እባካችሁ በኦቲዝም ስም አትነግዱ!
"ከወላጆች አይን እንባ በዝታለች፣ እግዚአብሄርም ያያል !"
( መላኩ ብርሃኑ)
ኢትዮጵያ ውስጥ ኦቲዝም "እጅግ በጣም ውድ" ችግር ነው፡፡ ከኦቲዝም ጋር በተያያዘ የወላጅን ሸክም ለማቅለል የተዘረጋ ምንም አይነት ስርዓት ስለሌለ ኦቲዝም ወደአንድ ቤት ሲመጣ የዚያ ቤት ህይወት ከመሰረቱ ይናጋል።
ልጆቹ የሙሉ ጊዜ ጥበቃ ስለሚያስፈልጋቸው ወላጅ እየሰራ ከሆነ ስራውን፣ እየተማረ ከሆነም ትምህርቱን ለመተው ይገደዳል። ይህ ደግሞ ለኦኮኖሚ ጫና፣ ለስነልቡና ቀውስ፣ ለማህበራዊ ግንኙነት መዳከምና አልፎ ተርፎም ለከባድ የጤና ቀውስ ይዳርጋል።
እስኪ አስቡት !
ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ልጅ ኦቲዝም እንዳለበት ለመመርመር (Diagnose) ለማድረግ የላብሯቶሪ ወጪውን ሳይጨምር ለህክምና ባለሙያው ብቻ የሚከፈል እስከ 20 ሺህ ብርና ከዚያ በላይ ይደርሳል።
እስከ 25 ሺህ ብር የሚደርስ የሃገር ውስጥ ምርመራን እንተወውና እንደ yeast overgrowth, heavy metal test, OAT test, FRAT test ውጪ ልኮ ለማሰራት ከ100 -200 ሺህ ብር በላይ ይጠየቃል።
ኦቲዝም ያላቸው ልጆች ብዙውን ጊዜ ከአንጀታቸው ጋር የተያያዘ የጤና ችግር አለባቸው ተብሎ ስለሚታመን 'ግሉቲን እና ኬዚን' የሚባሉ ንጥረነገሮች ካሏቸው ምግቦች ነጻ መሆን አለባቸው። እኛ ሃገር ደግሞ “ግሉቲን ፍሪ፣ ኬዚን ፍሪ” የሚባሉት የምግብ አይነቶች በአቅርቦት ደረጃ ውስንና በጣም ውድ ናቸው።ከሰንዴ ዘርና ከወተት መራቅ አለባቸው።
ለነሱ የሚሆን ወተት ለመስራት የሚጠቅም አንድ ኪሎ 'አልመንድ' የሚባል ፍሬ በትንሹ እስከ 5 ሺህ ብር ያስወጣል። ምግባቸው ውድ በሆነው የንጹህ የወይራ ዘይት ካልሆነ በቀር በሌላ መሰራት አይችልም። ስኳርና ሰውሰራሽ ማጣፈጫ ስለማይጠቀሙ በምትኩ ቴምር ለመግዛት በኪሎ ከ1500-3500 ብር ድረስ ይጠይቃል።
በዚህ ሳቢያ ልጆቹ የሚወስዱት ምግብ አይነት ስለሚያንስ እንዳይጎዱ ሲባል 'ሰፕሊመንት' ያስፈልጋቸዋል። ለምሳሌ ለነሱ የሚሆን የአሳ ዘይት ዋጋው ከ 12 ሺህ እስከ 35ሺህ ብር ይሸጣል። ለጥቂት ቀን ብቻ የሚሆን ቫይታሚን ዲ ደግሞ እስከ 5 ሺህ ብር ይሸጣል። አቅም ላለው ወላጅ እንኳን ሌሎች ሌሎች ተጨምረው የሰፕሊመንት ዋጋ ብቻ በወር ከ50 ሺህ ብር በላይ ያስወጣዋል።
በአጠቃላይ ለአንድ ኦቲዝም ላለበት ልጅ የሚወጣው የአንድ ወር የምግብ ወጪ አንድ ቤት ውስጥ ለሙሉ ቤተሰብ ከሚወጣው የቀለብ ወጪ ይበልጣል።
ኦቲዝም በሽታ ስላልሆነ መድሃኒት የለውም፡፡ ለኦቲዝም የሚደረገው ድጋፍ በአብዛኛው የንግግር፣ የባህሪና የአካልና ሰውነት ቅንጅት ቴራፒ ነው፡፡ እዚህ ጋር ደግሞ ነጋዴዎቹ ተሰብስበዋል።
የሚችሉትም የማይችሉትም የሆነች ዛኒጋባ ተከራይተው እንሰጣለን ለሚሉት ተራፒ የሚያስከፍሉት ዋጋ በጣም ውድ ነው። ለአንድ ልጅ በወር 30 ሰዓት ቴራፒ ለመስጠት የሚከፈለው ገንዘብ የአንድ ልጅን የ6 ወር የግል ትምህርት ቤት ክፍያ ይበልጣል።
