3 months ago
ስፔን የ23ኛው ዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነች
********************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ስፔን አርጀንቲናን 1 ለ 0 በማሸነፍ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ሆናለች።
የጨዋታው መደበኛ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ በመጠናቀቁ አሸናፊውን ለመለየት 30 ደቂቃ ተጨምሯል።
በጭማሪው ክፍለ ጊዜ 106ኛው ደቂቃ ላይ ፌራን ቶሬስ ያስቆጠራት ግብ ስፔንን አሸናፊ አድርጋለች።
በዚህም ስፔን ከ16 ዓመታት በኋላ ውድድሩን አሸንፋ በታሪኳ ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ባለቤት ሆናለች።
#worldcup #fifaworldcup #fifaworldcup2026 #argentina #spain #finalmatch #football #sports

ስፔን 1-0 አርጀንቲና
*********
እየተካሄደ ባለው የ23ኛው ዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ስፔን 106ኛው ደቂቃ ላይ በፌራን ቶሬስ አማካኝነት ባስቆጠረችው ግብ 1 ለ 0 መምራት ጀምራለች።

አርጀንቲና 0 - 0 ስፔን :- የመደበኛ ሰዓት ውጤት
*****************
በአርጀንቲና እና በስፔን መካከል እየተደረገ የሚገኘው የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ መደበኛው የ90 ደቂቃ ክፍለ ጊዜ ያለምንም ግብ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።
በጨዋታው መደበኛ ክፍለ ጊዜ አሸናፊ ባለመገኘቱ፣ አሸናፊውን ለመለየት ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ አምርቷል።
ኤንዞ ፈርናንዴዝ ፓብሎ ኩባርሲ ላይ በሰራው ጥፋት 90+3 ደቂቃ ላይ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

በዓለም ዋንጫ የደረጃ ጨዋታ እንግሊዝ ፈረንሳይን አሸነፈች
**********************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ 3ኛ ደረጃን ይዞ ለማጠናቀቅ በግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚዎቹ ሀገራት መካከል የተካሄደው የደረጃ ጨዋታ፤ በእንግሊዝ 6 ለ 4 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
አስር ግቦች በተቆጠሩበት ጨዋታ፤ ለእንግሊዝ ዲክላን ራይስ፣ ኤዝሪ ኮንሳህ፣ ጁድ ቤሊንግሃም እንዲሁም ቡካዮ ሳካ(ሦስት) አስቆጥረዋል።
የፈረንሳይን ግቦች ደግሞ ኪሊያን ምባፔ(ሁለት)፣ ብራድሊ ባርኮላ እና ኡስማን ዴምቤሌ ከመረብ አሳርፈዋል።
በዚህም 3ኛ ደረጃን ያገኘችው እንግሊዝ የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች።
በጨዋታው ሁለት ግቦችን ያስቆጠረው ኪሊያን ምባፔ ደግሞ፤ በምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት 22ኛውን በዚህ ዓለም ዋንጫ ደግሞ 10ኛውን በማስመዝገብ የወርቅ ጫማ ሽልማት ፉክክሩን ከሊዮኔል ሜሲ በመላቅ አስቀድሞ መምራት ጀምሯል።
ማይክል ኦሊሴ በዓለም ዋንጫ ሰባት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል በፔሌ ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን አሻሽሏል።
#worldcup #fifaworldcup #fifaworldcup2026 #3rdplaceplayoff #england #france #football #sports

