማክበር አለመሆኑን ያብራራሉ። ይልቁንም፣ ማንም ሰው ብቻውን ስኬት ላይ እንደማይደርስ በማመን፣ ህይወታቸው በተለያዩ አጋጣሚዎች፣ እንዲሁም በትክክለኛው ጊዜ በደረሱላቸው ሰዎች እና ተቋማት ደግነት የተቀረጸ መሆኑን ለማሳየት ነው። መጽሐፉ በዋናነት የተጻፈው ቤተሰቦቻቸው ታሪካቸውን እንዲያውቁ፣ እንዲሁም በጉዟቸው ላይ ለረዷቸው መምህራን፣ ጓደኞች እና ተማሪዎች ምስጋና ለማቅረብ ነው።
በካላማዙ ኮሌጅ ያሳለፉት 34 ዓመታት በሙያ ህይወታቸው ውስጥ ትልቅ ስፍራ እንዳለው የሚያወሱት ፕሮፌሰሩ፣ ኮሌጁ ሙያዊ ክህሎታቸውን ከማሳደግ ባሻገር ማንነታቸውን ሙሉ በሙሉ የተቀበለ እና ያከበረ የመጀመሪያው ተቋም እንደነበር ይመሰክራሉ። ኮሌጁ ከነጭ-ተኮር ተቋምነት ወደ አካታች እና ብዝሃነት ወዳለው ማህበረሰብ ሲቀየር በዓይናቸው ማየታቸውም በህይወታቸው ትልቅ ስፍራ ከሚሰጡት ክስተቶች አንዱ ነው።
ጡረታ ከወጡ በኋላ ጊዜያቸውን ከልጅ ልጆቻቸው ጋር በማሳለፍ በማንበብ እና ከህይወት አጋራቸው ጋር በመጓዝ ላይ የሚገኙት ፕሮፌሰር አህመድ፣ ይህን መጽሐፍ ለማጠናቀቅ ወደ ስድስት ዓመታት ገደማ እንደፈጀባቸው ገልጸዋል። የህትመት እና የስርጭት ሂደቱንም የጥራት ደረጃውን ለመጠበቅ ሲሉ ሙሉ በሙሉ በራሳቸው ወጪ እንዳከናወኑት ጠቁመው፣ አንባቢያን መጽሐፉን ለዚሁ ዓላማ ከተዘጋጀው ድረ-ገጽ ላይ ማግኘት እንደሚችሉ አስታውቀዋል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የብራዚል እግር ኳስ ኮከብ ኔይማር ጁኒየር ብራዚል ከዓለም ዋንጫው ውጪ መሆኗን ተከትሎ ከዓለም አቀፍ እግር ኳስ ጨዋታ ራሱን ማግለሉን አስታውቋል። በሜትላይፍ ስታዲየም በተደረገው የዓለም ዋንጫ የ16ቱ ዙር ጨዋታ ብራዚል በኖርዌይ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፋ ከውድድሩ ውጪ ሆናለች።
በዚህ አሰቃቂ ሽንፈት ማጠቃለያ ላይ የ34 ዓመቱ ኮከብ ኔይማር በሜዳው ላይ በዕንባ ተውጦ ታይቷል። በጨዋታው ሁለተኛ አጋማሽ ላይ በቅያሬ የገባው ኔይማር፣ በጭማሪ ሰዓት የተሰጠውን የፍጹም ቅጣት ምት ወደ ጎል በመቀየር የቡድኑን የጎል ልዩነት ቢያጠብብም ብራዚልን ከሽንፈት ሊታደግ አልቻለም። ይህ ጨዋታ በረጅም የእግር ኳስ ታሪኩ ለሀገሩ ያደረገው የመጨረሻው ዓለም አቀፍ ጨዋታ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን፣ ከጨዋታው በኋላ ባደረገው መግለጫ ከብሔራዊ ቡድኑ በይፋ ጡረታ መውጣቱን ይፋ አድርጓል።

ለ38 ዓመታት በስዊዲን ኤምባሲ ያገለገሉት አስካለ አበበ በክብር ተሸኙ
#fastmereja I በኢትዮጵያ የስዊድን ኤምባሲ ውስጥ ላለፉት 38 ዓመታት በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ በታማኝነት እና በትጋት ሲያገለግሉ የቆዩት አንጋፋዋ ሰራተኛ ወይዘሮ አስካለ አበበ በክብር ስራቸውን አጠናቀው ጡረታ መውጣታቸውን ኤምባሲው አስታውቋል።
ለአራት አስርት ዓመታት ገደማ በዘለቀው የአገልግሎት ዘመናቸው በርካታ አምባሳደሮችን፣ የዲፕሎማቲክ ቡድኖችን እና እንግዶችን በደገፉት ወይዘሮ አስካለ አበበ አሸኛኘት ላይ በቪዲዮ መልዕክት ጭምር ምስጋና የቀረበላቸው ሲሆን፣ የኤምባሲው የስራ ባልደረቦችም በቆይታቸው ላበረከቱት አስተዋጽዖ ያላቸውን አክብሮት ገልጸውላቸዋል።

ቀብር
የአቶ ሀይሉ ሀብተሚካኤል አጭር የሕይወት ታሪክ
#ethiopia | አቶ ሀይሉ ሀብተሚካኤል ከአባታቸው ከአቶ ሀብተሚካኤል አስናቀ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አበበች ገ/ጻዲቅ በሰሜን ሸዋ፣ በይፋትና ጥሙጋ አውራጃ፣ ልዩ ስሙ ደግማት በተባለ ሥፍራ መስከረም 19 ቀን 1940 ዓ.ም ተወለዱ።
ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።
ወደ ሥራ ዓለም በመግባትም በ1964 ዓ.ም በኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ፋብሪካ (ፔፕሲ ) ተቀጥረው፣ በታማኝነትና በትጋት እስከ ጡረታ ዘመናቸው ድረስ አገልግለዋል።
በትዳር ሕይወታቸው ከወ/ሮ አመለወርቅ ተክሉ ጋር ትዳር መስርተው 5 ወንድና 2 ሴት (በአጠቃላይ 7) ልጆችን አፍርተዋል፤ እንዲሁም 13 የልጅ ልጆችን ለማየት በቅተዋል።
አቶ ሀይሉ በእርጅናና በሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው፣ በተወለዱ በ78 ዓመታቸው ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የክቡር አባታችን የቀብር ሥነ ሥርዓት ነገ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ላይ በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ይፈጸማል።

