23 hours ago
በረከቷ ይደርብንና ሲንጋፖር ህጻናቶቿን በገንዘብ እየደገፈች ነው
#ethiopia | ሲንጋፖራውያን ሦስት እና ከዚያ በላይ ልጆችን እንዲወልዱ ለማበረታታት ታስቦ በተጀመረው አዲስ የመንግሥት የገንዘብ ድጋፍ መርሐግብር፣ በመጀመሪያው ዓመት ውስጥ ብቻ ወደ 5,000 የሚጠጉ ህጻናት ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል።
በሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ ባለፈው ዓመት ይፋ በተደረገው ‘የትላልቅ ቤተሰቦች መርሐግብር’ መሠረት፣ ከየካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለሚወለድ ሦስተኛና ከዚያ በላይ ለሆነ እያንዳንዱ ልጅ ቤተሰቦች እስከ 16,000 የሲንጋፖር ዶላር (12,427 የአሜሪካ ዶላር) የሚደርስ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ።
ይህ የድጋፍ ማዕቀፍ የረጅም እና የአጭር ጊዜ የገንዘብ እፎይታን የሚሰጥ ሲሆን፣
ለልጁ አካውንት የሚደረግ የ10,000 የሲንጋፖር ዶላር ድጋፍ ገንዘቡ ለልጁ ወይም ለእህትና ወንድሞቹ የቅድመ-መደበኛ ትምህርት እና የጤና እንክብካቤ ወጪዎችን ለመሸፈን ይውላል።
ለእያንዳንዱ አዲስ ለሚወለድ ልጅ ከሚሰጠው መደበኛ የ5,000 ዶላር ድጋፍ በተጨማሪ፣ በቀጥታ በእናቲቱ አካውንት ውስጥ የሚገባ ተጨማሪ 5,000 የሲንጋፖር ዶላር ይሰጣል። ይህም ከእርግዝና፣ ከወሊድ፣ እንዲሁም ከቤተሰብ አባላት የሕክምና ወጪዎች ጋር የተያያዙ ክፍያዎችን ለመሸፈን ያገለግላል።
መሥፈርቱን የሚያሟሉ ህጻናት ዕድሜያቸው ከአንድ እስከ ስድስት ዓመት እስኪደርስ ድረስ በየዓመቱ የ1,000 የሲንጋፖር ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ። ይህ ደግሞ እንደ አስቤዛ፣ የውሃና መብራት ክፍያዎች፣ እንዲሁም የትራንስፖርት ወጪዎችን የመሳሰሉ የእለት ተእለት የቤተሰብ የኑሮ ጫናዎችን ለማቃለል ያለመ ነው።
የሲንጋፖር የማህበራዊ እና ቤተሰብ ልማት ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ለ‘ዘ ስትሬትስ ታይምስ’ ጋዜጣ እንደገለጹት፣ እስከ መጋቢት ወር ድረስ ወደ 5,000 የሚጠጉ ህጻናት የተሻሻለውን የልጆች ዕድገት እና የሕክምና የገንዘብ ድጋፎችን በተጨባጭ አግኝተዋል።
መርሐግብሩ ከየካቲት 2025 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ሦስተኛና ከዚያ በላይ ልጅ የነበራቸው ቤተሰቦችም ከዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ። እነዚህ ቤተሰቦች ከጥር 1 ቀን 2019 እስከ የካቲት 17 ቀን 2025 የተወለደ ልጅ ካላቸው፣ የተወሰኑ ቅድመ-ሁኔታዎችን አሟልተው የዓመታዊ የገንዘብ ድጋፉ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ በዘገባው ተመላክቷል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

1 day ago
✨መልካም የእረፍት ቀን!
በቅዳሜና እሑድ የዳታ ጥቅሎች የእረፍት ቀንዎን ከቤተሰብዎ ጋር በደስታ ያሳልፉ።
💁♂️ በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/telebir... ያገኟቸዋል፡፡
#weekendpackage #ethiotelecom #telebirr #telebirrsuperapp #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

ምክክር፦ ብቸኛው የፈተናዎቻችን ማለፊያ
*****************
ኢትዮጵያ በዘመናት ፈተና ውስጥ አልፋ ለዛሬ የደረሰችው በሕዝቦቿ ልዩ መስተጋብር እና ጥብቅ አንድነት ነው።
ታሪካችንን ወደኋላ ስንቃኝ በሕብረት ጦርነቶችን አሸንፈን የጋራ ነጻነታችንን ያስከበርን፣ በአንድ መሶብ ዙሪያ ከብበን በጋራ የበላን፣ "እኔ ልደፋልህ/ልደፋልሽ" መባባልን የመሰለ ድንቅ ባህል ያዳበርን ሕዝቦች ነን።
ሀገር በባዕዳን ተደፈረች ሲባል የውስጥ ልዩነታችንን ወደ ጎን ትተን ወደ ጦር ሜዳ የተመምነው እና ኢትዮጵያን በፈተናዎች ውስጥ ጠብቀን ያኖርነው በዚህ የጋራ ሥነ-ልቦና ነው።
ይሁን እና ይህ ሁሉ ታሪክ እያለን ዛሬ ላይ "በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብለን በመመካከር ችግሮቻችንን መፍታት ለምን ተሳነን?" የሚለው ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ የሚሻ ጉዳይ ነው።
የዘመናዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ አመጣጥ ከታሪካዊ እሴቶቻችን ጋር በእጅጉ የተላተመ ነው። የፖለቲካው ስብራት ያመጣው ትልቁ መጥፎ ጠባሳ የጋራ ትርክትን አዳክሞ የልዩነት፣ የመጠፋፋት እና የጥላቻ ትርክትን ማንገሡ ነው።
አንዱን አግልሎ እና ሙሉ ለሙሉ አሸንፎ ሥልጣን ላይ የመውጣት የዜሮ ድምር ፖለቲካ የኢትዮጵያ ትልቁ በሽታ ነው።
ይህ አካሄድ እርስ በርስ የመደጋገፍና ችግርን የመካፈል መልካም ባህላችንን በመሸርሸር፣ “እኔ ካልመራሁ ሀገር ትፍረስ” ወደሚል አደገኛና ራስ ወዳድነት የተሞላበት አስተሳሰብ አሸጋግሮናል።
ይህ የውስጥ መከፋፈልና ቀውስ ደግሞ ለውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነትና ተፅዕኖ ሰፊ በር ከፍቷል።
ኢትዮጵያ በዚህ የታሪክ አዙሪት ውስጥ ስታልፍ ሥጣኔዋን ማስቀጠል ተስኗታል። በሕብረት ለነጻነት በጦር የተዋደቁት ልጆቿ ድህነትን ለማጥፋት ባለመተባበራቸው የተሟላ ሉዓላዊነቷን ማረጋገጥ ተስኗት ኖራለች።
የሚያሳዝነው እውነታ ይህን የፖለቲካ ቋጠሮ ለመፍታት የሚያስችል ለዘመናት የኖረ ድንቅ ሀገር በቀል የሽምግልና እና የዕርቅ ባህል እያለን በበቂ ሁኔታ አለመጠቀማችን ነው።
ችግሮቻችንን ከማኅበረሰባዊ እሴቶቻችን፣ ከሃይማኖት አባቶች ተሰሚነት እንዲሁም እንደ ገዳ፣ የጆካ፣ አባጋር፣ መካባን ከመሳሰሉ ጠንካራ ማኅበረሰባዊ የፍትሕ እና የዕርቅ ሥርዓቶቻችን ማዕቀፍ ውጪ በሆነ መንገድ ለመፍታት መሞከራችን ከባድ ዋጋ አስከፍሎናል።
ከውጭ በገቡ ፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለሞች ብቻ ለመጓዝ መሞከራችን እና ባህላዊ የዕርቅ ሥርዓቶቻችንን ከፖለቲካ መጠቀሚያነት ነጻ አድርገን አለማጎልበታችን ለዛሬው የውይይት ባህል መጥፋት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል።
ታዲያ አሁን ምን ማድረግ አለብን?
መፍትሔው ወደ አውዳችን መመለስ ነው። የውጭ ተፅዕኖን ለመቋቋም መጀመሪያ የራስን ቤት ማጽዳት እና ሕብረትን ማጠናከር የግድ ይላል።
ፖለቲከኞች እና የሐሳብ መሪዎች የመሸናነፍ ሳይሆን የመደማመጥ እንዲሁም ለሀገር ሰላም ሲሉ ግትር የሆነ አቋምን የማለዘብ ባህልን በተግባር ሊያሳዩ ይገባል።
በተለይም ወጣቱ ትውልድ በዲጂታሉ ዓለም ያለውን ስሜታዊነት ወደ ጎን በመተው ምክንያታዊ ውይይቶችን ሊያበረታታ ይገባል።
ሚዲያው፣ የትምህርት ሥርዓቱ፣ የኪነ-ጥበብ ዘርፉ ካለፉት ቁስሎች ይልቅ ወደ ፊት በሚያገናኙን የጋራ እሴቶች እና የወደፊት ዕጣ ፈንታችን ላይ ሊያተኩር ግድ ይላል።
በዚህ ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ላይ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሚና እጅግ የጎላ ነው። ኮሚሽኑ የጠፋውን የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ለመመለስ የተዘረጋ ዘመናዊ የቤተሰብ መሶባችን ሊሆን ይገባዋል።
አሁን የተጀመሩት የምክክር ሂደቶች ሁሉን አሳታፊ፣ ከፖለቲካዊ ጨዋታ ነጻ የሆኑ እና እውነተኛ ማኅበረሰባዊ ስብራቶቻችንን የሚጠግኑ እንዲሆኑ የሚቻለው ሁሉ ተደርጓል።
ሀገራዊ ምክክሩ ባህላዊ የዕርቅ እሴቶቻችንን ከዘመናዊ የመንግሥት ግንባታ ጋር አዋሕዶ የዘለቄታ ሰላም የምናመጣበት ታላቅ ዕድል ነው።
በጠረጴዛ ዙሪያ የማይፈታ የትኛውም የፖለቲካ ችግር በጦር ሜዳ ዘላቂ መፍትሔ እንደማያገኝ ታሪካችን ከበቂ በላይ አስተምሮናል።
በመሆኑም ሁላችንም ወደኋላ ከጎተተን የ“እኔ እበልጥ” ክፉ ልማድ ወጥተን ለምክክሩ ስኬት የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #nationaldialogue #dotstream #peacebuilding #nationalunity

2 days ago
🏢 አዲስ እይታ፣ አዲስ ሕይወት — ከ Ultima Real Estate ጋር!
የቤተሰብዎን የ ሕልም ቤት እውን የሚሆንበት ወርቃማ ዕድል! በአዲስ አበባ እምብርት፣ በውኗ መስቀል ፍላወር ላይ የተገነቡት ዘመናዊ እና ቅንጡ አፓርታማዎቻችን ለእናንተ ዝግጁ ናቸው።
ለልጆችዎ ምቾት እና አስተማማኝ ነገን ለመፍጠር ዛሬውኑ ይወስኑ።
💥10% ቅድመ ክፍያ ብቻ!
ቀሪውን ረዘም ባለ የክፍያ አማራጭ።
የላቀ ጥራት፣ አስተማማኝ ደህንነት እና ማራኪ እይታ በአንድ ላይ።
📞 አሁኑኑ ይደውሉና የሕልምዎን ቤት ይረከቡ!
📱 +251 996 000 000
📱 +251 995 222 222

