Logo
FastMereja
ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ከሐዋርያዊ ኃላፊነታቸው በጡረታ አስረከቡ

​#fastmereja | የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የነበሩት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ሱራፌል በጡረታ ምክንያት ከኃላፊነታቸው ተሰናብተዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ፣ ካርዲናሉ ቀደም ብለው ያቀረቡትን የጡረታ ጥያቄ በዛሬው ዕለት ተቀብለዋል።

​የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቀኖናዊ አሰራርን ተከትሎ የቀረበው ይህ ጥያቄ በቅድስት መንበር በኩል ተቀባይነት አግኝቷል። ውሳኔው በቅድስት መንበር ልዩ መልዕክተኛ ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ በኩል ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ የካርዲናሉ የረጅም ዘመን አገልግሎት በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው ነው።

​በብፁዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ቦታ ላይ፣ ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ረዳት ጳጳስ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ተስፋስላሴ ተተኪ ሊቀጳጳስ ሆነው መሾማቸው ታውቋል።

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.