ከስንብት ሐዘን ማግስት የሚደረግ የክብር ፍልሚያ
*******************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ዋዜማ ላይ ቆመናል። ዓለም ዋንጫ በግማሽ ፍፃሜ በለስ ያልቀናቸውን፣ ድል ከነርሱ ጋር ያልነበረውን እንዲሁ አያሰናብትም። ለሦስተኝነት ማዕረግ ዳግም ያፋልማል።
23ኛው ዓለም ዋንጫ ፍሎሪዳ ላይ የግማሽ ፍፃሜ ተሸናፊዎቹን ዛሬ እኩለ ሌሊት 6 ሰዓት ፍሎሪዳ ሚያሚ ላይ ያፎካክራል። በእርግጥ በብዙዎች፣ በተለይም በተሸናፊ ብሔራዊ ቡድኖች ዘንድ የደረጃው ጨዋታ ለመጫወት የተመረጠ አይደለም።
የዛሬው መርኃ ግብር ግን ብሔራዊ ቡድኖቹ ከሚያደርጉት ፉክክር ባልተናነሰ፣ በኮከብ ግብ አስቆጣሪነት በመላቅ የወርቅ ኳስ ሽልማቱን ለማግኘት ባለው ፉክክር ለውጥ እንደሚያስከትል ይጠበቃል። ከሊዮኔል ሜሲ ጋር የኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ፉክክሩን በ8 ግቦች እየመራ የሚገኘው ኪሊያን ምባፔ እንዲሁም እያንዳንዳቸው ስድስት ግቦች ያስቆጠሩት ጁድ ቤሊንግሃም እና ሀሪኬን ከባለ አምስት ግቡ የዓለም ኮከብ ኡስማን ዴምቤሌ ጋር በሚያደርጉት የኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ፉክክር ላይ አንዳች ለውጥ ሊያስከትል የሚችል ጨዋታ እንደሚሆን ታምኗል።
በዚህ መሀል ግን ከሽንፈት ማግስት የሚደረግ፤ ከዓለም ዋንጫ ስንብት ሀዘንም ሳያገግሙ የሚመጣ መርኃ ግብር መሆኑ የተጫዋቾችን ተነሳሽነት መቀነሱ፣ የተመልካቾችን ጉጉትም ማሳነሱ አይቀርም። ቶማስ ቱሄል ይህን የሚያስረግጥ ሃሳብ ነው የሰነዘሩት። "የእኛም ሆነ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ይህን ጨዋታ የማድረግ ፍላጎት የላቸውም" በማለት በውድድሩ ሙሉ የለፉትና የተዘጋጁት ለዓለም ሻምፒዮንነት በመሆኑና፤ ያም ባለመሳካቱ ለዚህ ጨዋታ የሚኖራቸውን ጉጉትና ፍላጎት እንደቀነሰው ተናግረዋል።
ቱሄል ይህንን ቢሉም የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዲዲየር ዴሻው ግን ከዚህ በአንፃራዊነት የተለየ ሃሳብ ነው የሰነዘሩት። 3ኛ ደረጃም ቢሆን የተሻለ መሆኑን በማንሳት፤ እርሱን ለማሳካት የቻሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። አክለውም የተፈጠረው ሀዘን የዓለም ሻምፒዮን ከመሆን ፅኑ መሻት የመጣ መሆኑን ጠቅሰው፤ የሆነውን ከመቀበል ውጪ አማራጭ የለንም ብለዋል።
በግማሽ ፍፃሜው እንግሊዝ እየመራች የነበረችውን ጨዋታ የኋላ ኋላ በአርጀንቲና 2 ለ 1 ተሸንፋ የፍፃሜ መንገዷ ሲቋረጥ፤ በአንፃሩ ፈረንሳይ ባልተጠበቀ ሁኔታ በስፔን ፍፁም ብልጫ ተወስዶባት 2 ለ 0 ተረታ ነው ከፍፃሜው የቀረችው።
የ23ኛው ዓለም ዋንጫ 103ኛው ጨዋታ በሁለት ሃሳቦች መሀል፤ የጨዋታውን አስፈላጊነት ተጠይቅ ውስጥ በሚከቱና የኮከብ ግብ አግቢነት ፉክክሩ ላይ የሚኖረውን ሚና በሚያጎሉ መሀል ሆኖ፤ እኩለ ሌሊት 6፡00 ሰዓት በሚያሚ ጋርደን ሀርድ ሮክ ስታዲየም ይካሄዳል።
በእድሪስ አህመድ

አርጀንቲና ወደ ዓለም ዋንጫ ፍፃሜ አለፈች
***************
በ23ኛው የዓለም ዋንጫ በአትላንታ ስታዲየም በእንግሊዝና አርጀንቲና መካከል የተካሄደው ተጠባቂ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በአርጀንቲና 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ለአርጀንቲና የአሸናፊነት ግቦቹን በ85ኛው ደቂቃ ኤንዞ ፈርናንዴዝ እንዲሁም በጭማሪ ሰዓት (90+3) ላውታሮ ማርቲኔዝ ከመረብ አሳርፈዋል። ለእንግሊዝ ብቸኛዋን ግብ በ55ኛው ደቂቃ አንቶኒ ጎርደን አስቆጥሯል።
የወቅቱ የዓለም ሻምፒዮን አርጀንቲና ለዋንጫው ክብሯን ለማስጠበቅ የፊታችን እሁድ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር ታላቅ የፍፃሜ ጨዋታዋን ታደርጋለች።
የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ተሸናፊዎቹ ፈረንሳይና እንግሊዝ ደግሞ የፊታችን ቅዳሜ ሌሊት 3ኛ ደረጃ ይዞ ለማጠናቀቅ የሚጫወቱ ይሆናል።
#worldcup #fifaworldcup2026 #fifaworldcup #england #argentina #semifinal #football #sports

