18 days ago
በፈርዖኖቹ ሚዛን፤ ኢትዮጵያ አትመዘንም!
የካይሮ ፖለቲከኞች የለመዱትን የዛቻ እና የለቅሶ ዜማ መልሰው ሲያዜሙት መስማት አዲስ ነገር መሆኑ ቀርቷል።
ሰሞኑን የግብፅ መስኖና ውሃ ሀብት ሚኒስትር የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን “ሕገ-ወጥ” ሲሉ ፈርጀው፣ “ብሔራዊ የውሃ ደህንነታችንን ለመጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ የመውሰድ መብታችን የተጠበቀ ነው” ሲሉ በቁጭትና በትዕቢት መካከል የተሰነቀረ መግለጫ ሰጥተዋል።
ይህ አባባል ግን በበሰለ ዲፕሎማሲያዊ ሚዛን ሲመዘን፣ ሌሊት አልፎ ቀን በፈነጠቀበት ዘመን የሚቃዥ የትላንት ሕልመኛ ሰንካላ ምክንያት እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም።
የፈርዖኖች ምድር ፖለቲከኞች አሁንም ድረስ ዓለም የተቀየረች አይመስላቸውም። በቅኝ ግዛት ዘመን የተጻፉና ኢትዮጵያ ያልፈረመችባቸውን ያረጁ የውሃ ክፍፍል ስምምነቶች እንደ ሕግ እየቆጠሩ፣ “ታሪካዊ መብታችን አልተከበረም” ብሎ መጮህ ራስን ማታለል ነው።
የሕዳሴው ግድብ ግንባታ በአካል ተጠናቅቆ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት በጀመረበትና የካይሮን የዛቻ ‘ማዕበል’ በዲፕሎማሲያዊ እና በሳይንሳዊ እውነታዎች ባፈረሰበት በዚህ ወቅት፣ ግድቡን “ሕገ-ወጥ” ብሎ መጥራት የተጨባጩን ዓለም እውነታ ከመካድ የሚመጣ የፖለቲካ ቅዥት ነው።
የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሠረት የተጣለው በካይሮ ፈቃድ ወይም በፓሪስና ለንደን የቅኝ ግዛት ውሎች አይደለም። ግድቡ በኢትዮጵያውያን የደም፣ የላብ እና የእንባ ጠብታ የተገነባ የሉዓላዊነት ሐውልት ነው።
እያንዳንዱ የኮንክሪት ክምችት፣ እያንዳንዱ የስባሪ ሳንቲም መዋጮ እና የሕዝባችን ቁርጠኝነት ያቆመው እውነት እንጂ በካይሮ ጠረጴዛ ላይ በሚፈረም የይሁንታ ወረቀት የሚጸድቅ የልመና ፕሮጀክት አይደለም።
ኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሀብት ተጠቅማ ሕዝቧን ከጨለማ ለማውጣት የምታደርገው ጥረት በማንም ሀገር ፈቃደኝነት ላይ አይንጠለጠልም።
ግብፅ ለዓመታት በዓባይ ውሃ ላይ ብቻዋን ስትደሰትና ስታባክን፣ ኢትዮጵያ ግን 85 በመቶ የሚሆነውን የውሃ ምንጭ እያመነጨች በጨለማ ስትማቅቅ መኖሯ የታሪክ መዛባት ነበረ። ዛሬ ያ የታሪክ መዛባት በኢትዮጵያውያን ክንድ ታርሟል። ካይሮ ይህንን እውነት “የተጠናቀቀ እውነታ” ብላ ለመቀበል መቸገሯ የራሷ የፖለቲካ ሥነ-ልቦና ቀውስ እንጂ የኢትዮጵያ የቤት ሥራ ሊሆን አይችልም።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም እና ሕልውና በአንድ ወንዝ ፍሰት ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም። ዛሬ የኢትዮጵያ ጂኦፖለቲካዊ ቁመና በዓባይ ወንዝ እና በቀይ ባሕር በሁለቱ ወሳኝ ውሃዎች ላይ የተመሰረተ ነው።
ዓባይ የሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ ትንሳኤ፣ የኢንዱስትሪ ልማት እና የብርሃን ምንጭ ሲሆን፤ ቀይ ባሕር ደግሞ የውጭ ንግድ፣ የቀጣናው ስትራቴጂካዊ ተጽዕኖ እና የሉዓላዊነት ማረጋገጫ ማማ ነው። እነዚህ ሁለት ውሃዎች የኢትዮጵያ የሕልውና ሁለት ገፆች በመሆናቸው አንዱ ለአንደኛው ዋስትና ነው።
ግብፅ በዓባይ ላይ የምታሳየው እምቢተኝነት እና የምሥራቅ አፍሪካን ቀጣና የማመስ ፍላጎት፣ ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ ያላትን ስትራቴጂካዊ የባሕር በር ይዞታ ይበልጥ እንድታጠናክር የሚያስገድዳት እንጂ ወደኋላ የሚያስፈገፍጋት አይደለም።
ካይሮ ፈረሶቿን ጋልባ በኢትዮጵያ ጓሮ ለመቅበዝበዝ የምታደርገው ሙከራ፣ የዚሁ በቀይ ባሕር እና በዓባይ ውሃዎች መካከል የተዘረጋውን የኢትዮጵያን ስትራቴጂካዊ የበላይነት ለመቀነስ የሚደረግ አቅመ-ቢስ መወራጨት ነው።
ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ላይ ያቀረቧቸው ቁጥሮች የራሳቸውን ስግብግብነት የሚያጋልጡ እንጂ ለኢትዮጵያ ወቀሳ ሊሆኑ አይችሉም። እርሳቸው እንዳሉት የግብፅ ዓመታዊ የውሃ ኮታ 55.5 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ግን በየዓመቱ በቢሊየኖች የሚቆጠር የዝናብ ውሃ ታገኛለች ይላሉ። ይህ ትልቅ የፖለቲካ ስላቅ ነው!
ተፈጥሮ የሰጠንን የዝናብ ውሃ እየቆጠሩ፣ እኛ ግን ከምንጩ የሚመነጨውን ወንዝ እንዳንነካ መከልከል ምን ይባላል?
ዝናብ ስለዘነበ ብቻ አንድ ሀገር የተፈጥሮ ወንዟን የመጠቀም መብቷ ይገፈፋልን? ግብፅ በረሃ ላይ ተቀምጣ፣ የዓባይን ውሃ ብቻ ሳይሆን በከርሰ-ምድር ውስጥ ያለውን ግዙፍ የውሃ ክምችት እና የባሕር ውሃ ማጣሪያን መጠቀም እየቻለች፣ የኢትዮጵያን የልማት ሕልም በውሃ ጥማት ሰበብ ለማገት መሞከሯ ፍጹም ስግብግብነት ነው።
ኢትዮጵያ የምትከተለው መርህ ግልጽ ነው፦ ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ የውሃ አጠቃቀም። የታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ላይ ጉልህ ጉዳት ሳታደርስ፣ የራሷን ሕዝብ ከድህነት የመታደግ መብቷን ትጠቀማለች። ካይሮ ግን “የእኔ ብቻ ካልሆነ” በሚል የድሮው የባለቤትነት መንፈስ “ሕጋዊ ስምምነት” እያለች የምታቀርበው ሰነድ የኢትዮጵያን እጅ ለመጠፍነግ የሚደረግ ሴራ ስለሆነ ፍጹም ተቀባይነት የለውም።
የካይሮ ፖለቲከኞች የዛቻ መግለጫዎችን ማውጣት እና ግድቡን “ሕገ-ወጥ” ማለታቸውን ሊቀጥሉ ይችላሉ፤ ምክንያቱም ለውስጥ ፖለቲካቸው ፍጆታና ለሕዝባቸው ማስተገሻ ፕሮፓጋንዳ ያስፈልጋቸዋል። ነገር ግን በምድር ላይ ያለው እውነታ አይቀየርም።
የሕዳሴው ግድብ የኢትዮጵያ የቁርጠኝነት ሐውልት ሆኖ ዓባይን እየገደበ፣ ብርሃን እየፈነጠቀ ይኖራል። ኢትዮጵያ በዓባይ እና በቀይ ባሕር ላይ ያላት ብሔራዊ ጥቅም በማንም ዛቻ አይገታም። የካይሮ ስጋት የሚቀረፈው ወደ እውነት በመመለስ እና ከኢትዮጵያ ጋር በእኩልነት መርህ ላይ በመነጋገር እንጂ፣ ያረጀ የቅኝ ግዛት ሕልምን እያዩ “እርምጃ እወስዳለሁ” በሚል የድሮ ፉከራ አይደለም።
የዓባይ ውሃ በካይሮ ፈቃድ አይፈስም፤ የኢትዮጵያ ልማትም በፈርዖኖች ሚዛን አይመዘንም።
በኃይለኢየሱስ መኮንን

26 days ago
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) እና የአባይ ወንዝ አጠቃቀም፡ ህጋዊ እና ታሪካዊ ትንተና
አጭር ጥናታዊ የህግ ጹሁፍ
አዘጋጅ፦ ፋንታሁን ደለለው
1. መነሻ (Introduction)
የአባይ (ናይል) ወንዝ ለዘመናት በበላይኛው እና በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት መካከል የታሪካዊ፣ ህጋዊ እና ፖለቲካዊ ውዝግቦች መነሻ ሆኖ ቆይቷል። ኢትዮጵያ ከ85% በላይ የሚሆነውን የአባይ ውሃ የምታበረክት ቢሆንም፣ በታሪክ አጋጣሚዎች እና በቅኝ ግዛት ስምምነቶች ምክንያት ሀብቷን እንዳትጠቀም ተፅዕኖ ሲደረግባት ቆይቷል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) መገንባት መጀመር የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት የመጠቀም ሉዓላዊ መብት በተግባር ያረጋገጠ ትልቅ የታሪክ ምዕራፍ ነው። ይህ አጭር ጥናታዊ ጽሁፍ የኢትዮጵያን እና የግብፅን የህግ ክርክሮች፣ አለምአቀፍ ድንጋጌዎችን እና የኢፌድሪ ህገ-መንግስትን መሰረት በማድረግ የተዘጋጀ የህግ ትንተና ነው።
2. የግብፅ እና የሱዳን ስምምነቶች እና የህግ ክርክሮች
ግብፅ እና ሱዳን በአባይ ወንዝ ላይ ያላቸውን የውሃ ድርሻ እና የይገባኛል ጥያቄ የሚመሰርቱት በቅኝ ግዛት ዘመን እና ከዛ በኋላ በተደረጉ የሁለትዮሽ ስምምነቶች ላይ ነው።
ሀ) የ1929 ስምምነት፦ በእንግሊዝ (የምስራቅ አፍሪካ ቅኝ ግዛቶቿን ወክላ) እና በግብፅ መካከል የተደረገ ሲሆን፣ ግብፅ በወንዙ ላይ የቪቶ (የመከልከል) መብት እንዲኖራት እና በላይኛው ተፋሰስ ሀገራት የሚገነቡ ማናቸውም የልማት ስራዎች የግብፅን ፍላጎት እንዳይነኩ የሚደነግግ ነው።
ለ) የ1959 ስምምነት፦ በግብፅ እና በሱዳን መካከል ብቻ የተደረገ የሁለትዮሽ ውል ሲሆን፣ ጠቅላላ የወንዙን የውሃ ፍሰት ሙሉ በሙሉ በመከፋፈል 55.5 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ለግብፅ፣ 18.5 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ደግሞ ለሱዳን የሰጠ ስምምነት ነው። ኢትዮጵያ ከዚህ ውል ሙሉ በሙሉ ተገልላለች።
የህግ ተቀባይነት ድክመት (Res inter alios acta)፦ በአለምአቀፍ የውል ህግ መርህ መሰረት፣ በሁለት ወገኖች መካከል የተደረገ ስምምነት ሶስተኛ ወገንን ሊያስገድድ አይችልም። ኢትዮጵያ በእነዚህ ስምምነቶች ላይ ያልተፈራረመች በመሆኑ እና መብቷን በግልፅ የነፈጉ በመሆናቸው፣ እነዚህ ስምምነቶች በኢትዮጵያ ላይ ምንም አይነት ህጋዊ ተፈጻሚነት የላቸውም።
3. አለምአቀፍ የውሃ ስምምነቶች እና መርሆች
ዘመናዊው አለምአቀፍ የውሃ ህግ በቅኝ ግዛት ዘመን የነበሩ የይገባኛል ጥያቄዎችን ውድቅ በማድረግ ፍትሃዊ አጠቃቀምን ያበረታታል። እ.ኤ.አ የ1997 የተባበሩት መንግስታት የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ኮንቬንሽን (UN Watercourses Convention) ሁለት ዋና ዋና መርሆችን ያስቀምጣል፦
ሀ) ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ አጠቃቀም (Equitable and Reasonable Utilization)፦ እያንዳንዱ ተፋሰስ ሀገር ሌሎችን ሳይጎዳ ከሀብቱ ተጠቃሚ የመሆን መብት አለው። ኢትዮጵያ የህዝቦቿን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ለማሟላት ወንዙን የመጠቀም መብቷ በዚህ መርህ የተደገፈ ነው።
ለ) ጉልህ ጉዳት አለማድረስ (No Significant Harm)፦ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ሀብታቸውን ሲጠቀሙ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ የለባቸውም። የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውሃ ፍሰትን የማይቀንስ (Non-consumptive) የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በመሆኑ በታችኞቹ ሀገራት ላይ ጉልህ ጉዳት አያደርስም።
4. የኢፌድሪ ህገ-መንግስት እና የኢትዮጵያ መብት
የኢፌድሪ ህገ-መንግስት የመንግስትን እና የህዝብን መብትና ግዴታዎች በግልፅ ያስቀምጣል፦
ሀ) አንቀፅ 40(3)፦ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት እና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግስት እና የህዝብ ብቻ መሆኑን ይደነግጋል። ይህም መንግስት የአባይን ወንዝ ለሀገር ልማት የማዋል ሙሉ ሉዓላዊ ስልጣን እንዳለው ያረጋግጣል።
ለ) አንቀፅ 89(1) እና 92(1)፦ መንግስት የሀገሪቱን የተፈጥሮ ሀብቶች በሙሉ በማቀናጀት ዜጎች ህይወታቸው እንዲሻሻል እና ከድህነት እንዲወጡ የማድረግ ህገ-መንግስታዊ ግዴታ አለበት። ታላቁ የህዳሴ ግድብ ይህንን ህገ-መንግስታዊ ግብ ለማሳካት የተገነባ ዋነኛ ብሄራዊ ፕሮጀክት ነው።
5. የናイル ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት (CFA)
የቅኝ ግዛት ስምምነቶችን ሙሉ በሙሉ በመሻር በናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል አዲስ የህግ ማዕቀፍ ለመፍጠር የተዘጋጀው የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት (CFA) በቅርቡ (እ.ኤ.አ 2024) አስፈላጊው የሀገራት ቁጥር ፈርመውት ስላፀደቁት በይፋ ስራ ላይ ውሏል። ይህ ስምምነት የኢትዮጵያን እና የሌሎችን የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ፍትሃዊ የመጠቀም መብት በህግ ያረጋገጠ ትልቅ ድል ነው።
6. ታሪካዊ እና አለምአቀፋዊ ሀገርአቀፍ ድጋፍ
ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ ጠንካራ የውስጥ እና የውጭ ድጋፎችን አግኝታለች፦
• የሀገር ውስጥ አንድነት፦ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በገንዘቡ፣ በእውቀቱና በጉልበቱ ግድቡን በባለቤትነት ደግፏል።
• የአፍሪካ ህብረት አቋም፦ 'ለአፍሪካ ችግሮች የአፍሪካዊ መፍትሄ' በሚለው መርህ መሰረት የአፍሪካ ህብረት የድርድር መድረኩን በመምራት የውጭ ጣልቃገብነትን ተከላክሏል።
• የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት አጋርነት፦ እንደ ኡጋንዳ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ሩዋንዳ ያሉ ሀገራት የኢትዮጵያን ፍትሃዊ የመጠቀም መብት ይደግፋሉ።
7. ማጠቃለያ (Conclusion)
በማጠቃለያው፣ የኢትዮጵያ የአባይን ወንዝ የመጠቀም መብት በተፈጥሮ ህግ፣ በአለምአቀፍ የውሃ ህግጋት (ፍትሃዊ አጠቃቀም) እና በሀገር ውስጥ ህገ-መንግስት የተደገፈ ፅኑ መብት ነው። የቅኝ ግዛት ዘመን የሁለትዮሽ ስምምነቶች ኢትዮጵያን አይገድዱም። የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ እና የCFA ስምምነት ስራ ላይ መዋል የኢትዮጵያን የታሪክ የበላይነት ወደ ህግ የበላይነት ቀይሮታል።
8. ማጣቀሻዎች (References)
1. United Nations Convention on the Law of the Non-Navigational Uses of International Watercourses (1997).
2. Agreement on the Nile River Basin Cooperative Framework (CFA), 2010 (Entered into force in 2024).
3. Declaration of Principles (DoP) on the GERD signed by Ethiopia, Egypt, and Sudan (2015).
4. The Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia (1995), Articles 40, 89, and 92.
አዘጋጅ ፋንታሁን ደለለው , Lawyer , 0929101037
በ word እና PDF በቴሌግራም በአማረኛ እና እንግሊዘኛ ያገኙታል። https://t.me/Fantahunlawye...
email :- delelewfantahun20102010.com
https://www.facebook.com/s...
#ethiopia
#governmentpolicy
#ethiopianculture

ፑቲን የአፍሪካ በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ያላቸው ውክልና እንዲያድግ ጥሪ አቀረቡ
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የጸጥታው ምክር ቤት ውክልናቸውን ያላገኙ የአፍሪካ፣ እስያ እና ላቲን አሜሪካ ሀገራትን በሚያካተት መልኩ እንዲሰፋ ጥሪ አቀረቡ።
ፕሬዚዳንቱ በሕንድ ኒው ዴልሂ በተካሄደው 18ኛው የብሪክስ (BRICS) አባል ሀገራት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ሩሲያ ተመድ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የሚጫወተውን ማዕከላዊ ሚና ለማስጠበቅ እና ለማጠናከር ትልቅ ትኩረት እንደምትሰጥ ገልጸዋል።
የድርጅቱን ውጤታማነት ለማሻሻልም የብሪክስ አባላት በጋራ መስራታቸውን መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ፑቲን ሲናገሩ "የተመድ የጸጥታው ምክር ቤትን ማስፋፋት—በተለይም የእስያ፣ አፍሪካ እና ላቲን አሜሪካ ሀገራትን ውክልና በመጨመር—ለዚህ ግብ መሳካት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል" ብለዋል
ከዚህ በተጨማሪ እንደ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF)፣ የዓለም ባንክ እና የዓለም የንግድ ድርጅት (WTO) ያሉ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ተቋማት ከወቅታዊው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ እውነታዎች ጋር ለመላመድ እየተቸገሩ በመሆናቸው ማሻሻያ የማድረግ ረጅም ጊዜ የቆየ አስፈላጊነት እንዳለ አመልክተዋል።
ተቋማቱ በዓለም ግንባር ቀደም ኢኮኖሚዎች መካከል ለሚደረግ ውይይት አሁንም አስፈላጊ መስመሮች መሆናቸውን ጠቁመው፣ የብሪክስ ሀገራት በእነዚህ ተቋማት ውስጥ ያላቸውን ቅንጅት እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል። ስለ ብሪክስ እድገት ሲያብራሩም፤ አባል ሀገራቱ ከፍተኛ ምሁራዊ እና ቴክኖሎጂያዊ አቅም እንዳላቸው ገልጸው፣ ይህም ለስብስብ ትልቅ ብልጫ መሆኑን ተናግረዋል።
ብሪክስ በዓለም አቀፍ አስተዳደር ዋና ማዕከላት መካከል ራሱን በብቃት ማረጋገጡንና በዓለም አቀፍ ፖለቲካ፣ ደህንነት፣ የኢኮኖሚ ትብብር እና ሰብአዊ ጉዳዮች ላይ የሚታዩ நகርዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በአባላቱ የጋራ ውሳኔዎች ላይ የተመሰረቱ እየሆኑ መምጣታቸውን ተናግረዋል። አክለውም አዲስ እየጎለበተ በሚገኘው የብዙ-ማዕከል (multipolar) ዓለም አቀፍ ሥርዓት ውስጥ፣ የብሪክስ ሀገራት ብዙ ወገንተኝነትን ለማጠናከር፣ በርካታ ሀገራትን በዓለም አቀፍ አስተዳደር ውስጥ ለማሳተፍ እና በዋና ዋና ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ በጋራ መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል
ሆኖም የብዙ-ማዕከል ዓለም ምስረታ ያለ እንቅፋት እየሄደ እንዳልሆነ የጠቆሙት ፑቲን፤ ዓለምን "የበለጸገ አትክልት ቦታ" እና "ዱር አራዊት የሚኖሩበት ጫካ" ብለው በመክፈል በሌሎች ኪሳራ ለመኖር ከለመዱና በቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ከሚያስቡ አካላት በኩል ግፊት እየገጠመው እንደሆነ ተናግረዋል። እነዚህ ወገኖች እየተቀየረ የመጣውን እውነታ ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን እና እየወጡ ያሉ ተፎካካሪዎቻቸውን ለማገደብ የታሪፍ ጦርነትን፣ ማዕቀቦችን እና "ኃይልን" ጨምሮ በሁሉም መንገድ እየሞከሩ እንደሆነ አብራርተዋል።

1 month ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የረጅም ጊዜ የፖለቲካ ልምድ ያላቸው እና በአሁኑ ወቅት የትምህርት ሚኒስትር የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ ግብፅ ኢትዮጵያን ለማዳከም የምትከተለው አሮጌ የፖለቲካ ሴራ መቼም ቢሆን እንደማይሳካ እና ውሎ አድሮ ግን ራሷን ካይሮን ዋጋ እንደሚያስከፍላት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ፕሮፌሰሩ ከENA ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ የካይሮ የውክልና ፖለቲካ እና የኢትዮጵያን የልማት ፕሮጀክቶች የማደናቀፍ ያልተቋረጠ ሙከራ በአዲሱ የዓለም አቀፍ የጂኦ-ፖለቲካ እውነታ ውስጥ "የሞኝነት አካሄድ" ሲሉ በጥብቅ ተችተውታል።ፕሮፌሰር ብርሃኑ በትንታኔያቸው ግብፅ የኢትዮጵያን እድገት ለመገደብ የሄደችበትን ረጅም ርቀት በአብነት አንስተዋል።
"የግብፅ መሪ ብትሆኑ ኖሮ እስቲ ቆም ብላችሁ አስቡ፤ ኢትዮጵያውያን ግድቡን እንዳይገነቡ ለረጅም ጊዜ ሞክራችኋል። ግን ማስቆም ቻላችሁ? አልቻላችሁም!" በማለት የግብፅ ጥረት ከንቱ መቅረቱን አስረድተዋል። ይልቁንም ኢትዮጵያ ይህንን ፈተና ተቋቁማ ይበልጥ ጠንካራ መሆኗን እና አስፈላጊ ከሆነም ሌሎች ተጨማሪ ግድቦችን የመገንባት አቅም መፍጠሯን ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ፣ ኢትዮጵያ የታችኛው ተፋሰስ ሀገር የሆነችውን ግብፅን በውሃ ጥም የመግደልም ሆነ የመጉዳት ምንም ዓይነት ፍላጎት እንደሌላት አስረግጠው ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ያለው የኃይል አሰላለፍ ለውጥ እና ጫና፣ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የትብብር ፖለቲካን እንዲከተሉ የሚያስገድድ ነው። ፕሮፌሰር ብርሃኑ እንዳስጠነቀቁት፣ "አፍሪካውያን በአንድነት ካልቆምን በስተቀር፣ ይህ ተለዋዋጭ የዓለም አቀፍ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ውጦ ሊያስቀረን ይችላል።" አህጉሪቱ በቅኝ ግዛት ዘመን ለዘመናት የከፈለችው ዋጋ ዋነኛ ምክንያት፣ ከውጭ ለሚመጣ ጫና በአንድነት መቆም አለመቻሏ መሆኑን በማስታወስ፤ ዛሬም ማሕበረሰባችንን በመከፋፈል እና አንዱ ሌላውን ለማዳከም በመሞከር የሚመጣ አንዳችም አሸናፊነት እንደሌለ፣ ይልቁንም "ሁላችንም ተሸናፊዎች" እንደምንሆን አስገንዝበዋል።
ግብፅ ሌሎች ኃይሎችን (Proxies) በመጠቀም ኢትዮጵያን ለማተራመስ የምታደርገው ጥረት ጊዜያዊ ፈተናዎችን ሊፈጥር ቢችልም፣ የቀጠናውን የኃይል ሚዛን ግን በመሰረታዊነት ሊቀይረው አይችልም። በመሆኑም በቀጠናው ያሉ ሀገራት ዘላለማዊ ጠላቶች አለመሆናቸውን በመገንዘብ፣ ከንቱ ከሆነ መናቆር ወጥተው ለህዝቦቻቸው ብልጽግና በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ፕሮፌሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
እርስ በርስ ከመዳከም ይልቅ አቅምን አስተባብሮ በጠረጴዛ ዙሪያ መወያየት ከተደጋጋሚው እና "ከማይረባው" የሴራ ፖለቲካ እጅግ የላቀ ብልህነት መሆኑን በማስመር ትንታኔያቸውን አጠቃልለዋል።