Sponsored by
Surafel
2 days ago
እባካችሁ በኦቲዝም ስም አትነግዱ!
"ከወላጆች አይን እንባ በዝታለች፣ እግዚአብሄርም ያያል !"
( መላኩ ብርሃኑ)
ኢትዮጵያ ውስጥ ኦቲዝም "እጅግ በጣም ውድ" ችግር ነው፡፡ ከኦቲዝም ጋር በተያያዘ የወላጅን ሸክም ለማቅለል የተዘረጋ ምንም አይነት ስርዓት ስለሌለ ኦቲዝም ወደአንድ ቤት ሲመጣ የዚያ ቤት ህይወት ከመሰረቱ ይናጋል።
ልጆቹ የሙሉ ጊዜ ጥበቃ ስለሚያስፈልጋቸው ወላጅ እየሰራ ከሆነ ስራውን፣ እየተማረ ከሆነም ትምህርቱን ለመተው ይገደዳል። ይህ ደግሞ ለኦኮኖሚ ጫና፣ ለስነልቡና ቀውስ፣ ለማህበራዊ ግንኙነት መዳከምና አልፎ ተርፎም ለከባድ የጤና ቀውስ ይዳርጋል።
እስኪ አስቡት !
ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ልጅ ኦቲዝም እንዳለበት ለመመርመር (Diagnose) ለማድረግ የላብሯቶሪ ወጪውን ሳይጨምር ለህክምና ባለሙያው ብቻ የሚከፈል እስከ 20 ሺህ ብርና ከዚያ በላይ ይደርሳል።
እስከ 25 ሺህ ብር የሚደርስ የሃገር ውስጥ ምርመራን እንተወውና እንደ yeast overgrowth, heavy metal test, OAT test, FRAT test ውጪ ልኮ ለማሰራት ከ100 -200 ሺህ ብር በላይ ይጠየቃል።
ኦቲዝም ያላቸው ልጆች ብዙውን ጊዜ ከአንጀታቸው ጋር የተያያዘ የጤና ችግር አለባቸው ተብሎ ስለሚታመን 'ግሉቲን እና ኬዚን' የሚባሉ ንጥረነገሮች ካሏቸው ምግቦች ነጻ መሆን አለባቸው። እኛ ሃገር ደግሞ “ግሉቲን ፍሪ፣ ኬዚን ፍሪ” የሚባሉት የምግብ አይነቶች በአቅርቦት ደረጃ ውስንና በጣም ውድ ናቸው።ከሰንዴ ዘርና ከወተት መራቅ አለባቸው።
ለነሱ የሚሆን ወተት ለመስራት የሚጠቅም አንድ ኪሎ 'አልመንድ' የሚባል ፍሬ በትንሹ እስከ 5 ሺህ ብር ያስወጣል። ምግባቸው ውድ በሆነው የንጹህ የወይራ ዘይት ካልሆነ በቀር በሌላ መሰራት አይችልም። ስኳርና ሰውሰራሽ ማጣፈጫ ስለማይጠቀሙ በምትኩ ቴምር ለመግዛት በኪሎ ከ1500-3500 ብር ድረስ ይጠይቃል።
በዚህ ሳቢያ ልጆቹ የሚወስዱት ምግብ አይነት ስለሚያንስ እንዳይጎዱ ሲባል 'ሰፕሊመንት' ያስፈልጋቸዋል። ለምሳሌ ለነሱ የሚሆን የአሳ ዘይት ዋጋው ከ 12 ሺህ እስከ 35ሺህ ብር ይሸጣል። ለጥቂት ቀን ብቻ የሚሆን ቫይታሚን ዲ ደግሞ እስከ 5 ሺህ ብር ይሸጣል። አቅም ላለው ወላጅ እንኳን ሌሎች ሌሎች ተጨምረው የሰፕሊመንት ዋጋ ብቻ በወር ከ50 ሺህ ብር በላይ ያስወጣዋል።
በአጠቃላይ ለአንድ ኦቲዝም ላለበት ልጅ የሚወጣው የአንድ ወር የምግብ ወጪ አንድ ቤት ውስጥ ለሙሉ ቤተሰብ ከሚወጣው የቀለብ ወጪ ይበልጣል።
ኦቲዝም በሽታ ስላልሆነ መድሃኒት የለውም፡፡ ለኦቲዝም የሚደረገው ድጋፍ በአብዛኛው የንግግር፣ የባህሪና የአካልና ሰውነት ቅንጅት ቴራፒ ነው፡፡ እዚህ ጋር ደግሞ ነጋዴዎቹ ተሰብስበዋል።
የሚችሉትም የማይችሉትም የሆነች ዛኒጋባ ተከራይተው እንሰጣለን ለሚሉት ተራፒ የሚያስከፍሉት ዋጋ በጣም ውድ ነው። ለአንድ ልጅ በወር 30 ሰዓት ቴራፒ ለመስጠት የሚከፈለው ገንዘብ የአንድ ልጅን የ6 ወር የግል ትምህርት ቤት ክፍያ ይበልጣል።
በቁጥር ጥቂት የሆኑት 'የልዩ ፍላጎት አካቶ' ያላቸው ትምህርት ቤቶች ክፍያ ዋጋ ደግሞ አይወራ። ታዋቂ ነን የሚሉት አንዳንዶቹ ትምህርት ቤቶች በወር እስከ 100 ሺህ ብር ያስከፍላሉ። በጨበጣ ያለምንም እውቀት ኦቲዝምን ቢዝነስ ያደረጉ አንዳንድ ነጋዴ ግለሰቦች የከፈቱት ትምህርት ቤት ደሞ አለ። አዳሪ ብለው እስከ 300ሺህ ብር በወር ያስከፍላሉ።
ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤቶች እንኳን የማያስከፍሉትን አይነት ገንዘብ የሚያስከፍሉ አካቶ ት/ቤቶችና በኦቲዝም ስም የተቋቋሙ ተቋማት በጣም ብዙ ናቸው፡፡
በዚህ ላይ ልጁ ትምህርት ቤት ሲሄድም ሆነ ሲመለስ ሰርቪስ የሚጠቀም ከሆነ ወላጆች ለመጓጓዣው ከመደበኞቹ ህጻናት በእጥፍ እንዲከፍሉ ይደረጋሉ፡፡
ይህን ይህን ሳይ በሃገሬ ተስፋ እቆርጣለሁ። ስርዓት ያልተዘረጋለት፣ ደንብና ህግ ያልወጣለት፣ በሙስና ሰንሰለት የተጨማለቀ ፣ ከኤንጂኦ እስከ ግለሰቦች ድረስ በኦቲዝም ስም የጦፈ ንግድ ሲካሄድ ሃይ ባይ የታጣበት ሃገር ላይ ነን ያለነው።
እንደኔ ጠለቅ ብሎ ለሚያየው እዚህ ዘርፍ ላይ ያለው መጨመላለቅና ብዝበዛ በጣም ይሰቀጥጣል፡፡
መቼም በጥቂቱ ካነሳሁት እውነት አንጻር በዚህ ዘመን የኑሮ ውድነት አንድ ወላጅ ቤት ኦቲዝም ሲደረብበት በስነልቡናም፣ በገንዘብም ምን ያህል ከባድ የህይወት መርግ እንደሚፈጥር ካሰባችሁት ይበቃል፡፡
እናንት 'ሞራል አልባ' ነጋዴዎች! እንዲህ ባለ 'ውድ' ችግር ላይ አይናችሁን አጥባችሁ ገንዘብ ለማጋበስና መሄጃ አጥቶ የተቸገረውን ወላጅ ለመበዝበዝ እንዴት ህሊናችሁ እሺ አላችሁ ግን? (በርግጥ ህሊና የላችሁም!)
በጣም ነው የሚያሳዝነው፡፡ይህ'ኮ ኢሰብአዊነት ነው። ወንጀል ነው። የሞራል ዝቅጠት ነው። ዛሬ ከኔ ባልተሻለ ጥቂት ንባብ ብቻ ተነስታችሁ ቤት ተከራይታችሁና ማዕከል ከፍታችሁ ‘ባለሙያ ነን’ እያላችሁ 'ቢዝነስ' የምትሰሩ ፣ ቲክቶኩንና ሶሻል ሚዲያውን ያጣበባችሁ ሰዎች ... ምናችሁን ነው የሚያማችሁ? ነገ'ኮ ይህ በህጋዊነት ሽፋን ያለቁጥጥር በተለቀቀ ሜዳ ላይ ስትፋንኑ የበደላችሁት ወላጅ እንባ ቤታችሁ ድረስ ይመጣል።
ኦቲዝም ላይ እንሰራለን ብላችሁ የምትደሰኩሩ ሃኪሞችምም፣ ሳይኮሎጂስቶችም፣ ቴራፒስቶችም፣ አካቶ ትምህርት ቤቶችም፣ማዕከላትም ቆም ብላችሁ ብታስቡ ይበጃችኋል!
ይህ ምርጫ ያጣ… ተመልካች ያጣ፣ ልጄ ቢሻሻልልኝ ብሎ እዚህም እዚያም መፍትሄ ፍለጋ የሚኳትን ወላጅ በኦቲዝም ምክንያት ጥሪቱን አሟጦ ሌሎች ልጆቹን የሚያሳድግበትና ቤቱን የሚመራበት ገንዘብ እስኪያጣ ድረስ ሲቸገር እናንተ አላግባብ በዘረፋችሁት ገንዘብ ሰላም፣ ጤናና የሰላም እንጀራ አይኖራችሁም ።
አያሳዝናችሁም ግን ? በናንተ የዋጋ ውድነትና ሳቢያ አቅም አጥቶ ዕድሜውን ሙሉ ‘ለልጄ ይህንን ሳላደርግለት’ ብሎ በጸጸት እንባ የሚታጠብ ወላጅ ግን አያሳዝናችሁም?
በዚህ ወላጅ ላይ ህይወት ላይ እየተጫወታችሁ እስከመቼ ራሳችሁን ታበለጽጋላችሁ ?
አንድ ቀን ግን ይመጣል! አላግባብ ለምትሰበስቡት ትርፍ አንድ ቀን እግዚአብሄር ይፈርድባችኋል ! የወላጅ እንባ በቤታችሁና በልጆቻችሁ ላይ ይመጣል። ያኔ እናንተም ቁጭ ብላችሁ ታለቅሳላችሁ !
(ማሳሰቢያ ፤ ይህ ጽሁፍ በሃቅ የሚሰሩ፣ ልጆቹንና ወላጆችን ለመርዳት የሚለፉትን ባለሙያዎች አይመለከትም)
ሜርድ!!

🎁✨ ለምንወዳቸው ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ከቴሌብር ስጦታ በመግዛት እናበርክትላቸው!
በስጦታ:-
💰 የዲጂታል ሳንቲሞችን በቴሌብር መግዛት
🎉 ለጓደኞችና ለቤተሰብ ስጦታዎችን መላክና መቀበል (ከውጭ ሀገር መቀበል)
💵 የተቀበሉትን የዲጂታል ሳንቲሞች ወደ ገንዘብ መቀየር
🤝 የበጎ አድራጎትና የገቢ ማሰባሰቢያ በቀላሉ መክፈትና መደገፍ ይችላሉ።
በድረ-ገጽ https://web.sitota.et ፣ በቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/3S1hQqd ወይም በራሱ መተግበሪያ https://bit.ly/4lfevOH ያገኙታል!
#sitota #digitalgift #ethiotelecom #telebirr #telebirrsuperapp #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

3 days ago
የስልሳ ዓመታት የታማኝነት ጉዞን የሚዘክር የቤተሰብ እና የአንድነት የጎዳና ላይ ሩጫ ሊካሄድ ነው
#ethiopia | ኮሜርሺያል ኖሚኒስ የስልሳ ዓመታት የሥራ ጉዞውን እና የቆየ የታማኝነት አገልግሎቱን ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀው የጎዳና ላይ ሩጫ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
በተቋሙ አዘጋጅነት የሚከናወነው በዚህ የ5 ኪሎ ሜትር የነፃነት እና የአንድነት መርሃ ግብር ላይ የድርጅቱ ሠራተኞች፣ ደንበኞች፣ አጋር ድርጅቶች እና የባለድርሻ አካላት በጋራ ይሳተፋሉ።
የዝግጅቱ ዋና ዓላማ በተጠቃሚው ማህበረሰብ፣ በሠራተኞች እና በደንበኞች መካከል ያለውን ማህበራዊ ትስስር ይበልጥ ማጠናከር እና ቤተሰባዊ መቀራረብን መፍጠር ነው።
ለሩጫው የተዘጋጁ ቲሸርቶችን በኮሜርሺያል ኖሚኒስ ዋና መሥሪያ ቤት እና በአዲስ አበባ በሚገኙ በተመረጡ ቅርንጫፎች ማግኘት ይቻላል።
እያንዳንዱ ቲሸርት በ500 ብር የሚሸጥ ሲሆን፣ ክፍያውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000770855237 (CN for Event Management) ወይም በሲቢኢ ብር መፈጸም ይቻላል።
ቲሸርቶቹን ለማግኘት እና መረጃ ለመጠየቅ በሚከተሉት የቅርንጫፍ ስልክ ቁጥሮች ማነጋገር ይቻላል
ዋና መሥሪያ ቤት +251-932-151385
መገናኛ ቅርንጫፍ +251-913-597811
ቦሌ ቅርንጫፍ +251-913-076712
አራዳ ቅርንጫፍ +251-921-853930
ሳሪስ ቅርንጫፍ +251-912-082257
የካ ቅርንጫፍ +251-910-163606
መርካቶ ቅርንጫፍ +251-951-104612
ልደታ ቅርንጫፍ +251-913-612395
ኮልፌ ቅርንጫፍ +251-911-917647
ቂርቆስ ቅርንጫፍ +251-911-827569
ቃሊቲ ቅርንጫፍ +251-931-272727
የሩጫው መነሻ መስመር ከአትላስ መኪና ማቆሚያ ተነስቶ ወደ ኡራኤል ቤተክርስቲያን አደባባይ ከመድረሱ በፊት ወደ ግራ በመታጠፍ ወደ አትላስ ኢንተርናሽናል ሆቴል ያመራል።
በመቀጠልም በቦሌ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን እና በሸገር ሕንፃ አጠገብ አልፎ መድረሻውን ድጋሚ በአትላስ መኪና ማቆሚያ ያደርጋል።
ይህ ታላቅ ስፖርታዊ መርሃ ግብር ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የሚከናወን ይሆናል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
በ6630 ነፃ የስልክ መስመር
ወይም
በ0932151385 እና በ0904032498
ደውሎ መረዳት ይቻላል።
#commercialnominees #familyrun #healthylifestyle #running #community #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

