የ69 ዓመታቸው አዛውንት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን ገብተዋል።
በትምህርት ዓለም ውስጥ ዕድሜ ገደብ እንደሌለው በተግባር ያሳዩት የ69 ዓመቱ አዛውንት አባባ ወልደየስ አያና አሻቦ ዘንድሮ በሚሰጠው 4ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ላይ በመቀመጥ አዲስ ታሪክ አስመዝግበዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ልዩ ስሟ ዳንጋራ ሳላጣ በተባለች ቀበሌ ተወልደው ያደጉት አባባ ወልደየስ፣ ቀደም ሲል ማህበረሰባቸውን በቀበሌ አስተዳዳሪነት ከስድስት ዓመታት በላይ በታማኝነት ያገለገሉ የሀገር ሽማግሌ ናቸው።
በደርግ ዘመን በትውልድ አካባቢያቸው እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ ተምረው ቢያጠናቅቁም፣ በወቅቱ በነበረው የትምህርት አደረጃጀት፣ የአገዛዝ ሥርዓትና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአቅራቢያቸው አለመኖር ምክንያት ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደው ነበር።
ይሁን እንጂ ለትምህርት ያላቸው ፍቅርና ቁጭት ሳይቀንስ ከረጅም ዓመታት ቆይታ በኋላ በ2015 ዓ.ም ወደ ገበታ በመመለስ ከ9ኛ ክፍል ጀምረው በመማር ዛሬ ለዚህ ትልቅ ሀገር አቀፍ ፈተና ለመብቃት ችለዋል።
አባባ ወልደየስ የ6 ልጆች አባት ሲሆኑ፣ የቤተሰብ ኃላፊነትንና የማህበረሰብ አገልግሎትን ከትምህርት ጉዟቸው ጋር ጎን ለጎን አስማምተው ማስኬዳቸው ልዩ ያደርጋቸዋል።
ይበልጡኑ ደግሞ ከገዛ ልጆቻቸው ጋር በአንድ የመማሪያ ክፍል ውስጥ ተቀምጠው መማራቸውና ለፈተናውም በጋራ መዘጋጀታቸው ልዩ ደስታ እንደፈጠረላቸው ይናገራሉ።
እኩዮቻቸው ወደ ጡረታ በሚገቡበት ዕድሜ መጽሐፍ አንግበው ወደ ትምህርት ቤት የተመላለሱበት ዋና ዓላማ በመንግሥት ተቀጥሮ ለመሥራት ሳይሆን፣ አሁን የሚሰሩትን የግብርና ሥራ በዘመናዊ መንገድ ለማሻሻልና በተሻለ ሁኔታ ለማምረት የሚያስችላቸውን ሳይንሳዊ ዕውቀት ለማግኘት እንደሆነ ያስረዳሉ።
ይህ አስደናቂ ታሪክ “የተማረ ሰው የሥራ ዕድል ፈጣሪ እንጂ ተቀጣሪ ብቻ መሆን የለበትም” የሚለውን ዘመናዊ ትርክት በተግባር የሚያሳይ ነው።
በትጋትና በጽናት ከተጓዙ ዕድሜ ለማንኛውም ስኬት እንቅፋት ሊሆን እንደማይችል ለሚያነበውና ለወጣቱ ትውልድ ትልቅ መነሳሻ እንደሚሆን ይታመናል።
የዩኒቨርሲቲው ህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኝነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት እንዲሁም መላው የፈተና አስተባባሪ ግብረ-ሃይል ለአባባ ወልደየስ መልካም ምኞቱን እየገለጸ፣ ይህ ፈተና የረጅም ጊዜ ራዕያቸውን የሚያሳኩበት እንዲሆን ተመኝቷል።
Via ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ
Seledadotio

23 days ago