Logo
Getu Temesgen
የስልሳ ዓመታት የታማኝነት ጉዞን የሚዘክር የቤተሰብ እና የአንድነት የጎዳና ላይ ሩጫ ሊካሄድ ነው
#ethiopia | ኮሜርሺያል ኖሚኒስ የስልሳ ዓመታት የሥራ ጉዞውን እና የቆየ የታማኝነት አገልግሎቱን ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀው የጎዳና ላይ ሩጫ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

በተቋሙ አዘጋጅነት የሚከናወነው በዚህ የ5 ኪሎ ሜትር የነፃነት እና የአንድነት መርሃ ግብር ላይ የድርጅቱ ሠራተኞች፣ ደንበኞች፣ አጋር ድርጅቶች እና የባለድርሻ አካላት በጋራ ይሳተፋሉ።

የዝግጅቱ ዋና ዓላማ በተጠቃሚው ማህበረሰብ፣ በሠራተኞች እና በደንበኞች መካከል ያለውን ማህበራዊ ትስስር ይበልጥ ማጠናከር እና ቤተሰባዊ መቀራረብን መፍጠር ነው።

ለሩጫው የተዘጋጁ ቲሸርቶችን በኮሜርሺያል ኖሚኒስ ዋና መሥሪያ ቤት እና በአዲስ አበባ በሚገኙ በተመረጡ ቅርንጫፎች ማግኘት ይቻላል።

እያንዳንዱ ቲሸርት በ500 ብር የሚሸጥ ሲሆን፣ ክፍያውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000770855237 (CN for Event Management) ወይም በሲቢኢ ብር መፈጸም ይቻላል።

ቲሸርቶቹን ለማግኘት እና መረጃ ለመጠየቅ በሚከተሉት የቅርንጫፍ ስልክ ቁጥሮች ማነጋገር ይቻላል

ዋና መሥሪያ ቤት +251-932-151385
መገናኛ ቅርንጫፍ +251-913-597811
ቦሌ ቅርንጫፍ +251-913-076712
አራዳ ቅርንጫፍ +251-921-853930
ሳሪስ ቅርንጫፍ +251-912-082257
የካ ቅርንጫፍ +251-910-163606
መርካቶ ቅርንጫፍ +251-951-104612
ልደታ ቅርንጫፍ +251-913-612395
ኮልፌ ቅርንጫፍ +251-911-917647
ቂርቆስ ቅርንጫፍ +251-911-827569
ቃሊቲ ቅርንጫፍ +251-931-272727

የሩጫው መነሻ መስመር ከአትላስ መኪና ማቆሚያ ተነስቶ ወደ ኡራኤል ቤተክርስቲያን አደባባይ ከመድረሱ በፊት ወደ ግራ በመታጠፍ ወደ አትላስ ኢንተርናሽናል ሆቴል ያመራል።

በመቀጠልም በቦሌ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን እና በሸገር ሕንፃ አጠገብ አልፎ መድረሻውን ድጋሚ በአትላስ መኪና ማቆሚያ ያደርጋል።

ይህ ታላቅ ስፖርታዊ መርሃ ግብር ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የሚከናወን ይሆናል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ
በ6630 ነፃ የስልክ መስመር
ወይም
በ0932151385 እና በ0904032498
ደውሎ መረዳት ይቻላል።
#commercialnominees #familyrun #healthylifestyle #running #community #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

17 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.