12ኛ ዙር የደም ልገሳ መርሃ ግብር
የዓለም የደም ለጋሾች ቀን እና
የተስፋ አዲስ ቤተሰቦች 3ኛ ዓመት በዓል ማክበር
📅 ሰኔ 6 እና 7, 2018 ዓ.ም.
📍 በኢትዮጵያ 20 + ከተሞች
አንድ የደም ልገሳ እስከ ሦስት ሰዎች ሕይወት ሊያድን ይችላል። በየቀኑ በሆስፒታሎቻችን ውስጥ ለቀዶ ሕክምና፣ ለአደጋ ተጎጂዎች፣ ለካንሰር ታማሚዎች፣ ለእናቶች እና ለሌሎች በርካታ ሕሙማን ደም በአስቸኳይ ያስፈልጋል።
ይህ 12ኛው ዙር የደም ልገሳ መርሃ ግብር የተስፋ አዲስ ቤተሰቦች ለ3 ዓመታት ሲያከናውኑት የቆየውን የሰብዓዊነት ጉዞ የሚያከብር ሲሆን፣ በዓለም የደም ለጋሾች ቀን ላይም ለሕይወት አዳኝ ለጋሾች የምስጋና መልዕክት ያስተላልፋል።
እርስዎ የሚለግሱት ደም ለአንድ ቤተሰብ ተስፋ፣
ለአንድ ታማሚ ሕይወት፣
ለአንድ እናት ፈገግታ፣
ለአንድ ልጅ ነገን ሊሰጥ ይችላል።
🤝 ሁላችንም በጎ ፈቃደኞች፣ ወጣቶች፣ ቤተሰቦች፣ ተቋማት እና ማኅበረሰቡ በአጠቃላይ በዚህ ታላቅ የሕይወት ማዳን ተግባር እንዲሳተፉ በክብር እንጋብዛለን።
🩸 ደም መለገስ ሕይወት መስጠት ነው!
ኑ! በደማችን አዲስ ታሪክ እንፃፍ! ❤️🩸
#worldblooddonorday #የደም_ልገሳ #ተስፋ_አዲስ_ቤተሰቦች #donatebloodsavelives #20ከተሞች_አንድ_ዓላማ #ሕይወትን_እናድን

✨🎁 ዑምራ ሮሚንግ ጥቅል!
ከመደበኛ ታሪፍ በ10% ቅናሽ የቀረቡትን የዑምራ ሮሚንግ ጥቅሎችን በመግዛት ከቤተሰብዎ፣ ወዳጅዎና የሥራ አጋሮችዎ ጋር እንደተገናኙ ይቆዩ!
👉 ጥቅሎቹን ለመጠቀም የሮሚንግ አገልግሎትዎን ያስጀምሩ!
✅ በቴሌብር፣ በ *999# ፣ በማይ ኢትዮቴል እንዲሁም በአርዲ ቻትቦት ያገኗቸዋል፡፡
🔗 ለተጨማሪ መረጃ: https://bit.ly/41k72p0
#ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

የዓለም ዋንጫ : በኮካ ኮላ
#ethiopia | የዓለም ዋንጫ መክፈቻን አስመልክቶ የኮካ ኮላ ኩባንያ ያዘጋጀው ደማቅ የምሽት መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል እየተካሄደ ነው
የኮካ ኮላ ኩባንያ ከፊፋ የዓለም ዋንጫ ጋር የዘለቀውን የግማሽ ክፍለ ዘመን ታሪካዊ አጋርነት ለመዘከርና የዘንድሮውን 23ኛውን ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ውድድር መጀመር ለማብሰር ያዘጋጀው ልዩ የክብር ምሽት በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ይህ ታላቅ መርሃ ግብር በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የስፖርት አፍቃሪዎች የውድድሩን መክፈቻ ስነ ስርዓትና የመጀመሪያ ጨዋታ ለመታደም በአንድነት ከሚሰበሰቡበት ታሪካዊ ቅጽበት ጋር ተስማሚ በሆነ መልኩ እየተከናወነ ነው።
በዚህ ማራኪ ድባብ ባለው መድረክ ላይ በርካታ ታዋቂ ሰዎች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ የስፖርት ቤተሰቦችና ጋዜጠኞች ተገኝተው ምሽቱን በልዩ የሙዚቃ ዝግጅቶች፣ የፈጠራ ስራዎችና የተለያዩ መዝናኛዎች እያደመቁት ይገኛሉ።
በመርሐግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮካ ኮላ ሲኒየር ማርኬቲንግ ማናጀር ሜሮን ብርሃኑ እግር ኳስ ከስፖርትነቱ ባለፈ ሰዎችን በጋራ ስሜትና ፍቅር የሚያስተሳስር ሁለንተናዊ ቋንቋ መሆኑን ገልጸዋል።
የ2026ቱ የፊፋ የዓለም ዋንጫ በታሪክ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሀገራትና ጨዋታዎች የሚስተናገዱበት ግዙፍ ውድድር መሆኑን የጠቆሙት ማናጀሯ፣ ኮካ ኮላ ትርጉም ባላቸው አቀራረቦች የኢትዮጵያን እግር ኳስ አፍቃሪዎች ከውድድሩ ደስታ ጋር ይበልጥ ለማገናኘት ቁርጠኛ መሆኑን አብራርተዋል።
በሌላ በኩል የኮካ ኮላ ቢቨሬጅስ አፍሪካ ተወካይ በበኩላቸው ኩባንያው በኢትዮጵያ ስላለው ጠንካራ ተሳትፎና ምርት ስርጭት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ አምስት ፋብሪካዎች እንደሚንቀሳቀሱና ከእነዚህም ውስጥ በአዲስ አበባ፣ ሰበታ፣ ባሕር ዳር እንዲሁም በድሬዳዋ የሚገኙት አራቱ ፋብሪካዎች የኮካ ኮላ ምርቶችን በሙሉ አቅማቸው እያመረቱ ለገበያ እያቀረቡ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
ከማሸጊያ ጋር በተያያዘም ለተለያዩ የደንበኞች ፍላጎት ተስማሚ የሆኑ ከ300 ሚሊ ሊትር ተመላሽ የብርጭቆ ጠርሙስ ጀምሮ ለጉዞ የሚመቹ የ350 እና የ500 ሚሊ ሊትር እንዲሁም ለቤተሰብና ለስብሰባዎች የሚሆኑ የ1.5 ሊትር የፒኢቲ ማሸጊያዎችን እያቀረቡ መሆኑን አስረድተዋል።
የዓለም ዋንጫውን ታላቅ ስሜትና የኮካ ኮላን ደማቅ ድባብ በቀጥታ ወደ እናንተ ማድረሳችንን እንቀጥላለን።
ውጤት
60" ሜክሲኮ 1 - 0 ደቡብ አፍሪካ
#worldcup #cocacola #football #skylighthotel #fifaworldcup #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

