የዓድዋ ድል መታሰቢያን የጎበኘው ‘ዲላን ፔጅ’ ኢትዮጵያ በቅኝ ያልተገዛችበትን ታሪካዊ ዳራ በአድናቆት ተመልክቶታል
**********************
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮችን ያፈራው እንግሊዛዊው የቲክቶክ ተፅዕኖ ፈጣሪ ‘ዲላን ፔጅ’ በኢትዮጵያ እያደረገው ባለው ጉብኝት የሀገራችንን ገጽታ ለዓለም በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል።
ዲላን በአዲስ አበባ ቆይታው የወንዝ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በመዲናዋ የተከናወኑ ቁልፍ የልማት ሥራዎችን እና የቱሪስት መዳረሻዎችን ተዟዙሮ ተመልክቷል።
በጉብኝቱ መሃል በአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት መስክ አረንጓዴ ዐሻራውን በማሳረፍ የልማት ተሳትፎውን በማኅበራዊ ሚዲያ ለተከታዮቹ አጋርቷል።
ዝነኛው ቲክቶከር በፒያሳ የሚገኘውን የዓድዋ ድል መታሰቢያም የጎበኘ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ያልተገዛችበትን ታሪካዊ ፋና በአድናቆት ተመልክቷል።
በስፍራው ሲደርስ ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን፤ በባህላዊ የአፈላል ሥነ-ሥርዓት የተዘጋጀለትን የኢትዮጵያ ቡና ከመቅመስ በተጨማሪ የመታሰቢያ ስጦታዎች ተበርክተውለታል።
ዲላን ስለኢትዮጵያ ጉብኝቱ በሰጠው አስተያየት፣ ጉብኝቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስለ አፍሪካ ያለውን የተዛባ አመለካከት ለመቀየር የሚያግዝ እንደሆነም ተናግሯል።
ተፅዕኖ ፈጣሪው ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ወደፊት ሐረር እና አፋርን ጨምሮ የተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎችን ለመጎብኘት ያለውን ፍላጎት ገልጿል።
በቢታኒያ ሲሳይ
#dylanpage #ethiopia #addisababa #adwa #adwavictorymemorial #corridordevelopment #riversidedevelopment #greenlegacy #ebc

5 months ago