ኢትዮጵያ ታከናውናለች፡ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች እና መዋቅራዊ ለውጦች
*********************
የኢትዮጵያ መንግሥት ተግባራዊ ባደረገው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የፋይናንስ ዘርፉን ለማዘመን እና ለማጠናከር ሰፋፊ ሥራዎችን አከናውኗል።
በዋናነት ማክሮ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ከኮታ አሠራር ወጥቶ በገበያ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ተደርጓል።
የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ወለድን መሰረት ወዳደረገ ሥርዓት የተሸጋገረ ሲሆን፣ ማዕከላዊ ባንኩ መንግሥትን በቀጥታ በገንዘብ ፋይናንስ ማድረግ እንዲያቆም በመደረጉ ላለፉት 24 ወራት ለገንዘብ ሚኒስቴር ምንም አይነት ብድር አልሰጠም።
በዚህም ጥብቅ የፖሊሲ እርምጃ ከ30 እስከ 34 በመቶ ደርሶ የነበረውን የዋጋ ግሽበት ወደ ነጠላ አሃዝ ዝቅ ማድረግ ተችሏል።
ብሔራዊ ባንክም የዋጋ መረጋጋትን ቀዳሚ ተልዕኮው አድርጎ ራሱን የቻለ ገለልተኛ ተቋም ከመሆኑም ባሻገር የፋይናንስ እና ገበያ ዘርፍ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊዎችን በመሰየም በዓለም አቀፍ የኦዲት ተቋማት በየዓመቱ ኦዲት እየተደረገ ይገኛል።
በሌላ በኩል የባንክ ኢንዱስትሪው ጤናማነት በከፍተኛ ሁኔታ ማደግ ችሏል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ያልተመለሰ የ845 ቢሊዮን ብር የብድር ጫና የነበረበት ቢሆንም፣ መንግሥት ይህንን ብድር ወደ ቦንድ በመቀየሩ ባንኩን ከከፍተኛ ቀውስ ታድጎታል፤ ካፒታሉም በሶስት እጥፍ እንዲያድግ ተደርጓል።
የባንክ ኢንዱስትሪው አጠቃላይ ያልተመለሰ የብድር ምጣኔ ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው 5 በመቶ ጣሪያ በታች በመሆን 3.07 በመቶ ላይ ብቻ ይገኛል።
የባንኮች የካፒታል ብቃት ምጣኔ ከተቀመጠው የ8 በመቶ ዝቅተኛ መስፈርት በላይ በመሆን 19.1 በመቶ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ የፈሳሽ ገንዘብ ምጣኔያቸውም 30.43 በመቶ መድረስ ችሏል።
በአጠቃላይ ባለፉት ስምንት ዓመታት የባንኮች የሀብት መጠን በ680 በመቶ እንዲሁም የተቀማጭ ገንዘብ መጠን በ654 በመቶ ከፍተኛ እድገት አሳይቷል።
አሁን ላይ ካለው 3.94 ትሪሊዮን ብር ብድር እና ቦንድ ውስጥ 93.8 በመቶ የሚሆነው ብድር ለግል ዘርፉ የተሰጠ መሆኑ የግል ዘርፉን የኢኮኖሚ ተሳትፎ አጠናክሮታል።
የፋይናንስ ሥርዓቱን ይበልጥ ለማስፋት ታሪካዊ የሆነው የካፒታል ገበያ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ሴኩሪቲስ ኤክስቼንጅ (ESX) ተቋቁመዋል።
ከዚህ ቀደም ተገቢውን ትኩረት አጥቶ ለነበረው የኢንሹራንስ ዘርፍም ራሱን የቻለ ገለልተኛ ተቆጣጣሪ አካል ተመስርቷል።
የዲጂታል ፋይናንስ ሽግግሩን በተመለከተም አስደናቂ ለውጥ የታየ ሲሆን፣ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ 24.2 ትሪሊዮን ብር የዲጂታል ግብይት ተፈጽሟል፡፡
በየቀኑ በሞባይል ገንዘብ 10.6 ቢሊዮን ብር በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
እንዲሁም የመንግሥት የጡረታ ፈንድ መጠባበቂያ በሰባት እጥፍ በማደግ 470 ቢሊዮን ብር መድረስ ችሏል።
የባንክ ዘርፉን በሂደት ለውጭ ባንኮች ክፍት ለማድረግ የተወሰነው ውሳኔ ፉክክርን በመፍጠር፣ ኢንቨስትመንትን በመሳብ እና የባንክ አገልግሎትን በማዘመን የዘርፉን አጠቃላይ አቅም ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #ebcdotstream #finance #financialgoals #development

2 months ago
ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ከሐዋርያዊ ኃላፊነታቸው በጡረታ አስረከቡ
#fastmereja | የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የነበሩት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ሱራፌል በጡረታ ምክንያት ከኃላፊነታቸው ተሰናብተዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ፣ ካርዲናሉ ቀደም ብለው ያቀረቡትን የጡረታ ጥያቄ በዛሬው ዕለት ተቀብለዋል።
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቀኖናዊ አሰራርን ተከትሎ የቀረበው ይህ ጥያቄ በቅድስት መንበር በኩል ተቀባይነት አግኝቷል። ውሳኔው በቅድስት መንበር ልዩ መልዕክተኛ ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ በኩል ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ የካርዲናሉ የረጅም ዘመን አገልግሎት በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው ነው።
በብፁዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ቦታ ላይ፣ ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ረዳት ጳጳስ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ተስፋስላሴ ተተኪ ሊቀጳጳስ ሆነው መሾማቸው ታውቋል።

(ዘ-ሐበሻ ፋይናንስ ዜና ዳሰሳ) ለሁለት አስርት ዓመታት ገደማ... የዓለማችን ታላላቅ ባለሀብቶች በኤሎን መስክ በሚመራውና ለህዝብ አክሲዮን ገበያ ዝግ በነበረው ግዙፉ 'ስፔስ ኤክስ' የሮኬት አምራች ኩባንያ ውስጥ ድርሻቸውን በጸጥታ ሲያከማቹ ቆይተዋል። አሁን ግን ኩባንያው 1.8 ትሪሊዮን ዶላር በሚገመት ዋጋ የመጀመሪያውን የህዝብ አክሲዮን ሽያጭ (IPO) ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ሲሆን ይህ እርምጃ ቀድመው መዋዕለ ንዋያቸውን ያፈሰሱ ባለሀብቶችን በቬንቸር ካፒታል ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ግዙፍ ትርፍ እንዲያጋብሱ መንገድ ከፍቶላቸዋል።
ከዚህ ታሪካዊ ትርፍ ግንባር ቀደም ተጠቃሚ ከሚሆኑት መካከል አንጋፋው የአክሲዮን ገበያ ባለሙያ ሮን ባሮን፣ የካቲ ውድ ተቋም የሆነው አርክ ኢንቨስት እና የጋራ ፈንድ ግዙፉ ፊደሊቲ ኢንቨስትመንትስ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ። ከእነዚህም በተጨማሪ እንደ ፋውንደርስ ፈንድ፣ ሴኮያ ካፒታል እና አንድሬሰን ሆሮዊትዝ የመሳሰሉ የቬንቸር ካፒታል ተቋማት፣ እንዲሁም ዲ-ዋን ካፒታል ፓርትነርስ እና ኮቱ ማኔጅመንት የተባሉ ሄጅ ፈንዶች የዚህ ዶፍ ትርፍ ተካፋይ ይሆናሉ። የተወሰኑ የጡረታ ፈንዶች እና የዩኒቨርሲቲ የገንዘብ ተቋማትም የድርሻቸውን እንደሚያገኙ ይጠበቃል።
እነዚህ ትርፎች ኩባንያው ስኬታማ መሆኑ ሙሉ በሙሉ ከመረጋገጡ በፊት በድፍረት ኢንቨስት ላደረጉ ባለሀብቶች እጅግ አስገራሚ ናቸው። ሮን ባሮን ለመጀመሪያ ጊዜ በ2017 ኩባንያው ከ22 ቢሊዮን ዶላር በታች ይገመት በነበረበት ወቅት በሰራተኞች የአክሲዮን ሽያጭ በኩል ድርሻ የገዙ ሲሆን፣ ከዚያ ወዲህ በ27 የገንዘብ ማሰባሰብ ዙሮች ላይ ተሳትፈዋል። ባለፈው መጋቢት ወር መገባደጃ ላይ ስፔስ ኤክስ በ10.4 ቢሊዮን ዶላሩ የባሮን ፓርትነርስ ፈንድ ውስጥ 33 በመቶ፣ እንዲሁም በባሮን አሴት ፈንድ ውስጥ 25.5 በመቶ ድርሻ በመያዝ የተቋሙ ትልቁ እና ወሳኙ ኢንቨስትመንት ሆኖ ተመዝግቧል። ባሮን ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ ስፔስ ኤክስ በፕላኔታችን ላይ ትልቁ እና ከፍተኛ ትርፋማ ኩባንያ ይሆናል ብለው እንደሚያምኑ የተናገሩ ሲሆን፣ ተቋማቸው ላለፉት ዓመታት ወደ 2 ቢሊዮን ዶላር ገደማ መዋዕለ ንዋይ ያፈሰሰ መሆኑንና አሁን የዚህ ኢንቨስትመንት ዋጋ ወደ 12 ቢሊዮን ዶላር ማደጉን አስታውቀዋል።
የካቲ ውድ "አርክ ቬንቸር ፈንድ" የኩባንያው ፈጣን እድገት ሌላኛው ዋነኛ ተጠቃሚ ነው። ስፔስ ኤክስ በመጋቢት ወር የፈንዱን 11.4 በመቶ ድርሻ የያዘ ሲሆን፣ በፖርትፎሊዮው ውስጥ ትልቁ ኢንቨስትመንት ሆኗል። ካቲ ውድ ተቋማቸው ስፔስ ኤክስን ከሮኬት አምጣቂነት በላይ በሰፊው እንደሚመለከተው ገልጸው፣ በስታርሺፕ፣ ስታርሊንክ እና አሁን በተገዛው የ xAI ኩባንያ አማካኝነት ለሰፊው የጠፈር ኢኮኖሚ የሚሆን የተሳሰረ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መሠረተ ልማት እየገነባ ነው ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። የኩባንያው ቀጣይ የእድገት ምዕራፍ በነባሩ የፋልከን 9 አምጣቂ እና በስታርሊንክ የሳተላይት ኔትወርክ ብቻ ሳይሆን አዳዲስ የንግድ እድሎችን በጠፈር ላይ በሚከፍተው በዘመናዊው 'ስታርሺፕ' የሮኬት ስርዓት ጭምር እንደሚመራ ያምናሉ።
ከፊደሊቲ ኢንቨስትመንትስ በላይ ከስፔስ ኤክስ እድገት ተጠቃሚ የሆነ ባህላዊ የሀብት አስተዳዳሪ ተቋም የለም ሊባል ይችላል። በቦስተን የሚገኘው ይህ ተቋም በ2015 ስፔስ ኤክስ 10 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ይገመት በነበረበት ጊዜ አክሲዮኖችን መግዛት ጀምሮ ነበር። አሁን ኩባንያው በፊደሊቲ ግዙፍ ፈንዶች ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ በመያዝ ወደር የለሽ ትርፍ አስገኝቶለታል።
እነዚህ አስደናቂ ትርፎች የኩባንያውን እድገት ብቻ ሳይሆን ባለሀብቶቹ አደጋን ተጋፍጠው በኤሎን መስክ ላይ የነበራቸውን እምነት ያሳያሉ። ሌሎች ብዙ ኩባንያዎች አክሲዮኖቻቸውን ለብዙሃን ሲያከፋፍሉ፣ ስፔስ ኤክስ ግን ማን ኢንቨስት ማድረግ እንዳለበት በጥብቅ ይቆጣጠር ነበር። ይህ ጥብቅ አሰራር መጀመሪያ ላይ ለገቡት ባለሀብቶች ከፍተኛ ድርሻ እንዲይዙ እና በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንዲያተርፉ ረድቷቸዋል።
የጡረታ ፈንዶች እና ዩኒቨርሲቲዎችም ከስፔስ ኤክስ የአክሲዮን ገበያ መግባት ከፍተኛ ትርፍ ለማግኘት ተዘጋጅተዋል። ለምሳሌ ያህል የኦንታሪዮ መምህራን የጡረታ ፈንድ ቴክኖሎጂውን በመመልከት አስተማማኝ የኢንቨስትመንት እድል መሆኑን አምኖበት በ2019 ከ200 ሚሊዮን ዶላር በላይ ፈሰስ አድርጓል። በተመሳሳይ መልኩ የዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ (ሴንት ሉዊስ) ከአስር ዓመት በፊት 50 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ኢንቨስት ያደረገ ሲሆን፣ አሁን ይህ ድርሻ የዩኒቨርሲቲው 17 ቢሊዮን ዶላር ከሚገመተው አጠቃላይ ሃብት ውስጥ ከ10 በመቶ በላይ የሚሆነውን በመሸፈን አስገራሚ የሃብት እድገት አሳይቷል።