4 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የ2026ቱ የ"ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ" (Miss World Ethiopia) ዘውድ አሸናፊ የሆነችው ሩት ይርጋለም፣ ወጣቶች ለስኬት እንዲተጉ፣ እንዲሁም በሕፃናት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል ማኅበረሰቡ በጋራ እንዲቆም ጥሪ አቀረበች።
ሩት ይህንን መልእክት ያስተላለፈችው በአዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ማዕከል ውስጥ በተዘጋጀ የልምድ ልውውጥ እና አነቃቂ መድረክ ላይ ለተገኙ ወጣቶች እና ተጋባዥ እንግዶች ባደረገችው ንግግር ነው።
ላለፉት ስድስት ዓመታት በሞዴሊንግ ዘርፍ ውስጥ ማሳለፏን የገለጸችው ሩት፣ የ"ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ" ዘውድን ከመድፋቷ በፊት ፊሊፒንስን ጨምሮ በተለያዩ ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያን ወክላ ተሳትፋለች። ይሁን እንጂ ስኬቷ በአቋራጭ የመጣ አለመሆኑን ያስረዳችው አሸናፊዋ "እዚህ ደረጃ ለመድረስ አሥር ጊዜ ወድቄያለሁ (ተሸንፌያለሁ)፤ ስኬት የዕድል ወይም የተሰጥኦ ብቻ ጉዳይ ሳይሆን የጽናት እና የጠንካራ ሥራ ውጤት ነው" በማለት ወጣቶች በውድቀት ተስፋ እንዳይቆርጡ መክራለች።
በንግግሯ የሥራ ፈጠራን እና የዲጂታል ዓለምን ዕድሎች ያነሳችው ሩት ይርጋለም፣ የሥራ ፈጠራ ማለት ድርጅት መክፈት ብቻ ሳይሆን የማኅበረሰብን ችግር መፍታት መሆኑን አብራርታለች። በተለይም ወጣቶች ዲጂታሉ ዓለም የፈጠረውን ሰፊ ዕድል በመጠቀም የራሳቸውን ዓለም አቀፍ ብራንድ መገንባት እንደሚችሉ አበረታታለች።
ከውበት ውድድሩ ማዕረግ ባለፈ "Beauty with a Purpose" (ውበት ከዓላማ ጋር) በሚለው የውድድሩ መርህ መሠረት፣ በሴቶች እና ሕፃናት ደህንነት ላይ አተኩራ እየሰራች መሆኑን አስታውቃለች። በተለይም የሕፃናትን የአእምሮ ጤና መጠበቅ ላይ ትኩረት ሰጥታ የተናገረች ሲሆን፣ ሕፃናት ከማያውቁት ሰው ብቻ ሳይሆን የቅርብ የቤተሰብ አባል ከሆኑ ሰዎች ጭምር ለሚደርስባቸው ጾታዊ እና አካላዊ ጥቃት ድምፅ መሆን እንደሚገባ በአጽንኦት አሳስባለች።
በማጠቃለያዋም ይህንን በሕፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ለመከላከል እና መፍትሔ ለማምጣት ወደፊት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) ያካተተ ቴክኖሎጂን ለመጠቀም እቅድ እንዳላት ጠቁማ ስኬት ማለት ማዕረግ ማግኘት ብቻ ሳይሆን የወደቁትን ማንሳት መሆኑን ተናግራለች።
ሩት ይህንን መልእክት ያስተላለፈችው በአዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ማዕከል ውስጥ በተዘጋጀ የልምድ ልውውጥ እና አነቃቂ መድረክ ላይ ለተገኙ ወጣቶች እና ተጋባዥ እንግዶች ባደረገችው ንግግር ነው።
ላለፉት ስድስት ዓመታት በሞዴሊንግ ዘርፍ ውስጥ ማሳለፏን የገለጸችው ሩት፣ የ"ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ" ዘውድን ከመድፋቷ በፊት ፊሊፒንስን ጨምሮ በተለያዩ ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያን ወክላ ተሳትፋለች። ይሁን እንጂ ስኬቷ በአቋራጭ የመጣ አለመሆኑን ያስረዳችው አሸናፊዋ "እዚህ ደረጃ ለመድረስ አሥር ጊዜ ወድቄያለሁ (ተሸንፌያለሁ)፤ ስኬት የዕድል ወይም የተሰጥኦ ብቻ ጉዳይ ሳይሆን የጽናት እና የጠንካራ ሥራ ውጤት ነው" በማለት ወጣቶች በውድቀት ተስፋ እንዳይቆርጡ መክራለች።
በንግግሯ የሥራ ፈጠራን እና የዲጂታል ዓለምን ዕድሎች ያነሳችው ሩት ይርጋለም፣ የሥራ ፈጠራ ማለት ድርጅት መክፈት ብቻ ሳይሆን የማኅበረሰብን ችግር መፍታት መሆኑን አብራርታለች። በተለይም ወጣቶች ዲጂታሉ ዓለም የፈጠረውን ሰፊ ዕድል በመጠቀም የራሳቸውን ዓለም አቀፍ ብራንድ መገንባት እንደሚችሉ አበረታታለች።
ከውበት ውድድሩ ማዕረግ ባለፈ "Beauty with a Purpose" (ውበት ከዓላማ ጋር) በሚለው የውድድሩ መርህ መሠረት፣ በሴቶች እና ሕፃናት ደህንነት ላይ አተኩራ እየሰራች መሆኑን አስታውቃለች። በተለይም የሕፃናትን የአእምሮ ጤና መጠበቅ ላይ ትኩረት ሰጥታ የተናገረች ሲሆን፣ ሕፃናት ከማያውቁት ሰው ብቻ ሳይሆን የቅርብ የቤተሰብ አባል ከሆኑ ሰዎች ጭምር ለሚደርስባቸው ጾታዊ እና አካላዊ ጥቃት ድምፅ መሆን እንደሚገባ በአጽንኦት አሳስባለች።
በማጠቃለያዋም ይህንን በሕፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ለመከላከል እና መፍትሔ ለማምጣት ወደፊት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) ያካተተ ቴክኖሎጂን ለመጠቀም እቅድ እንዳላት ጠቁማ ስኬት ማለት ማዕረግ ማግኘት ብቻ ሳይሆን የወደቁትን ማንሳት መሆኑን ተናግራለች።
Sponsored by
Surafel
4 days ago
12ኛ ዙር የደም ልገሳ መርሃ ግብር
የዓለም የደም ለጋሾች ቀን እና
የተስፋ አዲስ ቤተሰቦች 3ኛ ዓመት በዓል ማክበር
📅 ሰኔ 6 እና 7, 2018 ዓ.ም.
📍 በኢትዮጵያ 20 + ከተሞች
አንድ የደም ልገሳ እስከ ሦስት ሰዎች ሕይወት ሊያድን ይችላል። በየቀኑ በሆስፒታሎቻችን ውስጥ ለቀዶ ሕክምና፣ ለአደጋ ተጎጂዎች፣ ለካንሰር ታማሚዎች፣ ለእናቶች እና ለሌሎች በርካታ ሕሙማን ደም በአስቸኳይ ያስፈልጋል።
ይህ 12ኛው ዙር የደም ልገሳ መርሃ ግብር የተስፋ አዲስ ቤተሰቦች ለ3 ዓመታት ሲያከናውኑት የቆየውን የሰብዓዊነት ጉዞ የሚያከብር ሲሆን፣ በዓለም የደም ለጋሾች ቀን ላይም ለሕይወት አዳኝ ለጋሾች የምስጋና መልዕክት ያስተላልፋል።
እርስዎ የሚለግሱት ደም ለአንድ ቤተሰብ ተስፋ፣
ለአንድ ታማሚ ሕይወት፣
ለአንድ እናት ፈገግታ፣
ለአንድ ልጅ ነገን ሊሰጥ ይችላል።
🤝 ሁላችንም በጎ ፈቃደኞች፣ ወጣቶች፣ ቤተሰቦች፣ ተቋማት እና ማኅበረሰቡ በአጠቃላይ በዚህ ታላቅ የሕይወት ማዳን ተግባር እንዲሳተፉ በክብር እንጋብዛለን።
🩸 ደም መለገስ ሕይወት መስጠት ነው!
ኑ! በደማችን አዲስ ታሪክ እንፃፍ! ❤️🩸
#worldblooddonorday #የደም_ልገሳ #ተስፋ_አዲስ_ቤተሰቦች #donatebloodsavelives #20ከተሞች_አንድ_ዓላማ #ሕይወትን_እናድን
የዓለም የደም ለጋሾች ቀን እና
የተስፋ አዲስ ቤተሰቦች 3ኛ ዓመት በዓል ማክበር
📅 ሰኔ 6 እና 7, 2018 ዓ.ም.
📍 በኢትዮጵያ 20 + ከተሞች
አንድ የደም ልገሳ እስከ ሦስት ሰዎች ሕይወት ሊያድን ይችላል። በየቀኑ በሆስፒታሎቻችን ውስጥ ለቀዶ ሕክምና፣ ለአደጋ ተጎጂዎች፣ ለካንሰር ታማሚዎች፣ ለእናቶች እና ለሌሎች በርካታ ሕሙማን ደም በአስቸኳይ ያስፈልጋል።
ይህ 12ኛው ዙር የደም ልገሳ መርሃ ግብር የተስፋ አዲስ ቤተሰቦች ለ3 ዓመታት ሲያከናውኑት የቆየውን የሰብዓዊነት ጉዞ የሚያከብር ሲሆን፣ በዓለም የደም ለጋሾች ቀን ላይም ለሕይወት አዳኝ ለጋሾች የምስጋና መልዕክት ያስተላልፋል።
እርስዎ የሚለግሱት ደም ለአንድ ቤተሰብ ተስፋ፣
ለአንድ ታማሚ ሕይወት፣
ለአንድ እናት ፈገግታ፣
ለአንድ ልጅ ነገን ሊሰጥ ይችላል።
🤝 ሁላችንም በጎ ፈቃደኞች፣ ወጣቶች፣ ቤተሰቦች፣ ተቋማት እና ማኅበረሰቡ በአጠቃላይ በዚህ ታላቅ የሕይወት ማዳን ተግባር እንዲሳተፉ በክብር እንጋብዛለን።
🩸 ደም መለገስ ሕይወት መስጠት ነው!
ኑ! በደማችን አዲስ ታሪክ እንፃፍ! ❤️🩸
#worldblooddonorday #የደም_ልገሳ #ተስፋ_አዲስ_ቤተሰቦች #donatebloodsavelives #20ከተሞች_አንድ_ዓላማ #ሕይወትን_እናድን
4 days ago
የዓለም ዋንጫ እና አርሲ ሱዴ
ሰዓቱ ምሽት ነው። አየሩ በአርሲ ሱዴ ቀዝቃዛ ንፋስ ታጅቦ በናፍቆት ይሞቃል። ዛሬ ዓለም በሜክሲኮ፣ አሜሪካ እና ካናዳ አስተናጋጅነት ለሚጀመረው የዓለም ዋንጫ በዝግጅት ላይ ሳለች፣ የእኔ ትውስታ ግን ከሃያ ዓመታት በፊት ወደ ነበረችው ኩላ ከተማ ያንገላታኛል።
ያ ዘመን... ቴሌቪዥን በየቤቱ አልነበረም። የኢቲቪ እሁድ መዝናኛን ለመመልከት 50 ሳንቲም በእጅ ይዞ፣ በአንድ ትልቅ ስክሪን ፊት ለፊት ተሰባስቦ የመታየት ጣፋጭ ድካም የነበረበት ዘመን ነበር።
ኩላ፣ ያቺ ትንሽዬ የወረዳ ከተማ፤ ከመኪና ወርደህ "የእከሌ ቤት የት ነው?" ብለህ ብትጠይቅ፣ ከመንገድ ዳር የሚጫወቱት ህፃናት "እኔ ላሳይህ!" ብለው የሚሻሙልህ፣ እያንዳንዱ ነዋሪ የአንዳችንን ማንነት የሚያውቅባት የሞቀች ከተማ። በዚያን ዘመን መብራት የሚባል ነገር አልነበረም። ጨለማውን የሚገፈው የአፍወርቅ እና የዲደዓ ቪዲዮ ቤቶች ጄኔሬተር ድምፅ ብቻ ነበር። ማታ ማታ የውጪ ፊልሞችን፣ በዓል ሲመጣም የኢቲቪን ፕሮግራሞች በነጻም እያስከፈሉ ያሳዩን ነበር። በተለይ የስቅለት ለሊት ቪዲዮ... ያ ድባብ ዛሬም ድረስ በአይኔ ይደቀናል።
የሩጫ ውድድር፣ ዓለም ዋንጫ እና አፍሪካ ዋንጫ ሲመጣ ደግሞ ከተማዋ ትናወጣለች! የአፍወርቅ እና የዲደዓ ቪዲዮ ቤቶች በሰው ተጨናንቀው የትንፋሽ እስራት ይፈጠራል። በስሜት መጮህ፣ በጎል መዝለል፣ በሽንፈት ማዘን... ያ ሁሉ ስሜት የጋራ ነበር። አንዳንድ ጊዜ የተመልካቹ ብዛት ሲበዛ፣ የወረዳው መስተዳደር ጽ/ቤት ጄኔሬተር በማንሳት የራሱን በር ለህዝቡ ይከፍት ነበር። ያኔ፣ በአንድ ስክሪን ፊት የተሰባሰበው የኩላ ወጣት እና ታዳጊ፣ እንደ አንድ ቤተሰብ ነበር የሚሰማው።
ዛሬ ግን ዘመኑ ተቀይሯል። ዓለም ዋንጫው በቴክኖሎጂው ዓለም ተውቦ፣ በእጅ ስልክ ስክሪን እየተመለከትን ነው። ርቀቶች ተሰርዘዋል።
የዛሬይቱ ኩላ ምን ትመስል ይሆን? በየቪዲዮ ቤቱ ትከሻ ለትከሻ ተያይዘን የዓለም ዋንጫን ስንመለከት የነበርን ታዳጊዎች ዛሬ የት ደረስን? ምናልባት አንዳንዶቻችን በአሰላ፣ በአዳማ፣ በአዲስ አበባ፣ አንዳችን በውጪ አገር፣ አንዳችንም በኩላ የልጅነት ትዝታችንን እየናፈቅን በየስልካችን ስንመለከት ይሆን?
ወይ ጊዜ! ያ የጋራ ትዝታ፣ ያ የተሰባሰበ ደስታ ዛሬም በልቤ ውስጥ የከበረ ቦታ አለው። ዛሬ ዓለም ዋንጫ ሲጀመር፣ ከሁሉም በላይ የናፈቀኝ ያ በኩላ ከተማ የነበረው የቡድን መንፈስ እና ያ የዋህ የልጅነት ደስታ ነው።
የት ናችሁ የልጅነት ጓደኞቼ? ያ የኩላ ምሽት፣ ያ የዓለም ዋንጫ ወኔ ዛሬም ትዝ ይላችሁ ይሆን?

ለንግድዎ፣ ለቤተሰብዎ እና ለኢንቨስትመንትዎ ፍጹም ምርጫ — በሳር ቤት / ቡልጋሪያ!
የአፍሪካ ህብረት አቅራቢያ በሚገኘው ስትራቴጂካዊና ተፈላጊ ስፍራ በሆነው ሳር ቤት (ቡልጋሪያ ሳይት) ዘመናዊ የንግድ ሱቆችን እና ምቹ የመኖሪያ አፓርታማዎችን በተለያዩ የካሬ አማራጮች እያቀረብን ነው።
የንግድ ሱቆች (Commercial Shops)
የካሬ አማራጭ፦ ከ25 ካሬ እስከ 75 ካሬ
ተመራጭ ለ፦
• ፋርማሲ
• ሬስቶራንት
• ባንክ
• የተለያዩ የንግድ ተቋማት
የመኖሪያ አፓርታማዎች (Apartments)
የካሬ አማራጮች፦
ካሬ አማራጭ ቅድመ ክፍያ
• 81 ካሬ =727,128
• 111 ካሬ =996,435
• 134 ካሬ =1,202,904
.168 ካሬ = 1, 508,119
• 182 ካሬ =1, 633,795
ቀላል የክፍያ ስርዓት በ10% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት ይሁኑ!
እጅግ ተመጣጣኝ ዋጋዎች እና ልዩ የክፍያ አማራጮች ተዘጋጅተዋል።
ማሳሰቢያ
ይህ ልዩ የዋጋ ቅናሽ የተዘጋጀው ለውስን ቤቶች ብቻ ነው። እድሉን እንዳያመልጥዎ አሁኑኑ ይደውሉ!
📞 +251-970-214 444
📞 +251-926- 777 011