እንግሊዝ 0 - 0 አርጀንቲና :- የመጀመሪያ አጋማሽ ውጤት
**************
በአትላንታ ስታዲየም በእንግሊዝ እና አርጀንቲና መካከል እየተካሄደ የሚገኘው እጅግ ተጠባቂ የዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የመጀመሪያው 45 ደቂቃ ያለምንም ግብ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።
#worldcup #fifaworldcup2026 #fifaworldcup #england #argentina #semifinal #football #sports
**************
በአትላንታ ስታዲየም በእንግሊዝ እና አርጀንቲና መካከል እየተካሄደ የሚገኘው እጅግ ተጠባቂ የዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የመጀመሪያው 45 ደቂቃ ያለምንም ግብ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።
#worldcup #fifaworldcup2026 #fifaworldcup #england #argentina #semifinal #football #sports
3 months ago
ፈረንሳይና አርጀንቲና በቅጣት ምቶች እኩል ሪከርድ አላቸው
#ethiopia | በመጨረሻዎቹ ሶስት የፊፋ ዓለም ዋንጫ ውድድሮች (2018፣ 2022 እና 2026) ፈረንሳይና አርጀንቲና እያንዳንዳቸው 8 የፍፁም ቅጣት ምቶች ተሰጥተዋል።
ይህ መረጃ ሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች በተጠቀሱት ሦስት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ተመሳሳይ ቁጥር ያለው የፍፁም ቅጣት ምት እንዳገኙ ያሳያል።
በ2026 የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ ከሞሮኮ ጋር በተደረገው ጨዋታም ፈረንሳይ የፍፁም ቅጣት ምት አግኝታ ቢሆንም፣ ኪሊያን ምባፔ ወደ ግብ መቀየር አልቻለም።
#fifaworldcup #france #argentina #mbappe #messi #getu

"ጨዋታው ተጭበርብሯል፤ ዓለም ሁሉ አይቶታል!"
— አሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን
* የግብፅ–አርጀንቲና ጨዋታ በዳኝነት ውሳኔዎች መነጋገሪያ ሆነ
#ethiopia | በ2026 የዓለም ዋንጫ የ16 ዙር ማጣሪያ አርጀንቲና ግብፅን 3 ለ 2 በሆነ አስደናቂ ውጤት አሸንፋ ወደ ሩብ ፍጻሜ ብታልፍም፣ ከውጤቱ በላይ በሜዳ ላይ የታዩት የዳኝነት ውሳኔዎችና ውዝግቦች የዓለም ስፖርት ሚዲያዎችን እያናወጡ ይገኛሉ።
ከ2 ጎል መሪነት እስከ መጨረሻው ደቂቃ "ንፁህ ቀውስ" (Pure Chaos)
ግብፅ በመጀመሪያው ክፍለ ጨዋታ "እንደ ፒራሚድ ፀንታ" ድንቅ የመከላከል ብቃት በማሳየት አርጀንቲናን በከባድ ሁኔታ ፈትና ነበር። ሆኖም አርጀንቲና ከሁለት ጎሎች መመራት በኋላ ተስፋ ሳትቆርጥ ባሳየችው አስደናቂ የመመለስ ብቃት ጨዋታውን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሲል በነበረው ከፍተኛ ውጥረት ዳኛው በስምንት ደቂቃ ውስጥ ብቻ 5 የቢጫ ካርዶችን ለመምዘዝ ተገዷል።
"ሁሉም ነገር ስለ ገንዘብ ነው፤ ሜሲ እንዲቆይ ይፈልጋሉ!" — የአሰልጣኙ ሆሳም ሀሰን ቁጣ
ከጨዋታው በኋላ የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን በሰጡት እጅግ ቅሬታ የተሞላበትና ያልተጠበቀ መግለጫ ፊፋንና የዳኝነት ቡድኑን በኃይለኛ ቃላት ወርፈዋል፦
*ስለ ቪአይአር (VAR) ውሳኔዎች፦
"በመሐመድ ሳላህ ላይ የተሰራው ጥፋት (የፍጹም ቅጣት ምት) በVAR ሳይታይ ቀርቷል፤
ሁለተኛው ጎላችንም ባልታወቀ ምክንያት ተሰርዟል።
ማክ አሊስተር ማሊያ ሲጎትት እያየን VAR አልተፈተሸም።"
ስለ ፈረንሳዩ ዳኛ ምደባ፦
"አርጀንቲና በ2022 ፈረንሳይን ማሸነፏን ተከትሎ በነበረው ሁኔታ የዚህን ፈረንሳዊ ዳኛ መመደብ ቀድመን ተቃውመን ነበር።"
"እውነቱን ለመናገር ጨዋታው በግልጽ የተጭበረበረ ነበር። ሁሉም ነገር ስለ ገንዘብ ነው። ሊዮኔል ሜሲ በውድድሩ ውስጥ እንዲቆይ ይፈልጋሉ። አርጀንቲና እንድታሸንፍ ይህን ያህል የሚፈልጉ ከሆነ ሌላውን ቡድን ለምን ለውድድር ይጠሩታል?"
የአሰልጣኙ ሆሳም ሀሰን ውሳኔ፦
"ከደረሰብን ኢፍትሃዊነት የተነሳ ከእንግዲህ አንድም ደቂቃ የዚህን ዓለም ዋንጫ ጨዋታ አልመለከትም!"
የእግር ኳስ ተንታኞች፦
የግብፅን አስደናቂ ተጋድሎና የአርጀንቲናን እስከ መጨረሻው የመታገል መንፈስ እያደነቁ ቢሆንም፣ የዳኝነት ውሳኔዎቹ ግን ጨዋታውን መበላሸታቸውን ይስማማሉ።
የፊፋ (FIFA) ምላሽ፦
እስካሁን ድረስ ፊፋ በአሰልጣኙ ክስ ላይ የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም፤ ክሶቹም በገለልተኛ አካል አልተረጋገጡም።
የእናንተስ አስተያየት ምንድነው?
የአፍሪካ እግር ኳስ አፍቃሪያን!
በግብፅ ላይ የተፈጸመው የዳኝነት ውሳኔ ትክክል ነበር ወይስ አሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን እንዳሉት አድልዎ ተፈጥሯል?
**ሀሳባችሁን በኮሜንት መስጫው ላይ ያካፍሉን!
አለባቸው ደሳለኝ ከለንደን
**#fifaworldcup #egypt #argentina #hossamhassan #mohamedsalah #messi #africa #footballnews **