በዓለም መድረኮች የአፍሪካን ድምጽ የምታጎላው ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በታሪኳ ሙሉ ሉዓላዊነቷን አስከብራ የኖረች የነፃነት ምልክት ብቻ ሳትሆን፤ የመላው አፍሪካውያን ድምፅ በዓለም አቀፍ መድረክ ጎልቶ እንዲሰማ የቀዳሚነትን ሚና ስትጫወት የኖረች የአህጉሩ የዲፕሎማሲ ማዕከል ናት።
ከተባበሩት መንግሥታት ጉባኤዎች እስከ ብሪክስ እንዲሁም በበርካታ የዓለም መድረኮች ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እኩልነት፣ ነፃነትና ልማት በፅናት የምትቆረቆርና የምትሞግት ሀገር ነች፡፡
ኢትዮጵያ የቀድሞውን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ የአሁኑን የአፍሪካ ህብረት በመመስረት ሂደት መሃንዲስ በመሆን የነበራት ሚና ታሪካዊ ነው።
የኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ዋና ከተማ በመሆን የአህጉሪቱ ሀገራት በአንድ ጥላ ስር እንዲሰበሰቡ አድርጋለች።
በቅኝ ግዛት ስር የነበሩ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ነፃነታቸውን እንዲጎናፀፉ የገንዘብ፣ የዲፕሎማሲና የሎጂስቲክስ ድጋፍ በማድረግ የአህጉሪቱን ነፃነት ያረጋገጠች ቀንዲል፤ የጽናት ተምሳሌት ናት።
በዓለም አቀፍ መድረኮች የአፍሪካ ድምፅ የማይሰማበትና ፍትሃዊ ያልሆኑትን ዓለም አቀፍ አካሄድን ለመቀየር በግንባር ቀደምትነት እየተሟገተች፤ መፍትሄ እንዲሰጥ በማሳመን ዘልቃለች።
በተለይም አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ቋሚ ውክልና እንዲኖራት ጠንካራ የዲፕሎማሲ ትግል እያደረገች ትገኛለች።
በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች (ኮፕ) የበካይ ጋዝ ልቀት አነስተኛ በሆነባት ነገር ግን የጉዳቱ ሰለባ ለሆነችው አፍሪካ የካሳ እና የፋይናንስ ድጋፍ ጥያቄዎችን በፅናት በማቅረብ የአፍሪካን አቋም ስታንጸባርቅ ቆይታለች።
በተጨማሪም በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አማካኝነት የቀጣናውን ተፈጥሮ መልሶ የመንከባከብ ቁርጠኝነትን በተግባር በማሳየት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምሳሌ ሆናለች።
በአጠቃላይ ኢትዮጵያ እንደ ትናንቱ ዛሬም፤ ወደፊትም የምትቀጥለው የአፍሪካ ድምፅ፣ ጋሻና መሪ በመሆን ነው።
በዲፕሎማሲያዊ ከፍታዋና በጠንካራ የፓን አፍሪካኒዝም እምነቷ የአፍሪካን ክብርና ጥቅም በዓለም አቀፍ ደረጃ ማስከበሯን ትቀጥላለች።
በመልካም ፈቃዱ

ቅኝ ያልተገዙት ሁለቱ ሀገራት በአዲስ ምዕራፍ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ታይላንድ በጂኦግራፊ የተራራቁ ሀገራት ናቸው። አንድ ግዙፍ ታሪክ ግን ያቀራርባቸዋል፤ የዓለም ታሪክ ሀገራቱን “በቅኝ ግዛት ያልተንበረከኩ” ብሎ መዝግቧቸዋል።
ሁለቱም ሀገራት በ19ኛው እና በ20ኛው ክፍለ ዘመን የነበረውን የአውሮፓ ቅኝ ግዛት ማዕበል ተቋቁመው ሉዓላዊነታቸውን ጠብቀው ማቆየት የቻሉ ታሪክ ተጋሪዎች ናቸው።
በቀድሞ ስሟ ሲያም (የአሁኗ ታይላንድ) በ19ኛው ክፍለ ዘመን እንግሊዝና ፈረንሳይ በደቡብ ምስራቅ እስያ ሰፊ ግዛቶችን ሲቆጣጠሩ፣ በሁለቱ ኃያላን መንግሥታት መካከል ስትራቴጂያዊ ሚዛንነቷን ተጠቅማ ነፃነቷን ጠብቃለች፤ የታይላንድ ጥበበኛ መሪዎች ሀገራቸውን በዲፕሎማሲና በፖሊሲ ማሻሻያዎች ከቅኝ ግዛት ታድገዋል።
በተመሳሳይ ወቅት አውሮፓ አፍሪካን ስትቀራመት ኢትዮጵያ በዓድዋ ጦርነት ጣሊያንን በማሸነፍ ነፃነቷን ያስጠበቀች ሀገር ሆና ተመዝግባለች።
ለሁለቱም ሀገራት ታሪካቸው የብሔራዊ ኩራት ምንጫቸው ነው። ይህ የታሪክ ተጋሪነት በሁለቱ ሀገራት መካከል የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እርሾ ሆኗል። ይህ የጋራ ትርክት በሁለቱ ሀገራት መካከል የመከባበርና የመተማመን መንፈስ እንዲፈጠር አስተዋፅኦም አድርጓል።
ታይላንድና ኢትዮጵያ መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን በ1956 ዓ.ም የጀመሩ ሲሆን ÷ ይህንን ግንኙነታቸውን ተከትሎም የንግድና የባሕል ግንኙነታቸውን አጠናክረው ቆይተዋል፡፡ ከትናንት እስከ ዛሬ የተሻገረው የሀገራቱ ግንኙነት ኢትዮጵያ ለምትከተለው ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ እንደማሳያ የሚቆጠር ነው።
ሁለቱ ሀገራት የዜጎችን ጥበቃን በተመለከተ ስምምነቶች ያሏቸው ሲሆን ታይላንድ ወደ ማይናማር ተጭበርብረው ተወስደው የነበሩ ኢትዮጵያውያንን ደህንነታቸውን ተጠብቆ እንዲመለሱ ድጋፍ አድርጋለች።
ኢትዮጵያና ታይላንድ የጋራ የኢኮኖሚ እድገት መሻትን ይጋራሉ፤ ይህም ለአዳጊ ባለኢኮኖሚ ሀገራቱ በደቡብ ደቡብ ቅኝት ሌላ የትብብር መድረካቸው ነው። እንዲሁም ባንኮክ በህክምና ቱሪዝም ሰፊ ልምድ ያላት ሲሆን አዲስ አበባ በዘርፉ የአፍሪካ ፊት ቀደም የመሆን ግብ አስቀምጣለች።
በብራዚል በተካሄደው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ ወቅት የታይላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪስ ሳንጋምፖንሳ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ጋር በመገናኘት በተለይ በቱሪዝምና በህክምና አገልግሎት ዘርፎች የትብብር እድሎችን መርምረው ነበር።
ዛሬ ይህ እያደገ የመጣ ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉዋንግኬትክየው በኢትዮጵያ እያደረጉት ያለው የስራ ጉብኝት የመጀመሪያው በከፍተኛ ሃላፊነት ያለ የታይላንድ መሪ ይፋዊ ጉብኝት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
ይህም ታይላንድ ከአፍሪካ አጋሮቿ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው። ዛሬ ሁለቱ ሀገራት የተለያዩ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።
ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ጠቃሚ የማምረቻና የሎጂስቲክስ ማዕከል ተደርጋ የምትታይ በመሆኗ፣ ይህ ጉብኝት በኢትዮጵያና በታይላንድ መካከል እያደገ የመጣውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ተደርጎ ተወስዷል።
በአፈወርቅ እያዩ

Sponsored by
Surafel
2 months ago
ራስ አሉላ አባነጋ፡ የቀይ ባሕር ዳርቻው ነበልባል እና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የዘላለም ዘብ
*************************
በአሥራ ዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ የአፍሪካ አህጉር በአውሮፓ ኃያላን የቅኝ ግዛት ሽሚያ እጅግ ፈታኝ በሆነ የታሪክ ማዕበል ውስጥ ስትላጋ፣ የኢትዮጵያ ህልውና በከፍተኛ አደጋ ላይ ወድቆ ነበር።
በተለይም የኢትዮጵያ የትንፋሽ ቱቦ የሆነው የቀይ ባሕር ዳርቻ እና የምጽዋ ወደብ፣ የእንግሊዝ፣ የፈረንሳይ፣ የጣሊያን፣ እንዲሁም የግብፅ የጥቅም ግጭት ማዕከል ሆኖ ይመሰቃቀል ነበር።
በዚህ እጅግ ውስብስብ፣ አደገኛ እና አሻጥር በበዛበት የዓለም አቀፍ ፖለቲካ መድረክ ላይ፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ከውጭ ወራሪዎች ለመከላከል እንደ ትልቅ ዋርካ ጸንተው የቆሙት ታላቁ ዐርበኛ እና የጦር ጄኔራል ራስ አሉላ አባነጋ ነበሩ።
የሀገር ድንበር ከባሕር እንደሚጀምር በሚገባ የተገነዘቡት እኚህ ታላቅ የጦር ጠቢብ ሙሉ ሕይወታቸውን የሰሜኑን በር በመጠበቅ እና ወራሪዎችን በማርበድበድ አሳልፈዋል።
የግብፅን ትንኮሳ መመከት፡ የጉንደት እና የጉራዕ አንጸባራቂ ድሎች
የራስ አሉላ አባነጋ የጀግንነት እና የሀገር ፍቅር ታሪክ የሚጀምረው አውሮፓውያን ቀይ ባሕርን ከመቆጣጠራቸው አስቀድሞ፣ በቀጣናው ሰፊ የቅኝ ግዛት ህልም ሰንቃ የነበረችውን የግብፅን ወረራ በመመከት ነው።
በ1868 ዓ.ም ግብፆች ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር ለማድረግ አስበው በአውሮፓውያን እና በአሜሪካውያን የጦር መኮንኖች የሚመራ እጅግ ዘመናዊ መሣሪያ የታጠቀ ጦር በምጽዋ በኩል ወደ መሀል ሀገር ላኩ።
ይህ ጦር የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ደፍሮ ሲገባ በወቅቱ ሻለቃ የነበሩት አሉላ አባነጋ በኅዳር ወር 1868 ዓ.ም በጉንደት ጦርነት ላይ የግብፅን ጦር አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ወደር የለሽ ጀግንነትን ፈጸሙ።
ራስ አሉላ በፈጠሩት አስደናቂ ወታደራዊ ታክቲክ የግብፅ ጦር አዛዥ የነበረው ዴንማርካዊው ሶረን አረንድሩፕ ተገደለ፤ ጦሩም ሙሉ በሙሉ ተደመሰሰ።
የግብፅ መንግሥት በጉንደት የተከናነበውን ውርደት ለመበቀል በማሰብ በዚያው ዓመት (በየካቲት 1868 ዓ.ም.) በድጋሚ በከፍተኛ ዝግጅት በራቲብ ፓሻ እና በአሜሪካዊው ጄኔራል ሎሪንግ የሚመራ ከበፊቱ የገዘፈ ጦር ይዞ በጉራዕ ላይ ዘመተ።
ታዲያ በዚህ እጅግ ወሳኝ በሆነ የህልውና ጦርነት ላይ ራስ አሉላ የዐፄ ዮሐንስን ጦር በግንባር ቀደምትነት በመምራት የግብፅን ሠራዊት ድል አደረጉ።
በጉራዕ ሜዳ ላይ የግብፅ ጦር የፈረሰበት እና ከፍተኛ የጦር መሳሪያ የተማረከበት የራስ አሉላ ወታደራዊ ጥበብ የኢትዮጵያን ሰሜናዊ ድንበር ከግብፅ ስጋት ሙሉ በሙሉ ነጻ ያወጣ ነበር።
ለዚህ ውለታቸው እና ለግሩም አመራራቸው ዐፄ ዮሐንስ "ራስ" የሚለውን ማዕረግ ሸልመው የመረብ ምላሽ (የአሁኗ ኤርትራ) አስተዳዳሪ አድርገው ሾሟቸው።
የቀይ ባሕር አደራ እና የመረብ ምላሽ አስተዳደር
ራስ አሉላ አባነጋ እጅግ ፈታኝ እና ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያለውን የሰሜን ድንበር ግዛት (መረብ ምላሽን) እንዲያስተዳድሩ ሲሾሙ ኃላፊነታቸው የኢትዮጵያን የባሕር በር ከውጭ ጠላቶች የመጠበቅ፣ ጠላት ድንበር ጥሶ ወደ መሀል ሀገር እንዳይገባ እንደ ጸና ዓለት የመቆም ታላቅ ሀገራዊ አደራ ነበር።
በዚህ ታላቅ ኃላፊነታቸው ዘመን፣ ራስ አሉላ የመንግሥታቸውን ማዕከል ወደ አሥመራ በማዛወር ከተማዋን በከፍተኛ ደረጃ አስፋፉ።
ወታደራዊ ሎጂስቲክስን እና ፈጣን የጦር እንቅስቃሴን ታሳቢ በማድረግ፣ ከአሥመራ ወደ ምጽዋ የሚወስደውን አሮጌ እና አደገኛ የተራራ መንገድ በማስፋት ለፈረሰኛ ጦር እና ለመድፍ ማጓጓዣ ምቹ እንዲሆን አድርገው አሠርተዋል።
ይህ እርምጃቸው የባሕር በሯን ደኅንነት በቅርበት ለመቆጣጠር እና ጠላት ከምጽዋ ወደ ምድር ሀገር የሚያደርገውን ማንኛውንም እንቅስቃሴ በአጭሩ ለመቅጨት ያስቻላቸው ታላቅ የስትራቴጂ ሊቅነታቸውን የሚያሳይ ነበር።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ የደም ስር የሆነው ቀይ ባሕር፣ በአሉላ ንቁ ዓይኖች ስር ወደር የለሽ ጥበቃ ተደርጎለታል።
የሂዊት ውል፡ ለኢትዮጵያ የባሕር በር የተከፈለ ደም
በ1870ዎቹ ዓ.ም መጀመሪያ በሱዳን የተቀሰቀሰውን የደርቡሽ አመጽ ተከትሎ የተከበቡትን የግብፅ ወታደሮች በሰላም ለማስወጣት እንግሊዝ የኢትዮጵያን እርዳታ ጠየቀች።
በዚህም መሠረት ግንቦት 26 ቀን 1876 ዓ.ም በዓድዋ ከተማ በተፈረመው የሂዊት ውል፣ ኢትዮጵያ የግብፅ ወታደሮችን በግዛቷ አቋርጠው በሰላም በማስወጣት ምትክ ግብፆች በኃይል ይዘውት የነበረው የቦጎስ ግዛት እንዲመለስላት እና በምጽዋ ወደብ ዕቃዎችን ከቀረጥ ነጻ በነጻነት እንድታስገባ ተስማማች።
ራስ አሉላም ይህንን ስምምነት በማክበር በኩፊት ጦርነት ላይ የደርቡሽን ጦር በጀግንነት ደምስሰው የራሳቸውን ወታደሮች ደም አፍስሰው የግብፅ ወታደሮችን በሰላም ምጽዋ በማድረስ የሀገራቸውን ቃል ኪዳን በተግባር ጠበቁ።
የታሪክ ክህደት እና የአሉላ የነበልባል ቁጣ
ሆኖም ግን የአውሮፓውያን የፖለቲካ ተንኮል እና እምነት ማጉደል ድንበር የለሽ ነበር። እንግሊዞች የገቡትን ዓለም አቀፋዊ ቃል በግልጽ በማጠፍ፣ የፈረንሳይን የጂቡቲ መስፋፋት ለመግታት እና የቀይ ባሕርን ስትራቴጂያዊ የበላይነት የራሳቸው አሻንጉሊት በሆነ ኃይል ሥር ለማድረግ ሲሉ የኢትዮጵያ ታሪካዊ የባሕር በር የሆነችውን ምጽዋን የካቲት 1877 ዓ.ም ታዳጊ ለነበረችው የጣሊያን ኃይል አሳልፈው ሰጡ።
ይህ የእንግሊዞች ፀያፍ የዲፕሎማሲ ክህደት ራስ አሉላን እጅግ አስቆጣቸው። አሉላ የአውሮፓውያንን በሁለት ቢላዋ (Double standard) እና ተንኮል በጥልቀት ተረዱ።
ከእንግዲህ ወዲህ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የባሕር በር በውል እና በወረቀት ሳይሆን፣ በብረት እና በደም ብቻ እንደሚጠበቅ ቆርጠው ተነሱ። ጠላት ምጽዋ ላይ መሽጎ ወደ መሀል ሀገር ለመዝለቅ ሲያደባ፣ ራስ አሉላ እንደ ነበልባል እሳት ሆኑባቸው ።
የጣልያንን መስፋፋት መግታት፡ ከአይለት እስከ ታላቁ የዶጋሊ ድል
ጣልያኖች ምጽዋን ከተቆጣጠሩ በኋላ፣ ቀስ በቀስ ወደ መሀል ኢትዮጵያ ለመስፋፋት ሙከራ ማድረግ ጀመሩ። በ1879 ዓ.ም ሣሃጢ እና ዋዓ በተባሉ ቦታዎች ምሽግ ሠርተው ድንበር ሲጥሱ፣ ራስ አሉላ ወዲያውኑ የመብረቅ ያህል በፍጥነት እርምጃ ወሰዱ።
መጀመሪያ አይለት በተባለ ቦታ ላይ የጣልያንን ጦር በድንገት በማጥቃት ኃይላቸውን አሽመድምደው ጠንካራ መልዕክት አስተላለፉ።
ራስ አሉላ ለጣሊያን ጄኔራሎች፣ "ይህች ምድር የኛ ናት፣ ከምጽዋ አልፋችሁ አንድ ስንዝር መግባት አትችሉም፤ የመጣችሁበትን ባሕር ጠጥታችሁ እዚያው እለቁ እንጂ ወደ ሀገሬ አትገቡም" የሚል ጥብቅ እና የማያወላውል የሉዓላዊነት ማስጠንቀቂያ ላኩ።
ጣሊያኖች ይህንን የጀግና ማስጠንቀቂያ ንቀው፣ የሣሃጢን ምሽግ ለማጠናከር ተጨማሪ ጦር ይዘው ወደ ፊት ሲገሰግሱ ራስ አሉላ ጥር 18 ቀን 1879 ዓ.ም. በዶጋሊ አሸዋ ላይ ጠበቋቸው።
በታላቅ የጦር ስትራቴጂ እና ወደር በማይገኝለት የሀገር ፍቅር ወኔ 500 የሚጠጉ ዘመናዊ መሣሪያ የታጠቁ የጣሊያን ወታደሮችን ከነአዛዣቸው ከኮሎኔል ዴ ክሪስቶፎሪስ ጋር ሙሉ በሙሉ ደመሰሷቸው።
የዶጋሊው ድል መላውን አውሮፓ ያስደነገጠ፣ የጣሊያንን የቅኝ ግዛት ህልም ያጨለመ፣ የኢትዮጵያን የማይደፈር ሉዓላዊነት በተግባር ያረጋገጠ እና ራስ አሉላን የቀይ ባሕር ዳርቻ የማይበገር ጠባቂ ያሰኘ ታላቅ ታሪካዊ ኩራት ነው።
የዓድዋው ጀግና፡ የጣልያንን ወረራ በድጋሚ መቅጨት
የራስ አሉላ አባነጋ የሀገር ዘብነት በዶጋሊ ብቻ አላበቃም። ከዓመታት በኋላ የጣሊያን ጦር ዳግም ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛትነት ለመያዝ በከፍተኛ ትዕቢት ሲዘምት፣ በየካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በተደረገው ታላቁ የአድዋ ጦርነት ላይ ራስ አሉላ የዐፄ ምኒልክን ሀገራዊ ጥሪ ተቀብለው ከነሙሉ ሠራዊታቸው በግንባር ቀደምትነት ተሰለፉ።
የአሉላ የጦር መረጃ እና የስትራቴጂ ብቃት በዓድዋ ጦርነት ላይ የላቀ እና ወሳኝ ሚና ተጫውቷል።
ጣልያኖች የኢትዮጵያን ጦር በድንገት ለማጥቃት ሌሊት የሚያደርጉትን ስውር እንቅስቃሴ የራስ አሉላ ሰላዮች ቀድመው በማወቅ መረጃውን ለዐፄ ምኒልክ አደረሱ።
በዚህም የኢትዮጵያ ጦር ሳይዘናጋ ዝግጁ ሆኖ ጠላትን እንዲጠብቅ አስቻሉ። በጦርነቱ ዕለትም የጣሊያንን የጄኔራል አልበርቶኔን ጦር በመክበብ፣ የጠላትን የማፈግፈጊያ መንገድ በመዝጋት እና በማጥቃት ረገድ የራስ አሉላ ወታደሮች የፈጸሙት ጀግንነት የኢትዮጵያን የመጨረሻ ድል ካረጋገጡት የብረት ምሰሶዎች አንዱ ነበር።
አሉላ ጣልያንን ከባሕር በር ጀምሮ እስከ ዓድዋ ተራሮች ድረስ ዕረፍት የነሱ፣ የሀገር ሉዓላዊነት የቁርጥ ቀን ጠበቃ ነበሩ።
የውስጥ ባንዳዎችን ማጽዳት፡ ሀገርን የማዳን ጽናት
የራስ አሉላ የሀገር ፍቅር ጥልቀት የሚለካው በውጭ ወራሪዎች ላይ በነበራቸው ቆራጥ አቋም ብቻ አልነበረም። የውጭ ጠላት ሀገር ውስጥ ዘልቆ መግባት የሚችለው የውስጥ ከዳተኞች (ባንዳዎች) በር ሲከፍቱለት መሆኑን ጠንቅቀው ያውቁ ነበር።
በመሆኑም፣ በጣሊያን የብር ስጦታ፣ በሥልጣን ጥማት እና በውጭ ኃይሎች የሐሰት ቃል ኪዳን ታውረው የሀገራቸውን ሉዓላዊነት አሳልፈው ለመስጠት የሚሞክሩ የውስጥ ባንዳዎችን እና ከዳተኞችን ያለ ምንም ርህራሄ ተፋልመዋቸዋል።
ለራስ አሉላ ሀገርን መውደድ ማለት የሀገርን ጠላት፣ የውጭም ሆነ የውስጥ፣ በእኩል ጽናት መታገል መሆኑን በተግባር አስተምረዋል።
ለእሳቸው ኢትዮጵያዊነት ከምንም እና ከማንም በላይ የከበረ፣ በብር የማይሸጥ እና በሥልጣን የማይለወጥ ቅዱስ እሴት ነበር።
ጠላትን ፊት ለፊት በሚደረግ ጦርነት ማሸነፍ እንደሚቻለው ሁሉ፣ ከውስጥ ሆነው የሀገርን አንድነት የሚቦረቡሩትን ባንዳዎች ማጽዳት የሀገርን ህልውና ለማስቀጠል ዋነኛው እና የማይታለፈው እርምጃ መሆኑን በተግባር አሳይተዋል።
ራስ አሉላ አባነጋ መላ ዘመናቸውን የሰሜኑን ድንበር እና የቀይ ባሕርን ዳርቻ በንቃት ሲጠብቁ ያሳለፉ የኢትዮጵያ የነጻነት ተምሳሌት ናቸው።
ከጉንደት እና ጉራዕ የግብፅ ጦርነት አንስቶ እስከ ዶጋሊ፣ ከአይለት አሸዋ እስከ ዓድዋ ተራሮች ድረስ፣ የኢትዮጵያ አፈር በውጭ ወራሪዎች እንዳይረገጥ የከፈሉት ታላቅ መስዋዕትነት እና ያሳዩት ቆራጥ ወታደራዊ አመራር፣ ዛሬም ድረስ በትውልዱ ልብ ውስጥ በአኩሪ ታሪክነት ይኖራል።
የእሳቸው ታሪክ የሩቅ ዘመን ተረት ሳይሆን፣ ዘመናዊት ኢትዮጵያ የብሔራዊ ስነ-ልቦናዋን የምትገነባበት፣ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዋን በንቃት የምትቃኝበት፣ የውስጥ ባንዳዎችን አደጋ የምትገነዘብበት እና ታሪካዊ የባሕር በር ጥያቄዋን በጽናት የምታስጠብቅበት የዘላለም የነጻነት ትምህርት ቤት ነው።
ራስ አሉላ አባነጋ የቀይ ባሕር ዳርቻው ነበልባል፣ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የማይደፈር ጠበቃ እና እውነተኛ የሀገር ፍቅር ትርጉም ምን እንደሆነ በደማቸው ጽፈው ያለፉ የማይሞቱ ጀግና ናቸው!
የክብር ስማቸው በታሪክ ገጾች ላይ ለዘላለም ሲያበራ ይኖራል!
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
#ethiopia #ebc #ebcdotstream #redsea #rasalula

