6 months ago
አሮን ራምሴ በ35 ዓመቱ ከእግር ኳስ ሜዳ ተሰናበተ!
#ethiopia | ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ በክህሎቱና በጽናቱ የእግር ኳስ አፍቃሪዎችን ቀልብ ሲስብ የነበረው ዌልሳዊው አማካይ ''አሮን ራምሴ''፣ በይፋ ከእግር ኳስ ዓለም መገለሉን አስታውቋል።
ራምሴ የእግር ኳስ ህይወቱን በወጣትነት እድሜው በካርዲፍ ሲቲ የጀመረ ቢሆንም፣ ደማቅ ስሙ የተገነባው ግን በለንደኑ አርሰናል ነው።
በአርሰናል (2008-2019) ለ11 ዓመታት በመድፈኞቹ ቤት በቆየባቸው ጊዜያት 3 የኤፍ ኤ ካፕ (FA Cup)እና 3 የኮሚዩኒቲ ሺልድ** ዋንጫዎችን አንስቷል።
በተለይም በኤፍ ኤ ካፕ ፍፃሜዎች ላይ ያስቆጠራቸው ወሳኝ ጎሎች በአርሰናል ደጋፊዎች ዘንድ ሁሌም በታላቅ ክብር ያስታውሱታል።
በጁቬንቱስ ወደ ጣሊያን በማምራትም የሴሪ አ፣ የጣሊያን ዋንጫ እና የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን በስብስቡ ውስጥ ማካተት ችሏል።
በሬንጀርስ፣ በፈረንሳዩ ኒስ፣ በድጋሚ በካርዲፍ ሲቲ እና በሜክሲኮው ፑማስ አጭር ቆይታዎችን በማድረግ የእግር ኳስ ህይወቱን አጠናቋል።
ራምሴ ለሀገሩ ዌልስ ባደረጋቸው 86 ጨዋታዎች 21 ጎሎችን በማስቆጠር የሀገሩን እግር ኳስ ወደ አዲስ ምዕራፍ ካሸጋገሩት የወርቅ ትውልድ አባላት አንዱ ነው። ዌልስ በአውሮፓ ዋንጫ ላይ ለነበራት ስኬታማ ተሳትፎ የእሱ ሚና ላቅ ያለ ነበር።
ራምሴ ጎል ባስቆጠረ ቁጥር በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ ዝነኛ ሰዎች ህልፈት ይከሰታል በሚል ለአመታት ‘የራምሴ እርግማን’ (The Ramsey Curse)የሚለው ወሬ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲናፈስ ቆይቷል። እርግጥ ነው፣ ይህ በአጋጣሚዎች የተሞላ አዝናኝ አፈ ታሪክ ቢሆንም፣ ለተጫዋቹ ግን ልዩ መጠሪያ ሆኖት አልፏል።
በአጠቃላይ አሮን ራምሴ በጉዳት ቢፈተንም ተስፋ ባለመቁረጥና በሜዳ ላይ ባለው ብልሃተኛ እንቅስቃሴው የሚታወስ ድንቅ ተጫዋች ነበር። መልካም የጡረታ ዘመን ለራምሴ!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #aaronramsey #arsenal #juventus #wales #footballretirement #legend #ramseycurse #cardiffcity

12 months ago
የጤና ሚኒስቴር የህይወት ዘመን ተሸላሚ ፕሮፌሰር ጽጌ ገብረማርያም
#ethiopia | የህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት ሽልማት ተሰጣቸው።
በጉራጌ ዞን በሙህርና አክሊል ወረዳ ተወለዱ።
የመጀመሪያ ደረጃና መልስተኛ 2ኛ ደርጃ ትምህርታቸውን በዲላ ከተማ አጼ ዳዊት ት/ቤት፣ የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በይርጋዓለም ከተማ ራስ ደስታ ዳምጠዉ ክፍተኛ 2ኛ ድርጃ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡
የመጀመሪያና የማስተርስ ድግሪያቸውን በፋርማሲ ዘርፍ ከአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ፣ የፒ.ኤች ዲ. ድግሪያቸውን ከUniversity of Wales በፋርማሲ ዘርፍ በማዕርግ አግኝተዋል።
በጀርመን ሀገርም post-doctoral ምርምር አካሂደዋል።
የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረጋቸውን ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡
ከ1988 ዓ.ም ጀምሮ ከ30 ዓመታት በላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ውስጥ የፋርማሲቲካል ዲፓርትመንት በኃላፊነት፣ የፋርማሲቲካል ትምህርት ቤት በዲንነት፣ የድህረ ምረቃ ጥናትና ምርምር በም/ፕሬዝዳንትነትነት ያገለገሉ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ውስጥ በፋርማሲቲካል ቴክኖሎጂ ዘርፍ በምርምር፣ በማስተማር እና በማማከር እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
የቂሊንጦ ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ፓርክ ፍኖተ ካርታ ዝግጅት ላይ፣ የባዮቴክኖሎጂ R&D እቅድ እና ግብይት ስትራቴጂ ዝግጅት፣ የ10 ዓመት የኢትዮጵያ የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ዕቅድ ዝግጅት፣ በኢትዮጵያ የሳይንስ አካዳሚ ብሔራዊ የምርምር ካውንስል ማቋቋሚያ ላይ የጋራ ስምምነት ጥናት፣ የብሔራዊ መድሃኒቶች ፖሊሲ ክለሳ ላይ ተሳትፈዋል፣ ባላቸው የላቀ የስራና የትምህርት ዝግጅት እንዲሁም ብሔራዊ እና ክልላዊ ስትራቴጂዎችን ለመቅረጽ አስተዋፅዖ ያደረጉ ቴክኒካል ሰነዶችን አዘጋጅተዋል።
በአ/አ/ዩ 50ኛ ኢዩቤልዩ በዓል በምርምር የወርቅ ሚዳልያ እና ሰርተፊኬት፣ የታዋቂዉና ታላቅ ክብር ያልዉን የጆርጅ ፎርስተር የምርምር ሽልማት፣ ከአሌክሳንደር ቮን ሁምቦልት ፋውንዴሽን ሽልማት አግኝተዋል፣ AAU የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህይወት ዘመን ምርጥ ተመራማሪ ሽልማት፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የላቀ የፋኩልቲ ሽልማት፣ ሁምቦልት አምባሳደር ሳይንቲስት የወርቅ ሜዳሊያ ሽልማት፣ ከኢትዮጵያ ፋርማሲዩቲካል ማኅበር ሽልማትንም አግኝተዋል፡፡
ከ50 በላይ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በመተባበር የረጅም ጊዜ አቅም ግንባታን በድህር/ምረቃ ፕሮግራሞችን ምርምር ላይ አመቻችተዋል፡፡
ከ175 በላይ የምርምር ውጤቶችን በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ አሳትመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ መሥራችና አባል፣ የአርማወር ሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የሳይንስ አማካሪ ቦርዱ ናቸው፡፡
ፕሮፌሰር ጽጌ ገብረማርያም፤ የህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ጤና ሚኒስቴር በ27ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ተሸላሚ በማድረግ መርጧቸዋል፡፡
ከጤና ሚኒስቴር

Comments