3 months ago
የዓድዋ ድል መታሰቢያን የጎበኘው ‘ዲላን ፔጅ’ ኢትዮጵያ በቅኝ ያልተገዛችበትን ታሪካዊ ዳራ በአድናቆት ተመልክቶታል
**********************
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮችን ያፈራው እንግሊዛዊው የቲክቶክ ተፅዕኖ ፈጣሪ ‘ዲላን ፔጅ’ በኢትዮጵያ እያደረገው ባለው ጉብኝት የሀገራችንን ገጽታ ለዓለም በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል።
ዲላን በአዲስ አበባ ቆይታው የወንዝ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በመዲናዋ የተከናወኑ ቁልፍ የልማት ሥራዎችን እና የቱሪስት መዳረሻዎችን ተዟዙሮ ተመልክቷል።
በጉብኝቱ መሃል በአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት መስክ አረንጓዴ ዐሻራውን በማሳረፍ የልማት ተሳትፎውን በማኅበራዊ ሚዲያ ለተከታዮቹ አጋርቷል።
ዝነኛው ቲክቶከር በፒያሳ የሚገኘውን የዓድዋ ድል መታሰቢያም የጎበኘ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ያልተገዛችበትን ታሪካዊ ፋና በአድናቆት ተመልክቷል።
በስፍራው ሲደርስ ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን፤ በባህላዊ የአፈላል ሥነ-ሥርዓት የተዘጋጀለትን የኢትዮጵያ ቡና ከመቅመስ በተጨማሪ የመታሰቢያ ስጦታዎች ተበርክተውለታል።
ዲላን ስለኢትዮጵያ ጉብኝቱ በሰጠው አስተያየት፣ ጉብኝቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስለ አፍሪካ ያለውን የተዛባ አመለካከት ለመቀየር የሚያግዝ እንደሆነም ተናግሯል።
ተፅዕኖ ፈጣሪው ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ወደፊት ሐረር እና አፋርን ጨምሮ የተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎችን ለመጎብኘት ያለውን ፍላጎት ገልጿል።
በቢታኒያ ሲሳይ
#dylanpage #ethiopia #addisababa #adwa #adwavictorymemorial #corridordevelopment #riversidedevelopment #greenlegacy #ebc

ጆኒ በ1ኛው ዙር አሸነፈ
* የ1 ሚሊዮን ብር የቦነስ ሽልማትም ተረከበ
* የንቃተ ህሊና ድፍረትና ፍልሚያ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የስፖርት ታሪክ የመጀመሪያው ፕሮፌሽናል የድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ውድድር በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በዛሬው ዕለት በከፍተኛ ድምቀት ተካሂዷል። በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የጆኒ ጁጁትና የንቃተ ህሊና ፍልሚያ በጆኒ አሸናፊነት ተደምድሟል።
ጆኒ ውድድሩ በጀመረ ጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ንቃተ ህሊናን መሬት ላይ ጥሎ በመደብደብ የቴክኒክ ብቃቱን አስመስክሯል። ከድሉ በኋላም "ማርሻል አርቲስት ነኝ የምትሉ ሁሉ አስልፌ እቀጠቅጣችኋለሁ" ሲል በኩራት ተደምጧል።
ከቦንጋ ተነስቶ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የቆመው ንቃተ ህሊና፣ ራሱን በኢንተርኔት ቪዲዮዎች አዘጋጅቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሮፌሽናል መድረክ መርገጡ ለብዙዎች መነቃቃትን ፈጥሯል። "ሽንፈት መነሻዬ ነው" በሚል መንፈስ ዳግም እንደሚመለስ ቃል ገብቷል።
ጆኒ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ወርቃማ ታሪኩን ጽፏል።
የዳኞችና የአዘጋጆቹ ከጆኒ ጋር ያላቸው ቅርበት እንዲሁም በንቃተ ላይ የታየው የስነ-ልቦና ጫና በውድድሩ ፍትሃዊነት ላይ ጥርጣሬ ፈጥሯል የሚሉ የስፖርት ቤተሰቦች አስተያየት ነበር።
በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የተካሄደው የታላቁ የድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ፍልሚያ በጆኒ አስደናቂ የበላይነት ተጠናቋል።
መላው አዲስ አበባ በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው ይህ መድረክ፣ ለጆኒ ታሪካዊ ድልን አጎናጽፎታል። የአሸናፊነት የክብር ቀበቶም ታጥቋል።
ታዛቢዎች ውድድሩ ለውድድሩ ድምቀት የተደረገ "ለኮፍ ለኮፍ" ነው ቢሉም፣ ክስተቱ ግን ለኢትዮጵያ MMA አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል።
መሸነፍ መጨረሻ አይደለም፤ ለመቧቀስ መድረኩ ላይ መገኘት ራሱ ድል ነው። ንቃተ ህሊና ፍርሃትንና ግፊትን አሸንፎ መድረክ ላይ መቆሙ የጀግንነት አክሊል ነው።
ነገ የታሪክ መጀመሪያ ሊሆን ይችላል!
ውድድሩ በሀገራችን ለሜክስድ ማርሻል አርት (MMA) ስፖርት እድገት አዲስ በር፤ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል።
#getu #mmaethiopia #johnnyvsnkate #nkatehilina #sweetbox #boxingethiopia #adwavictorymemorial #mixedmartialarts #ጆኒ #ንቃተህሊና #ፍልሚያ #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments