Logo
Getu Temesgen
የካሙዙ ካሳ ላላ መልዕክት

ሠላም ጤና ይስጥልኝ የተከበራችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን
#ethiopia | በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ጉምቱ የተባሉ የኪነጥበብ ባለሞያዎች እና በተለያዩ የሞያ ዘርፎች ላይ አንቱታን ያተረፉ ግለሰቦች ለህዝብ ጥቅም ለሀገር መፅናት ሲሉ በፖለቲካ ተሳትፈዉ ለህዝባቸዉ ይበጃል ያሉትን ታሪክ ሰርተዋል ፣ እየሰሩም ይገኛሉ። በአለም የፖለቲካ ጉዞም ቢሆን የኪነጥበብ ባለሞያዎች እና ስፖርተኞች ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በማኅበራዊና ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ብርቱ ተሳትፎ ሲያደርጉ ቆይተዋል።

የነበራቸውን ተሳትፎ በወፍ በረር ለመቃኘት ያክል:-
————
ሴኔጋል – ኢሱኑ ንዱር (Youssou N'Dour)

በዓለም የሙዚቃ መድረክ ተወዳጁ የሴኔጋል ዘፋኝ ኢሱኑ ንዱር፣ ለረጅም ዓመታት በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ድምጹን ካሰማ በኋላ፣ በ2012 የሴኔጋል የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው ተሾመ። በዚህ ሥልጣን የሀገሪቱን ቅርስ በማስጠበቅ ወጣቶችን በማብቃት ረገድ ትልቅ አሻራ አስቀርቷል።
————-
ላይቤሪያ – ጆርጅ ዊሃ (George Weah)

ከዓለም እግር ኳስ ታላላቅ ኮከቦች አንዱ የሆነው አፍሪካዊ የባሎን ዶር ተሸላሚ ጆርጅ ዌአ፣ ከሜዳ ጡረታ በኋላ ወደ ላይቤሪያ ፖለቲካ በመግባት ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት በ2018 የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆኖ ተመረጠ። የእርሱ ጉዞ ከስፖርት ወደ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር ከሚታወቁት ደማቅ ምሳሌዎች አንዱ ነው።
—————
ናይጄሪያ – ፌላ ኩቲ (Fela Kuti)

የአፍሮቢት ሙዚቃ አባት ተብሎ የሚጠራው ናይጄሪያዊው ፌላ ኩቲ፣ በዘፈኖቹ ብቻ ሳይሆን በጠንካራ የፖለቲካ ንቅናቄውም ይታወቃል። መንግሥትን ጥሩ ሲሰራ ደግፎ በደልና ብልሹ አስተዳደርን በግልጽ ተቃዉሞ የካላኩታ ሪፐብሊክ በመባል በሚታወቀው ማኅበረሰቡ ውስጥ ተደጋጋሚ ቅጣትና እስራት ቢደርስበትም፣ የአፍሪካን የሕዝብ ተነሳሽነት በሙዚቃ አብይ ምሳሌ ሆኖ ቆይቷል።
——————
ዩናይትድ ስቴትስ – ሮናልድ ሬገን (Ronald Reagan)

ከሆሊዉድ ታዋቂ ተዋናዮች አንዱ የነበረው ሮናልድ ሬገን፣ ከስክሪን ወደ ፖለቲካ በመሻገር ከ1967 እስከ 1975 የካሊፎርኒያ ገዥ ሆኖ አገልግሏል፣ በኋላም በ1981 የአሜሪካ 40ኛ ፕሬዚዳንት ሆኖ ተመረጠ። በሁለት የሥልጣን ዘመኑ በቀዝቃዛው ጦርነት ማብቂያ ላይ ትልቅ ሚና በመጫወት፣ የአሜሪካን ኢኮኖሚ በሪጋኖሚክስ ፖሊሲ በማሻሻል ከተዋንያን ወደ ዓለም አለቃነት የተሸጋገሩ ብርቱ ምሳሌ ነዉ።
———————-
ቦብ ማርሊ (Bob Marley)

የሬጌ ሙዚቃ ምልክት ቦብ ማርሊ በዘፈኖቹ የሰላም፣ የአንድነትና የፖለቲካ ነፃነት መልእክት አሰማ። በጃማይካ ከፍተኛ የፖለቲካ ግጭት በነበረበት ወቅት ሁለት ተቀናቃኝ አንጃዎችን በአንድ መድረክ ላይ በማሰባሰብ “One Love” ኮንሰርት በማዘጋጀት ታሪካዊ ስራን ሰርቷል። ምንም እንኳ መደበኛ የፖለቲካ ሹመት ባይይዝም፣ በዓለም ዙሪያ እንደ ታላቅ የሰላም አራማጅና ተጽዕኖ ፈጣሪ ይታወሳል።
——————-//
ካሊፎርኒያ – አርኖልድ ሽዋርዜኔገር (Arnold Schwarzenegger)