የኢትዮጵያ ትንሳኤ !
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብስራት አድማስ እና የዓለም ዓይኖች ማረፊያ እየሆነች ትገኛለች።
እሷ የታሪክ እምብርት፣ የሰው ዘር መገኛ እና የነፃነት ማኅተም ናት። ዛሬ ደግሞ በልጆቿ ጽናት እና በማይበገረው ህዝባዊ ወኔያቸው አዲስ የትንሳኤ ምዕራፍ እየተቀኘች ትገኛለች።
ይህ የትንሳኤ ብርሃን ለራሷ ብቻ ሳይሆን፣ ለመላው ጥቁር ህዝብ እና ለአፍሪካ አህጉር አዲስ የብስራት አድማስ እየቀደደ ነው።
የዚህች ታላቅ ሀገር ትንሳኤ ከባዶ የተነሳ ሳይሆን፣ ከጥንታዊው የክብር ሥርዓቷ እና ካልተደፈረው ማንነቷ የተቀዳ ነው። አፍሪካ በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ሥር በነበረችበት የጨለማ ዘመን፣ ኢትዮጵያ የነፃነት ብቸኛ ፋኖስ ሆና እንዳበራች ሁሉ፣ ዛሬም ያ የወርቃማ ታሪክ በዘመናዊው ትውልድ ልብ ውስጥ እንደገና እየተቀጣጠለ ይገኛል።
በመሆኑም ይህች የአናብስት ምድር የገጠሟትን ዘመናዊ ፈተናዎች፣ የኢኮኖሚ ጫናዎች እና ማህበራዊ ውጣ ውረዶች በራሷ ልጆች ጥረት እና ጥንካሬ እያሸነፈች ትገኛለች።
የኢትዮጵያ ህዝብ ታታሪነቱ፣ ለነጻነት ቀናኢነቱ፣ የማይበገረው ፅናቱ እና ለሀገሩ ያለው ጥልቅ ፍቅር አዲሱን የትንሳኤ መንገድ እያቀናው ነው።
በዚህ ጽናት ላይ የተገነባው የኢትዮጵያ ትንሳኤ የመላው አፍሪካም ትንሳኤ ነው። አፍሪካ ለዘመናት የድህነት፣ የጦርነት እና የተስፋ መቁረጥ ምድር ተደርጋ በምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ስትሳል ብትኖርም፤ ኢትዮጵያ ይህንን የተሳሳተ ትረካ በተግባር እየቀየረችው ትገኛለች።
ከኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እስከ ቢሾፍቱ የአውሮፕላን ማረፊያ፣ በታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶቿ፣ በአረንጓዴ ዐሻራዋ እና በኢኮኖሚ መነቃቃቷ አህጉራዊ ተምሳሌትነቷን በማደስ ላይ ትገኛለች።
የኢትዮጵያ ትንሳኤ አፍሪካውያን በራሳቸው አቅም ማደግ፣ መበልጸግ እና የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው መወሰን እንደሚችሉ የሚያሳይ ትልቅ የብስራት አድማስ ሆኖ፣ አህጉሪቱ ወደ አዲስ የነፃነት እና የብልጽግና ምዕራፍ እንድትሻገር ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተች ነው።
በዚህም የምክንያት ዛሬ የዓለም ዓይኖች ወደ እሷ እየተመለከቱ ነው። በዓለም ከሚታወቁት ግዙፍ ሚዲያዎች አንዱ የሆነው የአሜሪካው ሲኤንኤን የሰሞኑ ዘገባው ይህን ያመለክታል። ይህ ዘገባ የአድናቆት እና የግርምት እይታ ነው።
በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ በአቪየሽን እንዲሁም አጠቃላይ በልማት እያስመዘገበቸው ያለውን ዕምርታ በጥልቀት የዳሰሰው ሚዲያው የኢትዮጵያን ትክክለኛ መልክ ያሳዬ ነበር፡፡ በዚህም ሀገራችን የዓለም አቀፍ ባለሀብቶችን እና ቱሪስቶች ቀልብ ስባለች።
ሰፊው የገበያ እምቅ አቅሟ እና ስትራቴጂካዊ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጧ የዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከል እያደረጋት ሲሆን ፤ ከተፈጥሮ ውበቷ እስከ ጥንታዊ ስልጣኔዎቿ፣ ከላሊበላ እስከ አክሱም ዘመናትን የተሸገሩ ቅርሶቿ ደግሞ ዓለምን ማስደመማቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ትንሳኤ የሩቅ ህልም ሳይሆን የዕለት ተዕለት እውነታ እየሆነ የመጣ ተጨባጭ ክስተት ነው። በራሷ ውስጣዊ ዕምቅ አቅም፣ በህዝቦቿ ላብ እና ጥረት የምታስመዘግበው ስኬት የዓለምን መድረክ እየማረከ ይገኛል።
ኢትዮጵያ ትናንት የነፃነት ምልክት እንደነበረች ሁሉ፤ ዛሬ ደግሞ የብልጽግና እና የብስራት አድማስ ሆና በዓለም ፊት በኩራት ቆማለች ።

መዝሙረ ሄላም ላይ የተደረገ አጭር ኂሳዊ ንባብ
ከቢኒያም አቡራ
#ethiopia | አዳም ረታ ታሪክን ከነገሥታት፣ ከመሪዎች፣ ማኅበረሰቡ ባበጀው ድልድል ውስጥ ‹ላዕላይ› ከሚባሉት ደረጃዎች አንጻር አያስመለክተንም። ታሪካዊ ከሚባሉ አጋጣሚዎች ውስጥ የተዘነጉትን ጥቃቅን የታሪክ ኹነተ-ደቂቅ (micro-events) ይመርጣል። ይወስዳል መንገድ ላይ … “ቀዳዳ” በተሰኘው ታሪክ ላይ ፍንዳታውን ከሚሞት ዘመድ፣ ከሚደነግጥ ለማኝ፣ ከሚሰነጠቅ የወፍ እንቁላል፣ ከሚፈስ የእናት ወተት ጋር Micro-Macro Connection በመፍጠር የትልቁ ቀዳዳ መፈጠርን ከሚጢጢዬ ሽንቁሮች ጋር ያስተሳስርልናል። እንዲህ ያሉ የኒው ሂስቶሪሲዝም ባሕሪያትን ከዚህ ቀደም ባሳተማቸው መጻሕፍቱ ውስጥ በተለያየ መጠን እናገኛለን።
Adam Reta አዳም ረታ "መዝሙረ ሄላም" በተሰኘው በዐዲሱ መጽሐፉ ላይም በኢትዮጵያ ታሪካዊ-ፖለቲካዊ አጋጣሚ ውስጥ እንደ ዐውራ የሚታዩትን የእድገት በኅብረት ዘመቻን እንደነ-አሮን፣ እንደነቃል … ባሉ ገጸባሕርያት በኩል፣ የሰባ ሰባቱን ድርቅ በሄላም ጡት በኩል፣ “ጥላሁን ለምን ለምን ሞተ” እየተባለ ኢዮቤልዩ ቤተመንግሥት ጋር የተደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ በሡልጣን በኩል፣ የከተማ መሬት ዐዋጅን በተለያዩ ግለሰቦች በኩል … እናያለን። በዚህም የታሪክን ትልቅ ካርታ ለመረዳት የተረሱና የጠለሉ ታሪኮችን ይመረምራል። ስለዚህ ነቁጣዊ ማኅበራዊ ክስተቶችን ወደ ታሪክ ምኩራብ በማምጣት ከትልቁ የታሪክ ምሥል ጎን ያስተያያል። ይህ ደግሞ የኒው ሂስቶሪሲዝም ኹነኛ ማጠንጠኛ ነው።
ልክ “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ …” በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ባለው “የመንግሥቱ ጊዜ” በሚለው ድርሰት ውስጥ፣ ትልቁን “የታኅሣሥ ግርግር”ን እንደ መቼት አምጥቶ የተጻፈውና የተተኮረው ግን ኹነተ-ደቂቅ (micro-events) ላይ ነው። ስለግርማሜ ንዋይ፣ ስለኮሌኔል ወርቅነህ ገበየሁ፣ ሰለጄነራል ሙልጌታ ቡሊ አይደለም የሚያትተው። ስለአንድ ብላቴና ከእንቅልፍ መነሳት፣ ስለገበጣ ጨዋታ፣ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሕፃናትን አሰብስቦ ‹ኪራላይሶን› የሚያስብል ካሕን፣ ስለመንደር ውስጥ ሐሜቶች፣ ስለግለሰቦች ፍርሃት፣ በአጋጣሚ ስላየው አስደናቂ አሞራ … ያወጋል። የታሪክ አጋጣሚ አምጥቶ በታሪክ ውስጥ ግለሰቦች ላይ ስለሚረብበው የታሪክ መንፈስ ያትታል። ልክ እንደዚሁ መዝሙረ ሄላም ላይም ጽሑፉ ታሪክን አያብራራም፤ ነገር ግን ታሪክ እንዴት በሰው ልብ ውስጥ እንደሚኖር ያሳያል። በዚህ ኹነተ-ደቂቅ (micro-event) ምክንያት በዘመኑ ላይ ያገነገነውን ባሕላዊ እምነትን፣ የሥልጣን መዋቅርን፣ የወል ግንዛቤን አጨንቁረን እንድንመለከት ያስችለናል።
ከመንግሥት ሼልፍ ላይ ሳይኾን ከግለሰብ ጀርባ ላይ የተወሰደው የአዳም የአጻጻፍ መንገድ ከኒው ሂስቶሪስዝም ጽንሰ-ሐሳቦች ጋር በአንድ መም ላይ የሚሄዱ ናቸው። መዝሙረ ሄላም የተሰኘው ዐዲሱ የአዳም ረታ መጽሐፍ የኒው ሂስቶሪሲዝም ባሕርያትን ይጋራል። አንዳንድ ነገሮችን በዓይን መመልከት ባይቻልም በግብሩ (ቁስ ላይ በሚያደርገው ግፊት) ግን ይታወቃል። በመዝሙረ ሄላም መጽሐፍ ውስጥም አንዳንድ ነገሮችን በቀጥታ ማየት ባንችልም ቅሉ እነርሱን የሚያሳይልንን ነገሮች ግን እንቃኛለን። ዘማች ወጣት ተማሪዎችን እናያለን፤ መንግሥትን፣ ሕግንና ኃይልን ግን በቀጥታ አንመለከትም። የተማከለ ኃይል አናይም ግን የገጸባሕርያቱ የፍርሃት ምንጭ ከተማከለ ኃይል ጋር የተያያዘ ቀጭን መስመር መኖሩን እናያለን። መንግሥትም ቢኾን በቀጥታ አይገባም፤ ነገር ግን ፍርሃት እንደ ሥርዓት ዘዋሪ (system driver) ይኾናል። እንደ ሚሸል ፉኮ አገላለጽ ኃይል ከተማከለ ሥርዓት የሚመነጭ ሳይኾን በየትኛውም ቦታና ጊዜ በፍርሃት፣ በልማድ፣ በንግግር … ሊከሰት የሚችል ሂደት አይደል?
መዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክ እንደ “circulation of social energy” ቀርቧል። መዝሙረ ሄላም ላይ መረጃ ከመንግሥት አይመጣም፤ ከግለሰብ እንጂ። የከተማ መሬት ዐዋጅም ኾነ የተማሪዎች ዘመቻ በገጸባሕርያቱ ወሬ ውስጥ ነው የሚንቀረቀበው። ይህ የመረጃ ሥርዓት ኃይል ማን እንዳለው ማን እንደሌለው ያሳያል። እንግዲህ ይህ በፉኮኛ micro-power መኾኑ ነው። በመዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክ እንደ ወሬ እንጂ እንደ ሰነድ አይቀርብም።
ወሬ የፍርሃት ቤንዚን ነው … ፍርሃት ደግሞ በዝምታ መሸበብን ይፈጥራል … የዝምታ አፈ-ሙቅ ደግሞ ኃይለኛው እንዳይታይ ያደርጋል … የተደራጀው ኃይል ጥፋትን ሊያደርስ ባሰበ ቁጥር የወሬ ቤንዚን ይጨምራል። ሰዎች በዕቅብተ-ንግግር ራሳቸውን ሲሸብቡ ደርዝ ያለው ሙግት ይኮሰምናል፣ ንግግር ሲጠፋ ያልታወቀ አደጋ ይከሰታል፣ ፍርሃትም ይጨምራል። ያልታወቀ አደጋ ደግሞ ከታወቀ አካል ይመጣል። ስለዚህ ጥንስሱ የሚጀምረው ከወሬ እንደኾነ ያስመለክተናል። አዳም በመዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክን እንደ “circulation of social energy” ሲያቀርብ ፕሬዝዳንት፣ ጀነራል፣ ፕሮፌሰር የኾኑ ታሪክ ከላዕላይ ያስቀመጣቸው ሰዎች አያስፈልጉትም። በአንጻሩ ሄላም ለማን እንደሳመችው ተደርጎ ብርሃኔ ያስወራው ወሬ፣ የሄላም አባት ወታደር በመኾኑ ምክንያት በካሱ፣ በሄኖክ እናት የተነዛው ወሬ እና ሄላም ከሄኖክ ጋር የተቆራረጠችበት መንገድ እንዲሁም የሄላምን የጡት ወተት በተመለከተ የተነዛው ወሬን ይጠቀማል።
መዝሙረ ሄላምን ከድኅረ-ቅኝ-አገዛዝ የኂስ መንገድ አንጻር እንመልከተው።
እውን ቅኝ-ግዛት ተረት ኾኖ ቀርቷል? በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በሥነልቦና ረገድ የቅኝ አገዛዝ ዳናው ሙሉ ለሙሉ ጠፍቷል? አዳም በመዝሙረ ሄላም ጽሑፍ ውስጥ ከቅኝ-ግዛት በተወረሰ መዋቅር ምክንያት የተሰናከለን ሕይወት ሊያስመለክተን ይኾን?
“ከተሞች ከቅኝ ግዛት በኋላ ሁለት ዓይነት መልክ ይኖራቸዋል፤ ለጥቂቱ የተድላ፣ ለተቀረው ደግሞ የአሳር መንደር ይኾናሉ” ይላል ፍራንዝ ፋኖን። በመዝሙረ ሄላም ላይ እና “የቢሾፍቱ ልጆች ጥላሞት” የተሰኘው ድርሰት ላይም ይህንን ነው የምንመለከተው። “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ …” በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ካሉ ጽሑፎች መካከል “የቢሾፍቱ ልጆች ጥላ ሞት” አንዱ ነው። የቢሾፍቱ ልጆች ሆቴሉን ያዩታል፤ ግን አይገቡበትም። ሆቴሉ የሀገራቸው መሬት ላይ ነው፤ እነርሱ ግን ከሆቴሉ ውጭ ናቸው። መናፈሻው ውስጥ አንዲት የፈረንጅ ልጅ ጠግባ ለልጆቹ እንደ ውሻ ዳቦ ትወረውርላቸዋለች። አፈር ላይ የወደቀን ዳቦ አራግፈው ይመገባሉ። በገዛ ሐይቃቸው ዳር ላይ ናቸው፤ ሌሎች ግን በጀልባ እየተንሸራሸሩ ይንፈላሰሳሉ። ለፈረንጆቹ ያደረው ሞገስ የላንድሮቨር ተፈናጣጭ ኾኗል። ሌሎቹ ግን ከመኪናው ውጪ ናቸው። ሞገስ እንደ እነርሱ ሕጻን ቢኾንም ለፈረንጅ በማሸርገዱ የትምህርት ቤቱ ባለቤት ሲመስል ሌሎች ልጆች ግን በገዛ መምህራቸው ይብጠለጠላሉ። የቢሾፍቱ ልጆች፣ ነጻ በተባለች ሀገር እየኖሩ በቅኝ ግዛት ጥላ ይተዳደራሉ። የቢሾፍቱ ልጆች በገዛ መንደራቸው አካሉ በማይታይ የቅኝ ግዛት እጅ ይገፋሉ። ሞገስ አይናገርም፤ የሚናገርለት አለ። ልክ የቢሾፍቱ ልጆች ላይ በአንድ ከተማ ውስጥ ሁለት የከተማ ምሥል እንደምናገኘው ሁሉ “የስንብት ቀለማት” ላይም በአዲስ አበባ ውስጥ ሁለት የከተማ ምሥል እንመለከታለን። እንደ ዘድሬክ፣ ሳተርን፣ ከተስፋዬ ወደ አሸናፊ የተቀየሩ የድሎት ምሥሎች እና የእነምትክ ጉልት፣ የእትየ እልልታ የጉርሻ መሸጫ መስኮት ያሉ የእጦት ሥዕል እናገኛለን። መዝሙረ ሄላም ላይም እንዲህ ያለ በአንድ ከተማ ላይ የሁለት ምሥሎች አደባባይ እጀግ ብዙ ቦታ ይገኛል።
በሌላኛው የድኅረ-ቅኝ-ግዛት ኂስ (postcolonial criticism) መዝሙረ ሄላምን ስንመለከት መጀመሪያ ላይ “ፈረንጅ ሲያደንቀኝና ሲገረምብኝ የሰሙ የአገሬ ደነዞች በየተራ “ካላስ የኔ ጎሳ ናት” … እያሉ መሻማት ጀመሩ ትላለች - ሄላም። በኋላ ደግሞ በተነዛባት አጓጉል ወሬ … የሄላምን ጡት ንቀው፣ አንጓጥጠው፣ አባረዋት ሲያበቁ የፈረንጅ የዱቄት ወተትን ይመርጣሉ። ይህ በባሕላዊ ማንነትና በዘመናዊነት መካከል የሚዋልል ማኅበረሰብን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ የድኅረ-ቅኝ-ግዛት አካል ነው። በሌሎቹ የአዳም ሥራዎች ውስጥ ድኅረ-ቅኝ-ግዛት አተያይ በቋንቋና በኪነ-ጥበብ ምርጫ ውስጥ እንዴት እንደሚንፀባረቅ ያሳያል። በመዝሙረ ሄላም ላይ ደግሞ ምዕራባዊው ዓለም ለአገር በቀል መፍትኼ-ሥራይ የሚሰጠው ዋጋ ዝቅተኛ መኾኑንና የኢኮኖሚ ብዝበዛው አሁንም በረቂቅ መንገድ መቀጠሉን ያሳያል። እዚህ ላይ ሥዕለማርያም የተባለችዋን ገጸባሕርይ እና በውጭ ሀገራት የተነዙ ወሬዎችን ስንጨማምር ደግሞ የበለጠ ብዙ ለማለት ያስችላል።
መዝሙረ ሄላም ላይ እጅግ ብዙ ማኅበረሰባዊ ኂስ እናገኛለን። ለአብነት ያህል አንድ ሁለቱን እንቃኝ።
“መዝሙረ ሄላም” ላይ ማኅበረሰቡ በችላ-ባይነት አልያም በኾን ተብሎነት ልጆቹን ምን ያህል ተጠቂ እንዳደረጋቸው የሚያሳይ መልክ ተንጸባርቆበታል ማለት ይቻላል። ጋሽ ክብካብና ዘመናይ ኾን ብለው ቴዲና ሄላም ላይ የሚያደርሱትን፣ ተክለማርያም የወላጁን(የዘሪቱን) ችላ-ባይነት ለአብነት ማቅረብ ይቻላል። ማኅበረሰቡ ልጆችን “የነገ ተስፋዎች” ይላል፤ ነገር ግን ዛሬያቸው ላይ አይሠራም።
ማኅበረሰብ የመማጸኛ ከተማዎችን ወደ ተጨማሪ ግፍ መሥሪያ ቦታዎች እንደሚቀይር በአዳም መጻሕፍት ላይ በብዛት እንመለከታለን። “ይወስዳል መንገድ …” ላይ … “ቀዳዳ” በተሰኘው ታሪክ ላይ ማርታ ለደበበ በምትሰጠው ፍቅር ሳቢያ የሚሠራበትን ግፍ የምታስረሳ ብትኾንም ማኅበረሰቡ ግን ተጨማሪ ግፍ የሚሠራበት መሣሪያ ኾናለች። የስንብት ቀለማት ላይ ምኒልክ ከዚያ ሁሉ እስርና እንግልት በኋላ፣ “በፊያሜታ አርፋለሁ” ብሎ ቤቷ ሲሄድ ተጨማሪ ሕመም በጆሮው በኩል ጭንቅላቱ ላይ ይሻጥበታል። መዝሙረ ሄላም ላይም፣ ሄላም “ሙዚቃዬን ከሕዝብ ጆሮ ያደርስልኛል … ያሳርፈኛል …” ብላ የተመካችበት ምናሴ እንጦሮጦስ ይጨምራታል። ማኅበረሰባችን የመስቀል ተ ሠላጢን ግብር እንዳለው፣ ከላይ አሳልሞ ከታች በአንካሴው ጉድጓድ እንደሚምስ ያሳያል። ይህም የመልእክትን ወጭት ሰብሮ የወጣ ጥበባዊ አጻጻፍ ነው። በፈጣጣው የቀረበ የትችት ኮሶ አይደለም። ድንቅ ነው!
መዝሙረ ሄላም ላይ ከምናገኛቸው ዋና ዋና ገጸባሕርያት የተወሰኑት (አሮን፣ ቃል፣ ምናሴ፣ ሄላም) ላይ መጠነኛ ቅኝት እናድርግ።
auto-fiction ዓይነት አጻጻፍ ባለው የአሮን አተራረክ ውስጥ አሮን “system observer” መኾኑን እንገነዘባለን። ሥርዓቱን ያያል፣ ዘማቹን ያስተውላል፣ ቃለጉባኤ ይይዛል፣ ችግሩን ይመለከታል፣ ይጽፋል። አሮን የተገፋ ታሪክ ድምፅ ነው፤ ንቃት አለው፣ ግን የታሪክ ሂደትን የሚቀይር ኃይል የለውም፤ ስለዚህም ያ ሁሉ የጻፈውን ጽሑፍን ያጣል። የንቃት ችግር የለበትም፤ የማኅበራዊ ንቃት ድምፅነቱን ከዘመነ አባት ጋር ባደረገው ውይይት ውስጥ ተመልክተናል። ግን ደግሞ ይህ ብቻውን የቆመ ነጠላ ነገር ነው፤ ምክንያቱም ማኅበራዊ ተሳትፎ የለበትም። ቃል የተሰኘችው ገጸባሕርይም እንደ አሮን ናት፤ ንቃት ያላት፣ system observer ናት። ማኅበራዊ ንቃት ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ካላገዘው ግንጥል ጌጥ ነው። ቃልና አሮን ንቃት አላቸው፤ ግን ንቃታቸውን ተግባር አላገዘውም፤ ንቃቱን የሚተገብር አደረጃጀት የላቸውም። ስለዚህ ዕጣ-ፈንታቸው ውድቀት ይኾናል። በኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋውን ይህን የድግግሞሽ አዙሪት መዝሙረ ሄላም ላይ ደራሲ አዳም ረታ በሰላ ብዕር አስቀምጧል።
የደራሲና የአርታኢ ትስስር በተንጸባረቀበት በሄላም አተራረክ ውስጥ ምናሴ የተሰኘ ገጸባሕርይ እናገኛለን። ምናሴ የ-false collective consciousness ትእምርት ነው። ምናሴዎች ለሥልጣን ይሠራሉ፣ ራሳቸውን እንደ ነጻ ያስባሉ፤ ነገር ግን የሥርዓቱ የመጠቀሚያ መሣሪያ (system functionary) ናቸው። ምናሴዎች የኦልቪቴዎች ጥይት ናቸው። ምናሴዎች የሔላምዎች ስኬት ሳይኾን የገዛ ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙ የማኅበረሰቡ አካል ናቸው። ምናሴ በሌላ መነጽር ብናየው የመንግሥት ቢሮክራት የመካከለኛው መደብ ውክል ነው። ሀገሩ ከንጉሣዊ ሥርዓት ወደ ወታደራዊ ሥርዓት ቢቀየርም፤ ከወታደራዊ ሥርዓት ወደ ሌላ ሥርዓት ቢለወጥም ምናሴያውያን ግን አይቀየሩም። ሥርዓት ይቀየራል - ምናሴያውያን አይቀየሩም፣ ትእዛዝ ይፈጽማሉ፣ ይከድራሉ። ይህ በኢትዮጵያ ፖለቲካል-ታሪክ ውስጥ የተደጋገመ፣ ግን ደግሞ ያልተስተዋለ እውነት ነው።
ሄላም የወታደር ልጅ ናት፤ እንዲያሳድጋት በአደራ የተሰጠው ቤተሰብ የሚበድላት። የሷ ዓይነት ዕጣ ከደረሰው እንደ ወንድሟ ከምታየው ቴዲ ከሚባል ልጅ ጋር ታድጋለች። መጀመሪያ የሚልዮን፣ የኋላ ኋላ የምናሴ ፍቅረኛ የምትኾን ድምፀ-መረዋ ሴት ናት። ሁሉ ነገሯን ባጣችበት ወቅት ጡቷ ተአምር ያመርታል።
በመዝሙረ ሄላም ላይ የሄላም የጡት ወተት የአንዳች ነገር ውክል ይመስለኛል። ሻዕቢያ ለታጋይ ወጣቶች ማሳደጊያ ፈልጓት ሊሰርቃት መፈለጉ በቀላሉ የሚዘለል ነገር ነው? ወተት እና ጡት በመጀመሪያ እይታ የሕፃናት ትዝታ፣ የእናትነት ምሥል፣ የእምነት እና የጾታ መነሳሳት የተዋሃዱበትም አይደል? ወተት ሕይወት ነው? የመጀመሪያ ምግብ፣ ከእናት ወደ ልጅ የሚፈስም አይደል? በክርስቲያናዊ ምልክት ንጹሕነትን አይወክልም? ወተት ከ“ቅዱስ” ወደ “ሥጋዊ” የሚያስተላልፍ ድልድይ ነው ማለት እንችል ይኾን? የሄላምን ጡት የጠባ ታማሚ ልጅ እንዴት ጤናማ ሊኾን ቻለ? የምን ትእምርት ነው? ሄላም ከብዙ ወንድ ጋር የወጣች እንደመኾኗ ለዚህ ሰናይ ግብር ለምን የሷ ጡት ተመረጠ?
ሌላው፣ መዝሙረ ሄላም ላይ ኦልቬቲን እናገኛታለን። ኦልቬቲ የግራጫ ቃጭልዋ። መዝገቡ ንፋስ መውጫ ሳለ፣ ባልንጀራው ኤልያስ የብልግና ሀሁ ሊያስተምረው እፊቱ ያቆማት ቀይ ሰሌዳ ነበረች ኦልቬቲ። መዝሙረ ሄላም ላይ ምናሴን እና ቤተሰቡን የምታሾር ዐውራ ገጸባሕርይ ኾና ትከሰታለች። መዝሙረ ሄላም እና ግራጫ ቃጭሎች በጋለሞታይቱ በኦልቬቲ ብቻ ሳይኾን በዘመነ እንድርያስ እና በመዝገቡ ዱባለም ይገናኛሉ። ነጋ ዳቦ ጋጋሪውም በ-typological space መዝሙረ ሄላም ላይ እናገኘዋለን።
መዝሙረ ሄላምን ከህላዌነት (Existentialism) አንጻር እንመልከተው። ሄላም ትርጉም በማይሰጥ ዓለም ውስጥ እንዴት እንደምትኖር እናነባለን። የሀገሯ ዳር ድንበር እንዳይነካ አባት ብታዋጣም አሳዳጊዎቿ ግን የወላጅን ፍቅር አዋጥተው አይለግሷትም። ወርቅ አበድራ ጠጠር ትነፈጋለች። ዕቃ ለማገዝ ቤቷ ድረስ ለመጣው ሚልዮን ልቧን ትሰጣለች። ሀና የሸነቆረችውን ክፍተት ለሞላችበት ውለታዋ ክፍያ ይኾን ዘንድ ሚልዮን ለሄላም የወለፈንዴ ቡጢ ያሳርፍባታል። ለሕይወት ትርጉም ለመስጠት ባስ ውስጥ ካገኘችው ሄኖክ ጋር ብትሞክርም የበለጠ የሕይወት ትርጉም ይዛባባታል። የወታደር ልጅ መኾኗ ሄላምነቷን በዜሮ ያባዘዋል። የመጨረሻው ስንብትም ከሄኖክ ጓደኛ አፎት በሚወጣ ሰይፍ መቀላት ይኾናል። ከሄኖክ ጓደኛ ጀርባ የሚውለበለበው ባንዲራ ደግሞ የሄኖክ ሸሚዝ መኾኑ ደግሞ ቁስሉን እንደ አቡሰዲቅ ያደርገዋል። ለሕይወቷ ትልቅ ትርጉም ያለውን የሙዚቃ ሥራዋን፣ “ትርጉም ወዳለው
ነገር ይቀይርልኛል” ብላ በምትተማመንበት በምናሴ ትነጠቃለች። ተአምር በሚያስብለው በጡት ወተት ምክንያት ለሕይወቷ ትርጉም ለመስጠት ትታትራለች። የጡት ወተቷን ምርምር በማድረግ ለትልቅ ዓለምአቀፍ በጎ ተፅዕኖ ታደርጋለች ተብላ የተቆጠረችው ሥዕለማርያም የዓለም አቀፍ መሳለቂያና ትችት ምንጭ ትኾንባታለች። ይህ ሁሉ ትርጉም የሌለው ድግግሞሽ ነው። ይህ ደግሞ በሳርተር የተገለጸውን “existence without essence”-ን ያሳያል።
የህላዌነት መሠረታዊ ሐሳብ ነጻነት ነው፤ ግን ነጻነት ፍርሃትን ይወልዳል። ሄላም ለአሮን ፍቅሯን መናገር ትችላለች፤ ነገር ግን ዝምታን መርጣለች። የግራጫው መዝገቡ፣ የእንጀራ እናቱ የምታደርስበትን በደል እንደሚያውቀው ሁሉ ሄላምም ክብካብና ዘበናይ የሚያደርሱባትን አድሎ ታውቃለች፤ ግን ለረዥም ጊዜ ዝም ብላለች። ሄላም፣ ሙዚቃዋን ካጣች በኋላ ወደ ባንዱ ሄዳ መጋፈጥ ትችላለች፤ ነገር ግን አትሄድም … ይህ በሳርተርኛ bad faith ነው።
የሄላም ምርጫ ዝምታ ኾነ እንጂ ደካማ ናት ማለት አይደለም። “አልተናገርኩም ማለት አላውቀውም ማለት አይደለም” የሚል ዝምታ ነው ያላት። በሌላ ጎኑ ደግሞ ዝምታዋ፣ የለመደችውን ግፍ ከማታውቀው ዐዲስ ግፍ የመምረጥ ኹኔታ ነው። ዐዳዲስ ግፎችን ለመሸሽ በዝምታ አላዋቂነት ዛጎል ውስጥ የመደበቅ ብቃት ነው። የለመደችውን ግፍ የመከላከል አቅም ስላላት ባለመደችው ግፍ እንዳያጠፏት ሠግታ በውስጣዊ ንቃተ ሕሊና የዘየደችው ብልሃት ሊኾን ይችላል። ዝምታዋ የመቆየቷ ምሥጢር ነው። ደበበ ቀዝቃዛ ገለልተኛ ነኝ የሚለው ሰው ለመኖር ሲል ሳይታወቀው ስሜቱን የሚቆጣጠርበት መንገድን ለማስታወስ ነው።
“የስንብት ቀለማት” ገጸባሕርይ የኾነው ዮሴፍም ብዙ ነገር ያውቃል፤ ግን ዝም ይላል … ፊያሜታ ቂል መስሏት ትዘባርቃለች … እሱ ግን “አልተናገርኩም ማለት አላውቀውም ማለት አይደለም” የሚል የዝምታ መልስ ይመልስላታል። እሷ ግን ዝምታው አይገባትም። የ“ቀዳዳ”ው ደበበ እና “የስንብት …” ዮሴፍ ቀዳዳውን አይሞሉትም፤ እያዩት ይኖራሉ። ዶነሮች ጥሩ ፈንድ ሲለቁ ፊያሜታ ፕሮጀክቱን ለአሳምነው ትሰጠውና ዮሴፍን “ምን ዶነሮች እኮ ጠፉ ትለዋለች” … ዝም ይላል፤ ይታዘባል።
ቃል መሣሪያ ነበር፤ በዘመነ ደበበ፣ በዘመነ ዮሴፍ፣ በዘመነ ሄላም እና በዘመነ መዝገቡ ዱባለ ግን ቃል አደገኛ ኾኗል፤ ዝምታ ኹነኛ መጠጊያ ነው … ይህ ከደርግ በኋላ የተፈጠረ “traumatized literary silence” ማሳያ ነው። ስለኾነም ተራኪዎቹ (ደበበ፣ መዝገቡ፣ ዮሴፍ እና ሄላም) ለምን ዝም አሉ ሳይኾን "ዝምታን የሚያመነጭ ሥርዓት ምን ይኾን?" ብለን እንድንጠይቅ ያደርጋል። ግለሰብ ዝም ሲል፤ ሕዝብ በጸጥታ ይዋጣል፤ የዚያኔ የተማከለው ኃይል አፍ ያወጣል።
የአዳምን ዐዲሱን መጽሐፍ "በንባብ ይለቅ" ብለን መርቀናል።
ቢኒያም አቡራ
ሐምሌ 25 / 2018 ዓ.ም

