Logo
FIDEL POST NEWS
የ78 ዓመቱ አዛውንት የዕድል በር በድንገት ተከፈተላቸው፤ ከ134 ሚሊዮን ብር በላይ እርዳታ ተሰበሰበ

​በአሜሪካ ቴነሲ ግዛት ውስጥ የሚኖሩት የ78 ዓመቱ ሪቻርድ ፑሊ፣ በዕድሜያቸው መግፋት ምክንያት ሊያርፉ በሚገባበት ወቅት ለኑሮ ሲሉ በምግብ አቅርቦት (ዴሊቨሪ) ሥራ ላይ ተሰማርተው ቆይተዋል።

ባለቤታቸው ሥራ በማጣቷ ምክንያት ጥንዶቹ የዕለት ጉርሳቸውን ለመሸፈን በከፍተኛ ድካም ሲሰሩ ነበር።

​ታሪካቸው የተቀየረው ብሪታኒ ስሚዝ የተባለች ነርስ ቤት ቡና ለማድረስ በሄዱበት ወቅት ነው። አዛውንቱ በድካም ደረጃ ሲወጡ የተመለከተችው ስሚዝ፣ በደህንነት ካሜራ የቀረጸችውን ምስል በማህበራዊ ሚዲያ በማጋራት የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ከፈተች።

​በአጭር ጊዜ ውስጥ ከለጋሾች የተሰበሰበው ገንዘብ 850,000 ዶላር (ከ134 ሚልየን ብር በላይ) ደርሷል።

ይህ ያልተጠበቀ ስጦታ ሪቻርድ እና ባለቤታቸው ብሬንዳ ከእንግዲህ በድካም ሳይሆን በደስታና በሰላም የጡረታ ዘመናቸውን እንዲያሳልፉ ዕድል ፈጥሮላቸዋል።

​ምንጭ፦ GoFundMe
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.