3 months ago
የእንግሊዝ ስራ እና ጡረታ ቢሮ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ሚስቶች ላሏቸው ባሎች ጥቅማጥቅሞችን እንደሚጨምር አስታወቀ።
በብሪታንያ ሁለት ሚስት ማግባት በህግ የተከለከለ ቢሆንም ጋብቻው በባህር ማዶ ከሆነ ከአንድ በላይ ማግባት ጥሩ ነው፣ለዚህም ጥቅማ ጥቅሞችን እንደሚሰጥ አሳውቋል።
seledadotio

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ ይፋ የተደረገው አዲሱ ፕሮጀክት፣ ለረጅም ጊዜ በህዝብ ዘንድ ሲያስነሳ የነበረውን ወቀሳ ለመቅረፍ ያለመ ነው። ኩባንያው የባህር ዳሩን ታሪካዊ ጣና ሆቴል ከገዛ በኋላ ግንባታ ሳይጀመርበት መቆየቱን ተከትሎ ሲቀርብበት የነበረውን ትችት በማስቀረት፣ ሆቴሉን ወደ አለም አቀፍ ደረጃ ለማሳደግ ዛሬ በይፋ ስራ መጀመሩን አብስሯል።
አቶ ጀማል በንግግራቸው እንዳብራሩት፣ይህ ግንባታ የአለቃቸውን (የሼክ መሀመድ ሁሴን አል አሙዲን) ራዕይ ለማሳካት እና የመንግስትን የቱሪዝም ልማት ምሰሶ ለመደገፍ ታቅዶ የተጀመረ ነው። ፕሮጀክቱ በአገር በቀል ኢንጂነሮች እና በማርዮት ዓለም አቀፍ ሆቴል ቴክኒካል ድጋፍ የሚገነባ ሲሆን፣ በ18 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ቃል ተገብቷል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው አያይዘውም፣ ከዚህ ቀደም አንድ ባለስልጣንን "ጀማል አንተ እርሻ)ላይ ጎበዝ ነህ፣ ሆቴል ግን አትችልበትም" ብለው ላነሱባቸው ወዳጃዊ ትችት፣ ጡረታ ከመውጣታቸው በፊት በሆቴል ዘርፍም ስኬታማ መሆናቸውን በተግባር እንደሚያሳዩ አረጋግጠዋል። ኢትዮጵያ ከሼክ መሀመድ በፊት ከሂልተን ውጭ አለም አቀፍ ሆቴል እንዳልነበራት ያስታወሱት አቶ ጀማል፣ ሸራተን አዲስ ሲገነባ "እብደት ነው" ይባል እንደነበር በማስታወስ አሁንም ሚድሮክ በቱሪዝሙ ዘርፍ ትልቅ አብዮት እያመጣ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሚድሮክ ከዚህ ፕሮጀክት ባሻገር በሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ ግዙፍ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል። አቶ ጀማል እንዳስታወቁት፣ ኩባንያቸው አስር የማርዮት ሆቴሎችን ለመገንባት ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን፣ እነዚህንም ሆቴሎች በፍራንቻይዝ ለማስተዳደር "ዘ ፈርስት ግሩፕ" የተሰኘ ትልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያ ጋር ውል አስሯል።
በተጨማሪም የዌስቲን ሆቴል ግንባታ በዘንድሮው ወይም በሚቀጥለው የፈረንጆች አመት መባቻ ተጠናቆ ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል። ቀድመው የተጀመሩት የጅማ እና የሀዋሳ ፕሮጀክቶችም በፍጥነት እየተሰሩ መሆኑን የገለጹት ዋና ስራ አስፈፃሚው፣ የባህር ዳሩ አቫንቲ ሆቴልም ወደ "ፕሮቲያ ባይ ማርዮት" ለመቀየር በቅርቡ ስራ እንደሚጀመር ያላቸውን ተስፋ አጋርተዋል።