(ዘ-ሐበሻ ዜና ዳሰሳ) የሶማሌላንድ የሀገርነት ጥያቄ እና አለም አቀፍ እውቅና የማግኘት ፍላጎት በዋናነት የተመሰረተው በቅኝ ግዛት ወቅት በነበራት ግልጽ ድንበር፣ እ.ኤ.አ. በ1960 ለተወሰኑ ቀናት አግኝታው በነበረው ነጻነት እና በ1991 ያወጀችው ነጻነት አዲስ የመገንጠል ጥያቄ ሳይሆን የነበረን ሉዓላዊነት የመመለስ እርምጃ ነው በሚለው መከራከሪያ ላይ ነው። እንግሊዝ ከ1884 እስከ 1886 በሰሜን ሶማሊያ ከሚገኙ የጎሳ መሪዎች ጋር ባደረገችው የስምምነት ውል መሰረት የሶማሌላንድን ግዛት የመሰረተች ሲሆን፣ የውጭ ድንበሮቿም ከፈረንሳይ፣ ጣሊያን እና ኢትዮጵያ ጋር በተደረጉ አለም አቀፍ ስምምነቶች የተከለሉ ነበሩ። ሰኔ 26 ቀን 1960 ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነጻነቷን የተቀዳጀችው ሶማሌላንድ፣ ከአምስት ቀናት በኋላ በፈቃደኝነት ከጣሊያን ሶማሊያ ጋር በመዋሃድ የሶማሊያ ሪፐብሊክን መስርታለች። ይሁን እንጂ የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግስት በ1991 መውደቁን ተከትሎ፣ ሶማሌላንድ ከውህደቱ በፊት ወደ ነበራት ነጻነት መመለሷን በማወጅ የ1960ዋን ግዛቷን ይዛለች።
የሶማሌላንድ ዋነኛ የህግ መከራከሪያ አዲስ ነጻ የሚወጡ ሀገራት በቅኝ ግዛት ወቅት የነበራቸውን ድንበር ጠብቀው ሊቀጥሉ ይገባል የሚለው መርህ ነው። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በ1964ቱ የካይሮ ውሳኔው እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት የመመስረቻ ሰነዱ ላይ አባል ሀገራት በነጻነት ጊዜ የነበራቸውን ድንበር ሊያከብሩ እንደሚገባ አስፍረዋል። በመሆኑም ሶማሌላንድ አለም አቀፍ እውቅና ማግኘቷ የቅኝ ግዛት ድንበርን ከመጠበቅ ባለፈ አዲስ ድንበር የማካለል ስራ አይደለም በማለት ትከራከራለች። አቋሟም ከዚህ ቀደም ሉዓላዊ ሀገር እንደነበረች፣ የ1960ውን ውህደት በራሷ ፈቃድ እንደፈጸመች እና የ1991ዱ እርምጃዋም የከሸፈን ውህደት ማፍረስ እንጂ አዲስ ግዛትን ከሶማሊያ መገንጠል አይደለም በሚሉ ሶስት ምሶሶዎች ላይ የቆመ ነው። ይህ አቀራረብ ሶማሌላንድን ምንም አይነት የቅኝ ግዛት ወይም አለም አቀፍ ድንበር መሰረት ከሌላቸው የመገንጠል ጥያቄዎች የተለየች ያደርጋታል።
የሶማሌላንድን ሁኔታ ከኤርትራ ጋር ማነጻጸር የጉዳዩን የዲፕሎማሲ ውስብስብነት በደንብ ያሳያል። ሁለቱም ግዛቶች የተለየ የቅኝ ግዛት ታሪክ፣ ከማዕከላዊ መንግስት ጋር የተደረገ የትጥቅ ትግል እና ከ1991 በኋላ ውጤታማ የሆነ ራስን በራስ የማስተዳደር ልምድ አላቸው። ይሁን እንጂ የኤርትራ የነጻነት ጥያቄ የኢትዮጵያን የሽግግር መንግስት ፈቃድ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህዝበ ውሳኔ ታዛቢነትን በማግኘቱ ፈጣን አለም አቀፍ እውቅናን ሊያጎናጽፋት ችሏል። በሶማሌላንድ በኩል ግን ጠንካራ ተቋማትን መገንባት እና ህዝበ ውሳኔ ማካሄድ ብትችልም፣ ከሶማሊያ መንግስት የተገኘ ስምምነትም ሆነ እንደ ኤርትራው አይነት አለም አቀፍ ድጋፍ ባለማግኘቷ የዲፕሎማሲ እውቅናው ሊዘገይባት ችሏል። ይህ የሚያሳየው ውጤታማ አስተዳደር እና ታሪካዊ ድንበር መኖር ብቻውን በቂ እንዳልሆነ እና እውቅና ማግኘት በስምምነት፣ በቀጠናዊ ፖለቲካ እና በዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ላይ በእጅጉ የተመሰረተ መሆኑን ነው።
የአፍሪካ ህብረት በ2005 ወደ አካባቢው አጣሪ ቡድን ልኮ የሶማሌላንድ ጥያቄ በቅኝ ግዛት ድንበር እና በቀድሞ ነጻነቷ ላይ የተመሰረተ ታሪካዊ መነሻ እንዳለው ቢገነዘብም፣ አሁንም ድረስ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ቅድሚያ መስጠትን መርጧል። በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ሶማሌላንድን እውቅና መስጠት በሌሎች አካባቢዎች የመገንጠል ጥያቄዎችን ሊያነሳሳ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። ሶማሌላንድ በበኩሏ የድሮውን ድንበር መመለስ እንጂ አዲስ ድንበር መፍጠር አይደለም ስትል ምላሽ ትሰጣለች።
ሶማሌላንድ በቅኝ ግዛት ድንበር እና በቀድሞ ነጻነት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ የህግ መከራከሪያ ብታቀርብም፣ የኤርትራን ተሞክሮ ስንመለከት የህግ ትንታኔ ብቻውን እውቅናን እንደማያመጣ መገንዘብ ይቻላል። ሶማሌላንድ ከሶማሊያ ጋር የደረሰችበት ምንም አይነት ስምምነት ባለመኖሩ፣ የእውቅና ጉዳይ አሁንም ድረስ አለም አቀፍ ተቋማት የድሮዋን ሉዓላዊ ሀገር ዳግም መመለስ አድርገው ይቀበሉታል ወይስ የሶማሊያን የግዛት አንድነት የሚፈታተን ድርጊት አድርገው ይቆጥሩታል የሚለው ጉዳይ የፈተና መድረክ ሆኖ ቀጥሏል።

የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽና ቀጣናዊ ፋይዳው
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ባለፉት አስርት ዓመታት በሰላም ማስከበር፣ በግጭት አፈታት፣ በኤሌክትሪክ ኃይል ወጪ ንግድ፣ በቀጣናዊ ትስስር እና በንግድ ትብብር ረገድ ያበረከተችው አስተዋጽኦ ለጎረቤቶቿ ብሎም ለቀጣናው የምትሰጠውን ከፍ ያለ ትኩረት ያሳያል።
ኢትዮጵያ በታሪኳ የትኛውንም ጎረቤት ሀገር ወርራ አታውቅም፡፡ ከጎረቤቶቿ ጋር ያላት ግንኙነት ሰላማዊና በትብብር ላይ የተመሰረተ ሆኖ ቆይቷል፡፡
ጎረቤቶቿ ሰላም በራቃቸው ጊዜ ሁሉ፣ ሰላም ለማስከበር ቀድማ በመገኘት ትታወቃለች፡፡ ይህንንም በደቡብ ሱዳን፣ በሱዳን፣ በሶማሊያ እንዲሁም ከጎረቤቶቿ ራቅ ብላም በላይቤሪያ፣ በሩዋንዳ፣ በኮንጎ እና በሴራሊዮን በተግባር አስመስክራለች፡፡
በአህጉር ደረጃ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ቀንበር ሲማቅቁ የነበሩ አፍሪካውያን ወንድም እህቶች ነጻ ለመውጣት የሚያደርጉትን ጥረት በስልጠና፣ በሎጂስቲክስና በዲፕሎማሲ መስክ ጭምር መደገፏ አሌ የማይባል ሃቅ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ዛሬም የልማት ትሩፋቷን ለብቻዋ ዕድገትና ለውጥ የምትጠቀም ሀገር አይደለችም፡፡ ይልቁንም ልማቷን እና ለውጧን በማጋራት እና ለጎረቤቶቿ አብሮ መለወጥ እየሰራች ትገኛለች፡፡
በአፍሪካ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል አምራች ከሆኑ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ፤ ለጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ኤሌክትሪክ እየላከች ነው።
ይህ በአካባቢው የኢንዱስትሪ ልማት፣ የከተማ እድገት እና የህዝብ ኑሮ መሻሻል ላይ ቀጥተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ ነው።
በንግድ ረገድም ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና እና የአፍሪካ ህብረት "አጀንዳ 2063" የሚያስቀምጧቸውን የክልላዊ ውህደት ግቦች ለማሳካት የኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች፣ የድንበር ንግድ ማዕከላት እና የትራንስፖርት ኮሪደሮችን በማስፋፋት በቀጣናዊ ትስስር ማደግና መጠናከር ላይ ግዙፍ ኢንቨስትመንት እያካሄደች ነው።
ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ ሰላምና ደህንነት፣ እድገትና ልማት አበክራ የሰራቻቸው ስራዎች ለቀጣናውና ለሀገራቱ ያላትን አዎንታዊ ሚና በግልፅ ያሳያል። ሀገሪቱ የባህር በር ጥያቄዋ ምላሽ ሲያገኝ ይህ ቀጣናዊ ገንቢ ሚናዋ በምን ያህል መጠን ሊያድግና ሊባዛ እንደሚችል ለመገመት አያዳግትም፡፡
በታሪክ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ህዝብ ህጋዊ ስልጣን በሌለው አካል ህጋዊ የባሕር በር ባለቤትነቷን እንድታጣ ተደርጓል፡፡ የመደመር መንግሥት የተፈጸመውን ኢፍትሃዊና ታሪካዊ በደል በሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ የማስመለስ ጥያቄ አቅርቦ የበርካታ ሃያላን ሀገራትን ድጋፍ አግኝቷል፡፡ ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ ካለው ኢኮኖሚዋና የህዝብ ቁጥሯ አንጻር የባሕር በር አማራጭ ሊኖራት ይገባል።
በ60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የባሕር በር እያለ ኢትዮጵያ ተዘግታ ትኑር የሚል ኢፍትሐዊነት ተቀባይነት የለውም።
የባሕር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ የንግድ መውጫ መግቢያ ብቻ ሳይሆን፤ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የብሔራዊ ደህንነት እና የጂኦፖለቲካ ስትራቴጂ ቁልፍ ጥያቄ በመሆኑ ጥያቄዋ መልስ እስኪያገኝ አበክራ ትሰራለች፡፡
ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘቷ ጥቅሙ ለእርሷ ብቻ አይደለም። በአፍሪካ ቀንድ እና በጎረቤት ሀገራት ዘንድ ከፍ ያለ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የመፍጠር ሚና ይኖረዋል፡፡
በአካባቢው የንግድ ኮሪደሮች ስለሚፈጠሩ የወደብ አገልግሎት እንዲስፋፋ፣ የተለያዩ የመሰረተ ልማት አውታሮች እንዲገነቡ በማድረግ የንግድ ትስስርና አዳዲስ የስራ ዕድሎች ለመፍጠር ያስችላል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከታዳሽ ኃይል የምታመነጨው ኤሌክትሪክ ለቀጣናው በበቂ ሁኔታ ማቅረቧ ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋፋትና የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ ይረዳል።
ከዚህ ባሻገር የቀጣናዊ ሰላምና ጸጥታን በተመለከተ የጋራ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እያደገ ሲመጣ በሀገራት መካከል ከግጭት ይልቅ ትብብር እንዲጨምር ያደርጋል። ሀገራት በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በመሠረተ ልማት በተጠናከረ ሁኔታ ሲተሳሰሩ ሰላምን የመጠበቅ ፍላጎታቸውም በዛው ልክ ይጨምራል።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት የአፍሪካ ህብረት "አጀንዳ 2063" የሚጠይቀውን ቀጣናዊ ትስስር ለማጠናከር፣ የነፃ ንግድ ቀጣና ለመመስረት እና የመሠረተ ልማት ትስስርን ለማሳካት ጠንካራ መሠረት ለመጣል ያግዛል።
በመሆኑም የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ አፋጣኝ መልስ እንዲያገኝ ለማድረግ ሀገራት፣ ዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊ እና ቀጣናዊ ተቋማት ድጋፋቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል፡፡
በቴዎድሮስ ሳህለ

3 months ago
ፓን-አፍሪካዊ ኃይል የሆነው የመደመር ትውልድ
*******************
ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ለመላው ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ተምሳሌት በመሆን የፓን-አፍሪካኒዝም እሳቤ ተፈጥሯዊ ጉልበት ሆና ቆይታለች።
አውሮፓውያን አህጉሪቱን ለመቀራመት ሲነሡ፣ ኢትዮጵያ በከፍታ ላይ የቆመች እና ሥልጣኔን ያጣጣመች ዕድሜ ጠገብ ሀገር ናት።
ታሪካዊው የዓድዋ ድል እስከ አፍንጫው ታጥቆ የመጣውን የቀኝ ገዢ ኃይል በማንበርከክ የነጭ የበላይነትን እሳቤ ገልብጧል፤ የዓድዋ ድል ለፓን-አፍሪካኒዝም ንቅናቄ አዲስ ጉልበትና የይቻላል መንፈስን አጎናጽፏል።
የትናንቱ የፓን-አፍሪካኒዝም ትግል ማዕከል የፖለቲካ ነጻነት ሲሆን፣ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ዋነኛ ትግል የኢኮኖሚ ነጻነትን ማረጋገጥ ነው።
ታላቁ ፓን-አፍሪካኒስት ጁሊየስ ኔሬሬ እንዳስገነዘቡት፣ በመጀመሪያው የአፍሪካ ቅርምት ጎሳን ከጎሳ ያጋጨው የውጭ ኃይል፣ አሁን ደግሞ ሀገርን ከሀገር በማጋጨት አህጉሪቱን ደካማና የተከፋፈለች ለማድረግ ይጥራል። በእርግጥም በመከፋፈል ውስጥ የሚገኝ ክብርም ሆነ ታላቅነት የለም። ከተከፋፈልን ደካሞች እንሆናለን፤ ከተባበርን ግን በእኛ ላይ የሚመጡትን የጣልቃ ገብነት ኃይሎች አሳፍረን መመለስ እንችላለን።
በዚህ ታሪካዊ መጋጠሚያ ላይ፣ የኢትዮጵያ የመደመር ትውልድ ከራሱ አልፎ ቀጣናውን በፓን-አፍሪካዊ መንፈስ ለማስተሳሰር በጽናት ቆሟል። አፍሪካውያን የማይነጣጠሉ እና ዕጣ ፈንታቸው የተሣሠረ፣ የቀኝ ግዛት ድንበርን የሚሻገር የጠበቀ ወንድማማችነት ያላቸው ሕዝቦች ናቸው።
ለአብነት ያህል፣ ፉላኒ ጎሳ ከ19 በላይ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ሲገኝ፣ አካን በጋና እና አይቮሪኮስት፣ ኦሮሞ በኢትዮጵያ እና ኬንያ፣ አፋር በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ጅቡቲ፣ እንዲሁም ሶማሌ በቀጣናው የተለያዩ ሀገራት ተሰራጭቶ ይገኛል።
እ.አ.አ በ1902 በቅኝ ገዢዎች በተደረገ የድንበር ከለላ የበርታ ብሔረሰብ በሁለት ተከፍሎ በሱዳን እና በኢትዮጵያ እንዲኖር ተገዷል። ይህን ሐቅ ጠንቅቆ የተረዳው የመደመር ትውልድ፣ እነዚህን ሕዝቦች በፖለቲካ አጥር ማጠር እንደማይቻል በማመን፣ አፍሪካን እንደ አንድ ሕዝብ በማስተሣሠር የማበልጸግ ኃላፊነትን ወስዷል።
ኢትዮጵያ ይህንን የአብሮነት እና የመደመር እሳቤ በተግባር ለማሳየት የሰፋፊ መሠረተ ልማቶችን ትሥሥር እያከናወነች ትገኛለች። የአፍሪካ ኅብረትን አጀንዳ 2063 ለማሳካት እና ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውህደትን እውን ለማድረግ፣ ለጎረቤት ሀገራት ለምሳሌ ለጅቡቲ፣ ለሱዳን እና ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ የምጣኔ ሀብት ትሥሥር እያፋጠነች ነው።
ከኬንያ ጋር የተዘረጋው የመንገድ መሠረተ ልማት፣ እንዲሁም በውኃ ተፋሰሶች ላይ የሚሠሩ ታላላቅ ግድቦች የዚሁ ታላቅ ፓን-አፍሪካዊ አሰባሳቢ ትሥሥር አካላት ናቸው።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ባለፉት ሦስት ዐሥርት ዓመታት በሩዋንዳ፣ ላይቤሪያ፣ ሱዳን፣ ብሩንዲ እና ሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮውን በብቃት በመወጣት አህጉራዊ እና ቀጣናዊ መረጋጋትን አረጋግጧል። ይህም ኢትዮጵያ ለፓን-አፍሪካኒዝም ያላትን የተግባር ቁርጠኝነት ያረጋግጣል።
የ21ኛው ክፍለ ዘመን ፓን-አፍሪካኒዝም አፍሪካውያን በቅኝ ገዢዎች የተሰመሩላቸውን የፖለቲካ ድንበሮች በማንሣት፣ አህጉሪቱን ወደ አንድ የጋራ ነጻ ንግድ ቀጣና በማምራት የኢኮኖሚ ነጻነታቸውን የሚያረጋግጡበት ወሳኝ ምዕራፍ ነው።
የአፍሪካ ሕዝብ ብዛት ከ1.4 ቢሊዮን አልፎ ወደፊት በእጥፍ እንደሚያድግ ሲገመት፣ ይህ ታላቅ አምራች ኃይል እና ሰፊ ገበያ ትልቅ የመልማት አቅም ነው። በተጨማሪም አህጉሪቱ የተፈጥሮ ማዕድን፣ ነዳጅ፣ የውኃ ሀብት እና ሊታረስ የሚችል ሰፊ ለም መሬት፣ እንዲሁም የተለያዩ ማዕድናትን ጨምሮ የተትረፈረፈ ጸጋ ባለቤት ናት።
ከምዕራባውያን ገበያ ጥገኝነት ተላቅቀን ይህንን እምቅ ሀብት በማቀናጀት እና የምናመርተውን ምርት እርስ በርስ ብንለዋወጥ ታላቅ ስኬትን እንጎናጸፋለን።
ኢትዮጵያ ትናንት የፖለቲካ ነፃነት ዓርማ እንደነበረች ሁሉ፣ ዛሬ ደግሞ የመደመር ትውልድን በማስተባበር በቀጣናዊ ሰላም፣ በመሠረተ ልማት ዝርጋታ እና በአህጉራዊ ውህደት የላቀ ሚና በመጫወት ላይ ያለች ጽኑ ፓን-አፍሪካዊ ኃይል ናት።
አዲሱ ትውልድ አፍሪካውያን በመተባበር እና በወንድማማችነት ላይ የተመሠረተ ጠንካራ ኅብረት እንዲፈጥሩ በጽናት የቆመ ኃይል ሆኖ ይቀጥላል፤ ምክንያቱም ለአፍሪካውያን ችግር ብቸኛው መፍትሔ ያለው በራሳቸው በአፍሪካውያን እጅ በመሆኑ ነው።
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
#ethiopia #ebc #hornofafrica #medemer #medemergeneration #diplomacy

