Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ የራስ ገዝነት መብቱን ለመተግበር ባደረገው የመዋቅር ማስተካከያ ምክንያት ከ500 በላይ አስተዳደራዊ ሰራተኞች እና 50 መምህራን ያለመደብ መቅረታቸውን ኤስቢኤስ ራድዮ ከአውስትራሊያ ዘግበ። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ማንም ሰራተኛ እንዳልተባረረ ገልጸው፤ የተጎዱት በጡረታ፣ በካሳ ወይም በቅርቡ በሚጀመረው የንግድ እንቅስቃሴ እንደሚካተቱ ተናግረዋል።

ፎርቹን ጋዜጣ እንደዘገበው ደግሞ ምደባው ለአስተዳደር ሰራተኞች በፈተና፣ ለመምህራን ደግሞ በትምህርት ዝግጅት አግባብነት ላይ ተመስርቶ እየተከናወነ ነው። በሀገሪቱ ከሚገኙ 46 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የመጀመሪያው ሞዴል የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሪፎርም እርምጃ፣ ቀጣይ ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ ለሚዘጋጁት እንደ ጅማ፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ መቀሌ እና መሰል ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች ማሳያ ይሆናል ተብሏል።

5 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.