ከልደታ ጋራዦች እስከ ጄነራል ሞተር የዘለቀ የመኪና ፍቅር
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሸናፊ ጸጋዬ (ዶ/ር) ገና በ15 ዓመታቸው ነበር ህይወታቸው ከመኪና ጋር የተሳሰረው።
በሰፈር ውስጥ ባሉ ጋራዦች የጀመረው የመካኒክነት ሥራቸው በአሜሪካን ሀገር እስከ ጀነራል ሞተርስ ሊዘልቅ ችሏል።
በአዲስ አበባ ልደታ አካባቢ የተወለዱት አሸናፊ (ዶ/ር) በሙያቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የሰሩት መኪና እጅግ አብዝተው የሚወዱት የአሜሪካ መኪና መሆኑን ያስታውሳሉ፡፡
ለሰርግ ሰፈራቸው መጥቶ የነበረው እጅግ የሚወዱት ግዙፉ 1974 ካዲላክ ኤልዶራዶ መኪና በመበላሸቱ የመጠገን ዕድል ማግኘታቸውን ይናገራሉ፡፡
በኋላም ኑሯቸውን አሜሪካን ሀገር አድርገው በጀኔራል ሞተርስ ውስጥ በተለይም በልጅነታቸው ሲያደንቁት በነበረው ካዲላክ መኪና ላይ ለረጅም ዓመታት ለመስራት ዕድል ገጥሟቸዋል፡፡
ወደ አሜሪካ ከመጓዛቸው በፊት በምድር ጦር በመካኒክነት እንዲሁም በምግብ ማደራጃ እና በጭነት ማመላለሻ የቀጣና ረዳት ማናጀር ሆነው መስራታቸውን ያስታውሳሉ፡፡
በ19 ዓመታቸው ወደ አሜሪካ ያቀኑት አሸናፊ (ዶ/ር) በመጀመሪያ ካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ በሚገኝ አንድ የጣሊኖች ጋራዥ ውስጥ በመካኒክነት ስራቸውን ጀመሩ፡፡ ከዚያም ቮልስዋገን መኪና መሸጫ ውስጥ ተቀጥረው ለመስራት ዕድል አግኝተዋል፡፡
ወቅቱ ቴክኖሎጂ እየፈጠነ መሆኑን የተገነዘቡት ባለሙያው በዘርፉ በስፋት መስራት እንደሚገባ በማመን ወደ ትውልድ ሀገራቸው እየተመላለሱ ስልጠናና የማማከር ስራዎችን እየሰጡ ይገኛል።
በአሜሪካ ዕድሜያቸውን በሙሉ በመኪና ዙሪያ የሰሩ ሲሆን በዘርፉ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ኃላፊነቶች ሰርተዋል።
ስለ አውቶሞቲቭ ጉዳዮች የሚዳስስ (The Road to Detroit) የተሰኘ መፅሐፍ የደረሱ ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት ጡረታ ወጥተው በሙያቸው ሀገራቸውን በማገልገል ላይ ናቸው፡፡
የቴክኖሎጂ መዘመንና የሰው ሰራሽ አስተውሎት መምጣት የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪውን እየለወጠው ነው ይላሉ፡፡
በሀገራችን እያደገ የመጣውን የኤሌክትሪክ መኪኖች አገልግሎት በብዛት ስራ ላይ መዋሉ ወቅቱን ያገናዘበ መሆኑን ጠቁመው፤ በዘመናዊ መሳሪያዎች የተደራጁ ባለሙያዎች እና ማሰልጠኛዎች እንደሚያስፈልጉም ጠቅሰዋል፡፡
በሀራችን 70 በመቶ የሚሆነው ወጣት በመሆኑ ለዘመኑ የሚመጥን አምራች ኃይል ለመሆን ወደ ቴክኖሎጂ ፈጥነው መግባት እንዳለባቸውም ይመክራሉ፡፡
የቴክኒክ ትምህርት ቤቶችን በማጠናከር እና የካሪኩለም ለውጥ በማድረግ ብቃት ያላቸው ቴክኒሺያኖችን አሰልጥኖ ማውጣት ይገባለም ብለዋል፡፡
ጎልፍ ስፖርት እንደሚወዱ የሚናገሩት ባለሙያው፤ በአሜሪካ ከተዋወቋት ኢትዮጵያዊት የፋርማሲ ባለሙያ ጋር ተጋብተው ሁለት ልጆችን አፍርተዋል።
በተግባረ ዕድ ትምህርታቸውን የተከታተሉት አሸናፊ (ዶ/ር) ወደ አሜሪካን ሀገር ተጉዘው በአውቶሞቲቭ ዘርፍ እስከ 3ኛ ዲግሪ የዘለቀ ትምህርት ቀስመዋል፡፡
በቴዎድሮስ ሳህለ
ከአሸናፊ ጸጋዬ (ዶ/ር) ከፋና ፖድካስ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://www.youtube.com/wa...

4 months ago
አቶ ዋቆ በእድሜ ዘመናቸው ብዙ ለፉ አገለገሉ፣ አሁን የጡረታ እድሚያቸው ደርሶ ጡረታቸውን ለማስከበር ላይ ታች ሲሉ በባሌ ሮቤ ጎረምሶች ላይ ጣላቸው፣ አቶ ዋቆን ሲደብድቡ ቪዲዮ ቀርጸው በሶሻል ሚዲያ ላይ የለቀቁት ጎረምሶቹ ለአቶ ዋቆ ሲሳይን ይዞ ሲመጣ ጎረምሶቹን ለእስር ዳርጓል። አቶ ዋቆ አሁን በበርካታ ግለሰቦች የገንዘብ ድጋፍ ሲያገኙ በአዋሽ ባንክ በኩል ግማሽ ሚሊዮን ብር አግኝቷል።
4 months ago
አንጋፋው የጤና ባለሙያ አቶ ዋቆ ከአዋሽ ባንክ 500,000 ብር ተበረከተላቸው
#ethiopia | በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ መናኸሪያ ውስጥ በ35 ዓመታት የሥራ ልምድ ባላቸው አንጋፋ የጤና ባለሙያ ላይ የተፈጸመው አስነዋሪ ድብደባ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችና በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።
ተጎጂው አቶ ዋቆ ከዲር ይባላሉ። ግለሰቡ ላለፉት ሦስት አስርተ ዓመታት በላይ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ማለትም በታማኝነትና በቅንነት ሀገራቸውንና ህዝባቸውን ሲያገለግሉ የቆዩ ባለውለታ ናቸው።
አቶ ዋቆ አገልግሎታቸውን አጠናቅቀው የጡረታ መብታቸውን ለማስከበር ሰነዶቻቸውን በማደራጀት ላይ በነበሩበት ወቅት፣ በሮቤ ከተማ መነኸሪያ ውስጥ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች አማካኝነት ከባድ ድብደባና እንግልት ደርሶባቸዋል። ይህ ድርጊት በቪዲዮ ተቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያ መሰራጨቱ የብዙዎችን ልብ ሰብሯል።
አቶ ዋቆ የሀገር ባለውለታ ብቻ ሳይሆኑ፣ በ2009 ዓ.ም በነበረው የድንበር ግጭት ወቅት ዛሬ ደጋፊ ሊሆኑ የሚችሉ ልጆቻቸውን በሞት ያጡ አባት መሆናቸው ድርጊቱን የበለጠ አሳዛኝ ያደርገዋል።
ይህንን በሀገር ባለውለታ ላይ የደረሰውን ግፍና በደል የተረዳው አዋሽ ባንክ፣ ለባለሙያው ክብር ለመስጠትና ለደረሰባቸው ጉዳት መቋቋሚያ እንዲሆናቸው የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል። ባንኩ ይህንን ያደረገው ግለሰቡ ለሀገር ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ከግምት ውስጥ በማስገባትና የደረሰባቸውን ሞራል የሚጠግን ተግባር ለመፈጸም መሆኑ ተገልጿል።
ለአንጋፋ የሀገር ባለውለታዎች ይህ ስጦታ የተበረከተላቸው ታሜስል ኮሙኒኬሽንስ ባዘጋጀው የ2018 የፋሲካ ልዩ ኤክስፖ መድረክ ላይ ነው ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #fast_mereja #አቶ_ዋቆ_ከዲር #ሮቤ #ባሌ #ጤና_ባለሙያ #አዋሽ_ባንክ #ኢትዮጵያ #ፍትህ #humanity #ethiopia

አዋሽ ባንክና ታሜሶል ኮሙኒኬሽን ለሀገር ባለውለታዎች የገንዘብ ሽልማት አበረከቱ
#ethiopia | አዋሽ ባንክ ከታሜሶል ኮሙኒኬሽን ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሲያካሂድ የቆየው የአዋሽ ግራንድ ፕሮሞ ፋሲካ ኤክስፖ 2018 የማጠቃለያ መርሃ ግብር ደማቅ በሆነ የሽልማት እና የምስጋና ስነ-ስርዓት ተከናወነ።
በመርሐግብሩ ላይ በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት ሲዘዋወር በነበረው ምስል በባሌ ሮቤ ከተማ ጥቃት ደርሶባቸው የነበሩት የ35 ዓመታት የጤና ባለሙያው አቶ ዋቆ ከድር ቱጌ በአዋሽ ባንክ የ500 ሺህ ብር የክብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
አቶ ዋቆ ሀገራቸውን በህክምና ሙያ ሲያገለግሉ የቆዩና በግጭት ወቅት ልጃቸውን ያጡ የሀገር ባለውለታ ቢሆኑም፣ በጡረታ ጉዳያቸው ላይ በነበሩበት ወቅት በማስተዋል በጎደላቸው ወጣቶች ድብደባና እንግልት ደርሶባቸው የነበረ ሲሆን፣ ባንኩ ይህንን የሀገር ባለውለታ ክብር ለመመለስና መቋቋሚያ እንዲሆናቸው ይህንን ድጋፍ አድርጓል።
በሌላ በኩል በነርቭ ህመም እየተሰቃዩም ቢሆን ተስፋ ሳይቆርጡ በመስቀል አደባባይ መግቢያ ላይ መጽሐፍ በመሸጥ የሚተዳደሩት ታታሪው ደራሲ አንተነህ ወንድሙ የተለየ እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።
ደራሲ አንተነህ ላሳዩት አስደናቂ የስራ ትጋት አዋሽ ባንክ የ1 ሚሊዮን ብር ሽልማት የሰጠ ሲሆን፣ ታሜሶል ኮሙኒኬሽን ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን እና ሊያን ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በመተባበር ተጨማሪ 1 ሚሊዮን ብር በመጨመር በአጠቃላይ የ2 ሚሊዮን ብር ሽልማት ተረክበዋል።
የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው በመርሐግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ባንኩ በየዓመቱ ለማህበራዊ ኃላፊነት አገልግሎት ከ500 እስከ 700 ሚሊዮን ብር እንደሚመድብ ጠቁመው፣ ዛሬም የሀገር ባለውለታዎችንና ጠንካራ ዜጎችን በማገዙ ኩራት እንደሚሰማቸው ገልጸዋል።
በዚህ ታላቅ መርሃ ግብር ላይ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የባለ እጣዎች ሽልማት ይፋ ሲደረግ፣ ወጣት ሳሮን ሸዋንግዛው የዕለቱ ደማቅ ተሸላሚ ሆናለች።
ከአዲስ አበባ ጎፋ አካባቢ የመጣችው ወጣት ሳሮን፣ በኤክስፖው ማጠቃለያ ላይ በወጣው እጣ የቢዋይዲ ሴጉል 2025 (BYD Seagull 2025) ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪን ማሸነፍ ችላለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

