ሰላም፣ ደህና አደራችሁ?
የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ!
የሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጥ፣ የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያፋጥን እና የዜጎችን የኑሮ ደረጃ የሚያሻሽል መርሐ ግብር ነው።
ዋና ዓላማው በቤተሰብ ደረጃ እንደ ዶሮ፣ እንቁላል፣ ወተት፣ ማር እና ሌሎች የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን በማሳደግ የምግብ እጥረትን መቀነስ፣ የሥራ እድል መፍጠር እና የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት ነው።
የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ካስመዘገባቸው ትልልቅ ውጤቶች መካከል የምግብ ዋስትናን ማሻሻል ቀዳሚው ነው።
መርሐ ግብሩ የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር እና የቤተሰብ ገቢን ለማሻሻል ተጨባጭ ውጤቶች የተመዘገቡበት ሲሆን÷ በተለይ በህጻናትና በእናቶች ላይ የሚታዩ የሥነ ምግብ ችግሮችን ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
በርካታ ዜጎችም በዶሮ እርባታ፣ በወተት ላሞች እንክብካቤ፣ በአሳ እርባታ፣ በማር ምርት፣ በግብይት፣ በማጓጓዝ እና በምርት ማቀነባበር ዘርፎች የሥራ እድል አግኝተዋል።
የኑሮ ውድነትን በመቀነስ የሚጫወተው ሚናም ቀላል የሚባል አይደለም፡፡
በመርሐ ግብሩ በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች መጠን ሲጨምር በገበያ ላይ ያለው አቅርቦትም ተሻሽሏል።
የሌማት ትሩፋት የግብርናውን ዘርፍ በማጠናከር ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል።
የሀገር ውስጥ ምርትን በመጨመር ከውጭ የሚገቡ አንዳንድ ምርቶችን ለመተካት እድል የፈጠረ ሲሆን÷ ይህም የውጭ ምንዛሪ ወጪን ለመቀነስ አግዟል።
በአንጻሩ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን በማሳደግ የውጭ ምንዛሪ ገቢን የሚያሳድግ ሆኗል።
መርሐ ግብሩ በመንግሥት፣ በግሉ ዘርፍ እና በማህበረሰቡ መካከል የተቀናጀ ትብብር እንዲፈጠርም አድርጓል።
በዚህም በብዙ አካባቢዎች የልማት ሥራዎች በሕዝብ ተሳትፎ ይከናወናሉ።
መርሐ ግብሩ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ከመቻል አልፋ የግብርና ምርቶችን በብዛት ለውጭ ገበያ በማቅረብ ተወዳዳሪ ሀገር እንድትሆን ያስችላል።

4 days ago