4 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሜክሲኮ የአለም ዋንጫን ደህንነት ለመጠበቅ በስታዲየሞች የውሻ ሮቦቶችን አሰማርታለች፡፡ በሜክሲኮ እየተካሄደ ባለው የፊፋ አለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ በስታዲየሞች የደህንነት ጥበቃ እያደረጉ የሚገኙት የውሻ ሮቦቶች የበርካቶችን ቀልብ ስበዋል፡፡
እነዚህ ሮቦቶች ኤችዲ ካሜራ የተገጠመላቸውና በርካታ ህዝብ ባለበት ቦታ ላይ ቅኝት እንዲያደርጉ በሚል ዲዛይን የተደረጉ ናቸው፡፡ ‹‹ኬ6 ኤክስ›› የሚል መጠሪያ ያላቸው እነዚህ ሮቦቶች በጨለማም ማየት የሚችሉ ሲሆኑ ያዩትን ነገር ሁሉ በቀጥታ ለማእከላዊ ትእዛዝ ማእከል ያስተላልፋሉ፡፡ እንዲሁም በውስጣቸው በተገጠመው ስፒከር አማካኝነት ትእዛዝ ይሰጣሉ፡፡
ማለትም ለሰዎች ‹‹ወደኋላ ተመለስ፣ ውጣ ወይንም የያዝከውን ጣል›› የሚል መልእክት የሚናገሩ ናቸው፡፡ ከመጠናቸው አኳያ ፖሊሶች መድረስ ወደማይችሉባቸው ቦታዎች በመሄድም ፍተሻዎችን ያከናውናሉ፡፡ ከዚህ ቀደም በኮንካካፍ ሻምፒዮን ውድድር ወቅት ተሰማርተው ብቃታቸውን ያስመሰከሩም ናቸው፡፡ ለእነዚህ ሮቦቶች መከሰት ዋነኛ ምክንያት የሆነው ባለፈው አመት በሞንቴሪ አካባቢ በቅኝት ላይ የነበሩ 2 ፖሊሶች መገደል ነው፡፡ የከተማው ከንቲባ ሄክቶር ጋርሺያ በስራ ላይ ያሉ ፖሊሶች የሚደርስባቸውን ከአደጋ ለመቀነስ በቴክኖሎጂ እንዲታገዙ የሚል መመሪያ ያወጣሉ፡፡
ይህንን መመሪያ ተከትሎ አራት እግር ያላቸው ሮቦቶች በከተማው ውስጥ ሊሰማሩ ችለዋል፡፡ እነዚህ 4 ሮቦቶች ከተማውን በአጠቃላይ 145,000 ዶላር ያስወጡት ቢሆንም አሁን ግን ያለምንም ጦር መሳሪያና የፖሊሶች አካላዊ ጉዳት አደገኛ ወደሆነ ቦታ ጭምር እየገቡ ጥበቃ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ እንደዚህ አይነት የጥበቃ ስርአቶች በሲንጋፖር፣ ጣሊያን፣ ኔዘርላንድና ሌሎችም አገራት ስራ ላይ መዋላቸው የሚታወቅ ነው፡፡ የሞንቴሪ ከተማ አስተዳደር ለአለም ዋንጫ ውድድሮች ደህንነት እነዚህን የውሻ ሮቦቶች ብቻ አላሰማራም፡፡ ሁለት ብላክ ሀውክ ሄሊኮፕተሮች፣ 90 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች፣ ድሮኖችና የፀረ ድሮን ቴክኖሎጂ 24 ሰአት ሙሉ ከተማውን የሚቃኙና የሚጠብቁ ሲሆን እነዚህን የሚቆጣጠር አንድ ማእከላዊ ማእከልም ተቋቁሟል፡፡

"ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ሳትገዛም ድሃ ናት፤ በፈረንሳይ የተገዛችው ቬትናም ግን ዛሬ በልጽጋለች"
📌ቁጣን የቀሰቀሰው የ x ገጽ ልጥፍ
#ethiopia | የዓለማችን ቢሊየነር ኢሎን ማስክ እና ሴኔጋላዊቷ ስራ ፈጣሪ ማጋቴ ዋድ ሰሞኑን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ያራገቡት አወዛጋቢ ትርክት፣ በአፍሪካውያን እና በታሪክ ምሁራን ዘንድ ትልቅ ቁጣን ቀስቅሷል። ማጋቴ ዋድ "ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ሳትገዛም ድሃ ናት፤ በፈረንሳይ የተገዛችው ቬትናም ግን ዛሬ በልጽጋለች" በማለት የቅኝ ግዛትን አስከፊ ታሪክ ለማቃለል የሞከረች ሲሆን፣ ኢሎን ማስክም ለዚህ ታሪካዊ ስህተት አጋርነቱን አሳይቷል። ይሁን እንጂ ይህ መከራከሪያ ሆን ተብሎ የተመረጡ መረጃዎችን ብቻ በመጠቀም የተነዛ፣ ሚዛናዊነት የጎደለው እና የጥቁር ሕዝቦችን የነጻነት ተምሳሌት የሆነችውን ኢትዮጵያን ክብረ-ታሪክ ያጣጣለ ትልቅ የታሪክ ክህደት ነው።
የማጋቴ ዋድ ትልቁ የታሪክ ስህተት እና ማጭበርበር የሚጋለጠው፣ በእሷው አመክንዮ ውስጥ ያሉትን ግልጽ ተቃርኖዎች ስንመለከት ነው። ቬትናምን እንደ ብቸኛ የስኬት ማሳያ አድርጋ ስታቀርብ፣ ልክ እንደ ቬትናም በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ስር የነበሩ ነገር ግን ዛሬም ድረስ ከኢትዮጵያ በታች በሆነ የድህነት አዘቅት ውስጥ የሚገኙትን በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ሆን ብላ ዘንግታዋለች።
ኒጀር፣ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ቻድ፣ ማዳጋስካር እና ቡርኪና ፋሶን የመሳሰሉ ሀገራት ለዘመናት በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ስር ቆይተዋል። ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ በነፍስ ወከፍ ገቢያቸውም (GDP per capita) ሆነ በሰብዓዊ ልማት ጠቋሚያቸው (HDI) ከኢትዮጵያ በእጅጉ ያነሱ እና በዓለም መጨረሻ ላይ የሚገኙ ናቸው። ቅኝ ግዛት የብልጽግና እና የሰለጠነ መዋቅር ምንጭ ቢሆን ኖሮ፣ እነዚህ የፈረንሳይ ቅኝ ግዛቶች ዛሬ ለምን የዓለም አቀፍ የድህነት መለኪያ ሆኑ? አሁንም ድረስ ፈረንሳይ በዘረጋችው የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም መዋቅር (በተለይም በCFA ፍራንክ የገንዘብ ሥርዓት) የራሳቸውን ሀብት ማስተዳደር አቅቷቸው በከፍተኛ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ ይገኛሉ። ይህ ሐቅ "ቅኝ ግዛት የድህነት ምክንያት አይደለም" የሚለውን የማጋቴን መከራከሪያ ከመሠረቱ የሚያፈርስ ነው።
ቬትናም ዛሬ ላለችበት የኢኮኖሚ ከፍታ የበቃችው በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት በረከት ሳይሆን፣ እንዲያውም የፈረንሳይን እና የአሜሪካን አውዳሚ ጦርነቶች በከፍተኛ መስዋዕትነት አሸንፋ ከወጣች በኋላ ነው። ሀገሪቱ ከጦርነቱ ፍርስራሽ ተነስታ ያደገችው በ1986 (እ.ኤ.አ.) ተግባራዊ ባደረገችው 'ዶይ ሞይ' (Doi Moi) የተሰኘው የውስጥ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የእስያ ቀጠና በፈጠረላት ምቹ የንግድ ትስስር እንጂ የቅኝ ገዥዎች ትሩፋት አይደለም። የቬትናምን የላብ እና የደም ውጤት ለቅኝ ገዥዎች ታሪክ ማሳመሪያ ማድረግ ፍጹም ስህተት ነው።
ማጋቴ ዋድ የኢትዮጵያን ነጻነት ከድህነት ጋር አያይዛ ለማቅረብ መሞከሯ፣ የሀገሪቱን ታላቅነት እና የገጠማትን ውስብስብ ፈተና ካለመረዳት የመነጨ ነው። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ምድር የነጭ የበላይነትን በአድዋ ተራሮች ላይ በመቅበር፣ ለመላው ጥቁር ሕዝብ የነጻነት እና የፓን-አፍሪካኒዝም ፋና ወጊ የሆነች ታላቅ ሀገር ናት። በቅኝ አለመገዛቷ የኩራቷ እንጂ የድህነቷ መንስኤ አይደለም።
የኢትዮጵያ ዘመናዊ የኢኮኖሚ ፈተናዎች የመነጩት ከነጻነቷ ሳይሆን፣ በዙሪያዋ ከነበሩት የቅኝ ገዥ ኃይሎች ሴራ እና ከውስጣዊ ፖለቲካዊ ውጣ ውረዶች ነው። መላው አፍሪካ በቅኝ ግዛት ሲከፋፈል፣ ነጻዋ ኢትዮጵያ በቅኝ ገዥዎች ተከባ የባህር በር እንድታጣ እና ከዓለም አቀፍ ንግድ እንድትገለል ተደርጋለች። በቅርቡ ታሪክም በቀዝቃዛው ጦርነት የጂኦፖለቲካዊ ሽኩቻ ሰለባ በመሆን፣ እንዲሁም ደርግ በተከተለው አውዳሚ የማርክሲስት የኢኮኖሚ ሥርዓት እና በተራዘሙ የእርስ በርስ ጦርነቶች ምክንያት ኢኮኖሚዋ ክፉኛ ተጎድቷል። እነዚህ ሁሉ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ ኢትዮጵያ የራሷን ቋንቋ፣ ባህል፣ የቀን አቆጣጠር እና ሀገራዊ ኩራት ጠብቃ ያቆየች፤ ዛሬም በአፍሪካ ቀንድ ትልቅ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆን የቻለች ሀገር ናት።
የአፍሪካን ወቅታዊ ችግሮች ለመፍታት ራስን መመርመር፣ ሙስናን መዋጋት እና የተሻለ አስተዳደር መገንባት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ነገር ግን ይህንን ለማድረግ ሲባል የቅኝ ግዛትን አስከፊነት ማጠብ እና የኢትዮጵያን ደማቅ የነጻነት ታሪክ ማጠልሸት አይቻልም። ኢትዮጵያ ምንም እንኳን የኢኮኖሚ ፈተናዎች ቢኖሩባትም፣ የማንም ቅኝ ገዥ ሎሌ ሳትሆን የራሷን ዕድል በራሷ የወሰነች የአፍሪካ የቁርጥ ቀን ልጅ ናት። አህጉሪቱ ወደፊት መራመድ ያለባት የቅኝ ግዛትን ጠባሳ በማስተባበል ሳይሆን፣ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ የራስን ማንነት አጥብቆ በመያዝ እና ጠንካራ ኢኮኖሚን በነጻነት ላይ በመገንባት ሊሆን ይገባል።
#ዘሐበሻ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

የዓለማችን ቢሊየነር ኢሎን ማስክ እና ሴኔጋላዊቷ ስራ ፈጣሪ ማጋቴ ዋድ ሰሞኑን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ያራገቡት አወዛጋቢ ትርክት፣ በአፍሪካውያን እና በታሪክ ምሁራን ዘንድ ትልቅ ቁጣን ቀስቅሷል። ማጋቴ ዋድ "ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ሳትገዛም ድሃ ናት፤ በፈረንሳይ የተገዛችው ቬትናም ግን ዛሬ በልጽጋለች" በማለት የቅኝ ግዛትን አስከፊ ታሪክ ለማቃለል የሞከረች ሲሆን፣ ኢሎን ማስክም ለዚህ ታሪካዊ ስህተት አጋርነቱን አሳይቷል። ይሁን እንጂ ይህ መከራከሪያ ሆን ተብሎ የተመረጡ መረጃዎችን ብቻ በመጠቀም የተነዛ፣ ሚዛናዊነት የጎደለው እና የጥቁር ሕዝቦችን የነጻነት ተምሳሌት የሆነችውን ኢትዮጵያን ክብረ-ታሪክ ያጣጣለ ትልቅ የታሪክ ክህደት ነው።
የማጋቴ ዋድ ትልቁ የታሪክ ስህተት እና ማጭበርበር የሚጋለጠው፣ በእሷው አመክንዮ ውስጥ ያሉትን ግልጽ ተቃርኖዎች ስንመለከት ነው። ቬትናምን እንደ ብቸኛ የስኬት ማሳያ አድርጋ ስታቀርብ፣ ልክ እንደ ቬትናም በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ስር የነበሩ ነገር ግን ዛሬም ድረስ ከኢትዮጵያ በታች በሆነ የድህነት አዘቅት ውስጥ የሚገኙትን በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ሆን ብላ ዘንግታዋለች።
ኒጀር፣ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ቻድ፣ ማዳጋስካር እና ቡርኪና ፋሶን የመሳሰሉ ሀገራት ለዘመናት በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ስር ቆይተዋል። ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ በነፍስ ወከፍ ገቢያቸውም (GDP per capita) ሆነ በሰብዓዊ ልማት ጠቋሚያቸው (HDI) ከኢትዮጵያ በእጅጉ ያነሱ እና በዓለም መጨረሻ ላይ የሚገኙ ናቸው። ቅኝ ግዛት የብልጽግና እና የሰለጠነ መዋቅር ምንጭ ቢሆን ኖሮ፣ እነዚህ የፈረንሳይ ቅኝ ግዛቶች ዛሬ ለምን የዓለም አቀፍ የድህነት መለኪያ ሆኑ? አሁንም ድረስ ፈረንሳይ በዘረጋችው የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም መዋቅር (በተለይም በCFA ፍራንክ የገንዘብ ሥርዓት) የራሳቸውን ሀብት ማስተዳደር አቅቷቸው በከፍተኛ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ ይገኛሉ። ይህ ሐቅ "ቅኝ ግዛት የድህነት ምክንያት አይደለም" የሚለውን የማጋቴን መከራከሪያ ከመሠረቱ የሚያፈርስ ነው።
ቬትናም ዛሬ ላለችበት የኢኮኖሚ ከፍታ የበቃችው በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት በረከት ሳይሆን፣ እንዲያውም የፈረንሳይን እና የአሜሪካን አውዳሚ ጦርነቶች በከፍተኛ መስዋዕትነት አሸንፋ ከወጣች በኋላ ነው። ሀገሪቱ ከጦርነቱ ፍርስራሽ ተነስታ ያደገችው በ1986 (እ.ኤ.አ.) ተግባራዊ ባደረገችው 'ዶይ ሞይ' (Doi Moi) የተሰኘው የውስጥ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የእስያ ቀጠና በፈጠረላት ምቹ የንግድ ትስስር እንጂ የቅኝ ገዥዎች ትሩፋት አይደለም። የቬትናምን የላብ እና የደም ውጤት ለቅኝ ገዥዎች ታሪክ ማሳመሪያ ማድረግ ፍጹም ስህተት ነው።
ማጋቴ ዋድ የኢትዮጵያን ነጻነት ከድህነት ጋር አያይዛ ለማቅረብ መሞከሯ፣ የሀገሪቱን ታላቅነት እና የገጠማትን ውስብስብ ፈተና ካለመረዳት የመነጨ ነው። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ምድር የነጭ የበላይነትን በአድዋ ተራሮች ላይ በመቅበር፣ ለመላው ጥቁር ሕዝብ የነጻነት እና የፓን-አፍሪካኒዝም ፋና ወጊ የሆነች ታላቅ ሀገር ናት። በቅኝ አለመገዛቷ የኩራቷ እንጂ የድህነቷ መንስኤ አይደለም።
የኢትዮጵያ ዘመናዊ የኢኮኖሚ ፈተናዎች የመነጩት ከነጻነቷ ሳይሆን፣ በዙሪያዋ ከነበሩት የቅኝ ገዥ ኃይሎች ሴራ እና ከውስጣዊ ፖለቲካዊ ውጣ ውረዶች ነው። მላው አፍሪካ በቅኝ ግዛት ሲከፋፈል፣ ነጻዋ ኢትዮጵያ በቅኝ ገዥዎች ተከባ የባህር በር እንድታጣ እና ከዓለም አቀፍ ንግድ እንድትገለል ተደርጋለች። በቅርቡ ታሪክም በቀዝቃዛው ጦርነት የጂኦፖለቲካዊ ሽኩቻ ሰለባ በመሆን፣ እንዲሁም ደርግ በተከተለው አውዳሚ የማርክሲስት የኢኮኖሚ ሥርዓት እና በተራዘሙ የእርስ በርስ ጦርነቶች ምክንያት ኢኮኖሚዋ ክፉኛ ተጎድቷል። እነዚህ ሁሉ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ ኢትዮጵያ የራሷን ቋንቋ፣ ባህል፣ የቀን አቆጣጠር እና ሀገራዊ ኩራት ጠብቃ ያቆየች፤ ዛሬም በአፍሪካ ቀንድ ትልቅ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆን የቻለች ሀገር ናት።
የአፍሪካን ወቅታዊ ችግሮች ለመፍታት ራስን መመርመር፣ ሙስናን መዋጋት እና የተሻለ አስተዳደር መገንባት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ነገር ግን ይህንን ለማድረግ ሲባል የቅኝ ግዛትን አስከፊነት ማጠብ እና የኢትዮጵያን ደማቅ የነጻነት ታሪክ ማጠልሸት አይቻልም። ኢትዮጵያ ምንም እንኳን የኢኮኖሚ ፈተናዎች ቢኖሩባትም፣ የማንም ቅኝ ገዥ ሎሌ ሳትሆን የራሷን ዕድል በራሷ የወሰነች የአፍሪካ የቁርጥ ቀን ልጅ ናት። አህጉሪቱ ወደፊት መራመድ ያለባት የቅኝ ግዛትን ጠባሳ በማስተባበል ሳይሆን፣ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ የራስን ማንነት አጥብቆ በመያዝ እና ጠንካራ ኢኮኖሚን በነጻነት ላይ በመገንባት ሊሆን ይገባል።
የማጋቴ ዋድ ትልቁ የታሪክ ስህተት እና ማጭበርበር የሚጋለጠው፣ በእሷው አመክንዮ ውስጥ ያሉትን ግልጽ ተቃርኖዎች ስንመለከት ነው። ቬትናምን እንደ ብቸኛ የስኬት ማሳያ አድርጋ ስታቀርብ፣ ልክ እንደ ቬትናም በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ስር የነበሩ ነገር ግን ዛሬም ድረስ ከኢትዮጵያ በታች በሆነ የድህነት አዘቅት ውስጥ የሚገኙትን በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ሆን ብላ ዘንግታዋለች።
ኒጀር፣ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ቻድ፣ ማዳጋስካር እና ቡርኪና ፋሶን የመሳሰሉ ሀገራት ለዘመናት በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ስር ቆይተዋል። ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ በነፍስ ወከፍ ገቢያቸውም (GDP per capita) ሆነ በሰብዓዊ ልማት ጠቋሚያቸው (HDI) ከኢትዮጵያ በእጅጉ ያነሱ እና በዓለም መጨረሻ ላይ የሚገኙ ናቸው። ቅኝ ግዛት የብልጽግና እና የሰለጠነ መዋቅር ምንጭ ቢሆን ኖሮ፣ እነዚህ የፈረንሳይ ቅኝ ግዛቶች ዛሬ ለምን የዓለም አቀፍ የድህነት መለኪያ ሆኑ? አሁንም ድረስ ፈረንሳይ በዘረጋችው የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም መዋቅር (በተለይም በCFA ፍራንክ የገንዘብ ሥርዓት) የራሳቸውን ሀብት ማስተዳደር አቅቷቸው በከፍተኛ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ ይገኛሉ። ይህ ሐቅ "ቅኝ ግዛት የድህነት ምክንያት አይደለም" የሚለውን የማጋቴን መከራከሪያ ከመሠረቱ የሚያፈርስ ነው።
ቬትናም ዛሬ ላለችበት የኢኮኖሚ ከፍታ የበቃችው በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት በረከት ሳይሆን፣ እንዲያውም የፈረንሳይን እና የአሜሪካን አውዳሚ ጦርነቶች በከፍተኛ መስዋዕትነት አሸንፋ ከወጣች በኋላ ነው። ሀገሪቱ ከጦርነቱ ፍርስራሽ ተነስታ ያደገችው በ1986 (እ.ኤ.አ.) ተግባራዊ ባደረገችው 'ዶይ ሞይ' (Doi Moi) የተሰኘው የውስጥ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የእስያ ቀጠና በፈጠረላት ምቹ የንግድ ትስስር እንጂ የቅኝ ገዥዎች ትሩፋት አይደለም። የቬትናምን የላብ እና የደም ውጤት ለቅኝ ገዥዎች ታሪክ ማሳመሪያ ማድረግ ፍጹም ስህተት ነው።
ማጋቴ ዋድ የኢትዮጵያን ነጻነት ከድህነት ጋር አያይዛ ለማቅረብ መሞከሯ፣ የሀገሪቱን ታላቅነት እና የገጠማትን ውስብስብ ፈተና ካለመረዳት የመነጨ ነው። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ምድር የነጭ የበላይነትን በአድዋ ተራሮች ላይ በመቅበር፣ ለመላው ጥቁር ሕዝብ የነጻነት እና የፓን-አፍሪካኒዝም ፋና ወጊ የሆነች ታላቅ ሀገር ናት። በቅኝ አለመገዛቷ የኩራቷ እንጂ የድህነቷ መንስኤ አይደለም።
የኢትዮጵያ ዘመናዊ የኢኮኖሚ ፈተናዎች የመነጩት ከነጻነቷ ሳይሆን፣ በዙሪያዋ ከነበሩት የቅኝ ገዥ ኃይሎች ሴራ እና ከውስጣዊ ፖለቲካዊ ውጣ ውረዶች ነው። მላው አፍሪካ በቅኝ ግዛት ሲከፋፈል፣ ነጻዋ ኢትዮጵያ በቅኝ ገዥዎች ተከባ የባህር በር እንድታጣ እና ከዓለም አቀፍ ንግድ እንድትገለል ተደርጋለች። በቅርቡ ታሪክም በቀዝቃዛው ጦርነት የጂኦፖለቲካዊ ሽኩቻ ሰለባ በመሆን፣ እንዲሁም ደርግ በተከተለው አውዳሚ የማርክሲስት የኢኮኖሚ ሥርዓት እና በተራዘሙ የእርስ በርስ ጦርነቶች ምክንያት ኢኮኖሚዋ ክፉኛ ተጎድቷል። እነዚህ ሁሉ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ ኢትዮጵያ የራሷን ቋንቋ፣ ባህል፣ የቀን አቆጣጠር እና ሀገራዊ ኩራት ጠብቃ ያቆየች፤ ዛሬም በአፍሪካ ቀንድ ትልቅ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆን የቻለች ሀገር ናት።
የአፍሪካን ወቅታዊ ችግሮች ለመፍታት ራስን መመርመር፣ ሙስናን መዋጋት እና የተሻለ አስተዳደር መገንባት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ነገር ግን ይህንን ለማድረግ ሲባል የቅኝ ግዛትን አስከፊነት ማጠብ እና የኢትዮጵያን ደማቅ የነጻነት ታሪክ ማጠልሸት አይቻልም። ኢትዮጵያ ምንም እንኳን የኢኮኖሚ ፈተናዎች ቢኖሩባትም፣ የማንም ቅኝ ገዥ ሎሌ ሳትሆን የራሷን ዕድል በራሷ የወሰነች የአፍሪካ የቁርጥ ቀን ልጅ ናት። አህጉሪቱ ወደፊት መራመድ ያለባት የቅኝ ግዛትን ጠባሳ በማስተባበል ሳይሆን፣ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ የራስን ማንነት አጥብቆ በመያዝ እና ጠንካራ ኢኮኖሚን በነጻነት ላይ በመገንባት ሊሆን ይገባል።
5 months ago
"በዐይኔ በብረቱ ...!"
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም ማህበራዊ ጉዷንም፣ ገዷንም በድሯ ሸምና የሰው ልጅ የደረሰበትን ታላላቅ አብዮቶች ታስመለክተን ይዛለች ።
ይህ የዲጂታሉ ዘመን፣ አዲስ መስኮት ነው።
የዓለምን ታሪክ ሰፊ ንዋይ፣ ብዙ የሰው ኃይል እና ጊዜ በልቶ የመንገር ሩጫ በዚህ የመስኮት አቋራጭ በግለሰቦች ስልክና ካሜራ መዳፍ ላይ እየወደቀ ነው።
የማህበራዊ ትስስር ሜዳው ከትናንት ዛሬ፣ ከዛሬም ነገ ትተው ቢሄዱ ቆሞ አይጠብቅም። በዐይን ጥቅሻ ፈትለክ ነው። ለውጡ ፈጣን፣ ተለዋዋጭነቱ ነቅተው እንደ ቴኒስ ዳኛ ወዲህ ወዲያ አንገትዎን የሚነቀንቅ ሆኗል።
ወደ ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ የካሜራ ሌንሳቸውንና በሚሊየን የሚከተሏቸውን ዐይን ይዘው የሚመጡ የመስኮቱ ዘዋሪዎች ለኢትዮጵያ አዲስ ነጋሪት የሚጎስሙ ናቸው።
በሚሊየን የሚቆጠሩ ተከታዮቻቸው በየሰከንዱ ለሚለቀቁ ይዘቶች ሲሉ ዐይንና ጆሯቸውን በእነዚህ የዘዋሪዎች ዳና ላይ አድርገዋል።
ምክንያቱም ዓለም የዲጂታል ዝመና አብዮቷ ላይ ወደ ፊት እንጂ የኋልዮች ዳራዋን ለመመልከት አፍታም የላትም፤ ተከታዮቻቸውም ጊዜ የለቸውም። አጭር፣ ፈጣን፣ አዲስ ይናፍቃሉ።
የአሜሪካው ታዋቂ የቀጥታ ስርጭት አቅራቢ አይሾው ስፒድ፣ እንዲሁም ከ19 ሚሊየን በላይ የቲክቶክ ተከታዮች ያሉት የዲጂታል ዜና አቅራቢው ዲላን ፔጅ ወደ አዲስ አበባ መምጣት ኢትዮጵያ በአፍሪካ የዲጂታል ዲፕሎማሲና የቱሪዝም ስበት ማዕከል እየሆነች መምጣቷን የሚያሳይ ትልቅ የጂኦፖለቲካዊና የማኅበራዊ ሚዲያ ለውጥ ማሳያ ነው።
ቀድሞ በኢትዮጵያ ፍቅር የወደቀው ብሪታኒያዊው የቲክቶክ ዜና አቅራቢ ዲላን ፔጅ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታና ስለ ኢትዮጵያውያን የአንድነት መንፈስ በአዎንታ በመዘገብ መንፈሱ ከአካሉ ቀድሞ አዲስ አበባ ከደረሰ ከርሟል።
ይህ ፕሮጀክት በውጭ ዕዳ ሳይሆን በሕዝብ ቦንድና በላብ የተገነባ ነው በማለት አጉልቶ አሳይቷል።
ግድቡንም “በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የሚቀይረው የአፍሪካ የብርሃን ተስፋ” በማለት ለዓለም ማስተዋወቁን አንረሳም።
ዲላን በርካታ ቀናትን የሚወስደውን ታላቁን ጉዞዬን፣ በቅኝ ግዛት ባልተገዛችው ሀገር ኢትዮጵያ ጀምሬያለሁ በማለት ወደ አዲስ አበባ ሲገባ ይዞት የመጣው የካሜራ ሌንስ የኢትዮጵያን ጥንታዊነት ብቻ ሳይሆን አዲሱን የቴክኖሎጂ ምዕራፍም ጭምር የገለጠ ሆኗል።
በአዲስ አበባ ቆይታው የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን በጎበኘበት ወቅት፥ ይህን በቴክኖሎጂ የተቃኘ ቦታ ሳየው ተደምሜያለሁ፤ አፍሪካ ተቀይራለች፣ አዲሱን ገፅታዋን ለዓለም የሚያሳይ ቦታ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ብሏል።
አዲስ አበባ በቅርቡ ከ30 በላይ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡና በጥምረት ከ470 ሚሊየን በላይ ተከታዮች ያሏቸው ከ200 በላይ የዲጂታል ፈጣሪዎች የተሳተፉበትን የአፍሪካ ማኅበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪዎች ጉባኤን ማስተናገዷ የይዘት ፈጣሪዎች የዲፕሎማሲ ዋና ከተማ አድርጓታል።
በጉባኤው ላይ በቀረቡ መረጃዎች መሠረት ስለ አፍሪካ የሚሰራጩ የተዛቡና አሉታዊ ትረካዎች በአህጉሪቱ ላይ በየዓመቱ እስከ 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ የኢኮኖሚ ኪሳራ ያደርሳሉ።
ዲላን ፔጅ እና መሰል የይዘት ፈጣሪዎች ይህንን የተዛባ ምስል ለመስበር 'ሳይነገራችሁ በዓይናችሁ እዩት' በሚል መርህ እየመጡ ነው።
የዲላን ፔጅ ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን እንደ አዶናይ ያሉ የሀገር ውስጥ ይዘት ፈጣሪዎች የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው።
የተጽእኖ ፈጣሪዎች ጉብኝት የዲጂታል ዲፕሎማሲና የሀገር ገፅታ ግንባታ ወሳኝ ተግባር ሲሆን፥ የወቅቱ የሀያላን ሀገራት ፉክክር ገር ኃይል መሆኑን ላጤነ ዲፕሎማሲው ይገለጥለታል።
ገር ዲፕሎማሲ ሰዎችን ሳያስገድዱ፣ ወደውና ፈቅደው አንተ የምትፈልገውን ነገር እንዲያደርጉ የማድረግ ብቃት መሆኑን የጽንሰ ሀሳቡ ፈጣሪ አሜሪካዊው ጆሴፍ ናይ ያስረዳሉ።
ለጆሴፍ ምስጋና ይግባውና ሀገራት ከጦር መሳሪያ እሽቅድምድሞሽ ወደ ለስላሳው አቀራረብ ፊታቸውን እንዲያዞሩ አድርጓል።
ከአሜሪካ ገር መንገዶች መካከል ሆሊውድ፣ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ብራንዶች (አፕል, ጎግል, ማይክሮሶፍት)፣ ምግቦች (ማክዶናልድ፣ ኮካ ኮላ) እና ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ይጠቀሳሉ።
ለደቡብ ኮሪያ "ሃሊዩ" ወይም የኮሪያ ማዕበል። ይህም የኬ-ፖፕ ሙዚቃ፣ የኮሪያ ፊልሞችና ድራማዎች እንዲሁም የውበት ምርቶች፤ ለብሪታንያ የእንግሊዝኛ ቋንቋ፣ ቢቢሲ እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ገሩ መንገዳቸው ነው።
ሳዑዲ ዓረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እንደ ማንችስተር ሲቲ እና ኒውካስል ዩናይትድ የእግር ኳስ ክለቦችን በመግዛት እንዲሁም የዓለም ዋንጫዎችን በማዘጋጀትና እንደ ሮናልዶ ታዋቂ ተጫዋቾችን ወደ ሀገራቸው በማምጣት የዓለምን ትኩረት በመሳብ የሀገራቸውን ገጽታ እያደሱ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያም ምድረ ቀደምት፣ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ምልክት የአድዋ ድል፣ የፓን-አፍሪካኒዝም ማዕከል መሆኗ፣ የቡና መገኛነቷ፣ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎቿን በማስተዋወቅ የራሷን የዲጂታል ለስላሳ ኃይል እየገነባች ትገኛለች።
በዚህም በቱሪዝም ዘርፍ ላይ ፈጣን የኢኮኖሚ መነቃቃትን ይፈጥራል።
ኢትዮጵያ ይህንን ወርቃማ የዲጂታል ዲፕሎማሲ ዕድል በመጠቀም፣ የቱሪዝምና የኢኮኖሚ ምሰሶዎቿን ለማጠናከር በጥበብና በስልታዊ መሪነት ልትራመድበት ይጠበቃል።
ዲጂታሉ ዓለም በሮችን ከፍቷል፤ የኢትዮጵያን መልኮች በአዲሱ ነጋሪት ማስተጋባት የዛሬ ስራ ነው ።