አንጋፋው የጤና ባለሙያ ላይ የተፈጸመው ድብደባ
#fastmereja I በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ መናኸሪያ ውስጥ የ35 ዓመታት የሥራ ልምድ ያላቸው አንጋፋ የጤና ባለሙያ የደረሰባቸው የመንጋ ድብደባ ህዝቡን አስቆጥቷል። ግለሰቡ ለረጅም ዓመታት በጤናው ዘርፍ ሀገራቸውን ሲያገለግሉ የቆዩና በአሁኑ ወቅት የጡረታ ሰነዶቻቸውን እያስተካከሉ የሚገኙ አባት መሆናቸው ታውቋል።
ተጎጂው አቶ ዋቆ ከዲር ይባላሉ። ግለሰቡ በጤናው ዘርፍ ለ35 ዓመታት ያህል በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ማለትም በቄለም ወለጋ ሆስፒታል፣ በጎባ ሆስፒታል፣ በጊኒር ሆስፒታል፣ በራይቱ ጤና ጣቢያ ሲያገለግሉ የቆዩ ባለሙያ ናቸው።
አቶ ዋቆ አገልግሎታቸውን አጠናቅቀው የጡረታ መብታቸውን ለማስከበር ሰነዶቻቸውን በማደራጀት ላይ በነበሩበት ወቅት፣ በሮቤ ከተማ መነኸሪያ ውስጥ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች አማካኝነት (ቪዲዮ በፋስት መረጃ ቴሌግራም ላይ አለ) ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል።
እንደ ቤተሰብ አባላትና የቅርብ ወዳጆቻቸው ገለጻ፣ አቶ ዋቆ በ2009 ዓ.ም ከሶማሌ ክልል ጋር በነበረው የድንበር ግጭት ወቅት ዛሬ ደጋፊ ሊሆኑ የሚችሉ ልጆቻቸውን በሞት ያጡ አባት ናቸው። ይህን መሰል በሀገር ባለውለታ ላይ የተፈጸመ ግፍ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል።
ቪዲዮ 📍https://t.me/fastmereja

አሮን ራምሴ በ35 ዓመቱ ከእግር ኳስ ሜዳ ተሰናበተ!
#ethiopia | ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ በክህሎቱና በጽናቱ የእግር ኳስ አፍቃሪዎችን ቀልብ ሲስብ የነበረው ዌልሳዊው አማካይ ''አሮን ራምሴ''፣ በይፋ ከእግር ኳስ ዓለም መገለሉን አስታውቋል።
ራምሴ የእግር ኳስ ህይወቱን በወጣትነት እድሜው በካርዲፍ ሲቲ የጀመረ ቢሆንም፣ ደማቅ ስሙ የተገነባው ግን በለንደኑ አርሰናል ነው።
በአርሰናል (2008-2019) ለ11 ዓመታት በመድፈኞቹ ቤት በቆየባቸው ጊዜያት 3 የኤፍ ኤ ካፕ (FA Cup)እና 3 የኮሚዩኒቲ ሺልድ** ዋንጫዎችን አንስቷል።
በተለይም በኤፍ ኤ ካፕ ፍፃሜዎች ላይ ያስቆጠራቸው ወሳኝ ጎሎች በአርሰናል ደጋፊዎች ዘንድ ሁሌም በታላቅ ክብር ያስታውሱታል።
በጁቬንቱስ ወደ ጣሊያን በማምራትም የሴሪ አ፣ የጣሊያን ዋንጫ እና የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን በስብስቡ ውስጥ ማካተት ችሏል።
በሬንጀርስ፣ በፈረንሳዩ ኒስ፣ በድጋሚ በካርዲፍ ሲቲ እና በሜክሲኮው ፑማስ አጭር ቆይታዎችን በማድረግ የእግር ኳስ ህይወቱን አጠናቋል።
ራምሴ ለሀገሩ ዌልስ ባደረጋቸው 86 ጨዋታዎች 21 ጎሎችን በማስቆጠር የሀገሩን እግር ኳስ ወደ አዲስ ምዕራፍ ካሸጋገሩት የወርቅ ትውልድ አባላት አንዱ ነው። ዌልስ በአውሮፓ ዋንጫ ላይ ለነበራት ስኬታማ ተሳትፎ የእሱ ሚና ላቅ ያለ ነበር።
ራምሴ ጎል ባስቆጠረ ቁጥር በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ ዝነኛ ሰዎች ህልፈት ይከሰታል በሚል ለአመታት ‘የራምሴ እርግማን’ (The Ramsey Curse)የሚለው ወሬ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲናፈስ ቆይቷል። እርግጥ ነው፣ ይህ በአጋጣሚዎች የተሞላ አዝናኝ አፈ ታሪክ ቢሆንም፣ ለተጫዋቹ ግን ልዩ መጠሪያ ሆኖት አልፏል።
በአጠቃላይ አሮን ራምሴ በጉዳት ቢፈተንም ተስፋ ባለመቁረጥና በሜዳ ላይ ባለው ብልሃተኛ እንቅስቃሴው የሚታወስ ድንቅ ተጫዋች ነበር። መልካም የጡረታ ዘመን ለራምሴ!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #aaronramsey #arsenal #juventus #wales #footballretirement #legend #ramseycurse #cardiffcity

