Logo
SeledaPost
AAU ከ500 በላይ ሰራተኞቹን አሰናበተ‼️
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ የራስ-ገዝነት መብቱን ለመተግበር ባደረገው የመዋቅር ማስተካከያ ምክንያት ከ500 በላይ አስተዳደራዊ ሰራተኞች እና 50 መምህራን ያለ ምደባ ቀርተዋል።

ይሁን እንጂ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ማንም ሰራተኛ እንዳልተባረረ ገልጸው፣ የተጎዱት በጡረታ፣ በካሳ ወይም በቅርቡ በሚጀመሩ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንደሚካተቱ አረጋግጠዋል።

​ምደባው ለአስተዳደር ሰራተኞች በፈተና፣ ለመምህራን ደግሞ በትምህርት ዝግጅት አግባብነት ላይ ተመስርቶ የተከናወነ ነው።

​በሀገሪቱ ከሚገኙ 46 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የመጀመሪያው ሞዴል የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሪፎርም እርምጃ፣ ቀጣይ ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ ለሚዘጋጁት እንደ ጂማ፣ መቐለ፣ ባህር ዳር እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲዎች ትልቅ ማሳያ እንደሚሆን ተገልጿል።

Seledadotio
Seledadotio
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.