በሆሊዉድ ፊልሞች ተወዳጁ የቀድሞ የሰውነት ግንባታ ሻምፒዮንና ተዋናይ አርኖልድ ሽዋርዜኔገር፣ ወደ ፖለቲካ በመግባት ከ2003 እስከ 2011 የካሊፎርኒያ ግዛት 38ኛ ገዥ ሆኖ አገልግሏል። በሁለት ወገን በተካሄደ ልዩ ምርጫ ተመርጦ፣ በአካባቢ ጥበቃና በጀት ማሻሻያ ላይ ትኩረት በማድረግ ከፊልም ስኬት ወደ እውነተኛ አመራር የተሻገረ ምሳሌ ነዉ።
———————-
ዩክሬን – ቮሎዲሚር ዘለንስኪ (Volodymyr Zelenskyy)

ዩክሬናዊው ኮሜዲያንና ተዋናይ ቮሎዲሚር ዘለንስኪ፣ በሰራዉ ተከታታይ ድራማ ውስጥ ፕሬዚዳንትን በመጫወት ታዋቂነትን ካገኘ በኋላ፣ በ2019 በእውነት የዩክሬን ፕሬዚዳንት ሆኖ ተመረጠ። ከሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ሀገሩ ከባድ ጦርነት የገጠማት ሲሆን፣ ዘለንስኪ በአለም አቀፍ መድረክ የዩክሬንን ድምጽ በማሰማት የኮሜዲ ተዋናይነትን ወደ ጀግንነት የለወጠ አመራር አሳይቷል።
———————-
ቼክ ሪፐብሊክ – ቫችላቭ ሃቬል (Václav Havel)

የቼክ ጸሐፊ፣ ተውኔት ደራሲና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቫችላቭ ሃቬል፣ በኮሚኒስት አገዛዝ ዘመን በፅሑፎቹና በተግባሮቹ የሰላማዊ አብዮት (ቬልቬት አብዮት) መሪ ሆነ። ከአገዛዙ ውድቀት በኋላ በ1989 የቼኮዝሎቫኪያ ፕሬዚዳንት ሆኖተመረጠ፣ በኋላም የቼክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሆኖ እስከ 2003 አገልግሏል። የጸሐፊነት ብልሃቱን ወደ ዴሞክራሲ ግንባታ በመምራት ከባህል ወደ ፖለቲካ ከፍተኛ ለውጥ ካደረጉ ታላላቅ ሰዎች አንዱ
ነዉ።

ኔፓል ፣ ባለንድራ ሻህ(Balendra Shah) ፣

በሰፊው እሚታወቀዉ መጠሪያዉ Balen ነዉ፣ የቀድሞ ራፐር፣ ሂፕ-ሆፕ አርቲስት እና ስትራክቸራል መሐንዲስ ሲሆን ፣ የኔፓል አዲስ ብሔራዊ መሪ ሆኖ ተነስቷል። ይህም የባለን ፓርቲ የ Rastriya Swatantra Party (RSP) በማርች 5፣ 2026 ምርጫዎች ላይ ታሪካዊ አሸናፊነትን ተጎናፅፏል።

ባለንም በኔፓል ፖለቲካ ከወጣት መሪዎች አንዱ ያደርገዋል ።

———- #እናም የኪነጥበብ ባለሞያዎች በማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ መሳተፍ ለሀገርና ለሕዝብ የጎላ ጥቅም ከማበርከት ባለፈ፣ ለኪነጥበብ ዘርፉ ከፍተኛ መነቃቃትን እንደሚፈጥር በጽኑ አምናለሁ ::ይሄም እድል ለኢትዮጵያ ኪነጥበብ እድገትም ትልቅ ሚና እንዳለው በማመንና አርቱን ሌሎች አገራት በደረሱበት ለማድረስ እንዲሁም ሀገርን በፅኑ ከማገልገል አላማ በመነሳት በተጨባጭ ለሀገር እየሰራ ነዉ ፣ ህዝቤን እና ሀገሬን ወደ ብልፅግና ማማ ያደርሳል ያልኩትን የብልጽግና ፓርቲን ወክዬ ለመወዳደር እጩ መሆኔን ሳበስር ደስታ ይሰማኛል።

—-////—-///—-
በስተመጨረሻም : እነሆ በኢትዮጵያ ታሪክ ወርቃማ ጊዜ ላይ እንገኛለን
የኢትዮጵያ ስብራቶች እየተጠገኑ ነው። በኢትዮጵያ እምቅ ሀብቶች እየወጡ ነው።
የኢትዮጵያ ጂኦ ፓለቲካዊ ቁመና እየተቀየረ ነው፣
ሀገር በምክክር እና በሽግግር ፍትህ ቁርሾዋን እየሻረች፣ ነገዋን እየተለመች ነው፣
ኢትዮጵያ በብዙ ነገሮች እራስዋን የመቻል ዕቅዷን እያሳካች ነው፣
የኢትዮጵያ ህልም እውን ሆኖ፣ ሁለንተናዊ ብልፅግና በኢትዮጵያ እንዲረጋገጥ፣ ጉዞው በውጤት ተጀምሯል።
ይሄን ውጤታማ ጉዞ ይበልጥ ለማሳካት ብልፅግናን መምረጥ ወሳኙ ነገር ነው።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ!!!
ካሙዙ ካሣ

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.