የካሙዙ ካሳ ላላ መልዕክት
ሠላም ጤና ይስጥልኝ የተከበራችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን
#ethiopia | በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ጉምቱ የተባሉ የኪነጥበብ ባለሞያዎች እና በተለያዩ የሞያ ዘርፎች ላይ አንቱታን ያተረፉ ግለሰቦች ለህዝብ ጥቅም ለሀገር መፅናት ሲሉ በፖለቲካ ተሳትፈዉ ለህዝባቸዉ ይበጃል ያሉትን ታሪክ ሰርተዋል ፣ እየሰሩም ይገኛሉ። በአለም የፖለቲካ ጉዞም ቢሆን የኪነጥበብ ባለሞያዎች እና ስፖርተኞች ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በማኅበራዊና ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ብርቱ ተሳትፎ ሲያደርጉ ቆይተዋል።
የነበራቸውን ተሳትፎ በወፍ በረር ለመቃኘት ያክል:-
————
ሴኔጋል – ኢሱኑ ንዱር (Youssou N'Dour)
በዓለም የሙዚቃ መድረክ ተወዳጁ የሴኔጋል ዘፋኝ ኢሱኑ ንዱር፣ ለረጅም ዓመታት በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ድምጹን ካሰማ በኋላ፣ በ2012 የሴኔጋል የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው ተሾመ። በዚህ ሥልጣን የሀገሪቱን ቅርስ በማስጠበቅ ወጣቶችን በማብቃት ረገድ ትልቅ አሻራ አስቀርቷል።
————-
ላይቤሪያ – ጆርጅ ዊሃ (George Weah)
ከዓለም እግር ኳስ ታላላቅ ኮከቦች አንዱ የሆነው አፍሪካዊ የባሎን ዶር ተሸላሚ ጆርጅ ዌአ፣ ከሜዳ ጡረታ በኋላ ወደ ላይቤሪያ ፖለቲካ በመግባት ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት በ2018 የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆኖ ተመረጠ። የእርሱ ጉዞ ከስፖርት ወደ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር ከሚታወቁት ደማቅ ምሳሌዎች አንዱ ነው።
—————
ናይጄሪያ – ፌላ ኩቲ (Fela Kuti)
የአፍሮቢት ሙዚቃ አባት ተብሎ የሚጠራው ናይጄሪያዊው ፌላ ኩቲ፣ በዘፈኖቹ ብቻ ሳይሆን በጠንካራ የፖለቲካ ንቅናቄውም ይታወቃል። መንግሥትን ጥሩ ሲሰራ ደግፎ በደልና ብልሹ አስተዳደርን በግልጽ ተቃዉሞ የካላኩታ ሪፐብሊክ በመባል በሚታወቀው ማኅበረሰቡ ውስጥ ተደጋጋሚ ቅጣትና እስራት ቢደርስበትም፣ የአፍሪካን የሕዝብ ተነሳሽነት በሙዚቃ አብይ ምሳሌ ሆኖ ቆይቷል።
——————
ዩናይትድ ስቴትስ – ሮናልድ ሬገን (Ronald Reagan)
ከሆሊዉድ ታዋቂ ተዋናዮች አንዱ የነበረው ሮናልድ ሬገን፣ ከስክሪን ወደ ፖለቲካ በመሻገር ከ1967 እስከ 1975 የካሊፎርኒያ ገዥ ሆኖ አገልግሏል፣ በኋላም በ1981 የአሜሪካ 40ኛ ፕሬዚዳንት ሆኖ ተመረጠ። በሁለት የሥልጣን ዘመኑ በቀዝቃዛው ጦርነት ማብቂያ ላይ ትልቅ ሚና በመጫወት፣ የአሜሪካን ኢኮኖሚ በሪጋኖሚክስ ፖሊሲ በማሻሻል ከተዋንያን ወደ ዓለም አለቃነት የተሸጋገሩ ብርቱ ምሳሌ ነዉ።
———————-
ቦብ ማርሊ (Bob Marley)
የሬጌ ሙዚቃ ምልክት ቦብ ማርሊ በዘፈኖቹ የሰላም፣ የአንድነትና የፖለቲካ ነፃነት መልእክት አሰማ። በጃማይካ ከፍተኛ የፖለቲካ ግጭት በነበረበት ወቅት ሁለት ተቀናቃኝ አንጃዎችን በአንድ መድረክ ላይ በማሰባሰብ “One Love” ኮንሰርት በማዘጋጀት ታሪካዊ ስራን ሰርቷል። ምንም እንኳ መደበኛ የፖለቲካ ሹመት ባይይዝም፣ በዓለም ዙሪያ እንደ ታላቅ የሰላም አራማጅና ተጽዕኖ ፈጣሪ ይታወሳል።
——————-//
ካሊፎርኒያ – አርኖልድ ሽዋርዜኔገር (Arnold Schwarzenegger)
በሆሊዉድ ፊልሞች ተወዳጁ የቀድሞ የሰውነት ግንባታ ሻምፒዮንና ተዋናይ አርኖልድ ሽዋርዜኔገር፣ ወደ ፖለቲካ በመግባት ከ2003 እስከ 2011 የካሊፎርኒያ ግዛት 38ኛ ገዥ ሆኖ አገልግሏል። በሁለት ወገን በተካሄደ ልዩ ምርጫ ተመርጦ፣ በአካባቢ ጥበቃና በጀት ማሻሻያ ላይ ትኩረት በማድረግ ከፊልም ስኬት ወደ እውነተኛ አመራር የተሻገረ ምሳሌ ነዉ።
———————-
ዩክሬን – ቮሎዲሚር ዘለንስኪ (Volodymyr Zelenskyy)
ዩክሬናዊው ኮሜዲያንና ተዋናይ ቮሎዲሚር ዘለንስኪ፣ በሰራዉ ተከታታይ ድራማ ውስጥ ፕሬዚዳንትን በመጫወት ታዋቂነትን ካገኘ በኋላ፣ በ2019 በእውነት የዩክሬን ፕሬዚዳንት ሆኖ ተመረጠ። ከሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ሀገሩ ከባድ ጦርነት የገጠማት ሲሆን፣ ዘለንስኪ በአለም አቀፍ መድረክ የዩክሬንን ድምጽ በማሰማት የኮሜዲ ተዋናይነትን ወደ ጀግንነት የለወጠ አመራር አሳይቷል።
———————-
ቼክ ሪፐብሊክ – ቫችላቭ ሃቬል (Václav Havel)
የቼክ ጸሐፊ፣ ተውኔት ደራሲና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቫችላቭ ሃቬል፣ በኮሚኒስት አገዛዝ ዘመን በፅሑፎቹና በተግባሮቹ የሰላማዊ አብዮት (ቬልቬት አብዮት) መሪ ሆነ። ከአገዛዙ ውድቀት በኋላ በ1989 የቼኮዝሎቫኪያ ፕሬዚዳንት ሆኖተመረጠ፣ በኋላም የቼክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሆኖ እስከ 2003 አገልግሏል። የጸሐፊነት ብልሃቱን ወደ ዴሞክራሲ ግንባታ በመምራት ከባህል ወደ ፖለቲካ ከፍተኛ ለውጥ ካደረጉ ታላላቅ ሰዎች አንዱ
ነዉ።
ኔፓል ፣ ባለንድራ ሻህ(Balendra Shah) ፣
በሰፊው እሚታወቀዉ መጠሪያዉ Balen ነዉ፣ የቀድሞ ራፐር፣ ሂፕ-ሆፕ አርቲስት እና ስትራክቸራል መሐንዲስ ሲሆን ፣ የኔፓል አዲስ ብሔራዊ መሪ ሆኖ ተነስቷል። ይህም የባለን ፓርቲ የ Rastriya Swatantra Party (RSP) በማርች 5፣ 2026 ምርጫዎች ላይ ታሪካዊ አሸናፊነትን ተጎናፅፏል።
ባለንም በኔፓል ፖለቲካ ከወጣት መሪዎች አንዱ ያደርገዋል ።
———- #እናም የኪነጥበብ ባለሞያዎች በማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ መሳተፍ ለሀገርና ለሕዝብ የጎላ ጥቅም ከማበርከት ባለፈ፣ ለኪነጥበብ ዘርፉ ከፍተኛ መነቃቃትን እንደሚፈጥር በጽኑ አምናለሁ ::ይሄም እድል ለኢትዮጵያ ኪነጥበብ እድገትም ትልቅ ሚና እንዳለው በማመንና አርቱን ሌሎች አገራት በደረሱበት ለማድረስ እንዲሁም ሀገርን በፅኑ ከማገልገል አላማ በመነሳት በተጨባጭ ለሀገር እየሰራ ነዉ ፣ ህዝቤን እና ሀገሬን ወደ ብልፅግና ማማ ያደርሳል ያልኩትን የብልጽግና ፓርቲን ወክዬ ለመወዳደር እጩ መሆኔን ሳበስር ደስታ ይሰማኛል።
—-////—-///—-
በስተመጨረሻም : እነሆ በኢትዮጵያ ታሪክ ወርቃማ ጊዜ ላይ እንገኛለን
የኢትዮጵያ ስብራቶች እየተጠገኑ ነው። በኢትዮጵያ እምቅ ሀብቶች እየወጡ ነው።
የኢትዮጵያ ጂኦ ፓለቲካዊ ቁመና እየተቀየረ ነው፣
ሀገር በምክክር እና በሽግግር ፍትህ ቁርሾዋን እየሻረች፣ ነገዋን እየተለመች ነው፣
ኢትዮጵያ በብዙ ነገሮች እራስዋን የመቻል ዕቅዷን እያሳካች ነው፣
የኢትዮጵያ ህልም እውን ሆኖ፣ ሁለንተናዊ ብልፅግና በኢትዮጵያ እንዲረጋገጥ፣ ጉዞው በውጤት ተጀምሯል።
ይሄን ውጤታማ ጉዞ ይበልጥ ለማሳካት ብልፅግናን መምረጥ ወሳኙ ነገር ነው።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ!!!
ካሙዙ ካሣ

