አንጋፋው የጤና ባለሙያ ላይ የተፈጸመው ድብደባ
#fastmereja I በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ መናኸሪያ ውስጥ የ35 ዓመታት የሥራ ልምድ ያላቸው አንጋፋ የጤና ባለሙያ የደረሰባቸው የመንጋ ድብደባ ህዝቡን አስቆጥቷል። ግለሰቡ ለረጅም ዓመታት በጤናው ዘርፍ ሀገራቸውን ሲያገለግሉ የቆዩና በአሁኑ ወቅት የጡረታ ሰነዶቻቸውን እያስተካከሉ የሚገኙ አባት መሆናቸው ታውቋል።
ተጎጂው አቶ ዋቆ ከዲር ይባላሉ። ግለሰቡ በጤናው ዘርፍ ለ35 ዓመታት ያህል በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ማለትም በቄለም ወለጋ ሆስፒታል፣ በጎባ ሆስፒታል፣ በጊኒር ሆስፒታል፣ በራይቱ ጤና ጣቢያ ሲያገለግሉ የቆዩ ባለሙያ ናቸው።
አቶ ዋቆ አገልግሎታቸውን አጠናቅቀው የጡረታ መብታቸውን ለማስከበር ሰነዶቻቸውን በማደራጀት ላይ በነበሩበት ወቅት፣ በሮቤ ከተማ መነኸሪያ ውስጥ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች አማካኝነት (ቪዲዮ በፋስት መረጃ ቴሌግራም ላይ አለ) ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል።
እንደ ቤተሰብ አባላትና የቅርብ ወዳጆቻቸው ገለጻ፣ አቶ ዋቆ በ2009 ዓ.ም ከሶማሌ ክልል ጋር በነበረው የድንበር ግጭት ወቅት ዛሬ ደጋፊ ሊሆኑ የሚችሉ ልጆቻቸውን በሞት ያጡ አባት ናቸው። ይህን መሰል በሀገር ባለውለታ ላይ የተፈጸመ ግፍ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል።
ቪዲዮ 📍https://t.me/fastmereja

4 months ago