የዓድዋ ድል መታሰቢያን የጎበኘው ‘ዲላን ፔጅ’ ኢትዮጵያ በቅኝ ያልተገዛችበትን ታሪካዊ ዳራ በአድናቆት ተመልክቶታል
**********************
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮችን ያፈራው እንግሊዛዊው የቲክቶክ ተፅዕኖ ፈጣሪ ‘ዲላን ፔጅ’ በኢትዮጵያ እያደረገው ባለው ጉብኝት የሀገራችንን ገጽታ ለዓለም በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል።
ዲላን በአዲስ አበባ ቆይታው የወንዝ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በመዲናዋ የተከናወኑ ቁልፍ የልማት ሥራዎችን እና የቱሪስት መዳረሻዎችን ተዟዙሮ ተመልክቷል።
በጉብኝቱ መሃል በአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት መስክ አረንጓዴ ዐሻራውን በማሳረፍ የልማት ተሳትፎውን በማኅበራዊ ሚዲያ ለተከታዮቹ አጋርቷል።
ዝነኛው ቲክቶከር በፒያሳ የሚገኘውን የዓድዋ ድል መታሰቢያም የጎበኘ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ያልተገዛችበትን ታሪካዊ ፋና በአድናቆት ተመልክቷል።
በስፍራው ሲደርስ ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን፤ በባህላዊ የአፈላል ሥነ-ሥርዓት የተዘጋጀለትን የኢትዮጵያ ቡና ከመቅመስ በተጨማሪ የመታሰቢያ ስጦታዎች ተበርክተውለታል።
ዲላን ስለኢትዮጵያ ጉብኝቱ በሰጠው አስተያየት፣ ጉብኝቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስለ አፍሪካ ያለውን የተዛባ አመለካከት ለመቀየር የሚያግዝ እንደሆነም ተናግሯል።
ተፅዕኖ ፈጣሪው ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ወደፊት ሐረር እና አፋርን ጨምሮ የተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎችን ለመጎብኘት ያለውን ፍላጎት ገልጿል።
በቢታኒያ ሲሳይ
#dylanpage #ethiopia #addisababa #adwa #adwavictorymemorial #corridordevelopment #riversidedevelopment #greenlegacy #ebc

ታዋቂው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ዲላን ፔጅ የአረንጓዴ አሻራውን አስቀመጠ
#ethiopia | በማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተሰሚነትን ያተረፈው ዲላን ፔጅ በአዲስ አበባ የተለያዩ መስህብ ስፍራዎችን በመጎብኘት ላይ ይገኛል።
ከየተለያዩ ተቋማት ምልከታውም በኋላ በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳርቻ ስራዎችን ተዘዋውሮ በመመልከት ላይ ይገኛል።
ቲክቶከሩ በምልከታውም በወንዝ ዳርቻ ልማት የአረንጓዴ አሻራውን በማሳረፍ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት ስራ በማበረታት ለተከታዮቹ አጋርቷል።
ዲላን ፔጅ ጉብኝቱን አስመልክቶ በሰጠዉ አስተያየት “ይህ ጉብኝት በዓለማቀፍ ደረጃ ስለ አፍሪካ ያለውን የተዛባ አመለካከት የሚቀይር እንደሆነም ገልጿል።
በርካታ ቀናትን የሚወስደውን ታላቁን ጉዞዬን፣ በቅኝ ግዛት ባልተገዛችው ሀገር ኢትዮጵያ ጀምሬያለሁ የሚለው ተፅዕኖ ፈጣሪው ከአዲስ አበባ ባሻገርም ጥንታዊቷ የሐረር ከተማና አፋርን ጨምሮ የተለያዩ አካባቢዎችን ለመጎብኘት ማቀዱንም አስታውቋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #amn

ታዋቂው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ዲላን አዲስ አበባ ገባ
#ethiopia | በማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተሰሚነትን ያተረፈው ዲላን (ዲላን ፔጅ ) አዲስ አበባ ገብቷል።
ዲላን በቲክቶክ ብቻ ከ19 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት ሲሆን፣ አዲስ አበባ መግባቱን አስመልክቶ ባስተላለፈዉ መልእክት በርካታ ቀናትን የሚወስደውን ታላቁን ጉዞዬን፣ በቅኝ ግዛት ባልተገዛችዉ ሀገር ኢትዮጵያ ጀምሬያለሁ ብሏል።
ግርማ ሞገስ ያለው መልክዓ ምድር፣ በርካታ የታሪክ እና የሃይማኖት እሴቶች ያሏት ኢትዮጵያ የሰው ልጅ እና የቡና መገኛ መሆኗን ተናግሯል፡፡
ተፅዕኖ ፈጣሪዉ ዲላን ለተከታዮቹ፤ “ከምነግራችሁ ይልቅ ባሳያችሁ ይሻላል” በማለት ቀጠሮ ይዟል።
ኢትዮጵያ በርካታ የአርሰናል ደጋፊዎች ያሏት ሀገር መሆኗን እንደሰማ ጠቅሶ፣ ከእነሱ ጋርም ልዩ ጊዜ ለማሳለፍ ቀጠሮ መያዙን ገልጿል።
የዓለም አቀፍ ቱሪስቶች የስበት ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባም ዲላንን እንኳን ደህና መጣህ ብላ ተቀብላዋለች፡፡
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #addismedianetwork #voiceofgeneration #dylanpage #addisababa #ethiopia

ከምድር ባቡር ፉጨት እስከ ዲጂታል አድማስ፦ ከአንድ ክፍለ ዘመን የተሻገረው የኢትዮ-ፈረንሳይ የማይበጠስ ወዳጅነት!
*********************
ከንጉሥ ሳህለ ሥላሴ የሸዋ ግዛት እስከ ዘመናዊቷ ኢትዮጵያ፣ ከታላቁ ገጣሚ አርተር ራምቦ የሐረር ቆይታ እስከ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የትላንትናው ታሪካዊ ጉብኝት... በቅኝ ግዛት ያልተበከለውና በእኩልነት ላይ የተመሠረተው የኢትዮጵያና የፈረንሳይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዴት ዛሬም ድረስ እንደጸና አለ!
በዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ የሀገራት ግንኙነት እንደየዘመኑ የፖለቲካ ንፋስ መዋዠቅ እና መለዋወጥ የተለመደ ክስተት ነው።
ነገር ግን፣ ከክፍለ ዘመናት መፈራረቅ፣ ከርዕዮተ ዓለም ለውጦች እና ከዓለም አቀፍ ቀውሶች ተርፈው በጽኑ መሠረት ላይ የሚቆሙ ጥቂት የማይበጠሱ የወዳጅነት ገመዶች አሉ።
ከእነዚህ ብርቅዬ ታሪካዊ ትሥሥሮች መካከል የኢትዮጵያ እና የፈረንሳይ የሁለትዮሽ ግንኙነት በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው።
ይህ ግንኙነት የተፀነሰው በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንደታየው በቅኝ ግዛት ጌታና ሎሌነት ሳይሆን፣ በሁለት ሉዓላዊ እና ገለልተኛ መንግስታት መካከል በነበረ ፍፁም የእኩልነት መርሕ ላይ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።
የዚህን መረጃ ሙሉ ሐሳብ አስተያየት መስጫው ውስጥ ካለው ሊንክ ያገኛሉ፦
#ebc #ethiopia #france #diplomacy #relations

የጥቁር ሕዝቦች ድምፅ በተመድ አዳራሽ - ኢትዮጵያ ለነፃነት የከፈለችው ዲፕሎማሲያዊ ዋጋ
********************
(የዕለቱ መልዕክት)
ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያላቸው ትሥሥር እንደ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ብቻ የሚታይ ሳይሆን፣ በታሪክ አውድማ ላይ በፅናት እና በሉዓላዊነት የተገመደ የክብር ሰንሰለት ነው።
ከሰማንያ ዓመታት በፊት ዓለም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍርስራሽ ላይ ቆማ አዲስ ተስፋን ስትፈልግ፣ ኢትዮጵያ ከ51ዱ መሥራች ሀገራት መካከል አንዷ ሆና የቻርተሩን ሰነድ ስትፈርም ተራ ተሳታፊ አልነበረችም።
ይልቁንም፣ የዲፕሎማቶቻችን ድምፅ የኃያላንን የበላይነት ለመሞገት እና የደካማ ሀገራትን መብት ለማስጠበቅ የሚተጋ የፍትሕ ጩኸት ነበር።
በወቅቱ በቅኝ ግዛት ቀንበር ሥር ለነበሩት ወንድም የአፍሪካ እና የእስያ ሕዝቦች፣ ኢትዮጵያ ብቸኛ የነፃነት እና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ተሟጋች ሆና መቅረቧ፣ “ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ” የሚለውን ብሂል ወደ ጎን በመተው ለሰው ልጅ ሁሉ ነፃነት መቆሟን ያሳየ ታላቅ የሞራል ልዕልና ነበር።
ይህ የታሪክ አሻራ ዛሬም በደማቅ ቀለም እየተጻፈ ይገኛል። ኢትዮጵያ ላለፉት ሰማንያ ዓመታት በሚጠጋ ጊዜ ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ የሰላም ዘቦችን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በማሠማራት፣ በዓለም ሰላም ማስከበር ሂደት ውስጥ ያላትን የማይናወጥ ሚና በተግባር አሳይታለች።
የሀገራችን ሠራዊት በሄደበት ሥፍራ ሁሉ የሚታወቅበት የጥንካሬ፣ የዲሲፕሊን እና የሕዝባዊነት ገጽታ፣ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰላም አስከባሪ ሠራዊት ከሚያዋጡ ሀገራት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ አድርጓታል። ይህ መሥዋዕትነት ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለጎረቤቶቻችን እና ለመላው ዓለም ሰላም መቆማችንን የሚያረጋግጥ የቆራጥነት ማሳያ ነው።
በተመድ እና በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ሥር የሚከናወኑት እነዚህ ተልዕኮዎች፣ የኢትዮጵያን የሰላም አምባሳደርነት በዓለም አደባባይ ከፍ አድርገውታል።
ዛሬ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አዲስ አበባን በተደጋጋሚ መጎብኘታቸው እና የድርጅቱን 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እዚህ በታሪካዊቷ ከተማችን እንዲከበር መወሰኑ፣ እንዲሁ የተገኘ ድንገተኛ ክስተት አይደለም። ይህ ውሳኔ ኢትዮጵያ ለድርጅቱ ያበረከተችው ታሪካዊ አስተዋፅኦ እና ለዓለም ሰላም የከፈለችው መሥዋዕትነት የተሰጠው ታላቅ እውቅና ነው።
“መልካም ስም ከመቃብር በላይ ይውላል” እንዲሉ፣ የሀገራችን የዲፕሎማሲ ጥንካሬ እና የሠራዊታችን አኩሪ ገጽታ ለስምንት ዐሥርተ ዓመታት ተጠብቆ ቆይቶ ዛሬም በዓለም መድረክ ድምፃችን ጎልቶ እንዲሰማ አድርጎታል።
ይህም የአፍሪካን ዳግም መነሣት የሚያበስር ምልክት እና ለጋራ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ የሚያፋጥን የጥንካሬ ምሰሶ ነው።
ኢትዮጵያ እና ተመድ በዘላቂ ልማት ግቦች ዙሪያ ያላቸው ትብብርም ሌላው የትሥሥሩ ገጽታ ነው። ድህነትን ለማጥፋት፣ ፕላኔቷን ለመጠበቅ እና ለሁሉም ሰው ሰላምን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት፣ ሀገራችን ከድርጅቱ ጋር ያላትን ስትራቴጂክ አጋርነት ይበልጥ ያጠናክረዋል።
ወደፊትም ቢሆን ኢትዮጵያ የድርጅቱ ደጀን እና የልማት ተምሳሌት ሆና በመቀጠል፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ፍትሐዊ ሥርዓት እንዲሰፍን እና የጋራ ብልጽግና እንዲረጋገጥ የነበራትን የሞራል መሪነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ጥርጥር የለውም።
የታሪካችን ጥንካሬ እና የሠራዊታችን ፅናት ዛሬም ለዓለም ሰላም ዋስትና፣ ለትውልድም ኩራት ሆኖ ይቀጥላል።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
#ebc #ethiopia #diplomacy #un #un80

6 months ago
የኢትዮጵያ በተመድ የሰፈራ ውሳኔ ላይ የሰጠችው ድምፅ ያስከተለው ውዝግብ
የኔታ ሚዲያ
የኢትዮጵያ መንግሥት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በባለቤትነት በተያዙ የፍልስጤም ግዛቶች የሚካሄዱ የእስራኤል ሰፈራዎችን በሚያወግዝ የውሳኔ ሃሳብ ላይ "ተቃውሞ" (No) ድምፅ መስጠቷ በአገር ውስጥና በውጭ ዲፕሎማሲያዊ ክበቦች ከፍተኛ መነጋጋሪያ ሆኗል።
የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ባሳለፈው በዚህ የውሳኔ ሃሳብ ላይ አብዛኞቹ አባል አገራት ድጋፋቸውን ሲሰጡ ኢትዮጵያ ግን ውሳኔውን ከተቃወሙ ጥቂት አገራት ተርታ ተሰልፋለች።
ይህ ድርጊት ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከፍልስጤም ጎን በመቆም ለበርካታ አስርት ዓመታት ስታራምደው ከነበረው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ያፈነገጠ እንደሆነ ተነግሯል።
ይህንን ተከታሎ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች እና በፖለቲካ ተንታኞች ዘንድ የተለያየ አስተያየት እየተሰነዘረ ይገኛል ተቺዎች እንደሚሉት ይህ ድምፅ ኢትዮጵያ በታሪኳ በቅኝ አገዛዝ እና በአፓርታይድ ላይ የነበራትን ጠንካራና ታሪካዊ ተቃውሞ የሚንድ ነው።
ብዙዎች መንግሥት ለምን አቋሙን ለመቀየር እንደወሰነ ግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጥ እየጠየቁ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል አንዳንድ ተንታኞች ውሳኔው ከወቅታዊው ቀጠናዊ ፖለቲካ እና ኢትዮጵያ ከእስራኤል ጋር ካላት ስልታዊ ግንኙነት አንጻር የተወሰደ ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ።
ኢትዮጵያ በተለምዶ በአፍሪካ ሕብረት እና በተመድ መድረኮች የፍልስጤምን ነጻነትና የመወሰን መብት በመደገፍ ትታወቃለች። አሁን የታየው ለውጥ በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ታሪክ ውስጥ ትልቅ ክስተት ተደርጎ ተወስዷል።
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስካሁን ድረስ ስለዚህ ድምፅ አሰጣጥ በይፋ የሰጠው ዝርዝር መግለጫ የለም።

