በእግራቸው የሚጓዙ ሰወች ግን ወዴት ጠፉ?
አሜሪካ ታላቅ ሀገር ናት። ሰላም፣ እድል፣ ነፃነት፣ መብት እና የተሻለ የኑሮ ሁኔታ ትሰጣለች። ግን በዚህ ሁሉ ምቾት መካከል ብዙ ሰዎች የሚሰማቸው አንድ ረሀብ አለ፤ የሰው ረሀብ፣ የወዳጅነት ረሀብ፣ የማህበራዊ ኑሮ ረሀብ።
ቴክኖሎጂ ከዓለም ጋር አገናኘን፣ ግን አንዳንዴ ከጎናችን ካለው ሰው አራቀን። መኪናዎች ፈጣን አደረጉን፣ ግን መንገዱን ከእግረኛ አራቁት። ሥራና ፕሮግራም ውጤታማ አደረጉን፣ ግን ሰው ከሰው ጋር የሚቀመጥበትን ጊዜ አሳነሱት።
ሰው ለሰው መድኃኒት ነው። ምናልባት ዛሬ የሚያስፈልገን ትልቅ ነገር አይደለም፤በእግር መውጣት፣ ጎረቤትን ሰላም ማለት፣ ከወዳጅ ጋር ቡና መጠጣት፣ እና እንደገና ሰውን መፈለግ ብቻ ነው።
በእግር የሚጓዝ ሰው ግን ወዴት ገባ ትላላችሁ ?
አንዳንዴ ራሴን እንዲህ እያልኩ እጠይቃለሁ -ሰዎቹ ሁሉ የት ሄዱ? እግረኞቹ የት ገቡ? ወዳጆቻችንስ ምን ዋጣቸው? ጎረቤቶቻችን የታሉ? እላለሁ።
በዚህች በአሜሪካ እኔ በምኖርበት በሚኔሶታ ሁሉም መኪና አለው ብል ማጋነን አይመስለኝም። ሰዎች ወደ ስራ፣ ወደ ሱቅ፣ ወደ ቀጠሮ ቦታ በመኪናቸው ሄደው በመኪናቸው ይመለሳሉ ። በዚህ ምክንያት ይመስለኛል አንዳንድ ሰፈር አንድም እግረኛ አላይም ። ይገርማችኋል አንዳንዴ ሙሉ ሰፈሩን ዞራችሁ ብታዩ አንድ የግር ተጓዥ ላታገኙ ትችላላችሁ ። አንዳንዴ የእግረኛ መሄጃና የመንገድ ዳርቻዎች ጭር ከማለታቸው የተነሣ የተወረረ ከተማ ነው የሚመስሉት።
ህይወት ታሯሩጣለች እና ሁሉም ሰው የሆነ የሚያደርገው ነገር ያለው ይመስላል። በዚህ ምክንያት ከሰዎች ጋር የመገናኘት እድሉ በጣም የጠበበ ነው። እየተጓዝኩ የሆነ የማቀው ሰው ይመጣብኛል ወይም የማዋራው የማላቀውም ሰውም ቢሆን አገኛለሁ ብሎ ማሰብ ከባድ ነው። አብዛኛው ሰው ስራ ላይ ነው፣ ሌላው በተሽከርካሪ እየተጓዘ ነው ወይም ደግሞ በሌሎች ጉዳዮች ተይዟል። ባጠቃላይ በግር የሚጎዝ ሰው ብዙ አይታይም ።
ሰው ለማግኘት የምንችልባቸው ጥቂት ቦታዎች እንደ ግሮሰሪ፣ ምግብ ቤት፣ ካፌ እና መጠጥ ቤት ናቸው። ለአብዛኛው ሰው በተከታታይ ለመሰብሰብና ለመገናኘት የሚያስችለው ሌለኛው ቦታ ደግሞ የእምነት ቦታወች ናቸው። በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ቀን።
