Logo
Getu Temesgen
በጡረታ የተገለሉት አመራር ከፍተኛ ስልጣን ተሰጣቸው

*የቀድሞ የባህር ሀይሏ አመራሯ ጥቁር አሜሪካዊት ቁልፉን ተቋም ለመመራት ተሹመዋል።
#ethiopia |የአሜሪካ ሴኔት ባደረገው ምርጫ የቀድሞ የባህር ኃይል አባሏ
ዶ/ር ኤሪካ ሸዋርትዝ የአሜሪካ የበሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አድርጎ መረጠ።

ይህ ሹመት ተቋሙ ላለፈው አንድ አመት ገደማ ያህል ያለ ቋሚ መሪ በጊዜያዊ አመራር ሲመራ ከቆየ በኋላ የተሰጠ ትልቁ ሹመት ነው ተብሏል።

የቀድሞ የባህር ሀይል አባል ዶክተር ኤሪካ በታሪክ ሲ.ዲ.ሲን በመሪነት የሚያገለግሉ የመጀመርያዋ ጥቁር አሜሪካዊት ሴት አድርጓቸዋል።

ዶክተር ኤሪካ በጡረታ የተገለሉ የባህር ኃይል አመራር የነበሩ ሲሆን ቀደም ሲል የአሜሪካ የባህር ሀይል የጤና ስርዓትን በበላይነት የመሩ ብቁ የህክምና እና የአመራር ባለሙያ መሆናቸው ታውቋል።

ላለፉት 12 ወራት ያህል ቋሚ ዳይሬክተር ሳይኖረው የቆየው ሲዲሲ ለተደቀኑበት ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የጤና ስጋቶች አዲስ እና ጠንካራ አመራር ለማግኘት ያደረገው ጥረት በመጨረሻም ውጤት አምጥቶለታል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #usa #cdc #uscoastguard #drericaschwartz

1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.