‹‹ያለ እውቀት በሚነገር ቃል፤ በጎውን ሥራ/ምክር የሚያጨልም ይህ ማነው?!››
ስለመቄዶንያው ብንያም በለጠ፡- ያየነውን እንመስክራለን፤ የሰማነውን እንናገራለን!!
ሰሞኑን በማኅበራዊ ትስስር መድረክ የመቄዶንያው መስራች ብንያም በለጠን በተመለከተ ምክርና ወቀሳ አዘል የሆኑ ጽሑፎች ሲዘዋወሩ ነበር፡፡ የጽሑፎቹ ሐሳብ ከታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ፤ ከመጽሐፈ ኢዮብ አንድ ኃይለ-ቃልን አስታወሰኝ፡፡ ቃሉ እንዲህ ይላል፤
‹‹ያለ እውቀት በሚነገር ቃል፤ በጎውን ሥራ የሚያጨልም ይህ ማነው?!››
ከዚሁ የሐሳብ ሰበዝ ሳልወጣ በመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን ማእከል በነበረኝ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቆይታዬ የታዘብኩትን የግሌን ምስክርነት በጥቂቱ ላንሳ፡፡
ብንያምን የማውቀው ከዓመታት በፊት ኮተቤ በወላጆቹ ቤት 100 የሚሆኑ አረጋውያንና አእምሮ ሕሙማንን ሰብስቦ ሲረዳ ነው፡፡ በወቅቱ ማእከሉ ሙሉ በሙሉ ሥራውን ሲያካሂድ የነበረው በበጎ ፈቃደኛ አገልጋዮች ነበር፡፡ እናም አንድ ወቅት ላይ ከአንድ መነኩሴ አባት ጋር በመሆን በበጎ ፈቃደኝነት መቄዶንያን ለማገልግል አብረን ሄድን፡፡
ብንያም በትሕትና ከተቀበለን በኋላ የመጣንበትን ምክንያታችንን ገለጽንለት፡፡ ትሑት በሆነ መንፈስ ምስጋናውን ከገለጸልን በኋላ ፈቃዳችን ቢሆን ለተወሰኑ ጊዜያት እዛው ማእከሉ ውስጥ ከአረጋውያንና ከአእምሮ ሕሙማን ወገኖቻችን ጋር እየኖረን እንድናገለግል ጠየቀን፡፡ እኔም በዕድሜ አረጋዊ የሆኑትም መነኩሴ አባት በሐሳቡ ተስማማን፡፡
ብንያም ፈቃደኝነታችንን በአክብሮትና በምስጋና ከተቀበለ በኋላ በወላጆቹ ቪላ ቤት ውስጥ የአባቱና የእናቱን መኝታ ቤት ለጊዜው ማረፊያ ይሆነን ዘንድ ለእኔና ለመነኩሴው አባት እንዲሰጠን አደረገ፡፡ ልብ በሉ ብንያም ይህን ያማረውን የወላጆቹን መኝታ ቤት እኛ እንዳናርፍበት ሲሰጠን የእርሱ ማረፊያ ክፍል ግን በግቢው ውስጥ በጭቃ በተሠራ ሰርቪስ ቤት ውስጥ ነበር፡፡
ይህ ብቻ አይደለም በቆይታዬ እንደታዘብኩት፤ ብንያም አረጋውያኑ የበሉትን ይበላል፤ የለበሱትን ይለብሳል፤ አብሮአቸው ይውላል፤ አብሮአቸው ያድራል፡፡ እንደውም በማእከሉ ውስጥ ከእርሱ ይልቅ ልዩ እንክብካቤ የሚደረግላቸው አረጋውያን አባቶችና እናቶች ነበሩ፡፡
ይህን ገና ከጅምሩ የመቄዶንያ ቀኝ እጅ የሆነውና ሠርጉን ጭምር በመቄዶንያ ያደረገው ሰይፉ ፋንታሁን፤ አብረውት ይሠሩ የነበሩት ታዬ ወርቁ፣ ጋዜጠኛ ዕፀገነት/የኢቢኤሷ፣ የስፖርት ጋዜጠኛው ታደለ፤ ሀብታሙ አረጋ፤ ከተባበሩት መንግሥታት የምግብ ድ/ት ከጡረታ ከተገለሉ በኋላ የማእከሉ በጎ ፈቃደኛ የነበሩት ዶ/ር ጌታቸው ተድላ… በወቅቱ በማእከሉ አብረውን የነበሩ ሌሎች በጎ ፈቃደኞችና ማእከሉን ለመጎብኘት የሚመጡ ወገኖች ሁሉ የሚያውቁት፤ የሚመሰክሩት እውነታ ነው፡፡
በመጨረሻም፤
መቄዶንያ የሰዎች እንጂ የመላእክት ስብስብ ያለበት ቦታ አይለደም፡፡ እግር ጥሎት ለሄደም ሆነ በማእከሉ በቅርበት ለሚከታተል ሰው ሊታዘባቸው የሚችላቸው ጥቃቅንም ሆነ ጉልህ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ የማእከሉ ዋና ግብ ግን የቀኑ ጸሐይ፣ የሌሊቱ ቁር የሚፈራረቅባቸውን አረጋውያን አባቶችና እናቶች ከጎዳና ላይ በማንሳት በቀሪ ጥቂት ዘመናቸውን እፎይ ብለው የሚያርፉበት መጠለያ፣ ምግብ፣ አልባሳትና ቤተሰባዊ እንክብካቤ ማሟላት ነው፡፡ ይህን ደግሞ መቄዶንያ ደጋግ ልብ ካላቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖች ጋር በመሆን በስፋት እየሠራ ነው፡፡
ተቺዎቹ፤ ‹‹ብንያም አለባበሱን እንዲቀይር ከመምከርም ባሻገር ምስኪን መስሎ መታየት ምንድ ነው? ነቃ ነቃ በል እንጂ…›› በሚል ላነሱት አስተያየት ይህን ብዬ ጽሑፌን ልቋጭ፡፡
ህንዳውያን ‹‹ታላቁ ነፍስ›› በማለት የሚጠሯቸው የህንድ የነጻት አባት ማሕተመ ጋንዲ በሕይወት ዘመናቸው ልብሳቸው አንድና ተመሳሳይ ነበር፡፡ እኚህ ሰው ከህንዳውያኑ ተራ ዜጎች የተለየ አለባበስና አመጋገብ አልነበራቸውም፡፡ እርሳቸውን ለማግኘት/ለመጎብኘት ለሚመጡት ለታላላቅ የዓለማችን መሪዎች ሆነ ለምድራችን ምስኪኖችንና ጎስቋሎች የነበራቸው አቀባባል፤ የሚያሳዩት ክብር፣ የሚሰጡት ፍቅርና ትሕትና ተመሳሳይ ነበር፡፡
ጋንዲ በአለባበሳቸውም ሆነ በአኗኗራቸው ይህን ተራ መንገድ የተከተሉት ወደውና ፈቅደው እንጂ ገንዘብ ስለቸገራቸው አይደለም፡፡ እኚያ ታላቅ ሰው ባላቸው ተቀባይነት፣ ክብርና ዝና የተነሳ ወርቅ መልበስ፣ በወርቅ ሰሀን መብላት የሚያስችል ዕድል የነበራቸው ታላቅ ሰው ነበሩ፡፡ ግን እርሳቸው ያን መንገድ አልፈለጉትም፡፡ ተራ መስለው ግን ደግሞ ታላቅ ሥራን ሠርተው ያለፉ የምድራችን ታላቅ ሰው ናቸው፡፡
እንደ መውጫ፤
መቄዶንያን/ብንያምን በተመለከተ ችግር አለ ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ የሚሏቸውን ችግሮች ለመቅረፍ ተባብሮ መስራት እንጂ ከውጪ ሆነ መተቸት ለውጥ ያመጣል ብዬ አላስብም፡
ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ፤ ‹‹ነገር ግን በጎ ሥራ ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናና ክብር፤ ሰላምም ይሆንላቸዋል፤›› እንዲል፤ ወንድማችን ብንያም ስላደረገኸውና እያደረግኽ ስላለው የበጎነት ሥራ ከፈጣሪ ዘንድ ምስጋናና ክብር፤ የበዛ ሰላም ይሁንልህ!!
ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው!!
በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን)፤