በእግራቸው የሚጓዙ ሰወች ግን ወዴት ጠፉ?
አሜሪካ ታላቅ ሀገር ናት። ሰላም፣ እድል፣ ነፃነት፣ መብት እና የተሻለ የኑሮ ሁኔታ ትሰጣለች። ግን በዚህ ሁሉ ምቾት መካከል ብዙ ሰዎች የሚሰማቸው አንድ ረሀብ አለ፤ የሰው ረሀብ፣ የወዳጅነት ረሀብ፣ የማህበራዊ ኑሮ ረሀብ።
ቴክኖሎጂ ከዓለም ጋር አገናኘን፣ ግን አንዳንዴ ከጎናችን ካለው ሰው አራቀን። መኪናዎች ፈጣን አደረጉን፣ ግን መንገዱን ከእግረኛ አራቁት። ሥራና ፕሮግራም ውጤታማ አደረጉን፣ ግን ሰው ከሰው ጋር የሚቀመጥበትን ጊዜ አሳነሱት።
ሰው ለሰው መድኃኒት ነው። ምናልባት ዛሬ የሚያስፈልገን ትልቅ ነገር አይደለም፤በእግር መውጣት፣ ጎረቤትን ሰላም ማለት፣ ከወዳጅ ጋር ቡና መጠጣት፣ እና እንደገና ሰውን መፈለግ ብቻ ነው።
በእግር የሚጓዝ ሰው ግን ወዴት ገባ ትላላችሁ ?
አንዳንዴ ራሴን እንዲህ እያልኩ እጠይቃለሁ -ሰዎቹ ሁሉ የት ሄዱ? እግረኞቹ የት ገቡ? ወዳጆቻችንስ ምን ዋጣቸው? ጎረቤቶቻችን የታሉ? እላለሁ።
በዚህች በአሜሪካ እኔ በምኖርበት በሚኔሶታ ሁሉም መኪና አለው ብል ማጋነን አይመስለኝም። ሰዎች ወደ ስራ፣ ወደ ሱቅ፣ ወደ ቀጠሮ ቦታ በመኪናቸው ሄደው በመኪናቸው ይመለሳሉ ። በዚህ ምክንያት ይመስለኛል አንዳንድ ሰፈር አንድም እግረኛ አላይም ። ይገርማችኋል አንዳንዴ ሙሉ ሰፈሩን ዞራችሁ ብታዩ አንድ የግር ተጓዥ ላታገኙ ትችላላችሁ ። አንዳንዴ የእግረኛ መሄጃና የመንገድ ዳርቻዎች ጭር ከማለታቸው የተነሣ የተወረረ ከተማ ነው የሚመስሉት።
ህይወት ታሯሩጣለች እና ሁሉም ሰው የሆነ የሚያደርገው ነገር ያለው ይመስላል። በዚህ ምክንያት ከሰዎች ጋር የመገናኘት እድሉ በጣም የጠበበ ነው። እየተጓዝኩ የሆነ የማቀው ሰው ይመጣብኛል ወይም የማዋራው የማላቀውም ሰውም ቢሆን አገኛለሁ ብሎ ማሰብ ከባድ ነው። አብዛኛው ሰው ስራ ላይ ነው፣ ሌላው በተሽከርካሪ እየተጓዘ ነው ወይም ደግሞ በሌሎች ጉዳዮች ተይዟል። ባጠቃላይ በግር የሚጎዝ ሰው ብዙ አይታይም ።
ሰው ለማግኘት የምንችልባቸው ጥቂት ቦታዎች እንደ ግሮሰሪ፣ ምግብ ቤት፣ ካፌ እና መጠጥ ቤት ናቸው። ለአብዛኛው ሰው በተከታታይ ለመሰብሰብና ለመገናኘት የሚያስችለው ሌለኛው ቦታ ደግሞ የእምነት ቦታወች ናቸው። በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ቀን።
በብዙ የአፍሪካ ሀገራት ሁኔታው ከዚህ በእጅጉ የተለየ ነው። መንገዶቹ በሰዎች የተሞሉ ናቸው። ሰው ከመኪና ጋር እየተጋፋ ነው የሚሄደው ። ሰዎች ይበዛሉ፣ ከሚያቁትም ከማያቁትም ጋር ቀኑን ሙሉ ያወራሉ፣ ሁሌም የሚታይ ብዙ ህዝብ አለ። ስለዚህ በሰዎች ተከበው ስለሚውሉ ብቻቸውን ሆነው እንኳ ብቸኝነት አይሰማቸውም። ሁሌም ከሰዎች ጋር በመሆናቸው ምክንያት ኑሮ ቢከብድም የዚህ ማህበረሰብ አካል እንደሆኑ ይሰማቸዋል ።
ወደዚህኛው አሜሪካ ስመልሳችሁ ደግሞ የታዘብኩት ነገር በብዙ ቤተሰቦች ውስጥ የሆነ የተቀየረ ነገር አለ። የአንድ ቤተሰብ አባላት አንድ ክፍል ውስጥ ሆነው ላይነጋገሩ ይችላሉ። አዲሱ ትውልድ ጎኑ ካለው ሰው ይልቅ ከኮምፒውተሩ ፣ ከታብሌቱ ፣ ፌስቡክ ኢንስታግራም ቲክታክ ወይም ከእጅ ስልኩ ጋር መጫወትን ይመርጣል።
የዚህ አደጋው በጊዜ ሂደት ይህ ጤናማ ያልሆነ ባሕርይ ይለመድና የህይወት ዘዬ ይሆናል። ብቸኝነት ራሱ የተለመደ ነገር ይሆናል። ብዙ ሰዎች የተመጠነ ማህበራዊ ግንኙነት ይለምዱና ሰዎችን መፈለግ ያቆማሉ። ከሰው ጋር ያላቸውን መስተጋብር በቀነሱ ቁጥር ይበልጥ ምቾት እየተሰማቸው ይመጣል።
እኔ ሳየው ገለልተኛና ብቸኝነት የተሞላበት ህይወትን ለራሳችን እያለማመድን ይመስለኛል።
ቴክኖሎጂ በአንድ ጎኑ ከአለም ጋር ያገናኘን ቢሆንም በሌላ በኩል ደግሞ ጎናችን ካሉ ሰዎች ጋር እያለያየን መሆኑ ሀቅ ነው።አንድ ከአለም ጫፍ ካለ ሰው ጋር በሰከንድ ጊዜ ልንገናኝ ልናወጋ እንችላለን። ነገር ግር አንዳንዴ ጎረቤታችን የሚኖረው ሰው እንኳ ማን እንደሆነ አናውቅም።
አሜሪካ ታላቅ ሀገር ነች። ለሰዎች ሰላምን፣ እድልን፣ ነፃነትን፣ የመብት መከበርን እና የተሻለ የኑሮ ሁኔታን ታጎናፅፋለች። ይሁንና ግን በዚህ ሁሉ ምቾት መሀከል ሰዎች ሊያስታግሱት ያልቻሉት አንድ ረሀብ አለ። እሱም የሰው ረሀብ፣ የማህበራዊ ኑሮ ርሀብ።
ዲጂታል ቴክኖሎጂ በቀላሉ ያገናኘናል፤ ተሽከርካሪዎች ፍፁማዊ በሆነ መንገድ ወዲያ ወዲህ ያመላልሱናል። የተወጠሩ የስራ ግዜዎቻችን ውጤታማ ያረጉን ይሆናል፤ ሆኖም ግን ብዙ ሰዎች ከሰው ጋር መነጋገር ፣ቀለል ያለ የሻይ ቡና ላይ ወሬ፣ አሊያም የሆነ ማህበረሰብ አካል መሆን ያምራቸዋል ።
እውነት እንነጋገር ካልን አንዱ የዚህ የዘመናዊነት ኑሮ ተግዳሮት ከእርስ በርሳችን ይልቅ ከማሽንና ከግል የስራ ፕሮግራሞቻችን ጋር በአስከፊ ሁኔታ መጣመራችን ነው። ሰው ለሰው መድሀኒቱ አለ ያገሬ ሰው።
— ዶ/ር ሲራክ ኃይሉ
ከሚኔሶታ
የካይሮፕራክቲክ ሀኪም

ሰላም፣ ደህና አደራችሁ?
የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ!
የሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጥ፣ የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያፋጥን እና የዜጎችን የኑሮ ደረጃ የሚያሻሽል መርሐ ግብር ነው።
ዋና ዓላማው በቤተሰብ ደረጃ እንደ ዶሮ፣ እንቁላል፣ ወተት፣ ማር እና ሌሎች የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን በማሳደግ የምግብ እጥረትን መቀነስ፣ የሥራ እድል መፍጠር እና የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት ነው።
የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ካስመዘገባቸው ትልልቅ ውጤቶች መካከል የምግብ ዋስትናን ማሻሻል ቀዳሚው ነው።
መርሐ ግብሩ የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር እና የቤተሰብ ገቢን ለማሻሻል ተጨባጭ ውጤቶች የተመዘገቡበት ሲሆን÷ በተለይ በህጻናትና በእናቶች ላይ የሚታዩ የሥነ ምግብ ችግሮችን ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
በርካታ ዜጎችም በዶሮ እርባታ፣ በወተት ላሞች እንክብካቤ፣ በአሳ እርባታ፣ በማር ምርት፣ በግብይት፣ በማጓጓዝ እና በምርት ማቀነባበር ዘርፎች የሥራ እድል አግኝተዋል።
የኑሮ ውድነትን በመቀነስ የሚጫወተው ሚናም ቀላል የሚባል አይደለም፡፡
በመርሐ ግብሩ በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች መጠን ሲጨምር በገበያ ላይ ያለው አቅርቦትም ተሻሽሏል።
የሌማት ትሩፋት የግብርናውን ዘርፍ በማጠናከር ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል።
የሀገር ውስጥ ምርትን በመጨመር ከውጭ የሚገቡ አንዳንድ ምርቶችን ለመተካት እድል የፈጠረ ሲሆን÷ ይህም የውጭ ምንዛሪ ወጪን ለመቀነስ አግዟል።
በአንጻሩ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን በማሳደግ የውጭ ምንዛሪ ገቢን የሚያሳድግ ሆኗል።
መርሐ ግብሩ በመንግሥት፣ በግሉ ዘርፍ እና በማህበረሰቡ መካከል የተቀናጀ ትብብር እንዲፈጠርም አድርጓል።
በዚህም በብዙ አካባቢዎች የልማት ሥራዎች በሕዝብ ተሳትፎ ይከናወናሉ።
መርሐ ግብሩ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ከመቻል አልፋ የግብርና ምርቶችን በብዛት ለውጭ ገበያ በማቅረብ ተወዳዳሪ ሀገር እንድትሆን ያስችላል።

በ2014 ዓለም ዋንጫ የደመቀው ጀምስ ሮድሪጌዝ…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም ሕዝብ በጉጉት የሚጠብቀውና በየአራት ዓመቱ የሚደረገው ትልቁ የእግር ኳስ መድረክ ዓለም ዋንጫ ሁሌም አዳዲስ ክስተቶችን እያስመለከተ ያልፋል፡፡
የዓለም ዋንጫ በመጣ ቁጥር አዳዲስ ኮከቦችን እና በመድረኩ ድንገት ልዩነት ፈጥረው የእግር ኳስ ቤተሰብን ቀልብ የሚስቡ ተጫዋቾችን መመልከት የተለመደ ነው፡፡
ከመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ውድድር ጀምሮ እስከ ኳታሩ የዓለም ዋንጫ ድረስ የተለያዩ አስደናቂ ኮከቦች በመድረኩ መታየታቸው አይዘነጋም፡፡
በፈረንጆቹ 2014 ብራዚል ባዘጋጀችው የዓለም ዋንጫ ውድድር ደግሞ የመድረኩ ክስተት እና አስገራሚ ኮከብ ሆኖ ብቅ ያለው ኮሎምቢያዊው ተጫዋች ጀምስ ሮድሪጌዝ ነበር፡፡
በወቅቱ በመድረኩ ኮሎምቢያዊው የ22 ዓመቱ ተጫዋች ጀምስ ሮድሪጌዝ ሜዳ ላይ በሚያሳየው እንቅስቃሴ የብዙዎችን ትኩረት መሳብ ችሏል፡፡
ብራዚል ባዘጋጀችው መድረክ ጀርመን ዋንጫውን ጀምስ ግን የሁሉንም ልብ ነበር ያሸነፈው፡፡
በወቅቱ ተስፋዎች ሁሉ ልማደኛው የግብ አዳኝ ራዳሜል ፋልካኦ ላይ ቢሆንም እሱ መጎዳቱን ተከትሎ ኮሎምቢያ ከምድብ ታልፋለች ብሎ የገመተ አልነበረም፡፡
ኮሎምቢያ ግን አንድ የሚያሻግራት እና እግሮቹ እጅግ አስፈሪ የ22 ዓመት ወጣት ኮከብ ድንገት አገኘች፡፡
ብራዚላዊያን በደገሱት የ2014 የዓለም ዋንጫ ውድድር ላይ እንደ ጀምስ ሮድሪጌዝ የነገሰ ተጫዋች ማግኘት ከባድ ነበር፡፡
የእርሱን ያህል ግቦችን ያስቆጠረ፣ የእርሱን ያህል ለብሔራዊ ቡድኑ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከተ፣ በአስደናቂ እንቅስቃሴ እና በውብ ግቦች ተመልካቾችን ያዝናና አልነበረም።
በመድረኩ ስድስት ግቦችን ያስቆጠረው ወጣቱ ተጫዋች ከስድስቱ በኡራጓይ መረብ ላይ ያረፈችው ግብ የኮሎምቢያ እና የጀምስ መታሰቢያ ብቻ ሳትሆን ዓለም ዋንጫ በመጣ ቁጥር ከምርጦቹ አንዷ ሆና ተመዝግባለች፡፡
ጀምስ ሮድሪጌዝ ኡራጓይ ላይ ባስቆጠራት አስደናቂ ግብ ምርጥ ግብ በመባል የፑሽካሽ ሽልማትን አሸንፏል፡፡
ጀምስ ለኮሎምቢያ ባደረጋቸው እያንዳንዱ ጨዋታዎች ምርጥ ብቃቱን በማሳየት ሀገሩን ለሩብ ፍጻሜ አብቅቷል፡፡
ጀምስ ሮድሪጌዝ በዓለም ዋንጫው ስድስት ግቦችን በማስቆጠር ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን የውድድሩን የወርቅ ጫማ ማሸነፉ ይታወሳል፡፡
ከዓለም ዋንጫው ጎን ለጎን ገና ከውድድሩ ሳይመለስ እርሱን ለማስፈረም በርካታ ታላላቅ ክለቦች ፍላጎት ማሳየታቸው አይዘነጋም፡፡
የስፔኑ ኃያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ይህንን የኮሎምቢያ ወጣት እና በዓለም ዋንጫው የተለያዩ ሀገራት ደጋፊዎች ልብ ውስጥ የቀረውን ጥበበኛ ማስፈረሙ ይታወሳል፡፡
በወቅቱ ዓለም ላይ ያሉ በርካታ ክለቦች እሱን ለማስፈረም ቢፈልጉም ሪያል ማድሪድ የግሉ አደረገው፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ ከዓለም ዋንጫው በብራዚል ተሸንፎ ሲሰናበት የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ወደ ጀምስ በማቅናት አጽናንተውታል፡፡
ትልቅ ደረጃ ይደርሳል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ጀምስ ሮድሪጌዝ እንደተጠበቀው ሳይሆን መቅረቱ ይታወቃል፡፡
በወንድማኝ ጸጋዬ

