ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕና አለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) የ80 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ።
በስምምነቱ መሰረት ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 80 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የረዥም ጊዜ ብድር ያቀርባል ።
በተገኘው ገንዘብ ደግሞ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሸራተን አዲስ ሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴልን በዘመናዊ መልኩ ያድሳል፣በሸራተን ደረጃ አዲስ ሆቴል ይገነባል።
የብድር ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድና የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) የአፍሪካ ቀጠና ምክትል ፕሬዚዳንት ኢትዮዺስ ተፈራ በኬንያ ናይሮቢ ተፈራርመዋል።
ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ተቋም ጋር ከፍተኛ ፋይዳ ያለውን አጋርነት በማድረጋችን ለተቋሙ ያለንን አድናቆት መግለጽ እንወዳለን ያሉት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አሕመድ፤ ይህ አጋርነት የሀገሪቱን የሆስፒታሊቲ ዘርፍ ለማዘመን እንዲሁም በኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለው የሥራ ዕድል ፈጠራን በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።
የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የአፍሪካ ቀጠና ምክትል ፕሬዚዳንት ኢትዮዺስ ተፈራ በበኩላቸው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የአገልግሎት ዘርፉን የበለጠ እንዲያዘምንና ተጨማሪ የስራ እድል እንደፈጥር ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል።
ከአለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በሚገኘው ገንዘብ ሸራተን አዲስ ኤሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል ዘመኑን በሚመጥን መልኩ የሚታደስ ሲሆን በሸራተን የንግድ ምልክት የሚጠራ ተጨማሪ አዲስ ሆቴልም ይገነባል።
የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) የብድር አቅርቦት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አካል የሆነውን የሸራተን አዲስን ገጽታ በእጅጉ እንደሚለውጠው ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለማዘጋጀት መመረጧን ተከትሎ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሚሊኒየም አዳራሽ ቅጥር ግቢ ዘመናዊ ሆቴል (Moxy by Marriott) ፣ በመሀመድያ የመኖሪያ መንደር (Four Points by Sheraton) ሆቴሎች ግንባታን አስጀምሯል።
በቅርቡ የሚድሮክ ቤተሰብን የተቀላቀለው ዋቢሸበሌ ሆቴል (autograph collection by Marriot) ደረጃ ለጉባኤው ዝግጁ ለማድረግ ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ የእድሳት ስራው ተጀምሯል።
አፍሪካ ህብረት አጠገብ እየተገነባ ያለው ዌስት ኢን አዲስ (Westin Addis) ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በባህርዳር ከተማ (Four Points by Sheraton) እና (Protea by Marriott) ፣በጂማ እና ሃዋሳም በተመሳሳይ (Four Points by Sheraton) ሆቴሎችን እየገነባ ይገኛል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የላንጋኖ ሳቫና ሪዞርትን በግዥ የተረከበው ሲሆን በማርዮት ብራንዶች ደረጃ አለም አቀፍ ሪዞርት በመገንባት ወደ ስራ ይገባል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርና፣ በማእድን፣ በንግድና በሆስፒታሊቲ ዘርፍ በመሰማራት ከ80 ሺህ በላይ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር የቻለ ግዙፍ ተቋም ነው።

4 days ago