5 months ago
ኢትዮ ሆም ኤክስፖ 2026
በዩናይትድ ኪንግደም ለንደን ከመጋቢት 23 እስከ 25 የሚካሄደው ሆም ኤክስፖ 2026 ልዩ እና የመጀመሪያ የሚያደርገው ዋና ዓላማ በዩናይትድ ኪንግደም የሚኖሩ የዳያስፖራ ማህበረሰቡ አስተማማኝ በሆነ መንገድ የቤት ባለቤት እንዲሆን ለማስቻል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራቱ ነው።
በእንግሊዝ አገር የሚካሄደውን መድረክ በትብብር ካዘጋጁት ባለድርሻ አካላት መካከል አንዱ የሆኑት የኤድማር ቬንቸር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፋሲካ አብዛ፤ ኢትዮ ሆም ኤክስፖ 2026 የሚዘጋጅበት ለዳያስፖራ ማህበረሰቡ አገልግሎት ለመስጠት ያለመ ልዩ ግብ የሰነቀ መሆኑን ይናገራሉ።
እንደ እርሳቸው አነጋገር ይህ በእንግሊዝ አገር የሚካሄድ ኤክስፖ የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎችን፣የፋይናንስ ተቋማትን፣ፖሊሲ አውጭዎችን ፣ተግባሪዎችንና አስፈፃሚዎችን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ ጋር የማገናኘት ግብ አለው።
የዳያስፖራው ማህበረሰብ በሪል ስቴት አልሚዎች የበለጠ መተማመን እንዲኖረው ለማስቻል በማቀድ በተቀመጡ መመዘኛዎች እና የማጣራት ሥራ ከአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ጋር በመተባበር በማከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን ሂደቱንም በተገልጋዩ ማህበረሰብ ዘንድ መተማመን እንዲፈጥር ለማስቻል ቀርቦ ማወያየት እና ግንዛቤ ማስጨበጡ መሠረታዊ መሆኑን አቶ ፋሲካ ያስረዳሉ። ይህንኑ ለማሳካትም የፓናል ውይይት ለማካሄድ ዕቅድ መያዙን ገልፀዋል።
ይህ የዳያስፖራ ማህበረሰቡ በሀገሩ የቤት ባለቤት የመሆን ህልሙን እውን ከማድረግ እና የሪል ስቴት ዘርፉን ከማንቀሳቀስ አንፃር ጉልህ ሚና ያለው በመሆኑ በሌሎች አገራትም ለማስፋፋት የሚሠሩ መሆኑን ገልፀዋል።
" .....ሪል ስቴት አልሚ ድርጅቶች ፣ ወደ እንግሊዝ አገር በመምጣት ለዳያስፖራ ማህበረሰቡ አገልግሎታቸውን ብሎም ድርጅታቸውን የሚያስተዋውቁበት ዕድል ፈጥረናል። በአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት በተቀመጡ መመዘኛዎች ተጣርተው የሚመጡ በመሆናቸው የሚያቀርቡት አገልግሎት ታማኝ እንዲሆን ያስችላል። በሚካሄደውም ፓናል ላይ ያሉ ችግሮች ምንድናቸው? ገዥው እንዴት ተጠቃሚ መሆን ይችላል? የሚለውን እያነሳን እናወያያለን። ኢትዮ ሆም ኤክስፖ በዚህ መልክ ሊካሄድ ታስቧል።" ሲሉ አቶ ፋሲካ ተናግረዋል።
የሆም ኤክስፖ 2026 ዋና አዘጋጅ በለንደን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ ሲሆን ኤድማር ቬንቸር ኤክስፖውን ያስተባብራል። የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት እና የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት የሪል ስቴት አልሚዎችን እና የዳያስፖራውን ጥቅም ከማስጠበቅ አንፃር ድጋፍ በመስጠት ያዘጋጃሉ።
አቶ ፋሲካ "...ኤክስፖው ከሜይ 23 -ሜይ 25 ይካሄዳል።ሜይ 23 የፓናል ውይይት ሲደረግ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት የቤት ኤክስፖ ዕውን ይሆናል ።እነዚህ ቀናት ገዢው ከፋይናንስ ተቋማትና ከአልሚው ጋር የሚገናኝባቸው እና ውይይት የሚያደርግባቸው ቀናት ሆነው ይውላሉ። አጠቃላይ የሪል ስቴት አልሚዎቹ 30 የሚጠጉ ሲሆኑ ሁሉም ስለራሳቸው የሚያስተዋውቁበት አጋጣሚ የተፈጠረላቸው ስለሆነ በዚህ ዕድል እንደሚጠቀሙም ተስፋ እናደርጋለን " ብለዋል።
ይህንን መርሀ- ግብር ዕውን ለማድረግ ኤድማር ቬንቸር በማርች 30 2026 ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ሲሆን በዚህ መርሀ ግብር ላይም ከዳያስፖራው ኤጀንሲ፣ ከቻምበር ኦፍ ኮሜርስ ፣ከባንኮችና ከሪል ስቴት አልሚዎች የተውጣጡ ባለሙያዎች እንደሚታደሙ ይጠበቃል።እንደ ኤድማር ቬንቸር የሥራ ኃላፊዎች ከሆነ ከመግለጫው በኃላ ሁሉን አቀፍ የሆነ የፕሮሞሽን ሥራ ይከናወናል። የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በሚገኝባቸው የዕምነት ተቋማት፣የንግድ ማዕከላት በመድረስ ስለሆም ኤክስፖው በቂ መረጃ እንዲገኝ የተቻለንን እናደርጋለን ሲሉ የኤድማር ቬንቸር የሥራ ኃላፊ አቶ ፋሲካ አፅንዖት ሰጥተው ያስረዳሉ።
በተለይም ደግሞ በአሁኑ ወቅት ማህበራዊ ሚድያው ሰፋ ተደራሽነት ያለው በመሆኑ እነርሱን በመጠቀም መረጃውን ለማሠራጨት እንደሚሞከር ተገልጿል።
አቶ ፋሲካ የበለጠ ሀሣባቸውን ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ "... እኛ በማህበራዊ ሚድያ ብቻ አንወሰንም። ተፅዕኖ ፈጣሪ የማህበረሰብ መሪዎች ፣ በአንድ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመድረስ የማስተዋወቅ ሥራችንን አጠናክረን ቀጥለናል።መርሀ -ግብሩ የሚካሄድባቸውንም ስፍራዎች ከወዲሁ ይዘናል። ተሳታፊዎችን መመዝገብ ፣የጉዞ ሁኔታቸውን ማመቻቸት፣ እንዲህ ያሉ ዋና ዋና ቅድመ- ሁኔታዎችን አጠናቀን ጨርሰናል" ሲሉ አቶ ፋሲካ ይናገራሉ።
ኤድማር ቬንቸር ይህ ሥራ አንድ ተብሎ ከመጀመሩ አስቀድሞ በእንግሊዝ የተወሰነ ጥናት አድርጎ ነበር። ሁሉም በሚባል መልኩ አገሩ ላይ ቤት መገንባት ይፈልጋል። የጡረታ ዘመኑን አገሩ ላይ ማሳለፍ ይመርጣል። ወጣቱም ቢሆን አገሩ ላይ ቤት ገዝቶ ጥሩ የቢዝነስ አማራጭ ይሆንለታል።
የኤድማር ሰዎች ባጠኑት መሠረት በሁሉም የእድሜ፣የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች ቤት የመግዛት ፍላጎታቸው ከፍተኛ ነው። በቅርበት ሆኖ የሚያስረዳቸው ከተገኘ ደግም ቤት የማይገዙበት አንዳች ምክንያት አይኖርም ሲሉ ጥናታቸውን አፅንኦት ሰጥተው ያቀርባሉ።
ይህ ኤክስፖ ለአገሪቱም የውጭ ምንዛሪ በማስገባት በኩልና የንግድ እንቅስቃሴውን በማሳደግ ትልቅ አስተዋፅዖ እንደሚኖረውም ይታመናል።

የ78 ዓመቱ አዛውንት የዕድል በር በድንገት ተከፈተላቸው፤ ከ134 ሚሊዮን ብር በላይ እርዳታ ተሰበሰበ
በአሜሪካ ቴነሲ ግዛት ውስጥ የሚኖሩት የ78 ዓመቱ ሪቻርድ ፑሊ፣ በዕድሜያቸው መግፋት ምክንያት ሊያርፉ በሚገባበት ወቅት ለኑሮ ሲሉ በምግብ አቅርቦት (ዴሊቨሪ) ሥራ ላይ ተሰማርተው ቆይተዋል።
ባለቤታቸው ሥራ በማጣቷ ምክንያት ጥንዶቹ የዕለት ጉርሳቸውን ለመሸፈን በከፍተኛ ድካም ሲሰሩ ነበር።
ታሪካቸው የተቀየረው ብሪታኒ ስሚዝ የተባለች ነርስ ቤት ቡና ለማድረስ በሄዱበት ወቅት ነው። አዛውንቱ በድካም ደረጃ ሲወጡ የተመለከተችው ስሚዝ፣ በደህንነት ካሜራ የቀረጸችውን ምስል በማህበራዊ ሚዲያ በማጋራት የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ከፈተች።
በአጭር ጊዜ ውስጥ ከለጋሾች የተሰበሰበው ገንዘብ 850,000 ዶላር (ከ134 ሚልየን ብር በላይ) ደርሷል።
ይህ ያልተጠበቀ ስጦታ ሪቻርድ እና ባለቤታቸው ብሬንዳ ከእንግዲህ በድካም ሳይሆን በደስታና በሰላም የጡረታ ዘመናቸውን እንዲያሳልፉ ዕድል ፈጥሮላቸዋል።
ምንጭ፦ GoFundMe

Comments