የመደመር አንቀጽ
ትውልድ በአንድ ቤተሰብ ደረጃ ሲታይ፤ ወደላይና ወደ ታች የሚፈስ ወንዝ ነው። አባትና እናት፣ አያት፣ ቅድመ አያት እያለ ወደላይ፤ ልጅ፣ የልጅ ልጅ በማለትም ወደታች የሚተረተር የቤተሰብ ሠንሠለት ነው።
ልጅ የነበረው አባት፤ አባት የነበረው አያት፤ ቅድመ አያት... እየሆነ የሚፈጥረው ቅጥልጣይ ገመድ ነው፡፡ የቤተሰቡ ጥንካሬና መልካም ስም በእያንዳንዱ አስተዋጽዖና መልካም ሥራ ላይ ይመሠረታል። ስለዚህም የቀደመው ትውልድ፡ ቀጣዩ ትውልድ በመልካም እሴቶች የታነጸ እንዲሆን አበክሮ ይሠራል።
ሀገር የምትሠራውም እንደ ቤተሰብ በትውልድ ቅጥልጣይ ውስጥ ነው። በሀገር ደረጃ ትውልድ ሲባል በተቀራራቢ ዕድሜ ደረጃ የሚገኙ፣ በተመሳሳይ የታሪክ አጋጣሚዎች ውስጥ ያለፉ፣ በዘመኑ የእሳቤ _ ማዕቀፍ ውስጥ የተቀረጹና፣ ተመሳሳይ _ ጠባይን የሚያንጸባርቁ የየዘመኑ የኅብረተሰብ ከፍሎች ናቸው።
ማብቂያ የሌለው የሀገር ግንባታ ሂደት የሚከወነው፤ የየዘመኑ ትውልድ በሚሠራው መልካም ሥራና በሚቀጥለው ትውልድ ላይ በሚፈጥረው መልካም ተፅዕኖ ላይ ተመሥርቶ ነው።
የመደመር ትውልድ
ገጽ - 4
#ebc #ethiopia #ebcdotstream #medemer Ethiopian Broadcasting Corporation #generatio

5 days ago
🎤 ታላቅ የቀጥታ ሙዚቃ ኮንሰርት – በፖርትላንድ! 🎶
የሙዚቃ አፍቃሪዎች ተዘጋጁ!
Sami Dan በቀጥታ በፖርትላንድ ከተማ ለአንድ ልዩ የሙዚቃ ምሽት ይቀርባል።
📅 ቀን: ቅዳሜ ጁላይ 11
🕘 በሮች የሚከፈቱት: 9:00 ምሽት
📍 ቦታ: 1235 SE Grand Ave, Portland, OR 97214
✨ አስደሳች የቀጥታ ሙዚቃ
✨ የማይረሳ መዝናኛ
✨ ከወዳጆችና ከቤተሰብ ጋር የሚያምር ምሽት
🎟️ ትኬትዎን አሁኑኑ ያስያዙ!
📞 ለተጨማሪ መረጃ:
503-793-6787
503-849-8589
አዘጋጅ: PDX Habesha Entertainment
🎶 አይቀሩ! ይህ ልዩ የሙዚቃ ምሽት የእርስዎን ቅዳሜ ያደምቃል! 🎶
#samidan #portland #habeshaentertainment #liveconcert #music #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Aaram haram hai success ke liye👉እረፍት ሀጥያት ነው፤ ለስኬት ጥሩ አይደለም!(ሻሩክ ካሃን)
Rest is not good for success ይላል ሻሩክ ካሃን ።
ሻሩክ ካሃን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰብ ተነስቶ በዓለም ላይ በጣም ተፅዕኖ ፈጣሪ እና ታዋቂ ሰው ለመሆን በቅቷል። ሻሩክ ካሃን በታሪክ ውስጥ እጅግ ተምሳሌት እና አነሳሽ ከሆኑ ሰዎች አንዱ ነው።
ሻሩክ 8 ጊዜ የፊልምፌር ሽልማቶችን ያገኘ ብቸኛው የቦሊውድ ተዋናይ ሲሆን ይህም የቦሊውድ ፊልም ኢንደስትሪ ከፍተኛ ተዋናይ አድርጎታል። በጣም አነቃቂ ከሆኑ የሻሩክ ንግግሮች መካከል "Aaram Haram Hai Success Ke Liye" ተጠቃሽ ነው።
Aaram haram hai success ke liye ማለት እረፍት ሀጥያት ነው፤ ለስኬት ጥሩ አይደለም የሚል አቻ ትርጉም አለው።
ሻሩክ ወደ ስኬት ጫፍ እንዲደርስ ያደረጉት የሚከተላቸው የራሱ የአስተሳሰብ ውጤት ናቸው። ሻሩክ ስኬት ላይ ለመድረስ እነዚህ 3ቱን ቴክኒኮች በመጠቀም መሆኑን ተናግሯል።👇
1.ምን መብላት እንዳለብህ፣ መቼ ማረፍ እንዳለብህ በመሳሰሉ ነገሮች ግራ በመጋባት ጊዜህን አታባክን። እንደ ሻሩክ አባባል ጤናማ ኑሮ ለመኖር መስዋዕትነት ያስፈልጋል። ስኬታማ ለመሆን ከፈለጋችሁ የእረፍት ጊዜያችሁን ቀንሱ በመተኛት ለውጥ አይመጣም ብሏል።
2.ሻሩክ እንደሚለው መስዋዕትነትን ካልከፈልክ ስኬታማ አትሆንም። ወደፊት ስኬታማ ለመሆን ከፈለክ ምቾትህን መስዋዕት ማድረግ አለብህ።
ሻሩክ በቀን ከ4-5 ሰአታት ብቻ ይተኛል። ቀሪ ጊዜውን በስራ እንደሚያሳልፍ ተናግሯል።
3.በዚች ምድር እስከኖርክ ድረስ ፈተናዎች ያጋጥሙሃል፣ ምቾት ላይሰማህ ይችላል፣ ህመሙ ሊሰማህ ይችላል፣ ስኬትም ቆሞ አይጠብቅህም።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #selamshowbiz

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕና አለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) የ80 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ።
በስምምነቱ መሰረት ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 80 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የረዥም ጊዜ ብድር ያቀርባል ።
በተገኘው ገንዘብ ደግሞ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሸራተን አዲስ ሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴልን በዘመናዊ መልኩ ያድሳል፣በሸራተን ደረጃ አዲስ ሆቴል ይገነባል።
የብድር ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድና የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) የአፍሪካ ቀጠና ምክትል ፕሬዚዳንት ኢትዮዺስ ተፈራ በኬንያ ናይሮቢ ተፈራርመዋል።
ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ተቋም ጋር ከፍተኛ ፋይዳ ያለውን አጋርነት በማድረጋችን ለተቋሙ ያለንን አድናቆት መግለጽ እንወዳለን ያሉት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አሕመድ፤ ይህ አጋርነት የሀገሪቱን የሆስፒታሊቲ ዘርፍ ለማዘመን እንዲሁም በኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለው የሥራ ዕድል ፈጠራን በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።
የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የአፍሪካ ቀጠና ምክትል ፕሬዚዳንት ኢትዮዺስ ተፈራ በበኩላቸው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የአገልግሎት ዘርፉን የበለጠ እንዲያዘምንና ተጨማሪ የስራ እድል እንደፈጥር ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል።
ከአለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በሚገኘው ገንዘብ ሸራተን አዲስ ኤሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል ዘመኑን በሚመጥን መልኩ የሚታደስ ሲሆን በሸራተን የንግድ ምልክት የሚጠራ ተጨማሪ አዲስ ሆቴልም ይገነባል።
የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) የብድር አቅርቦት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አካል የሆነውን የሸራተን አዲስን ገጽታ በእጅጉ እንደሚለውጠው ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለማዘጋጀት መመረጧን ተከትሎ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሚሊኒየም አዳራሽ ቅጥር ግቢ ዘመናዊ ሆቴል (Moxy by Marriott) ፣ በመሀመድያ የመኖሪያ መንደር (Four Points by Sheraton) ሆቴሎች ግንባታን አስጀምሯል።
በቅርቡ የሚድሮክ ቤተሰብን የተቀላቀለው ዋቢሸበሌ ሆቴል (autograph collection by Marriot) ደረጃ ለጉባኤው ዝግጁ ለማድረግ ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ የእድሳት ስራው ተጀምሯል።
አፍሪካ ህብረት አጠገብ እየተገነባ ያለው ዌስት ኢን አዲስ (Westin Addis) ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በባህርዳር ከተማ (Four Points by Sheraton) እና (Protea by Marriott) ፣በጂማ እና ሃዋሳም በተመሳሳይ (Four Points by Sheraton) ሆቴሎችን እየገነባ ይገኛል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የላንጋኖ ሳቫና ሪዞርትን በግዥ የተረከበው ሲሆን በማርዮት ብራንዶች ደረጃ አለም አቀፍ ሪዞርት በመገንባት ወደ ስራ ይገባል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርና፣ በማእድን፣ በንግድና በሆስፒታሊቲ ዘርፍ በመሰማራት ከ80 ሺህ በላይ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር የቻለ ግዙፍ ተቋም ነው።