ስዊዘርላንድ ስምንተኛዋ ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀለች ሀገር ሆናለች
************************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ የ16ቱ ሀገራት ጥሎ ማለፍ የመጨረሻው ጨዋታ ስዊዘርላንድ ኮሎምቢያን አሸንፋለች።
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ እና ጭማሪው 30 ደቂቃ ያለግብ ተጠናቀው፤ አሸናፊውን ለመለየት በተሰጡ መለያ ምቶች ስዊዘርላንድ 4 ለ 3 ረታለች።
ስዊዘርላንድ በሩብ ፍፃሜው አርጀንቲናን የምትገጥም ይሆናል።
ፈረንሳይ ከ ሞሮኮ፣ ስፔን ከ ቤልጂየም እንዲሁም ኖርዌይ ከ እንግሊዝ ሌሎቹ የሩብ ፍፃሜ መርኃ ግብሮች ናቸው።
#worldcup #fifaworldcup #switzerland #colombia #quarterfinal #football #sports

Sponsored by
Surafel
3 months ago
አሜሪካ በቤልጂየም ተሸንፋ ከዓለም ዋንጫው ተሰናበተች
********************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ ከውድድሩ አዘጋጅ ሀገራት አንዷ የሆነችው አሜሪካ፤ በቤልጂየም 4 ለ 1 ተሸንፋ ከዓለም ዋንጫው ውጪ ሆናለች።
ቻርለስ ኬቴለር(ሁለት) እንዲሁም ሀንስ ቫናከን እና ሮሜሉ ሉካኩ የቤልጂየምን ማሸነፊያ ግቦች ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።
የአሜሪካን ብቸኛ ግብ ማሊክ ቲልማን ከመረብ አሳርፏል።
ቤልጂየም በሩብ ፍፃሜው የስፔን ብሔራዊ ቡድንን የምትገጥም ይሆናል።
#worldcup #fifaworldcup #usa #belgium #knockoutstage #football #sports

50"
ስፔንና ፖርቹጋል ያለ ግብ ወደ ሁለተኛው አጋማሽ ተሸጋገሩ
#ethiopia | በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የ16 ዙር ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ስፔን እና ፖርቹጋል እያደረጉት ያለው ፍልሚያ የመጀመሪያ አጋማሹ 0–0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
ሁለቱም ቡድኖች በጥንቃቄ ጨዋታቸውን ሲያካሂዱ ቢታዩም፣ ግብ ለማስቆጠር የተፈጠሩ እድሎችን ወደ መረብ መቀየር አልቻሉም። በመሆኑም ተጠባቂው ፍልሚያ ያለ ግብ ወደ ሁለተኛው አጋማሽ ተሸጋግሯል።
የዚህ ጨዋታ አሸናፊ ወደ ሩብ ፍጻሜ የሚያልፍ ሲሆን፣ ቀጣዩ 45 ደቂቃዎች የጨዋታውን ውጤት የሚወስኑ ይሆናሉ።
#fifaworldcup #spain #portugal #worldcup2026 #football #sports

ስፔን 0 - 0 ፖርቹጋል፦ የመጀመሪያ አጋማሽ ውጤት
****************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ የ16ቱ ሀገራት ጥሎ ማለፍ ስፔን ከፖርቹጋል እያደረጉት ያለው ጨዋታ፤ የመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ግብ ተጠናቋል።
#worldcup #fifaworldcup #portugal #spain #knockoutstage #football #sports

ብራዚል ከ23ኛው ዓለም ዋንጫ ተሰናበተች
**************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ የ16ቱ ሀገራት ጥሎ ማለፍ መርኃ ግብር ብራዚል በኖርዌይ 2 ለ 1 ተሸንፋ ከዓለም ዋንጫው ተሰናብታለች። ኖርዌይም በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሩብ ፍፃሜ አልፋለች።
የኖርዌይን የማሸነፊያ ግቦች 79ኛው እና 90ኛው ደቂቃ ላይ ኧርሊንግ ሀላንድ ከመረብ አሳርፏል። ለብራዚል ኔይማር ጁኒየር በፍፁም ቅጣት ምት 90+10 ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።
በጨዋታው በብራዚል በኩል ብሩኖ ጉማሬሽ 14ኛው ደቂቃ ላይ ያገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
ኖርዌይ በሩብ ፍፃሜው የሜክሲኮ እና እንግሊዝን አሸናፊ የምትገጥም ይሆናል።
በእድሪስ አሕመድ
#worldcup #fifaworldcup #brazil #norway #knockoutstage #football #sports

