በረከቷ ይደርብንና ሲንጋፖር ህጻናቶቿን በገንዘብ እየደገፈች ነው
#ethiopia | ሲንጋፖራውያን ሦስት እና ከዚያ በላይ ልጆችን እንዲወልዱ ለማበረታታት ታስቦ በተጀመረው አዲስ የመንግሥት የገንዘብ ድጋፍ መርሐግብር፣ በመጀመሪያው ዓመት ውስጥ ብቻ ወደ 5,000 የሚጠጉ ህጻናት ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል።
በሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ ባለፈው ዓመት ይፋ በተደረገው ‘የትላልቅ ቤተሰቦች መርሐግብር’ መሠረት፣ ከየካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለሚወለድ ሦስተኛና ከዚያ በላይ ለሆነ እያንዳንዱ ልጅ ቤተሰቦች እስከ 16,000 የሲንጋፖር ዶላር (12,427 የአሜሪካ ዶላር) የሚደርስ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ።
ይህ የድጋፍ ማዕቀፍ የረጅም እና የአጭር ጊዜ የገንዘብ እፎይታን የሚሰጥ ሲሆን፣
ለልጁ አካውንት የሚደረግ የ10,000 የሲንጋፖር ዶላር ድጋፍ ገንዘቡ ለልጁ ወይም ለእህትና ወንድሞቹ የቅድመ-መደበኛ ትምህርት እና የጤና እንክብካቤ ወጪዎችን ለመሸፈን ይውላል።
ለእያንዳንዱ አዲስ ለሚወለድ ልጅ ከሚሰጠው መደበኛ የ5,000 ዶላር ድጋፍ በተጨማሪ፣ በቀጥታ በእናቲቱ አካውንት ውስጥ የሚገባ ተጨማሪ 5,000 የሲንጋፖር ዶላር ይሰጣል። ይህም ከእርግዝና፣ ከወሊድ፣ እንዲሁም ከቤተሰብ አባላት የሕክምና ወጪዎች ጋር የተያያዙ ክፍያዎችን ለመሸፈን ያገለግላል።
መሥፈርቱን የሚያሟሉ ህጻናት ዕድሜያቸው ከአንድ እስከ ስድስት ዓመት እስኪደርስ ድረስ በየዓመቱ የ1,000 የሲንጋፖር ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ። ይህ ደግሞ እንደ አስቤዛ፣ የውሃና መብራት ክፍያዎች፣ እንዲሁም የትራንስፖርት ወጪዎችን የመሳሰሉ የእለት ተእለት የቤተሰብ የኑሮ ጫናዎችን ለማቃለል ያለመ ነው።
የሲንጋፖር የማህበራዊ እና ቤተሰብ ልማት ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ለ‘ዘ ስትሬትስ ታይምስ’ ጋዜጣ እንደገለጹት፣ እስከ መጋቢት ወር ድረስ ወደ 5,000 የሚጠጉ ህጻናት የተሻሻለውን የልጆች ዕድገት እና የሕክምና የገንዘብ ድጋፎችን በተጨባጭ አግኝተዋል።
መርሐግብሩ ከየካቲት 2025 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ሦስተኛና ከዚያ በላይ ልጅ የነበራቸው ቤተሰቦችም ከዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ። እነዚህ ቤተሰቦች ከጥር 1 ቀን 2019 እስከ የካቲት 17 ቀን 2025 የተወለደ ልጅ ካላቸው፣ የተወሰኑ ቅድመ-ሁኔታዎችን አሟልተው የዓመታዊ የገንዘብ ድጋፉ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ በዘገባው ተመላክቷል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

4 hours ago