ያለ በረራ ፈቃድ ለ17 ዓመታት አውሮፕላን ሲያበር የነበረው ካፒቴን ክስ ተመሰረተበት
አንድ የቀድሞ የኤር ካናዳ (Air Canada) አውሮፕላን አብራሪ ለዓመታት ተገቢው ፈቃድ ሳይኖረው በካፒቴንነት ሲያበር በመቆየቱ በቁጥጥር ስር ውሎ ክስ እንደተመሰረተበት የካናዳ ፖሊስ አስታወቀ።
የኦንታሪዮ ግዛት ነዋሪ የሆነው ጄፍሪ ዎል (Geoffrey Wall) የተባለው የ59 ዓመት ግለሰብ ከፈረንጆቹ 2009 እስከ 2025 ባሉት 17 ዓመታት ውስጥ ትላልቅ የንግድ የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ለማሽከርከር የሚያስችለው ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው በካፒቴንነት ሲሰራ መቆየቱን የፒል ክልላዊ ፖሊስ ገልጿል።
በዚህ የፈረቃ ዘመኑም ከ900 በላይ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ በረራዎችን ማድረጉ ታውቋል።
የፖሊስ ምክትል አዛዥ ኒክ ሚሊኖቪች እንደገለጹት ግለሰቡ የተጭበረበሩ የፈቃድ ሰነዶችን በመጠቀም ቀጣሪውን ተቋምና ተቆጣጣሪ አካላትን ሲያታልል ቆይቷል።
አዛዡ ሁኔታውን ሲያስረዱ "ይህ ድርጊት ልክ የቤተሰብ ህክምና ለመስጠት ፈቃድ ያለው ሐኪም በራሱ ቢሮ ውስጥ የጭንቅላት ቀዶ ጥገና እንደማድረግ ያህል ነው" ብለዋል።
ኤር ካናዳ በበኩሉ ባደረገው ማረጋገጫ ግለሰቡ የንግድ አውሮፕላን አብራሪነት ፈቃድ የነበረው ቢሆንም የትራንስፖርት አውሮፕላን አብራሪነት (Airline Transport Pilot License) ፈቃድ ሳይኖረው በተሳሳተ መንገድ ወደ ካፒቴንነት ማዕረግ ማደጉን አምኗል።
ጉዳዩ በሰነድ ፍተሻ ወቅት በታዩ ጉድለቶች ይፋ መሆኑንና ለተቆጣጣሪው አካል ሪፖርት መደረጉን ተቋሙ ገልጿል።
አየር መንገዱ አብራሪው ከስራው መታገዱንና በአሁኑ ወቅት የድርጅቱ ሰራተኛ እንዳልሆነ የገለጸ ሲሆን በበረራዎች ደህንነት ላይ የደረሰ ምንም ዓይነት አደጋ አለመኖሩንና በሌሎች አብራሪዎች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻም መሰል ችግር እንዳልተገኘ አስታውቋል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም፣ በዓለም ዋንጫው ታሪክ የመጀመሪያው ሶማሊያዊ ዳኛ በመሆን ታሪክ ለሰራው ኦማር አርታን ያላቸውን ጥልቅ አጋርነት እና ድጋፍ ገለጹ። ዳኛው በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዚህ ትልቅ መድረክ ቢመረጥም፣ በዓለም ዋንጫው ሜዳ ላይ ጨዋታዎችን እንዳይመራ መደረጉን (ከሜዳ መገለሉን) ተከትሎ ነው ዶ/ር ቴድሮስ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ የማጽናኛ መልዕክት ያስተላለፉት።
ዶ/ር ቴድሮስ በመልዕክታቸው "ኦማር አርታን የዓለም ዋንጫውን በመቀላቀል ብቻ ሳይሆን፣ የአፍሪካ ምርጥ እና የመጀመሪያው ሶማሊያዊ ዳኛ በመሆን ትልቅ ታሪክ ሰርቷል፤ ይህ ስኬቱ ደግሞ በምንም አይቀየርም" ብለዋል።
አክለውም ዳኛው የሙያው ማማ ላይ መድረሱ እና ሀገሩን ወክሎ መገኘቱ ብቻውን በትውልድ ሀገሩ ላሉ ወጣቶች ትልቅ መነሳሳትን የፈጠረ መሆኑን ገልጸው፣ ባገኘው እና ይገባው በነበረው የዓለም ዋንጫ ሜዳ ላይ እንዳይገኝ መደረጉ እጅግ እንዳሳዘናቸው አመልክተዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ይህ ክስተት በዓለም አቀፍ መድረክ የዳኛው የመጨረሻ ታሪክ እንደማይሆን በማስመርጥ፣ "ዓለም እንደ አንድ ቤተሰብ ከጎንህ ቆሟል፤ አሁን ላይ ጥንካሬን እመኝልሃለሁ፣ በቀጣይም በሌሎች በርካታ ታላላቅ የፍጻሜ መድረኮች ላይ እንደምንመለከትህ ተስፋ አደርጋለሁ" በማለት ከሶማሊያዊው ዳኛ ጎን መቆማቸውን አረጋግጠዋል።

7 days ago
የወንድማችን እጅጉ አበበን ሕይወት ለመታደግ
የተዘረጋ የረድኤት ጥሪ
#ethiopia | "ሰው ለሰው መድኃኒቱ ነው!" በሚለው እሴታችን መሠረት ወገንን የመርዳት ሌላው ታላቅ የሰብዓዊነት ጥሪ ቀርቧል።
በትውልድ ቦታው በከፋ ዞን ጠሎ ወረዳ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ውስጥ በከፍተኛ የሲስተም አስተዳዳሪነት ሙያ ሕዝብና ሀገሩን በቅንነትና በታማኝነት ሲያገለግል የቆየው ወንድማችን እጅጉ አበበ በአሁኑ ወቅት በብርቱ የጤና እክል ላይ ይገኛል።
ወንድማችን እጅጉ አጋጥሞት ከሚገኘውና እጅግ አስቸጋሪ ከሆነው የካንሰር ሕመም ጋር ብርቱ ትግል እያደረገ ይገኛል።
ሕመሙ ባስከተለበት ከባድ ስቃይና መክበድ ምክንያት በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ አልጋ ላይ ውሎ ሕክምና መከታተል ከጀመረ ከአራት ወራት በላይ ተቆጥረዋል።
በዚህም የሕክምና ቆይታው ወቅት እጅግ አድካሚና ከባድ የሆኑትን የኬሞቴራፒ እና የጨረር ሕክምናዎችን በመከታተል ላይ ይገኛል።
ይህ ፈታኝ ወቅት የእጅጉን አካላዊ ጥንካሬና ጤንነት ብቻ ሳይሆን የጠቅላላ ቤተሰቡን ሕልውና የፈተነ ሆኗል።
እጅጉ የታማሚነትን ስቃይ በጽናት እየተጋፈጠ ያለው የራሱን ሕይወት ለማዳን ብቻ ሳይሆን ከጀርባው የሚጠብቁትንና የእሱን እጅ የሚያዩትን የሁለት ንጹሐን ሕፃናት ልጆቹን ብሩህ ተስፋና የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለመታደግ ጭምር ነው።
የአንድ አባት መውደቅ የቤተሰብ ሕልውና መናጋት ከመሆኑም በላይ የሕፃናቱንም ብሩህ ተስፋ የሚያጨልም በመሆኑ ዛሬ እጅጉና ልጆቹ የእኛን የሁላችንንም የትብብርና የደግነት እጅ አጥብቀው ይሻሉ።
የለመድነውን መልካም ትብብራችንን እና የወገን ደራሽነት ባህላችንን በተግባር የምናሳይበት ሰዓት አሁን ነው።
የቻልነውን ያህል በገንዘብ ካልሆነም ይህንን የረድኤት መልዕክት በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በማጋራት ለታማሚውና ለቤተሰቡ ደራሽ እንድንሆን ጥሪ ቀርቧል።
የእኛ ጥቂት ሳንቲም ለዚህ ቤተሰብ ታላቅ ተስፋና የሕይወት መተርፊያ ናት።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000235379043
እጅጉ አበበ አዋጎ
ስልክ ቁጥር 0917254790
#የህይወትአድንጥሪ #የካንሰርህክምና #ጥቁርአንበሳሆስፒታል #የደግነትእጅ #ከፋ #ቤንችሸኮ #ሰብአዊነት #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

(ዘ-ሐበሻ ዕይታ) የዘማሪ እና ሰባኪ ታዲዮስ ግርማ "የመቅደሱ እምባ" የተሰኘውን መዝሙር ስንሰማ በውስጣችን የሚፈጥረው ስሜት ተራ የዜማ ጥበብ አይደለም፤ ይልቁንም የቆሰለ ልብ ጩኸት፣ የወቅቱ የሀገራችን የፖለቲካ እና የሃይማኖት ቀውስ መስተዋት፣ እንዲሁም ልክ እንደ ቀድሞ ነቢያት በድፍረት የቀረበ የማስጠንቀቂያ ደወል ነው። ይህንን መዝሙር በጥልቀት ስንመለከተው፣ ከሚያስተላልፈው መንፈሳዊ እና ማህበራዊ መልእክት ባሻገር ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር የተቆራኙ በርካታ እውነታዎችን እናገኛለን።
ዘማሪው የሀገሪቱን የደም መፋሰስ እያየ ዝም ማለት አልቻለም። የንጹሃን ደም መፍሰስ ሰማይ እንደደረሰ እና ፈጣሪም ለዚህ ፍርድ እንደሚሰጥ በግልጽ ይሞግታል። የባቢሎኑ ንጉሥ ብልጣሶር በእግዚአብሔር ንዋየ ቅድሳት ሲቀልድ ጣት መጥታ ግድግዳ ላይ እንደጻፈችበት ሁሉ (በትንቢተ ዳንኤል 5፥27 ላይ "ማኔ ቴቄል ፋሬስ" ወይም "ቴቄል፤ በሚዛን ተመዘንክ፥ ቀለህም ተገኘህ" እንደሚለው)፣ የዘመናችንም ገዥዎች በመለኮት ሚዛን ቀልለው መገኘታቸውንና "ዙፋኑን ልቀቅ" የሚል ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ይነግረናል። በተጨማሪም "እንደ ናቡቴ ደም ያንተም ደም ይፈሳል" በማለት፣ ንጉሥ አክዓብ የንጹሑን የናቡቴን ወይን ቦታ ለመቀማት ብሎ በግፍ ስላስገደለውና ፈጣሪ ውሾች ደሙን እንዲልሱት እንደፈረደበት (በ1ኛ ነገሥት 21፥19 ላይ የተጻፈውን) ታሪክ ያስታውሳል። ይህም "እጆቻችሁ ደም ተሞልተዋል" (ኢሳይያስ 1፥15) እንደሚለው፣ በግፍ ለሚገደሉ ዜጎች እግዚአብሔር ዝም እንደማይል የሚያሳይ የሰላ እና ደፋር መልእክት ነው።
ልብን ክፉኛ የሚነካው የመዝሙሩ ክፍል ዘማሪው የራሱን ቤተክርስቲያን ችግር ሳይሸሽግ በድፍረት የሚያጋልጥበት ነው። ቤተ መቅደስ የሰላም እና የመጠጊያ ስፍራ መሆኑ ቀርቶ የዘር ፖለቲካ ማራመጃ፣ እንዲሁም የጥቅም መገበያያ መሆኑን በብርቱ ያወግዛል። ዘማሪው የሚከተለውን ጠንካራ ስንኝ ሲያሰማ እንሰማለን፦
በዘር በቋንቋ ከፋፍለህ ሰጥተሃል፣
ጳጳሳቱ ተመዝነሃል፣
በዘር በቋንቋ የተሾማችሁ፣
ከመቅደሱ ውጡ ቆብ አውልቃችሁ፣
ስምንተኛው ሺ ደረሰ ህገ ቤተክርስቲያን ተጣሰ፣
የወለደ ልጅ ያለው ጳጳስ ስምንተኛው ሺ ደረሰ።
ይህ ስንኝ የቤተክርስቲያኒቱን ወቅታዊ ፈተናዎች ያለ ምንም ድብቅብቅ በቀጥታ የሚሞግት ነው። የመጀመሪያው ጉዳይ በዘር እና በቋንቋ ላይ የተመሰረተውን የሹመት ቀውስ ይመለከታል። ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ እና አግላይ ያልሆነች ተቋም ሆና ሳለች፣ የፖለቲካ እና የዘር ማከፋፈያ መሆኗን አጥብቆ ይቃወማል። ለዚህ መከፋፈል ተባባሪ የሆኑት እና በዘር የተሾሙት አባቶችም በመንፈሳዊው ሚዛን ቀልለው ስለተገኙ፣ ቆባቸውን አውልቀው ከመቅደሱ መውጣት እንዳለባቸው ያለ ፍርሃት ይሞግታል። ሐዋርያው ጳውሎስ "በክርስቶስ ኢየሱስ ሁላችሁ አንድ ናችሁና... አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም" (ገላትያ 3፥28) ብሎ ያፈረሰውን የዘር ግድግዳ፣ አሁን ላይ አባቶች ራሳቸው መልሰው ሲገነቡት ማየት እጅግ ያመዋል።
ሁለተኛው ነጥብ የቤተክርስቲያኒቱ ቀኖና እና ሥርዓት መጣስን ያሳያል። "ህገ ቤተክርስቲያን ተጣሰ የወለደ ልጅ ያለው ጳጳስ" የሚለው ቃል፣ የቤተክርስቲያኒቱን ጥብቅ ህግ መናድ ያሳያል። በኦርቶዶክስ ትውፊት ጳጳስ የሚመረጠው ከምንኩስና ሕይወት በመሆኑ፣ ዓለማዊ ፍላጎቱን የገደለ እና ቤተሰብ የሌለው መሆን አለበት። ነገር ግን ይህ የቅድስና ሥርዓት ተጥሶ ዓለማዊ እና ሥጋዊ ሕይወት ያላቸው ሰዎች ወደዚህ ከፍተኛ የመንፈሳዊ አመራር ሥፍራ መምጣታቸውን በከፍተኛ ኃዘን ይገልጻል።
ሦስተኛው ጉዳይ "ስምንተኛው ሺህ" የሚለው ትንቢታዊ አገላለጽ ነው። ይህ ብሂል በኢትዮጵያዊያን ዘንድ የክፋት መብዛትን፣ የስርዓት መበላሸትን እና የማይታሰብ ድርጊት የሚፈጸምበትን የኃጢአት ዘመን ለመግለጽ የምንጠቀምበት ነው። ዘማሪው በመቅደሱ ውስጥ እንዲህ ያለ የዘር ክፍፍል እና የቀኖና ጥሰት መታየቱ የዘመኑን ክፋት፣ የሥርዓቱን መፍረስ እና የመጨረሻውን የጥፋት ዘመን መቃረብ አመላካች መሆኑን እያስጠነቀቀን ይገኛል።
ከዚህ ሁሉ ትችት እና ማስጠንቀቂያ በኋላ መዝሙሩ ተስፋ ወደ መቁረጥ ሳይሆን ወደ እውነተኛው መፍትሄ ይመራናል። የኢትዮጵያ መፍትሄ ያለው በጉልበት ወይም በጦር መሳሪያ ሳይሆን በንስሐ እና ወደ እግዚአብሔር በመመለስ መሆኑን ያሳስበናል። "እንደ ራሔል የኢትዮጵያ እናት አልቅሳ" ሲል "ድምፅ በራማ ተሰማ፥ ልቅሶና መራራ ዋይታ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች... መጽናናትንም እንቢ አለች" (ኤርምያስ 31፥15) የሚለውን የነቢዩን ቃል በማስታወስ፣ የሀገሪቱ እናቶች በልጆቻቸው መሞት አንጀታቸው ማረሩን ይገልጻል። በመጨረሻም የኢትዮጵያ ጥንካሬ መንበርከክ መሆኑን በማንሳት፣ "ስሜ የተጠራበት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ... እኔ ከሰማይ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ" (2ኛ ዜና መዋዕል 7፥14) የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በተግባር እንድናውለው ጥሪ ያደርጋል።
ይህ መዝሙር ለፖለቲከኛውም ሆነ ለሃይማኖት መሪው መስተዋት ነው። "ባለ ማዕተቦች" እና እውነተኛ አማኞች ከስሜታዊነት ወጥተው ስለውድቀታቸው እንዲያስቡ፣ እንዲጸልዩ እና ወደ ፈጣሪያቸው እንዲመለሱ የሚጠይቅ የነፍስ ጥሪ ነው።
ለዘ-ሐበሻ ማርታ ከሚኒሶታ

