(ዘ-ሐበሻ ዜና) በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ ይፋ የተደረገው አዲሱ ፕሮጀክት፣ ለረጅም ጊዜ በህዝብ ዘንድ ሲያስነሳ የነበረውን ወቀሳ ለመቅረፍ ያለመ ነው። ኩባንያው የባህር ዳሩን ታሪካዊ ጣና ሆቴል ከገዛ በኋላ ግንባታ ሳይጀመርበት መቆየቱን ተከትሎ ሲቀርብበት የነበረውን ትችት በማስቀረት፣ ሆቴሉን ወደ አለም አቀፍ ደረጃ ለማሳደግ ዛሬ በይፋ ስራ መጀመሩን አብስሯል።
አቶ ጀማል በንግግራቸው እንዳብራሩት፣ይህ ግንባታ የአለቃቸውን (የሼክ መሀመድ ሁሴን አል አሙዲን) ራዕይ ለማሳካት እና የመንግስትን የቱሪዝም ልማት ምሰሶ ለመደገፍ ታቅዶ የተጀመረ ነው። ፕሮጀክቱ በአገር በቀል ኢንጂነሮች እና በማርዮት ዓለም አቀፍ ሆቴል ቴክኒካል ድጋፍ የሚገነባ ሲሆን፣ በ18 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ቃል ተገብቷል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው አያይዘውም፣ ከዚህ ቀደም አንድ ባለስልጣንን "ጀማል አንተ እርሻ)ላይ ጎበዝ ነህ፣ ሆቴል ግን አትችልበትም" ብለው ላነሱባቸው ወዳጃዊ ትችት፣ ጡረታ ከመውጣታቸው በፊት በሆቴል ዘርፍም ስኬታማ መሆናቸውን በተግባር እንደሚያሳዩ አረጋግጠዋል። ኢትዮጵያ ከሼክ መሀመድ በፊት ከሂልተን ውጭ አለም አቀፍ ሆቴል እንዳልነበራት ያስታወሱት አቶ ጀማል፣ ሸራተን አዲስ ሲገነባ "እብደት ነው" ይባል እንደነበር በማስታወስ አሁንም ሚድሮክ በቱሪዝሙ ዘርፍ ትልቅ አብዮት እያመጣ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሚድሮክ ከዚህ ፕሮጀክት ባሻገር በሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ ግዙፍ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል። አቶ ጀማል እንዳስታወቁት፣ ኩባንያቸው አስር የማርዮት ሆቴሎችን ለመገንባት ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን፣ እነዚህንም ሆቴሎች በፍራንቻይዝ ለማስተዳደር "ዘ ፈርስት ግሩፕ" የተሰኘ ትልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያ ጋር ውል አስሯል።
በተጨማሪም የዌስቲን ሆቴል ግንባታ በዘንድሮው ወይም በሚቀጥለው የፈረንጆች አመት መባቻ ተጠናቆ ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል። ቀድመው የተጀመሩት የጅማ እና የሀዋሳ ፕሮጀክቶችም በፍጥነት እየተሰሩ መሆኑን የገለጹት ዋና ስራ አስፈፃሚው፣ የባህር ዳሩ አቫንቲ ሆቴልም ወደ "ፕሮቲያ ባይ ማርዮት" ለመቀየር በቅርቡ ስራ እንደሚጀመር ያላቸውን ተስፋ አጋርተዋል።

1 month ago