ብራዚል 0 - 0 ኖርዌይ :- የመጀመሪያ አጋማሽ ውጤት
***************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ በብራዚል እና በኖርዌይ መካከል እየተደረገ ያለው ጨዋታ የመጀመሪያው 45 ደቂቃ ያለ ምንም ግብ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።

ኮሎምቢያ ጋናን በማሸነፍ ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ ተሸጋገረች
**************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ የ32ቱ ሀገራት ጥሎ ማለፍ ኮሎምቢያ ከ ጋና ያደረጉት ጨዋታ፤ በኮሎምቢያ 1 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ለኮሎምቢያ የማሸነፊያዋን ብቸኛ ግብ ጆን አሪያስ በ14ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።
ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ የተሸጋገረችው ኮሎምቢያ በቀጣይ ጨዋታዋ ከስዊዘርላንድ ጋር ትጫወታለች።
#worldcup #fifaworldcup #colombia #ghana #football #sports #ebc

አርጀንቲና ኬፕቨርዴን በማሸነፍ ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ ተሸጋገረች
*********
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ የ32 ሀገራት ጥሎ ማለፍ መርኃ ግብር አፍሪካዊቷን ደሴት ኬፕቨርዴን የገጠመችው አርጀንቲና 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ቀጣዩን የ16 ሀገራት ጥሎ ማለፍ ዙር ተቀላቅላለች።
ሊዮኔል ሜሲ ለአርጀንቲና ዳንኤል ዱዋርቴ ደግሞ ለኬፕቨርዴ 1 አቻ በተጠናቀቀው መደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ግቦቹን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።
አሸናፊውን ለመለየት በተጨመሩት 90 ደቂቃዎች፤ የአርጀንቲናን የማሸነፊያ ግቦች ያስቆጠሩት ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ እና ዲኔይ ቦርገስ(በራሱ መረብ ላይ) ሲሆን የኬፕ ቨሮዴን ግብ ሲድኒ ካብራል ከመረብ አሳርፏል።
ሻምፒዮኗ አርጀንቲና በቀጣዩ የጥሎ ማለፍ መርኃ ግብር ግብፅን የምትገጥም ይሆናል።
#worldcup #fifaworldcup #argentina #caboverde #lionelmessi #football #sports

ግብፅ አውስትራሊያን በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቀለች
**********************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ ግብፅ አውስትራሊያን በመርታት የ16ቱ ጥሎ ማለፍ ጉዞዋን አሳክታለች።
በጨዋታው ኢማም አሹር በ13ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ግብፅን መሪ ብታደርግም፣ በ55ኛው ደቂቃ ሞሀመድ ሀኒ በራሱ መረብ ላይ ባስቆጠራት ግብ አውስትራሊያ አቻ ሆና ነበር።
የጨዋታው መደበኛ ክፍለ ጊዜና ጭማሪው 30 ደቂቃ 1 ለ 1 ተጠናቆ ግብፅ በመለያ ምት 4 ለ 2 አሸንፋለች።
ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ የተሸጋገረችው ግብፅ በቀጣይ ጨዋታዋ ከአርጀንቲና እና ኬፕ ቨርዴ አሸናፊ ጋር ትጫወታለች።
#worldcup #fifaworldcup #switzerland #algeria #embolo #football #sports #ebc

ፖርቹጋል ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ ተሸጋገረች
*************************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ የ32ቱ ሀገራት ጥሎ ማለፍ ፖርቹጋል ከ ክሮሺያ ያደረጉት ጨዋታ፣ በፖርቹጋል 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል።
ለፖርቹጋል የማሸነፊያዎቹን ግቦች ክሪስቲያኖ ሮናልዶ (በፍፁም ቅጣት ምት) እንዲሁም ጎንካሎ ራሞስ አስቆጥረዋል።
ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በ6 የዓለም ዋንጫ ተሳትፎው 11ኛ ግቡን ነው ያስቆጠረው።
ለክሮሺያ ብቸኛዋን ግብ ኢቫን ፔሪሲች ከመረብ አሳርፏል።
ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ የተሸጋገረችው ፖርቹጋል በቀጣይ ጨዋታዋ ከስፔን ጋር ትጫወታለች።
#worldcup #fifaworldcup #portugal #croatia #cr7 #football #sports