ወንድማማቾቹ ቲዮ እና ሉካስ ሄርናንዴዝ በፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሉካስ ሄርናንዴዝ እና ቲዮ ሄርናንዴዝ በአውሮፓ ክለቦች እና በብሔራዊ ቡድን ስኬታማ ከሆኑ ወንድማማቾች መካከል ግንባር ቀደሞቹ ናቸው።
ወንድማማቾቹ የተከላካይ መስመር ተጫዋች መሆናቸው ብቻ ሳይሆን፥ በተመሳሳይ በግራ ተከላካይነት የሚጫወቱ መሆናቸው ግርምትን የሚፈጥረው ሌላኛው አጋጣሚ ነው፡፡
ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የጋራ ታሪክ መጻፍ የቻሉት ወንድማማቾቹ፤ ሁለቱም በግራ መስመር ተከላካይነት ላይ የሚጫወቱ በመሆናቸው በቦታው ተመራጭ ለመሆን ብርቱ ፉክክር ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡
በ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ ፈረንሳይ ባደረገችው የመጀመሪያ ጨዋታ ትልቁ ሉካስ ሄርናንዴዝ ከባድ የጉልበት ጉዳት ሲያጋጥመው፣ በምትኩ ተቀይሮ የገባው ወንድሙ ቲዮ ሄርናንዴዝ እንደነበር አይዘነጋም።
በተጨማሪም በ2021 ፈረንሳይ የቤልጂየምን ብሔራዊ ቡድን 3 ለ 2 ስታሸንፍ ሁለቱም ወንድማማቾች ጨዋታውን በቋሚነት አብረው ጀምረዋል፡፡
በጨዋታው ቲዮ ሄርናንዴዝ የማሸነፊያዋን ግብ አስቆጥሮ ወንድማማቾቹ ለፈረንሳይ አብረው ተሰልፈው ድል ማስመዝገብ ችለዋል።
አሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ በጥምረት ባዘጋጁት የ2026 የዓለም ዋንጫም በአሠልጣኝ ዲዲርዬ ዴሾ ጥሪ ደርሷቸው ውድድሩ ወደ ሚደረግበት ቦታ አቅንተዋል።
በዓለም ዋንጫ ከአንድ ቤተሰብ መጥተው በታላቁ መድረክ ከሚካፈሉ ቤተሰቦች መካከል ናቸው።
በሙባረክ ፋንታው

8 days ago
በጋዜጠኛ አብዲ ከማል ባለቤት አዲስ የሃገር ውስጥ የሂሳብ ቁጥር መከፈቱን ስለማሳወቅ!
በቅርቡ በሞት የተለየንን የወንድማችን ጋዜጠኛ አብዲ ከማል ቤተሰብን ለማገዝ የአቅማችሁን በመለገስ እንድትተባበሩን በጠየቅናችሁ ጊዜ ብዙዎቻችሁ የሂሳብ ቁጥሩ በባለቤቱ ቢሆን እንደምትመርጡ በቅንነት ሃሳባችሁን ሰጥታችሁ ተመልክተናል። በቅድሚያ ለአብዲና ለቤተሰቡ ላሳያችሁት ወገንተናዊነትና መቆርቆር ከልብ እያመሰገንን ይኸው ፈቃዳችሁን ለመፈጸም ባለቤቱ ሰሚራ ሙዘሚል በአስተባባሪዎች ከተከፈተው የጋራ የሂሳብ ቁጥር በተጨማሪ ለዚሁ አላማ የሚውል የሂሳብ ቁጥር በስሟ አውጥታለች።
የኢትዮዽያ ንግድ ባንክ
ሰሚራ ሙዘሚል
1000771271937
እባካችሁን ይህ የምታደርጉት አስተዋፅኦ ከሚጠብቃቸው በጣም አስቸጋሪ ጊዜ አንጻር በድንገት አባታቸውን ላጡት ሶስት ልጆቹ ፣ ብቻዋን ለቀረችው ባለቤቱና ለመላው ቤተሰቡ ትርጉሙ ብዙ ነው።
ከሀገር ውጭ ያላችሁ ደግሞ ከዚህ በታች በተያያዘው ሊንክ የበኩላችሁን ‘ጎፈንድሚ’ ላይ ለግሱን።
https://gofund.me/e1bdc8ed...
እባካችሁ አደራችንን እንድንወጣ አግዙን!

#ነውረኞቹን_ተጠንቀቁ‼️ #ያሳዝናል
ይህ ወንድማችን #ሚኒሊክ_ብርሀኑ ይባላል፣ከቤተሰቡ ከጠፋ 2ዓመት አልፎታል!የተጨነቀች እህቱ "እባካችሁን ወንድሜ ጠፍቶ ቀረብኝ ዛሬ ደግሞ ልደቱ ነበር እናት አባቱም እያለቀሱ ነው አግዙኝ"ብላ በፌስቡክ ለጥፈነው እናንተ ደጋጎችን አስቸግረን ነበር፣
ትላንት አንድ ኮማንደር ነኝ የሚል ሰው በተቀመጠው የእህቱ ስልክ ደውሎ" ትክክለኛ እህቱ ነሽ?እስካሁንስ የት ሄዳችሁ ነው?ልጁ እኮ ጭንቅላቱን በጥይት ተመቶ በአፋር ክልል ወታደራዊ ካምፕ ተኝቶ ነው የሚገኘው፣ፎቶውን እልክልሻለሁ፣ብታይው ታውቂዋለሽ ወይ?ብሎ ጠየቃት!አዎ ወንድሜ አደል አለችው!
በፍጥነት Edit ተደርጎ የታመመ ሰው ፎቶ ልኮላት የተጨነቀች እህት ስታየው እውነትም ወንድሟ ሚኒሊክ መስሏት እንኳን በህይወት ኖረልኝ"ምንድነው ማድረግ ያለብኝ?"ብላ ጠየቀችው፣
አንቺ ተረጋጊ መቀበል ከቻልሽ ሹፌር አመቻችና ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እልክልሻለሁ፣ብሎ የተባባሪውን የሹፌር ስልክ ላከላት!
ምስኪን እህት ፅዮን ሹፌሩ የተባለው ጋር ደውላ አወሩ፣አይዞሸ እኔም ወንድ ልጅ አይደለሁ፣መውደቂያዬን አላውቅም፣ለራሴ ስል ነው መልካም ማደርገው፣አላት፣የነዳጅ 8000ብር ላከችለት፣ወደ አዲስ አበባ እስኪመጣ ኦክስጅኑ መነቀል ስለማይችል ተመላሽ የሚሆን ማስያዣ 23500 ይፈልጋሉ ብሏት በድጋሚ ላከችለት፣አድራሻዋን ጠየቃት ስደርስ እደውላለው አላት፣
ትላንት ቀኑን ሙሉ በጉጉትና በተስፋ ጠበቀችው፣በየመሀሉ ስትደወልለት እዚህ ደርሻለው እያለ ተስፋ ሰጥቷታል፣ ሲመሽ አሁንስ ወንድሜ የት ደረስክ ስትለው መተሀራ ነኝ ተዘጋጂ ብሏታል!
ቶሎ በመድረሱ ገርሟታል፣ቀኑን ሙሉ እያለቀሰች ለአመታት ድምፁ እንኳ የናፈቃት ወንድሟን ለማየት ጓጉታለች፣ "አይኑ ግን ያያል?ብላ ደጋግማ ጠይቃለች!እስክትዳብሰው ጓጉታለች!!
ሰዓታት ሄዱ ቀኑን ሙሉ ስትደውልለት የነበረው ሹፌር ስልኩ ዝግ ሆነ፣ኮማንደር የተባለው ጋርም ስትደውል "ጥሪ አይቀበልም" አላት፣ ደነገጠች ስታሰላስል እንደተጫወቱባት ተረዳች፣ወደ ፖሊስ አመራች፣ "ሸውደውሻል ሌቦች ናቸው" አመልክቺ አሏት!!
በሰው ህይወት የሚጫወቱ አረ መ ኔዎችን ህጉ እንዴት ይሆን የሚቀጣቸው?ከመስረቃቸው የሚሄዱበት የወንጀሉ ርቀት አስቡት እስኪ😭 በውሸት በተቀነባበረ ፎቶ እንዲህ ሆኖ ሲያዩ ሌላ የሚጎዳ እናት አባት ቤተሰብ አለ እኮ፣ እንዴትስ ነው የሚያስችላችሁ? እባካችሁን ሌሎቻትሁ ተጠንቀቁ‼️
እህቱ ፅዮን "ከኔ ተማሩ ከወንጀለኞች ራሳችሁን ጠብቁ🙏 "ብላችኋለች!እናንተም መረጃው ለብዙዎች እንዲደርስ ሌላ ሰው እንዳይሸወድ #ሼር አድርጉ🙏 ለምታውቁት ሁሉ አሳውቁ‼️
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም" #ባይሽ_ኮልፌ

የአባቱን ፈለግ የተከተለው የዲያጎ ሲሞኔ ልጅ ጁሊያኖ ሲሞኔ…
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአትሌቲኮ ማድሪዱ ስኬታማ አሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኔ በተጫዋችነት ዘመኑ ለሀገሩ አርጀንቲና ትልቅ ክብርና ስኬትን ካስመዘገቡ ታላላቅ ኮከቦች ተርታ ይመደባል።
ለሀገሩ ብሔራዊ ቡድን ከ100 በላይ ጨዋታዎችን ያደረገው ሲሞኔ÷ አልቢሴሌስቴዎቹ በ1991 እና 1993 የኮፓ አሜሪካ ዋንጫን ሲያነሱ የቡድኑ የልብ ትርታና የሜዳ ላይ መሪ በመሆን ታሪክ ሰርቷል።
አሁን ደግሞ የዚህ ታላቅ ተጫዋች ፈለግ በልጆቹ እየተደገመ ይገኛል።
የአባቱን ፈለግ የተከተለው ወጣቱ ጁሊያኖ ሲሞኔ ከቀናት በኋላ በሚጀምረው የ2026 ዓለም ዋንጫ ላይ የአርጀንቲናን ብሔራዊ ቡድን ወክሎ ለመጫወት ተዘጋጅቷል።
በአሁኑ ሰዓት በአትሌቲኮ ማድሪድ ቤት በአባቱ ስር እየተጫወተ የሚገኘው ጁሊያኖ÷ ቀደም ሲል በአርጀንቲና ከ23 ዓመት በታች የኦሊምፒክ ቡድን ውስጥ በመካተት ሀገሩን መወከል ችሏል።
ይህ የቤተሰብ ስኬት በጁሊያኖ ብቻ የተገደበ ሳይሆን ከዚህ በፊት የዲያጎ ሲሞኔ የመጀመሪያ ልጅ የሆነው ጆቫኒ ሲሞኔም በተመሳሳይ ለዋናው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በመጫወት ግብ ማስቆጠር መቻሉ ይታወሳል።
አባት በክብር የተጫወተባትን ማልያ ልጆቹም ደግመው በመልበስ የቤተሰቡን ስም በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ላይ በደማቅ ቀለም እየጻፉት ይገኛሉ።

Comments