7 months ago
የጥቁር ሰው ኑዛዜ፦ በቴዲ አፍሮ ብዕር የተሳለ የዓድዋ ድል የደም ውል
ቴዲ አፍሮ "ጥቁር ሰው "በሚለው ዘፈኑ አድዋ የጥቁር ህዝብ የምጥ ቀን መሆኑን መስክሯል።ዘፋኙ "እኔን አልሆንም ነበር እኔ" ሲል፣ ታሪክ ዝም ብሎ ያለፈ ድርጊት ሳይሆን የዛሬው ማንነታችን "ፅንስ" መሆኑን ይነግረናል።
ይህ ልብ ሰባሪ አገላለፅ ነው ። ለምን? ምክንያቱም "ያ ድል ባይኖር ኖሮ ዛሬ የምንናገረው ቋንቋ፣ የምንለብሰው ልብስ፣ የምናመልከው አምላክና የምንጠራበት ስም የእኛ ባልሆነ ነበር" የሚል መርዶ አዘል እውነት ስላለው ነው።
ታሪክ ለህይወት የሚያስፈልገው ለተግባርና ለስቃይ ነው እንደሚባለው ቴዲ አፍሮም ያንን የ1888ቱን ስቃይ ወደ ዛሬው ትውልድ ወኔነት ቀይሮታል።
ሀቅ ነው ያለ አድዋ፣ እኛ "ባዶ" ነበርን!! ያድል ባይኖር "እኔ" የሚለው ቃል ትርጉም አልባ ይሆን ነበር። ይህ ዘፈን ስንሰማ በቅኝ ግዛት ቀንበር ስር የወደቁ ወንድሞቻችንን የጠፋ ማንነት እያስታወስን ለማልቀስ እንዳዳለን ወይም እናለቅሳለን። ምክንያቱም በቀኝ ግዛት ሰበብ ብዙ "እኔነታቸውን" የተነጠቁ ስላሉ።
ለዘመናት "ጥቁር" የሚለው ቃል የባርነት፣ የኋላ ቀርነትና የዝቅተኝነት ተምሳሌት ተደርጎ በአውሮፓውያን ሲሰበክ ኖሯል።ቴዲ አፍሮ ግን ይህንን የንቀት ቃል ወስዶ የክብር አክሊል አደረገው።
"ምኒልክ ጥቁር ሰው" ሲል፣ የፖለቲካ ምሁራን እንደሚሉት "የታሪክ የበላይነትን" ገልብጦታል። አፄ ምኒልክን እንደ አንድ ንጉሥ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ጥቁር ህዝብ "የመዳን ምልክት" አድርጎ ስሏቸዋል።
በግጥሙ ውስጥ "ኢጆሌ ቢያኮ ጀጀባዳ መሌ" የሚለው የኦሮምኛ ስንኝ ሲሰማ፣ ፖለቲካው ወደ ስነ-ልቦናዊ አንድነት ይለወጣል። በልዩነት ለቆሰለች ሀገር፣ ይህ ስንኝ የቁስል መድኃኒት ነው። "እርስ በርስ ከመናከስ ይልቅ፣ ለጋራ ክብር የፈሰሰውን ደም አስቡ" የሚል የለቅሶ ጥሪ ነው።
አንድን ህዝብ የሚያስተሳስረው የጋራ ስቃዩና የጋራ ድሉ ነው። ቴዲ አፍሮ ያንን የጋራ ደም በሙዚቃው ውስጥ ስላፈሰሰው፣ ስንኞቹ የፖለቲካ መፈክር ሳይሆኑ የልብ ትርታ ናቸው።
ቴዲ አፍሮ በ"ጥቁር ሰው" ግጥም ውስጥ የሳለው ምስል ደም የሚንጠባጠብበት ህያው ምስል ነው።
የባልቻ አባ ነፍሶ "መድፍ"፦ ባልቻ "ባያይ አይኔ ብረቱ" ተብሎ ሲገለጽ፣ ቴዲ የአካል ጉዳትን ለሀገር ክብር የመስጠት ከፍተኛው መስዋዕትነት አድርጎ ያቀርበዋል።
አይኑን ያጣው ጀግና በልቡ አይን ሀገሩን ሲጠብቅ ማሰብ፣ ለማንኛውም ስሜት ላለው ሰው አስለቃሽ ነው። "ሳልል ዋይ ሳልል ዋይ" የሚለው ዜማ፣ ስቃዩን ዋጥ አድርጎ ለሀገር መቆምን ይገልጻል።
የእቴጌ ጣይቱ "የቀፎ ንብ" ተምሳሌት፦ ሴትነትን ከሽንፈትና ከለቅሶ አውጥቶ፣ ወደ መሪነትና ወደ ቁጣነት ቀይሮታል። "ከፊት ሆና መራችው ንግስቱ" ሲል፣ አንዲት እናት ልጆቿን ለሞት ስትልክና ለነፃነት ስታሰልፍ ያለውን የመሪነት ግርማ ያሳያል። ይህ ጀግንነትን የሚያወድስ ረጅም ግጥም ተብሎ ብለን ብንጠራውም ድፍረት አያሰኝም።
ቴዲ "አይቀርም በማርያም ስለማለ" የኢትዮጵያዊያንን እምነት፣ ቃል ኪዳንና ለሞት ያላቸውን ግድየለሽነት በአንድ ላይ ይይዛል።
ንጉሡ ሲያውጅ፣ ህዝቡ በቃለ መሀላው ታስሮ ወደ አድዋ ይተማል። እዚህ ጋር ነው ለቅሶው የሚመጣው። እናት ልጇን፣ ሚስት ባሏን፣ ልጅ አባቱን "አይቀርም በማርያም ስለማለ" በሚል ቃል ተለይተው ወደማይመለሱበት የጦር አውድማ ይሄዳሉ።
ቴዲ አፍሮ ይህንን የናፍቆትና የቁርጠኝነት ትዕይንት በዜማው ሲያዋህደው፣ አድማጩ ራሱን በዚያ የጦር ሜዳ ጭስና አቧራ ውስጥ ያገኘዋል።
"ወይ ሳልለው ብቀር ያኔ" የሚለው ፀፀት፣ በታሪክ አጋጣሚ "አልመጣሁም" ቢል ኖሮ ዛሬ የሚኖረውን የባርነት ሕይወት እያሳሰበ ልብን በፍርሃትና በቁጭት ያንጠለጥላል።
"ጥቁር ሰው" ዝም ብሎ ዘፈን አይደለም። የሞቱት አባቶቻችን ለኛ የፃፉልን የደም ኑዛዜ ነው። ቴዲ አፍሮ ያንን ኑዛዜ በዜማ አንብቦልናል።
አድዋ ህልውናችን ነው። አድዋ ክብራችን ነው። አድዋ ውበታችን ነው። "ጥቁር ሰው"ዘፈን ይሄንን ነው የሚሰብከው።

የአድዋ ድል ጥያቄዎች። መልሳቹን ኮመንት ላይ አስቀምጡልን
1. እ.አ.አ በ1885 የተጠናቀቀውና አውሮፓውያን አፍሪካን ለመቀራመት የተስማሙበት ታሪካዊ ጉባዔ ምን ይባላል?
ሀ) የፓሪስ ስምምነት
ለ) የበርሊን ጉባዔ
ሐ) የአድዋ ውል
መ) የለንደን ስብሰባ
2. የታሪክ ተመራማሪው ፖል ሄንዝ የአድዋን ድል ከአውሮፓ ተሰሚነት አንጻር እንዴት ይገልጹታል?
ሀ) ለአውሮፓውያን ተጨማሪ ኃይል የሰጠ ክስተት
ለ) የአውሮፓ ተሰሚነት የቁልቁለት ጉዞ መነሻ
ሐ) በኢትዮጵያና ጣልያን መካከል የተደረገ ቀላል ግጭት
መ) ለአውሮፓውያን የባህር በር የከፈተ ድል
3. "ቪቫ ምኒልክ! ቪቫ ኢትዮጵያ!" በማለት የኢትዮጵያን ድል ያወደሰው ጣሊያናዊ ጋዜጠኛ ማን ይባላል?
ሀ) ኦቶ ቫን ቢስማርክ
ለ) ሪቻርድ ፓንክረስት
ሐ) ፊሊፖ ቱራቲ
መ) ሬይመንድ ጆናስ
4. ለአድዋ ድል ክብር ሲሉ 17 የአፍሪካ አገራት ያደረጉት ተግባር ምንድን ነው?
ሀ) የኢትዮጵያን የጦር ስልት መቅዳት
ለ) የሰንደቅ ዓላማ ቀለማቸውን ከኢትዮጵያ መውሰድ
ሐ) ዋና ከተማቸውን አዲስ አበባ ብለው መሰየም
መ) ለዳግማዊ ምኒልክ ሀውልት ማቆም
5. ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ በበርሊን ጉባዔ አፍሪካን ለመቀራመት ለተስማሙት ሦስት አገራት (ብሪታንያ፣ ፈረንሳይና ጣልያን) ለላኩላቸው "የሦስትዮሽ ስምምነት" የሰጡት ምላሽ ምን ነበር?
ሀ) ስምምነቱን በደስታ መቀበል
ለ) "እኔ በሌለሁበት የተወሰነውን አላውቅም" በማለት ውድቅ ማድረግ
ሐ) የተወሰነውን መሬት ለጣልያን አሳልፎ መስጠት
መ) ከአውሮፓውያን ጋር አብሮ ለመቀራመት ጥያቄ ማቅረብ
6. ስለ ዓፄ ምኒልክ ጀግንነት "በምድር ላይ ጀግና ጥራ ብትሉኝ ቀድሜ የምጠራው የንጉሥ ምኒልክን ነው" በማለት ምስክርነት የሰጡት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ማን ናቸው?
ሀ) አብርሃም ሊንከን
ለ) ጆን ኤፍ ኬኔዲ
ሐ) ባራክ ኦባማ
መ) ፍራንክሊን ሮዝቬልት
7. የናይጄሪያ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ናምዲ አዚኪዊ ስለ ኢትዮጵያ የሰጡት ትርጓሜ ምንድን ነው?
ሀ) ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት የተያዘች አገር ነች
ለ) ኢትዮጵያ ጥቁር ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርባት የታሪክ ዋቢ ነች
ሐ) ኢትዮጵያ የአውሮፓ አጋር ነች
መ) ኢትዮጵያ የባህር በር የሌላት ደካማ አገር ነች
8. ዓፄ ምኒልክ በኢትዮጵያ ካስተዋወቋቸው ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች መካከል የማይመደበው የቱ ነው?
ሀ) የመጀመሪያው ባንክ (አቢሲኒያ ባንክ)
ለ) የመጀመሪያው የባቡር መንገድ
ሐ) የመጀመሪያው የአውሮፕላን በረራ
መ) የመጀመሪያው ፖስታ ቤትና ስልክ
9. እንግሊዛዊው መሪ ዊንስተን ቸርችል የአድዋ ጦርነት በአውሮፓ ፖለቲካ ላይ ያመጣው ተጽዕኖ ምንድን ነው ይላሉ?
ሀ) የአውሮፓን ክብር ከፍ አደረገው
ለ) የጣልያን ዋጋ በዓለም ፖለቲካ ረገድ ወደ ታች እንዲወርድ አደረገ
ሐ) ለጣልያን ትልቅ ድል አስገኘ
መ) የቅኝ ግዛት መስፋፋትን አፋጠነ
10. ዓፄ ምኒልክን "ነገር ከዓይነ-ውኃ የሚያውቅ ብልህ ፖለቲከኛ (ዲፕሎማት)" ሲል የገለጻቸው የታሪክ ጸሐፊ ማን ነው?
ሀ) ፖል ሄንዝ
ለ) ሬይመንድ ጆናስ
ሐ) ሪቻርድ ግሪንፊልድ
መ) ፊሊፖ ቱራቲ

የአድዋ ጦርነት የተካሄደው እ.ኤ.አ በ1896 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1888 ዓ.ም) ሲሆን በወቅቱ በነበሩት በዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና በንግስት ጣይቱ ብጡል መሪነት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድነት ዘምቶ የጣሊያንን ወራሪ ጦር ድል ያደረገበት ታሪካዊ ክስተት ነው።
ከአራቱም ማዕዘናት የተሰባሰበው የኢትዮጵያ ጦር በዘር፣ በቋንቋና በሃይማኖት ሳይከፋፈል ለሀገሩ ሉዓላዊነት በአንድነት ቆሟል።
ንግስት ጣይቱ የመቀሌን ምሽግ የውሃ መስመር በማስዘጋት የተጫወቱት ሚና እና የአፄ ምኒልክ የጦር አመራር ጥበብ ለድሉ ወሳኝ ነበሩ።
ይህ ድል ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም በቅኝ ግዛት ስር ለነበሩ ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ብርሃን ሆኗል።
"ፓን አፍሪካኒዝም" ለተባለው ንቅናቄም መሰረት ጥሏል።
አድዋ የጦርነት ድል ብቻ ሳይሆን የክብር፣ የማንነት እና የፅናት መገለጫ ነው። ዛሬም ይህንን ታላቅ ታሪክ ስናስብ ያንን የቆየ የአንድነት መንፈስ ለዛሬው ትውልድ በድጋሚ ማደስ ይኖርብናል።
እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ዐድዋ፡- የአፍሪካና የመላው ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ብሩሕ ፋና!!
#ethiopia | ደቡብ አፍሪካዊው የፀረ-አፓርታይድ ታጋይ፣ የነጻነት አርበኛና የዓለም ሰላም ኖቤል ተሸላሚው፣ ኔልሰን ሮሂላላ ማንዴላ- የዐድዋ ድልን ፋይዳና ትሩፋት በተመለከተ፣ በአንድ ወቅት አፍሪካውያን መሪዎች በተገኙበት አንድ ትልቅ የስብሰባ መድረክ ላይ እንዲህ ብለው ነበር፤
"The Adowa Victory provided practical expression to Ethiopianism: self-worth, dignity, unity, confidence, self-reliance, race pride, spirituality, and freedom from colonialism."
ዐድዋ- በሺህ ዘመናት ታሪኳና ቅርስዋ፣ ገናና ሥልጣኔዋና አኩሪ ባህሏ ለምትታወቀው፣ በነጻነቷና በሉዓላዊነቷ ጸንታ የኖረችውን ሀገራችንን ኢትዮጵያን ዳግመኛ በዓለም መድረክ ከፍ ያደረገ ነው።
ዐድዋ የአፍሪካውያን፣ የአፍሪካ አሜሪካውያንና የመላው ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት አለኝታ፣ የወኔና ስንቅ የሆነ፤ ሰው የመሆን ከፈጣሪ ዘንድ የተቸረ መለኮታዊ ፍቅርንና ክብርን ያላቀ ነው፡፡
በርግጥም ኔልሰን ማንዴላ በንግግራቸው ለመጥቀስ እንደሞከሩት ዐድዋ- ለኢትዮጵያዊነት ዝርግፍ ጌጥ፣ የተደነቀ ውበት፣ ሰው የመሆን ክብርንና የመንፈስ ልእልናን ያጎናጸፈ፣ ከዘረኝነት እኩይ እሳቤን የናደ፤ የቅኝ ግዛት ቀምበር እንዲሰበር ያደረገ አንፀባራቂ ድል ነው፡፡
ታሪክ እንደሚነግረን ጥቁር ሕዝቦች ለአፍሪካዊ ማንነታቸው፣ ታሪካቸው፣ ቅርሳቸው፣ ነጻነታቸውና ሉዓላዊነታቸው መከበርና ዕውን መኾን የአኅጉሪቷ እልፍ ልጆቿ ደም እንደ ጅረት ፈሷል፣ አጥንታቸውም ተከስክሷል፡፡
አፍሪካውያንና መላው ጥቁር ሕዝብ በሰስትና በናፍቆት የሚያስቡትና የሚያዩት አረንጓዴው፣ ቢጫውና ቀዩ ሰንደቀ ዓላማችን፣ በጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ክቡር ደም መሥዋዕትነትና አጥንታቸው መከስከስ ያሸበረቀና ያንጸባረቀ ነው፡፡
ተወዳጇ ከያኒ እጅጋየሁ ሽባባው/ጂጂ ‹‹ዓድዋ›› በሚለው ተወዳጅ ዜማዋ ዜማዋ እንዲህ ብላ እንዳጎራጎረችው፤
"… የተሰጠኝ ሕይወት ዛሬ በነጻነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ከአጥንት፡፡
ስንት ወገን ወደቀ፣ በነጻነት ምድር፣
ትናገር ዓድዋ፣ ትናገር አገሬ፣
እንዴት እንደቆምኩኝ በፊታችሁ ዛሬ …፤"
ይህ ዛሬ በነጻነት የቆምንባት ምድር በብዙዎች፣ በእልፎች ክቡር ደም መሥዋዕትነት የጸና መኾኑን ለአፍታ እንኳን ልንዘነጋው አይገባም፡፡ በእነዛ ጥቁር መኾን እንደ ወንጀልና ክህደት በተቆጠረበት አስከፊ ዘመን፤ ለጥቁር ሕዝቦች ከእንሰሳ ያነሰ ክብር እንኳን በተነፈገበት የአፍሪካችን የጨለማና እንደ መርግ የከበደ የመከራ ዘመኗ- አፍሪካውያን የሰው ልጅ ሕሊና ሊሸከመው የማይችል ውርደትና መከራን አሳልፈዋል፡፡
ለዘመናት በእንዲህ ዓይነት ውርደትና መከራ ጀርባዋ ለጎበጠው አፍሪካና ለመላው ጥቁር ሕዝብ- እማማ ኢትዮጵያ አፍሪካውያንና ጥቁር ሕዝቦች ሁሉ በናፍቆትና በሰቀቀን የሚያስቧት፣ በዘላለም ቃል ኪዳን በልባቸው ጽላት የተጻፈች፣ የታተመች ከሩቅ አሻግረው የሚያይዋት አፍሪካዊት የነጻነት ቀንዲል፣ የነጻነታቸውና የሉዓላዊነታቸው የተስፋቸው፣ ምድር ነበረች፡፡
አገራችን ኢትዮጵያን በብዙዎች አፍሪካውያንና በመላው የጥቁር ሕዝብ ዘንድ የነጻነታቸው ተስፋና ብርሃን ተምሳሌት ሆና ከፍ ብላ እንደትታይ ያደረጓት በርካታ ታሪካዊ ሐቆች አሉ፡፡
ኢትዮጵያችን በሺሕ ዘመናት የሚለካው ታሪኳ፣ ጥንታዊና ገናና የኾነ ሥልጣኔዋ፣ ነጻነታቸውን አፍቃሪ ለኾኑ የዓለም ሕዝቦች ተምሳሌት የኾነው የልጆቿ የአይበገሬነት ጽኑ የነጻነት መንፈስ የሚጠቀስ ነው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ የሚነሣው አንጸባራቂው የዓድዋው ድል በግንባር ቀደምትነትና በዋነኝነት የሚጠቀስ ነው፡፡
ይህ መላው አፍሪካ በባርነት ቀንበር ስር ወድቆ በሚማቅቅበት ዘመን፣ ከምሥራቅ አፍሪካዊቷ፣ ጥንታዊት አገር የተሰማው የድል ብስራት፣ ለአውሮፓውያን ቅኝ ገዢዎች ሊሰሙትና ሊቀበሉት የተናነቃቸው ታላቅ መርዶ ነበር፡፡
በ1888 ዓ.ም. ከሮማ ገሥግሦ፣ ቀይ ባሕርን አቋርጦ ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት የመጣው ኃይል በጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ብርቱ ክንድ ተመቶ በታላቅ እፍረት ወደመጣበት ተመለሰ፡፡ ያ አንፀባራቂ የዓድዋ ድልም በጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ውስጥ አዲስ የታሪክ ምዕራፍን ከፈተ፡፡
የዚህ ድል ዜማም በዓለም ዙሪያ ሁሉ ከፍ ብሎ ተሰማ፡፡ በአውሮፓ የሚታተሙ ጋዜጦችም ድሉን አስመልክተው በፊት ገጾቻቸው ዘገቡ፡፡ ቪቫ ምኒልክ! ቪቫ ጣይቱ! የሚሉ የድል ብስራቶችና ዜናዎች በመላው ዓለም ናኙ፡፡
በአፍሪካ፣ በላቲን አሜሪካ፣ በካረቢያንና በጃሜይካ በዓድዋው የድል ስሜትና፣ በኢትዮጵያዊነት የነጻነት ተጋድሎ ሰሜት የተረገዙ ንቅናቄዎችም ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ፡፡ ዓድዋ የአፍሪካውያንና የመላው ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ቀንዲል ኾኖ ደምቆ፣ ፈክቶ አበራ፡፡ በባርነትና በቅኝ ግዛት ስር ኾነው የሚማቅቁ አፍሪካውያንና ጥቁር ሕዝቦችም ከዓድዋው ድል በኋላ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ማሰማት ጀመሩ፡፡
ሁጊንስና ጃክሰን የተባሉ አውሮፓውያን ምሁራን፤ An Introduction to African Civilizations with Main Currents in Ethiopian History, በሚል ርእስ ባስነበቡት መጽሐፋቸው እንደገለጹትም፤
"ዐፄ ምኒልክና የኢትዮጵያ ሰራዊት በኢጣሊያ ቅኝ ገዢ ኃይሎች ላይ የተጎነጸፉት ድል፣ ጥንታውያኑን ኢትዮጵያውያንን ዘመናት ያስቆጠረ ነጻነታቸውንና ሉዓላዊነታቸውን ዳግም በተግባር ያረጋገጠ ድል ነው፤" በማለት ምስክርነታቸውን ሲሰጡ፤
እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆርጅ በርኬሌይ ደግሞ፤ "የዓድዋ ድል ቅኝ ገዢ ተስፋፊ የኾኑ አውሮፓውያን ቆም ብለው እንዲያሰቡ ያደረጋቸው አንጸባራቂ ድል ነው፡፡" በማለት ነበር የገለጸው፡፡
ዐድዋ በቅኝ ግዛት ስር ወድቀው ሲማቅቁ ለነበሩ ለአፍሪካውያንና ለመላው ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ተስፋ ጮራን የፈነጠቀ፣ ለነጻነት ታጋዮች ትልቅ ወኔንና መነቃቃት የፈጠረ ድል ነው፡፡
ዐድዋ ለአፍሪካውያንና ለጥቁር ሕዝቦች ብቻ ሣይሆን ለሰው ልጆች ሁሉ- ሰው የመሆን ከፈጣሪ ዘንድ የተቸረን መለኮታዊ ፍቅርና ክብርን ከፍ ከፍ ያደረገ የድል፣ የነጻት ታላቅ ዓርማ ነው፡፡ ይህ የነጻት ድል በአፍሪካና በመላው ዓለም ሲሰማ፣ ዳግመኛ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በዓለም መድረክ አብቦ፣ ፈክቶና ደምቆ፣ ከፍ ከፍ ብሎ ታየ፡፡
ለመውጫ ያህል፤
የኬንያው የነፃነት ታጋይና ዐርበኛ ጆሞ ኬንያታ ለትምህርት እንግሊዝ አገር በነበሩበት ወቅት የዐድዋን ታላቅ የነጻነት መንፈስ በልባቸው የናኘውን ገጠመኝ እናስታውስ።
ነገሩ እንዲህ ነው። ጆሞ ኬንያታ በዩኒቨርስቲያቸው ቤተ-መጻሕፍት መደርደሪያ ላይ የኢትዮጵያን ታሪክ በሚተርከው መጽሐፍ ውስጥ ያገኙትን የዳግማዊ ዐጤ ምኒልክን ፎቶ ወደ ደረታቸው አስጠግተው በማቀፍ፣ ዓይኖቻቸው በደስታና በሲቃ እንባ ተሞልቶ እንዲህ አሉ፤
"ኦ! ምኒልክ የአፍሪካና ጥቁር ሕዝቦች ኩራት፣ ኦ! ኢትዮጵያ የአፍሪካ ድል ብስራት፣ የነጻነታችን ተስፋ መሬት፣ የልባችን ኩራት… የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ምልክት ታላቁ ንጉሥ ምኒልክ ሁሌም አከብርዎታለሁ!!"
ሰላም!!
ፍቅር እና ክብር የነጻነትን ክቡድ እና ክቡር መንፈስ ከዐድዋ ተራሮች እስከ አፍሪካና ዓለም ጫፍ ድረስ በክብር ለናኙት የዐድዋ ጀግኖች እናቶቻችንና አባቶቻችን ሁሉ!!
ፍቅር እና ክብር የነጻነትን ሕያውና ክቡድ መንፈስ በደማችን ላሰረፁብን፣ ኢትዮጵውያን ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ሁሉ!!
© Terefe Worku