ካናዳ ደቡብ አፍሪካን 1 ለ 0 በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቀለች
**********************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ በጥሎ ማለፍ ደቡብ አፍሪካ ከካናዳ ያደረጉት ጨዋታ በካናዳ 1 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ጨዋታው እስከ መደበኛው 90 ደቂቃ ያለ ምንም ግብ 0 ለ 0 ቀጥሎ የነበረ ቢሆንም፣ ስቴፈን ኢውስታኪዮ በጭማሪ ደቂቃ 90+2 ላይ ባስቆጠራት ግብ ካናዳን አሸናፊ ማድረግ ችሏል።
ውጤቱን ተከትሎ ካናዳ ደቡብ አፍሪካን ከውድድሩ በማሰናበት 16ቱን መቀላቀሏን አረጋግጣለች።
#worldcup #fifaworldcup #canada #southafrica #football #sports #ebc

#fifaworldcup | ኬፕ ቨርዴ በምድብ H የመጨረሻ ጨዋታዋ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር 0-0 አቻ በመለያየት፣ በ3 ነጥብ ወደ 16 ቡድኖች ጥሎ ማለፍ መብቷን አረጋግጣለች።
በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ዋንጫ የተሳተፈችው ምዕራባዊቷ የአፍሪካ ደሴት ሀገር ኬፕ ቨርዴ፣ ሦስቱንም የምድብ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት በማጠናቀቅ ታሪካዊ ስኬት አስመዝግባለች።
በሌላው የምድብ H ጨዋታ ስፔን ኡራጓይን 1-0 በማሸነፍ በ7 ነጥብ የምድቡን መሪነት ይዛ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች። የስፔንን ብቸኛ የድል ግብ አሌክስ ባዬና አስቆጥሯል።
በዚህ ውጤት መሠረት ስፔን እና ኬፕ ቨርዴ ወደ 16 ቡድኖች ጥሎ ማለፍ ሲቀላቀሉ፣ ኡራጓይ እና ሳዑዲ አረቢያ ከውድድሩ ተሰናብተዋል።
3 months ago
#fifaworldcup | ፈረንሳይ በ2026 የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ኖርዌይን 4-1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ብቃቷን በድጋሚ አረጋግጣለች።
በጨዋታው ፈረንሳይ ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ የበላይነቷን በማሳየት አስደናቂ የጥቃት እግር ኳስ አሳይታለች።
በተለይም ኦስማን ዴምቤሌ እና ኪሊያን ምባፔ በጥሩ ብቃታቸው የቡድኑን ድል ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።
ይህ ድል ፈረንሳይን በምድብ 1 ከጠንካራ ተፎካካሪዎቿ መካከል የበለጠ አጠናክሮ ወደ ጥሎ ማለፉ ሲያቃርባት፣ ቡድኑም ለዋንጫው ከዋና ተፎካካሪዎች አንዱ መሆኑን በድጋሚ አሳይቷል።
3 months ago
እንግሊዝ እና ጋና ያለ ግብ ተለያዩ
#ethiopia | በ2026 የዓለም ዋንጫ የምድብ 12 ሁለተኛ ጨዋታ፣ እንግሊዝ እና ጋና በቦስተን ስታዲየም ያደረጉት ፉክክር 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸውን በድል የጀመሩት ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በዚህ ጨዋታ ነጥብ በመጋራት ወደ 4 ነጥብ ከፍ ብለዋል።
እንግሊዝ በተለይም በጨዋታው የመጨረሻ ደቂቃዎች ተደጋጋሚ የግብ ሙከራዎችን ብታደርግም፣ የጋናን ጠንካራ መከላከል እና የግብ ጠባቂውን ጥሩ ብቃት ተሻግራ ግብ ማስቆጠር አልቻለችም።
በዚህ ውጤት እንግሊዝ በ4 ነጥብ የምድቡን መሪነት ስትይዝ፣ በካርሎስ ኪሮሽ የምትመራው ጋናም በተመሳሳይ 4 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።
የሁለቱም ቡድኖች ወደ ጥሎ ማለፍ ለማድረስ ያላቸው ዕድል አሁንም ጠንካራ ሲሆን፣ የመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ውጤት የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ እንደሚወስን ይጠበቃል።
#worldcup2026 #england #ghana #threelions #blackstars #football #fifaworldcup