በቁጥር ጥቂት የሆኑት 'የልዩ ፍላጎት አካቶ' ያላቸው ትምህርት ቤቶች ክፍያ ዋጋ ደግሞ አይወራ። ታዋቂ ነን የሚሉት አንዳንዶቹ ትምህርት ቤቶች በወር እስከ 100 ሺህ ብር ያስከፍላሉ። በጨበጣ ያለምንም እውቀት ኦቲዝምን ቢዝነስ ያደረጉ አንዳንድ ነጋዴ ግለሰቦች የከፈቱት ትምህርት ቤት ደሞ አለ። አዳሪ ብለው እስከ 300ሺህ ብር በወር ያስከፍላሉ።
ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤቶች እንኳን የማያስከፍሉትን አይነት ገንዘብ የሚያስከፍሉ አካቶ ት/ቤቶችና በኦቲዝም ስም የተቋቋሙ ተቋማት በጣም ብዙ ናቸው፡፡
በዚህ ላይ ልጁ ትምህርት ቤት ሲሄድም ሆነ ሲመለስ ሰርቪስ የሚጠቀም ከሆነ ወላጆች ለመጓጓዣው ከመደበኞቹ ህጻናት በእጥፍ እንዲከፍሉ ይደረጋሉ፡፡
ይህን ይህን ሳይ በሃገሬ ተስፋ እቆርጣለሁ። ስርዓት ያልተዘረጋለት፣ ደንብና ህግ ያልወጣለት፣ በሙስና ሰንሰለት የተጨማለቀ ፣ ከኤንጂኦ እስከ ግለሰቦች ድረስ በኦቲዝም ስም የጦፈ ንግድ ሲካሄድ ሃይ ባይ የታጣበት ሃገር ላይ ነን ያለነው።
እንደኔ ጠለቅ ብሎ ለሚያየው እዚህ ዘርፍ ላይ ያለው መጨመላለቅና ብዝበዛ በጣም ይሰቀጥጣል፡፡
መቼም በጥቂቱ ካነሳሁት እውነት አንጻር በዚህ ዘመን የኑሮ ውድነት አንድ ወላጅ ቤት ኦቲዝም ሲደረብበት በስነልቡናም፣ በገንዘብም ምን ያህል ከባድ የህይወት መርግ እንደሚፈጥር ካሰባችሁት ይበቃል፡፡
እናንት 'ሞራል አልባ' ነጋዴዎች! እንዲህ ባለ 'ውድ' ችግር ላይ አይናችሁን አጥባችሁ ገንዘብ ለማጋበስና መሄጃ አጥቶ የተቸገረውን ወላጅ ለመበዝበዝ እንዴት ህሊናችሁ እሺ አላችሁ ግን? (በርግጥ ህሊና የላችሁም!)
በጣም ነው የሚያሳዝነው፡፡ይህ'ኮ ኢሰብአዊነት ነው። ወንጀል ነው። የሞራል ዝቅጠት ነው። ዛሬ ከኔ ባልተሻለ ጥቂት ንባብ ብቻ ተነስታችሁ ቤት ተከራይታችሁና ማዕከል ከፍታችሁ ‘ባለሙያ ነን’ እያላችሁ 'ቢዝነስ' የምትሰሩ ፣ ቲክቶኩንና ሶሻል ሚዲያውን ያጣበባችሁ ሰዎች ... ምናችሁን ነው የሚያማችሁ? ነገ'ኮ ይህ በህጋዊነት ሽፋን ያለቁጥጥር በተለቀቀ ሜዳ ላይ ስትፋንኑ የበደላችሁት ወላጅ እንባ ቤታችሁ ድረስ ይመጣል።
ኦቲዝም ላይ እንሰራለን ብላችሁ የምትደሰኩሩ ሃኪሞችምም፣ ሳይኮሎጂስቶችም፣ ቴራፒስቶችም፣ አካቶ ትምህርት ቤቶችም፣ማዕከላትም ቆም ብላችሁ ብታስቡ ይበጃችኋል!
ይህ ምርጫ ያጣ… ተመልካች ያጣ፣ ልጄ ቢሻሻልልኝ ብሎ እዚህም እዚያም መፍትሄ ፍለጋ የሚኳትን ወላጅ በኦቲዝም ምክንያት ጥሪቱን አሟጦ ሌሎች ልጆቹን የሚያሳድግበትና ቤቱን የሚመራበት ገንዘብ እስኪያጣ ድረስ ሲቸገር እናንተ አላግባብ በዘረፋችሁት ገንዘብ ሰላም፣ ጤናና የሰላም እንጀራ አይኖራችሁም ።
አያሳዝናችሁም ግን ? በናንተ የዋጋ ውድነትና ሳቢያ አቅም አጥቶ ዕድሜውን ሙሉ ‘ለልጄ ይህንን ሳላደርግለት’ ብሎ በጸጸት እንባ የሚታጠብ ወላጅ ግን አያሳዝናችሁም?
በዚህ ወላጅ ላይ ህይወት ላይ እየተጫወታችሁ እስከመቼ ራሳችሁን ታበለጽጋላችሁ ?
አንድ ቀን ግን ይመጣል! አላግባብ ለምትሰበስቡት ትርፍ አንድ ቀን እግዚአብሄር ይፈርድባችኋል ! የወላጅ እንባ በቤታችሁና በልጆቻችሁ ላይ ይመጣል። ያኔ እናንተም ቁጭ ብላችሁ ታለቅሳላችሁ !
(ማሳሰቢያ ፤ ይህ ጽሁፍ በሃቅ የሚሰሩ፣ ልጆቹንና ወላጆችን ለመርዳት የሚለፉትን ባለሙያዎች አይመለከትም)
ሜርድ!!

4 months ago