Logo
Getu Temesgen
ሞቃዲሾ ምርጫ ስታደርግ ዋለች
#ethiopia | የብሪታኒያ ሶማሊላንድ እና የኢጣሊያ ሶማሊላንድ በሚል ለሁለት ተከፍላ በቅኝ ስትተዳደር የነበረችው ሶማሊያ ነጻነቷን ካገኘችበት 1960 ወዲህ ለተከታይ ዓመታት መደበኛ ምርጫን ስታደር ቆይታለች።

በ1969 የተደረገው ምርጫ ከተከወነ ከወራት በኋላ ወታደራዊ አዛዡ ጄነራል ሞሐመድ ሰዒድ ባሬ የመሩትን መፈንቅለ-መንግሥት ተከትሎ እርሣቸው በሥልጣን ላይ እስከቆዩበት 1991 ድረስ ሶማሊያ በወታደራዊ አገዛዝ ስር ከርማለች።

እርሣቸው ከሥልጣን ከተነሱ በኋላ በጎሣ እና ኃይማኖት በተከፋፈሉ ታጣቂዎች ስትታመስ የቆየችው ሶማሊያ፣ በ2004 የጎሣ ተወካዮች በሚሠጡት ድምጽ መሪዎቿን ስትመርጥም ቆይታ ነበር።

ከዚህ ዓመት ጀምሮ ግን ይህን የምርጫ መንገድ በመተው ቀጥተኛ ምርጫን ለማድረግ በተወሰነው መሠረት በመዲናዋ ሞቃዲሾ ድምጽ ሲሰጥ መዋሉን ያስነበበው ኢስት አፍሪቃ ኒውስ ነው ሲል። #tirtafm

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.