4 months ago
በዓለም ዋንጫ የአፍሪካ አህጉር ተወካዮች የሆኑት ኮትዲቯር እና ቱኒዚያ ዛሬ ወደ ሜዳ ይገባሉ
#ethiopia | በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ውድድር አፍሪካን ወክለው የሚሳተፉት ኮትዲቯር እና ቱኒዚያ ዛሬ ምሽት የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።
በዚህም መሠረት የዝሆኖቹ ሀገር ኮትዲቯር ከደቡብ አሜሪካዋ ጠንካራ ተጋጣሚ ኢኳዶር ጋር ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ ትገናኛለች።
በአውሮፓ ታዋቂ ሊጎች ውስጥ የሚጫወቱ በርካታ ባለክህሎት ተጫዋቾችን የያዘችው ኮትዲቯር ለኢኳዶር ከባድ ፈተና እንደምትሆን በስፋት ተገምቷል።
ሌላኛዋ የአፍሪካ ተወካይ ሰሜን አፍሪካዊቷ ቱኒዚያ በበኩሏ ከጠንካራዋ የአውሮፓ ሀገር ስዊድን ጋር ከሌሊቱ 11 ሰዓት ላይ ፍልሚያዋን ታደርጋለች።
ከእነዚህ ጨዋታዎች አስቀድሞ ምሽት ሁለት ሰዓት ላይ በዓለም እግር ኳስ ግዙፍ ስም ያላት ጀርመን ከካራካኦ ጋር የምታደርገው ጨዋታ በብዙዎች ዘንድ ይጠበቃል።
በተጨማሪም ኔዘርላንድ ከእስያዋ ተስፈኛ ሀገር ጃፓን ጋር የምታደርገው ጨዋታ የዛሬው ምሽት ሌላኛው አጓጊ መርሃ ግብር ነው።
ትናንት ምሽት በተከናወኑ ጨዋታዎች አውስትራሊያ ቱርኪዬን ሁለት ለባዶ ያሸነፈች ሲሆን ስኮትላንድ በበኩሏ ሃይቲን አንድ ለባዶ በሆነ ጠባብ ውጤት ማሸነፍ ችላለች።
በሌላ በኩል በአፍሪካ ኩራት የሆነችው ሞሮኮ ከዓለም እግር ኳስ ኃያሏ ብራዚል ጋር እንዲሁም ኳታር ከስዊዘርላንድ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ በተመሳሳይ አንድ ለአንድ በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።
#worldcup2026 #africanfootball #cotedivoire #tunisia #fifaworldcup #footballnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የዓለም ዋንጫ : በኮካ ኮላ
#ethiopia | የዓለም ዋንጫ መክፈቻን አስመልክቶ የኮካ ኮላ ኩባንያ ያዘጋጀው ደማቅ የምሽት መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል እየተካሄደ ነው
የኮካ ኮላ ኩባንያ ከፊፋ የዓለም ዋንጫ ጋር የዘለቀውን የግማሽ ክፍለ ዘመን ታሪካዊ አጋርነት ለመዘከርና የዘንድሮውን 23ኛውን ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ውድድር መጀመር ለማብሰር ያዘጋጀው ልዩ የክብር ምሽት በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ይህ ታላቅ መርሃ ግብር በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የስፖርት አፍቃሪዎች የውድድሩን መክፈቻ ስነ ስርዓትና የመጀመሪያ ጨዋታ ለመታደም በአንድነት ከሚሰበሰቡበት ታሪካዊ ቅጽበት ጋር ተስማሚ በሆነ መልኩ እየተከናወነ ነው።
በዚህ ማራኪ ድባብ ባለው መድረክ ላይ በርካታ ታዋቂ ሰዎች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ የስፖርት ቤተሰቦችና ጋዜጠኞች ተገኝተው ምሽቱን በልዩ የሙዚቃ ዝግጅቶች፣ የፈጠራ ስራዎችና የተለያዩ መዝናኛዎች እያደመቁት ይገኛሉ።
በመርሐግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮካ ኮላ ሲኒየር ማርኬቲንግ ማናጀር ሜሮን ብርሃኑ እግር ኳስ ከስፖርትነቱ ባለፈ ሰዎችን በጋራ ስሜትና ፍቅር የሚያስተሳስር ሁለንተናዊ ቋንቋ መሆኑን ገልጸዋል።
የ2026ቱ የፊፋ የዓለም ዋንጫ በታሪክ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሀገራትና ጨዋታዎች የሚስተናገዱበት ግዙፍ ውድድር መሆኑን የጠቆሙት ማናጀሯ፣ ኮካ ኮላ ትርጉም ባላቸው አቀራረቦች የኢትዮጵያን እግር ኳስ አፍቃሪዎች ከውድድሩ ደስታ ጋር ይበልጥ ለማገናኘት ቁርጠኛ መሆኑን አብራርተዋል።
በሌላ በኩል የኮካ ኮላ ቢቨሬጅስ አፍሪካ ተወካይ በበኩላቸው ኩባንያው በኢትዮጵያ ስላለው ጠንካራ ተሳትፎና ምርት ስርጭት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ አምስት ፋብሪካዎች እንደሚንቀሳቀሱና ከእነዚህም ውስጥ በአዲስ አበባ፣ ሰበታ፣ ባሕር ዳር እንዲሁም በድሬዳዋ የሚገኙት አራቱ ፋብሪካዎች የኮካ ኮላ ምርቶችን በሙሉ አቅማቸው እያመረቱ ለገበያ እያቀረቡ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
ከማሸጊያ ጋር በተያያዘም ለተለያዩ የደንበኞች ፍላጎት ተስማሚ የሆኑ ከ300 ሚሊ ሊትር ተመላሽ የብርጭቆ ጠርሙስ ጀምሮ ለጉዞ የሚመቹ የ350 እና የ500 ሚሊ ሊትር እንዲሁም ለቤተሰብና ለስብሰባዎች የሚሆኑ የ1.5 ሊትር የፒኢቲ ማሸጊያዎችን እያቀረቡ መሆኑን አስረድተዋል።
የዓለም ዋንጫውን ታላቅ ስሜትና የኮካ ኮላን ደማቅ ድባብ በቀጥታ ወደ እናንተ ማድረሳችንን እንቀጥላለን።
ውጤት
60" ሜክሲኮ 1 - 0 ደቡብ አፍሪካ
#worldcup #cocacola #football #skylighthotel #fifaworldcup #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የዓለም ዋንጫ መክፈቻ በስካይ ላይት ሆቴል! ⚽️
ኮካ ኮላ የ23ኛውን የፊፋ የዓለም ዋንጫ ድባብ በአዲስ አበባ አደምቆታል። የእግር ኳስ ቤተሰቦች በአንድ ላይ ሆነው ታሪካዊውን የመክፈቻ ፕሮግራም እየታደሙ ነው! 🏆🔥
#worldcup #cocacola #ethiopia #addisababa #fifaworldcup