አንገቴን አልደፋም !!
(መላኩ ብርሃኑ)
#ethiopia | ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት በጣም ውድ ነው። ራሴም መሬት የለኝም፡፡ ግን ደግሞ ባለመሬቱ ሁሉ የሃገሬ ሰው ብቻ ነው፡፡ ሄድኩ...ኬንያ፣ ዛምቢያን፣ታንዛኒያን አየሁ፡፡ ....አንተም ቁጠር ከፈለግክ...ሃምሳ ምናምን የአፍሪካ ሃገር ።
በሄድኩበት ያየሁትን ልንገርህ፡፡ ከቦሌ እስከ አብዮት አደባባይ የሚደርስ መሬት ታጥሮ ታያለህ። በሰዓት መቶ ኪ.ሜ በሚበር መኪና ውስጥ ሆነህ ስትጓዝ ራሱ የአጥሩ ርዝመት ይሰለችሃል፡፡
"ይህ መስሪያቤት ምን ይባላል?" ትላለህ ወሬ ለመጀመር። አገሬዎቹ ቀለል አድርገው ይመለሱልሃል።
"የሰር ሪቻርድ ማንትሴ ይዞታ ነው" ይሉሃል። ጭንቅላትህን ይዘህ ጩህ ጩህ ይልሃል፡፡ በመገረምህ ይገረማሉ፡፡
"የሱ እንደውም ትንሹ ነው...የሰር እከሌና ቤተሰቡ ይዞታ ይህንን ያህል 'ኤከር' ይሸፍናል ..." ይሉና በስም የተጠሩት ፈረንጆች በኪሎሜትር ሲሰላ ከአዲስ አበባ ቢሾፍቱ የሚደርስ የሚስል መሬት ባለቤት መሆናቸውን ይነግሩሃል። እኔ ም'ናገባኝ ካላልክ ...በዚህ ወሬ መሃል ፈራ ተባ እያልክ...አጠገብህ የተቀመጡ የሙያ ጓዶችህን ዘወር ዘወር እያልክ እያየህ አንድ ጥያቄ ትጠይቃቸዋለህ።
"እናንተስ ምን ያህል መሬት አላችሁ?"
....እርስ በርስ ተያይተው ይሳሳቃሉ።
"ብራዳ ! (ብራዘር)" ይሉሃል...እዚህ ጋር ቁጭታቸውን መተንፈስ የፈለጉ ይመስልሃል፡፡
"...እኛ ሃገር ሰፋ ሰፋ ያለው መሬት የነሰር እከሌ ነው" ይሉሃል፡፡ " መሬቱም ሪልእስቴቱም የነጮች ነው፡፡ እኛ ብዙም ሃብታም አይደለንም፡፡ ብዙዎቻችን ግን እነርሱ ጋር ተቀጥረን እንሰራለን....መሬትና ሃብት ከኛ 'ማይልስ አዌይ' ናቸው" ይሉሃል። ቁጥር ጠቅሰው፡፡ ያው እየሳቁ ነው የሚነግሩህ፡፡ በሳቃቸውና በፌዛቸው ውስጥ ግን ፊታቸው ላይ ከባድ ጸጸት እና ቁጭት ካላየህ እኔ ልቀጣ፡፡
ያኔ የሆነ ደስ የማይል ነገር ውስጥህን ውርር ያደርገዋል...የነዚህን ሰዎች ስነልቡና ቀደም ባሉት ቀናት ጥቂት ታዝበሃል ፡፡ ሆቴል ገብታችሁ ወደሩም የሚወስዳችሁን ሊፍት ልትሳፈሩ ቆማችሁ ሳለ...አንድ ነጭ ሲመጣ ለሱ ቅድሚያ ሰጥተው እነሱ ሲቀሩና ሊፍቱ ሞልቶ ጥሏቸው ሲሄድ አይተሃቸዋል፡፡አንተ ግን የጎንዩሽ ካዩህ ነጮቹ ጋር ሊፍቱ ውስጥ ተሳፍረሃል፡፡እነሱ ለምን ቀሩ?
... ደግሞም የሆነ ነገር ሰምተሃል፡፡"እዚያ ሃገር እኮ አንድ ነጭ እቃ ከጁ ቢወድቅበት ጥቁሩ የሃገሩ ዜጋ እቃውን አንሰቶ ይሰጠዋል" ብለውሃል፡፡ ለዚያውም 'ሶሪ' ብሎ !
ገንዘብ እያላቸው...ስልጣኔ ካንተ በተሻለ ገብቷቸው...ምናልባትም ጥሩ ቤትና መኪናም ኖሯቸው ....ግን ዝም ብሎ የሆነ የጎደላቸው ነገር እንዳለ ታያለህ፡፡ እነርሱ ያሉበትን ስነልቡና ብዙም 'ፊል' አያደርጉትም፡፡
በዚህ መሃል ወደራስህ ማንነት ስታስብ ነው የሆነ 'ኩራት ኩራት' የሚልህ..."ኢትዮጵያዊነትን ከነትርጉሙ ጮክ ብለህ ለሁሉም ንገር ንገር ፣ ለሃገሩ ህዝብ ሁሉ ለፍፍ ለፍፍ" ይልሃል፡፡ በቃ ጮክ ብለህ መደስኮር ያምርሃል።
" አንድ ነገር ልንገራችሁ ወንድሞች ?...እኔ ሃገር ኢትዮጵያ ብትመጡ አንድ ነጭ ዜጋ እንኳን ይህን ያህል መሬት ቀርቶ በስሙ አንድ ክፍል ቤት እንኳን ሊኖረው አይችልም" ስትላቸው ጆሯቸው ይቆማል፡፡ ያኔ ዋናውን ወሬሀን እዚህ ላይ እንደቦምብ ጣል ታደርጋለህ፡፡
"እኛ በጣም ድሆች ብንሆንም ሃገራችን ውስጥ ያለነው ሃብታሞች ግን እኛ ብቻ ነን፡፡ እኛው ራሳችን ብቻ ። ህንጻውም ፣ መሬቱም ጠቅላላ ሃብቱም ምንም ይሁን ምን የማንም ሳይሆን በኛው በኢትዮጵያውያውያን ብቻ የተያዘ ነው" ትላለህ፡፡ ስለብሄራዊ ኩራት ማውራት ስትጀምር ሃገርህ ውስጥ ያለው የድሃና ሃብታም ኑሮ ልዩነት... የመንግስት ጡንቻና ሞኖፖሊ.... የመሬትና ቤት 'ላም አለኝ በሰማይነት'...ሌሎች ሌሎች ቅሬታዎችህ ትዝ አይሉህም፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖም የነጭ ተገዢነት ስነልቡና ጫፍህም እንዳልደረሰ አስበህ ብቻ ነው የምትኩራራው፡፡
ይህንን 'ዲስኩርህን' ሰምተው እርስ በርስ ይተያዩና ስላንተና ስለሃገርህ የሚያውቁትን የሆነ ነገር ሲሉህ ...ያኔ ጀነን ማለት ይቃጣሃል፡፡ "ዩ አር ፍሮም ኢቶቢያ...ዛትስ ሁዋይ! " ሲሉህ የሞቀ ደምህ አናትህ ወጥቶ በደስታ ሲያሰክርህ ይሰማሃል።
ያውቁታል እነሱ ... በድፍን አፍሪቃ ውስጥ ያልተገዛ አንድ ህዝብ ማን እንደሆነ ያውቁታል፡፡ የተገዢነት ስነልቡና ያላዳሸቀው አዕምሮ የማን ብቻ እንደሆነ ያውቁታል፡፡ አባቶችህ በማንም ነጭ ፊት በቀለመህ ሳትሳቀቅ አንገትህን ቀና አድርገህ እንድታወራ ስላደረጉህ ...በኩራት የምትናገረው ታላቅ ታሪክ ባለቤት ስላደረጉህ የምታመሰግናቸው ያኔ ነው ...በጣም በርግጠኝነት!
እስኪ አንዴ ወጣ በል ከሃገርህ...ብዙ ሳትርቅ እዚሁ ጎረቤት ሃገር ሂድ። የምታገኛቸው አፍሪካውያን ወንድሞችህ አንተ አማራ ሁን ኦሮሞ፣ ከንባታ ሁን ሃዲያ፣ ትግሬ ሁን ምንትስ የሚያውቁልህ ምንም ነገር የለም። አንድ የሚያውቁት ነገር ከኢትዮጵያ መምጣትህንና ኢትዮጵያዊ መሆንህን ብቻ ነው ።
ሳልዋሽ እነግርሃለሁ፡፡ ድህነትህን ባይረሱልህም ይህንን ያንተን ማንነት በአደባባይ የሚያደንቁት፣ ለራሳቸው ጭምር የሚመኙት ማንነት ነው።
ብዙዎቹ አፍሪቃውያን እጅግ ደስ ብሏቸውም...አንዳንዶቹ ሳይወዱ በግድም... ብቻ በምንም ስሜት ውስጥ ሆነው የነጻነትህንም፣ የጀግና አባቶችህ ልጅ መሆንህንም ፣ ከጥቁር ህዝቦች የነጻነት ቀንዲል ሃገር የመጣህ ጀግና መሆንህንም .... ይህንን ሁሉ 'ኢትዮጵያ' የሚል ስም ጠርተው ለአንተ ያወርሱሃል፡፡ ይህንን የሚያደርጉት ግን ብሄርህን ቆጥረው ሳይሆን "ኢትዮጵያዊ ነህ" ብለው በታሪክ በሚያውቁህ ማንነትህ ስለተቀበሉህ ብቻ ነው።
አፍሪቃውያን ስለሃገርህ ኢትዮጵያ ማውራት ስትጀምር አፋቸውን ከፍተው የሚያዳምጡህ ወሬህ አንድ ነገር ላይ ያነጣጠረ ከሆነ ብቻ ነው። ስለሆቴልህ፣ ስለፋብሪካህ...ስለመንገድህ...ስለመንግስትህ፣ ስለትምህርትህ መስማት ደንታቸው አይደለም። ቅኝ ገዢዎቻቸው እየዘረፏቸውም ቢሆን ከተሞቻቸውን አልምተውላቸው ነው የሄዱት፡፡ መዘመንና ዘመናዊነት ለብዙዎች በቅኝ ለተገዙ የአፍሪቃ ከተሞች ብዙ ብርቅ አይደለም፡፡ ግን ዘመናዊነትን እየኖሩበትም እንደ ባዶ ቅል ነው። ካንተ ይበልጥ በአይናቸው ያዩት ....ነገር ግን ውስጡ ሆነው በደስታ ያልኖሩበት ፡፡ እነርሱ በፈተፈቱት ሌላ የሚጎርስበት ስልጣኔ ነው በሃገራቸው ያለው።
ወሬ ስትጀምር 'እህ!' ብለው... አይናቸውንም ቀልባቸውንም ተክለው የሚያደምጡህ መቼ መሰለህ? ... "ነጭ ልክ ነው" የሚል የሃበሻ አባዜህን ለጊዜው ሸሽገህም ቢሆን በሃገርህ አንተና አንድ ነጭ ያላችሁን ልዩነት ስትነግራቸው ብቻ ነው።
ስማኝማ! ....በጋዜጠኝነቴ እድል ገጥሞኝ ባየኋቸው የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ የሚገጥመኝ ነገር በአብዛኛው የነገርኩህን አይነት ታሪክ ነው።በሌላ በኩልም ሃገሬ ቅኝ ባለመገዛቷ ደሃ ሆነን መቅረታችንን አምነው ለኔ ለመንገር በጣም የሚዳፈሩም ገጥመውኛል፡፡
ሁለት ሶስቴ ስለተመላለስኩባት እንደሁ እንጃ ....ግን ኬኒያ ዝም ብዬ ደስ ትለኛለች። አገሪቷ በደንብ ሰልጥናለች። ኑሮው በአይን ሲያዩት ይመቻል። እኛ ጋ ብርቅ የሆነ ሁሉ እዚያ የሰለቸ ነገር ነው። 'ሞል' ብለህ ከምትጠራው ገበያ አቅም እዚህ ኢትዮጵያ ስሙ ፣ እዚያ ግን ራሱ በአካል አለ። ቀላሉን ምሳሌ ልንገርህ ብዬ ነው።
ግን ደግሞ ህዝቡን ጠጋ ብለህ አውራው። የሚነግርህ ነገር ይደብርሃል። በገዛ ሃገሩ ላይ የምር ኑሮ እየኖረ አይመስልህም...100 ዓመት የገዛችው እንግሊዝ ወደፊት ለመቶ አመት ቀድማ የጥቁር ኬንያዊነት ኩራት ሰርቃው ሄዳለች በቃ።
ከብዙ ገጠመኞቼ አንዱን ልምዘዝልህማ! ...ባለፈው ናይሮቢ የሄድኩ ጊዜ አንድ መካነ አራዊት ለመጎብኘት ከወዳጆቼ ጋር ወጣሁ። sheldrik elephant orphanage ይሉታል ቦታውን። ስደርስ ወደውስጥ ለመግባት በር ላይ ወረፋ አስያዙኝ። ነጮቹ ከኋላቸው ስትሰለፍ ጥቁር በመሆንህ ብቻ ቦርሳቸውን ጠበቅ አድርገው ይይዛሉ። በጣም ይደብራል።
ተራ ደርሶኝ ጠጋ አልኩ። አንዲት ነጭ አሮጊት ዴስክ ላይ ተቀምጣ ከእያንዳንዱ ጎብኚ 27 ዶላር መግቢያ ትቀበላለች። ቀና ብዬ ሳይ ገንዘብ መቀበያ ጎጆ መሳይ ቤት ላይ የፓርኩ ባለቤት ስም በትልቁ ተጽፏል። 'ሰር ዴቪድ ሼልድሪክ' ምናምን የሚባል እንግሊዛዊ ሰውዬ ነው። አስታውስ...ያለሁት ሎንዶን ሳይሆን ናይሮቢ ነው።
ለጉብኝት የተሰለፈ ጥቁር እያየሁ ግርምት ይሁን ምን ያልገባኝ አይነት ስሜት ውስጥ ነኝ ። ብቻ የአፍሪካን ዝሆን ለማየት ለአንድ የአውሮፓ ነጋዴ ዶላር ከፍዬ ገባሁ። ገብቼ ወደውስጥ ሳይ የነጭ መዓት ተሰብስቦ የሚያየው ትዕይንት በጣም ያሳቅቃል፡፡ የዝሆን አልሞሌዎችን በግዙፍ ጡጦ ወተት የሚያጠጡ የተጎሳቆሉ ጥቁር ኬንያውያን ሰራተኞችን እንደጉድ እያየ ይዝናናል።
የሆነ ነገሬ ሲደብረኝ ይታወቀኛል።የምሬን ነው። ዝሆን በቁሙ ሳይ የመጀመሪያዬ ቢሆንም አይኔ ያፈጠጠው ግን እነዚያ ከዝሆኑ ጋር ሲታገሉ በጭቃ የተጨማለቁ ጥቁሮች እና ህይወት የሰለቸው የመሰለ ፊታቸው ላይ ነው። በቆሻሻ ቱታ፣ በጭቃ በላቆጠ ቦቲ ጫማ ውስጥ ሆነው በአካባቢያቸው ለሚሆነው ሁሉ ስሜታቸው በድን፣ አይናቸውም ህይወት አልባ ሆኗል።ከዝሆን ጋር ይታገላሉ፡፡
በገዛ ሃገርህ፣ አምላክ በቸረህ በገዛ የተፈጥሮ ሃብትህ፣ እትብትህ በተቀበረበት በገዛ መሬትህ አንድ ነጭ ይቀጥርህና ሁሉንም ነገርህን ጠራርጎ ወስዶ ጉልበትህን በቀላል ክፍያ እየተገለገለ ይነግድብሃል። 27 ዶላር ከእያንዳንዱ ጎብኚ እየተቀበለ ለነዚህ ሰራተኞች በወር የሚከፍለው ስንት ሽልንግ እንደሆነ ግን የኬንያ እግዜር ይወቅ።
እናስ አያስጠላም? ....ይህ በአንተ ሃገር ላይ ቢሆንስ? እንደአንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ልብህ ፈቅዶ ይቀበለዋል?...አምጽ አመጽ አይልህም? ...አብዮት አያምርህም?...ምቾት ይሰጥሃል ?...አንተ ብትሆን የዚህን ትዕይንት ፈተና ቆመህ መጋፈጥ ትችለዋለህ? እነዚያን ጥቁር ወንድሞችህን እንደሌሉ ቆጥረህ የዝሆን አልሞሌዎች ጡጦ ሲጠቡ እያየህ ትፈነድቃለህ?...ትዝናናለህ?
ትንሽ ወጣ አልኩ መሰለኝ...በፈረንጆቹ መሃል ቆሜያለሁ...አጉረመረምኩ ፡፡ እኔ የሰው ሃገር ነጻነት ታጋይ አይደለሁ...ቼ ጉቬራ አይደለሁ...ግን ለነሱ ነጻነት ተመኘሁ፡፡
አጠገቤ ያሉት ...ሃገሩንና ህዝቡን 'ፎርግራንትድ' የወሰዱ የመሰላቸው እንግሊዝ መሳይ ፊት ያላቸው ነጮች ሁሉ ብዙ ጉዳዬ አላሉኝም...ዝም ብለው ግልፍጥ ነገር ናቸው!!...ሜርድ ነገር !!
እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ...ለጊዜው ዳቦ ዋናው ጥያቄዬ ሆኖ ቢቀጥልም ክብርና ኩራቴ ግን የዘለዓለም እጣ ፈንታዬ ነው።አባቶቼ በደማቸው የሰጡኝ፣ መላው አፍሪቃዊ ያጸደቀለኝ፣ የኩሩ ሃገር ዜጋ፣ የአድዋ ጀግኖች አባቶቼ ልጅ ነኝ።
ለዚህ ማዕረግ ያበቃሽኝ ዓድዋ ....ለዘለዓለም ኑሪልኝ!!
ይህንን ሞገስ እንዳገኝ ምክንያት የሆንከኝ ...ሃገሬን ከመበታተን፡ እንጀራዬን ከፓስታ ያተረፍክልኝ የአንድነትና የነጻነት ንጉስ አጼ ምኒሊክ ስምህ ይክበር።
አንገት በተደፋባት አህጉር የኔ አንገት ብቻ ቀና ያለው በአባቶቼ ደምና አጥንት ነው!!
ይኸው ነው!!

8 months ago
የእቴጌ ጣይቱ ህይወት የመጨረሻው ምዕራፍ የካቲት 4 ቀን 1910 ዓ.ም ተፈጸመ። ስጋቸው በእንጦጦ ማርያምና በኋላም በበዓታ ለማረፍ ቢበቃም፣ ስማቸውና ዝናቸው ግን ለዘላለም በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ታትሞ ይኖራል። የእሳቸው ታሪክ የሞት ታሪክ ሳይሆን፣ የህያውነትና የድል ታሪክ ነው። በዛሬው ትውልድ ውስጥ የጣይቱ መንፈስ ዳግም ሊቀሰቀስ ይገባል። ሀገራችን በፈተና ውስጥ ባለችበት በዚህ ወቅት፣ እንደ ጣይቱ ያለ ቆራጥነትና ሀገራዊ ፍቅር ካልተላበስን የአድዋን ድል መዘከር ብቻውን ትርጉም አይኖረውም።
"ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ" የሚለው ቅጽል ስም በትክክል ይገልፃቸዋል። ሀገሪቱ በጨለማና በቅኝ አገዛዝ ስጋት ውስጥ በነበረችበት ወቅት፣ እርሳቸው ብርሃን ሆነው መርተዋል። ዛሬም ቢሆን የሀገራችንን ችግሮች ለመሻገር እንደ ጣይቱ አይነት አርቆ አሳቢነት፣ እንደ ጣይቱ አይነት "ለሀገሬ አልደራደርም" የሚል ፅናትና እንደ ጣይቱ አይነት ፍፁም ኢትዮጵያዊነት ያስፈልገናል። ትውልዱ ከጣይቱ ሊማር የሚገባው ትልቁ ቁምነገር፣ ታሪክ የሚሰራው በንግግር ሳይሆን በተግባር መሆኑን ነው።
የእቴጌ ጣይቱ ብጡል ክብርና ዝና ለዘላለም በኢትዮጵያ ምድር ላይ ይኑር!!

ከጎንደር እስከ በርሊን፤ የጥቁር ሕዝቦች ድምፅ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ የዓለም አቀፉን የክብር ሽልማት ተቀበሉ
አዲስ አበባ — ታዋቂው ኢትዮጵያዊ የፊልም ባለሙያ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ በፊልም ጥበብ ዓለም ከፍተኛ ስም ካላቸው ሽልማቶች መካከል አንዱ የሆነውን «የበርሊን ካሜራ» (Berlinale Camera) የክብር ሽልማት ትናንት ማክሰኞ በጀርመን በርሊን ተቀብለዋል።
ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ የተወለዱት በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ ሲሆን እድገታቸውም በዚያው ነበር። አባታቸው አቶ ገሪማ ታፈረ ታዋቂ ደራሲና የታሪክ ተመራማሪ መሆናቸው ለኃይሌ ገሪማ ገና በልጅነታቸው ለታሪክና ለተረት ትረካ (Storytelling) ፍቅር እንዲያድሩ ትልቅ መሠረት ጥሎላቸዋል።
ይህ ከኢትዮጵያ ምድር የቀሰሙት የማንነትና የታሪክ እውቀት ነው ዛሬ ለደረሱበት ዓለም አቀፍ ዝና እና ለጥቁር ሕዝቦች ድምፅ የመሆን ብቃት ያበቃቸው።
የሽልማቱ ምክንያቶች፦
የበርሊን ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል (Berlinale) ለፕሮፌሰሩ ይህንን ታላቅ የክብር ሽልማት የሰጠው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፦
* የታሪክ ድምፅነት፦ በአፍሪካ ታሪክ፣ በቅኝ አገዛዝ፣ በማንነት እና በማኅበራዊ ፍትህ ላይ ላላቸው ጽኑ አቋም እና ታሪክን በፊልም የመተረክ ልዩ ብቃታቸው።
* የአፍሪካውያን ድምፅ፦ የአፍሪካውያንን እና የጥቁር ሕዝቦችን ታሪክ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ከፍ አድርገው በማሰማታቸው።
* መምህርነት፦ በሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ ለበርካታ አስርት ዓመታት በማስተማር በርካታ ወጣት የፊልም ባለሙያዎችን በማፍራታቸው።
ፕሮፌሰር ኃይሌ በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ «Black Lions – Roman Wolves» (ጥቁር አንበሶች ፤ የሮማ ተኩላዎች) የተሰኘውን አዲሱን የፊልም ፕሮጀክታቸውን አስተዋውቀዋል።
ይህ ፊልም እንደ ቀደሙት ዝነኛ ሥራዎቻቸው («ሰንኮፍ» እና «ጤዛ») ሁሉ የኢትዮጵያን የጀግንነት ታሪክ ለዓለም እንደሚያሳውቅ በትልቅ ጉጉት ይጠበቃል።
ይህ ሽልማት ለኢትዮጵያ የጥበብ ሰዎች ትልቅ መነሳሳት የሚፈጥርና የፕሮፌሰሩን የዕድሜ ልክ ቁርጠኝነት የዘከረ ነው።
የኔታ ሚዲያ ለሀገራችን ኩራት ለሆኑት ለፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ "እንኳን ደስ አልዎት" ይላል።
የኔታ ሚዲያ #hailegerima #berlinale2026 #ethiopia #የኔታ #የጥበብ_ሰው

🏆🎬 «የበርሊን ካሜራ» (Berlinale Camera) የክብር ሽልማት
#ethiopia | ፌስቲቫል (Berlinale) ላይ ለፊልም ጥበብ ዕድገት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለሙያዎች የሚሰጠውን «የበርሊን ካሜራ» (Berlinale Camera) የክብር ሽልማት ትናንት ማክሰኞ ተቀብለዋል።
ፕሮፌሰር ኃይሌ ለምን ተሸለሙ?
📜 የታሪክ ድምፅ፦
በአፍሪካ ታሪክ፣ በቅኝ አገዛዝ፣ በማንነት እና በማኅበራዊ ፍትህ ላይ ላላቸው ጽኑ አቋም እና ታሪክን በፊልም የመተረክ ብቃታቸው።
🌍 የአፍሪካውያን ድምፅ፦
የአፍሪካውያንን እና የጥቁር ሕዝቦችን ታሪክ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ከፍ አድርገው በማሰማታቸው።
🎓 መምህርነት፦
በሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ ለበርካታ አስርት ዓመታት በማስተማር በርካታ ወጣት የፊልም ባለሙያዎችን በማፍራታቸው።
አዲሱ የፊልም ፕሮጀክት፦
በሽልማት ስነ-ሥርዓቱ ላይ ፕሮፌሰሩ «ጥቁር አንበሶች ፤ የሮማ ተኩላዎች» (Black Lions – Roman Wolves) የተሰኘውን አዲሱን የፊልም ፕሮጀክታቸውን አስተዋውቀዋል።
ይህ ፊልም እንደ ቀደሙት ሥራዎቻቸው («ሰንኮፍ» እና «ጤዛ») ሁሉ የኢትዮጵያን የጀግንነት ታሪክ ለዓለም እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል።
ይህ ሽልማት ለኢትዮጵያ የጥበብ ሰዎች ትልቅ መነሳሳት የሚፈጥርና የፕሮፌሰሩን የዕድሜ ልክ ቁርጠኝነት የዘከረ ነው።
እንኳን ደስ አላችሁ!
ለሀገራችን ኩራት ለሆኑት ለፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ያለን አድናቆት የላቀ ነው።
#hailegerima #berlinale2026 #berlinalecamera #ethiopiancinema #africanfilm #teza #sankofa #blacklionsromanwolves #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Comments