በብዙ የአፍሪካ ሀገራት ሁኔታው ከዚህ በእጅጉ የተለየ ነው። መንገዶቹ በሰዎች የተሞሉ ናቸው። ሰው ከመኪና ጋር እየተጋፋ ነው የሚሄደው ። ሰዎች ይበዛሉ፣ ከሚያቁትም ከማያቁትም ጋር ቀኑን ሙሉ ያወራሉ፣ ሁሌም የሚታይ ብዙ ህዝብ አለ። ስለዚህ በሰዎች ተከበው ስለሚውሉ ብቻቸውን ሆነው እንኳ ብቸኝነት አይሰማቸውም። ሁሌም ከሰዎች ጋር በመሆናቸው ምክንያት ኑሮ ቢከብድም የዚህ ማህበረሰብ አካል እንደሆኑ ይሰማቸዋል ።
ወደዚህኛው አሜሪካ ስመልሳችሁ ደግሞ የታዘብኩት ነገር በብዙ ቤተሰቦች ውስጥ የሆነ የተቀየረ ነገር አለ። የአንድ ቤተሰብ አባላት አንድ ክፍል ውስጥ ሆነው ላይነጋገሩ ይችላሉ። አዲሱ ትውልድ ጎኑ ካለው ሰው ይልቅ ከኮምፒውተሩ ፣ ከታብሌቱ ፣ ፌስቡክ ኢንስታግራም ቲክታክ ወይም ከእጅ ስልኩ ጋር መጫወትን ይመርጣል።
የዚህ አደጋው በጊዜ ሂደት ይህ ጤናማ ያልሆነ ባሕርይ ይለመድና የህይወት ዘዬ ይሆናል። ብቸኝነት ራሱ የተለመደ ነገር ይሆናል። ብዙ ሰዎች የተመጠነ ማህበራዊ ግንኙነት ይለምዱና ሰዎችን መፈለግ ያቆማሉ። ከሰው ጋር ያላቸውን መስተጋብር በቀነሱ ቁጥር ይበልጥ ምቾት እየተሰማቸው ይመጣል።
እኔ ሳየው ገለልተኛና ብቸኝነት የተሞላበት ህይወትን ለራሳችን እያለማመድን ይመስለኛል።
ቴክኖሎጂ በአንድ ጎኑ ከአለም ጋር ያገናኘን ቢሆንም በሌላ በኩል ደግሞ ጎናችን ካሉ ሰዎች ጋር እያለያየን መሆኑ ሀቅ ነው።አንድ ከአለም ጫፍ ካለ ሰው ጋር በሰከንድ ጊዜ ልንገናኝ ልናወጋ እንችላለን። ነገር ግር አንዳንዴ ጎረቤታችን የሚኖረው ሰው እንኳ ማን እንደሆነ አናውቅም።
አሜሪካ ታላቅ ሀገር ነች። ለሰዎች ሰላምን፣ እድልን፣ ነፃነትን፣ የመብት መከበርን እና የተሻለ የኑሮ ሁኔታን ታጎናፅፋለች። ይሁንና ግን በዚህ ሁሉ ምቾት መሀከል ሰዎች ሊያስታግሱት ያልቻሉት አንድ ረሀብ አለ። እሱም የሰው ረሀብ፣ የማህበራዊ ኑሮ ርሀብ።
ዲጂታል ቴክኖሎጂ በቀላሉ ያገናኘናል፤ ተሽከርካሪዎች ፍፁማዊ በሆነ መንገድ ወዲያ ወዲህ ያመላልሱናል። የተወጠሩ የስራ ግዜዎቻችን ውጤታማ ያረጉን ይሆናል፤ ሆኖም ግን ብዙ ሰዎች ከሰው ጋር መነጋገር ፣ቀለል ያለ የሻይ ቡና ላይ ወሬ፣ አሊያም የሆነ ማህበረሰብ አካል መሆን ያምራቸዋል ።
እውነት እንነጋገር ካልን አንዱ የዚህ የዘመናዊነት ኑሮ ተግዳሮት ከእርስ በርሳችን ይልቅ ከማሽንና ከግል የስራ ፕሮግራሞቻችን ጋር በአስከፊ ሁኔታ መጣመራችን ነው። ሰው ለሰው መድሀኒቱ አለ ያገሬ ሰው።
— ዶ/ር ሲራክ ኃይሉ
ከሚኔሶታ
የካይሮፕራክቲክ ሀኪም

3 days ago