ዶናልድ ትራምፕ በፊፋ የዓለም ዋንጫ የትኬት ዋጋ መናር ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት አነጋጋሪ ምላሽ
ጋዜጠኛ፦
ክቡር ፕሬዝዳንት፣ አንዳንድ የውጭ ሀገር ደጋፊዎች በስታዲየሞች አካባቢ ባለው ከፍተኛ የትኬት እና የትራንስፖርት ክፍያ ላይ ቅሬታ እያሰሙ ይገኛሉ። ይህ ሁኔታ በዓለም ዋንጫው ላይ የሚታደመውን የህዝብ ቁጥር አይቀንሰውም ይላሉ?
ትራምፕ፦
አሜሪካ የነፃ እርዳታ ማዕከል አይደለችም። እኛ ለዓለም እያቀረብን ያለነው ምርጡን ትዕይንት በመሆኑ፣ ዋጋው የጥራቱ መገለጫ ነው። የትኬቶቹ መወደድ የእኛን ስኬታማነት ነው የሚያሳየው። አቅሙና ፍላጎቱ ያላቸው ደጋፊዎች ከፍለው ስታዲየም ገብተው ይመለከታሉ፤ የቀሩት ደግሞ ውድድሩን ከቤታቸው ወይም ከካፌዎች መከታተል ይችላሉ።
#ethiopia #donaldtrump #fifaworldcup #worldcup2026 #sportsnews #trump #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

8 months ago
ሜክሲኮ ለ2026ቱ የዓለም ዋንጫ "ሮቦት ውሾችን" በፀጥታ ጥበቃ ልታሰማራ ነው
#ethiopia | በቀጣዩ የ2026 የዓለም ዋንጫ አስተናጋጅ ከሆኑት አገራት አንዷ የሆነችው ሜክሲኮ፣ የውድድሩን የፀጥታ ሁኔታ ይበልጥ ለማጠናከር በቴክኖሎጂ የታገዙ "ሮቦት ውሾችን" ልታሰማራ መሆኑን አስታውቃለች።
እነዚህ አራት እግሮች ያሏቸው የሮቦት እንሰሳት፣ በተለይም የፖሊስ አባላት ወደማይደርሱባቸው ወይም አደገኛ ወደሆኑ አካባቢዎች ቀድመው በመግባት የቪዲዮ መረጃዎችን በቀጥታ ለቁጥጥር ማዕከሉ እንዲልኩ ተደርገው የተሰሩ ናቸው።
የሮቦት ውሾቹ ዋና ዋና ባህሪያት፦
* ሁለገብ እንቅስቃሴ፦ ባልተስተካከሉ መሬቶች እና አስቸጋሪ በሆኑ ስፍራዎች ላይ በቀላሉ የመንቀሳቀስ ብቃት አላቸው።
* ዘመናዊ ካሜራዎች፦ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ካሜራዎች የተገጠሙላቸው ሲሆን፣ የፀጥታ አካላት ስጋቶችን በሩቅ ሆነው እንዲቃኙ ይረዳሉ።
* ጥንካሬ፦ በማንኛውም የአየር ንብረትና መልክዓ ምድር ውስጥ ለመስራት የሚያስችል ጠንካራ ቁሳቁስ ተገጥሞላቸዋል።
ሜክሲኮ ይህንን ቴክኖሎጂ የምትጠቀመው የሰው ኃይል ሊገጥመው የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ እና ለዓለም ዋንጫው የሚመጡ እንግዶችን ደህንነት በላቀ ሁኔታ ለመጠበቅ እንደሆነ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ገልጸዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #mexico2026 #worldcup2026 #robotdogs #techsecurity #fifaworldcup #mexicosafety #innovation #አለምዋንጫ #ሜክ .ሲኮ #ቴክኖሎጂ

Comments