Logo
EBC
ከምድር ባቡር ፉጨት እስከ ዲጂታል አድማስ፦ ከአንድ ክፍለ ዘመን የተሻገረው የኢትዮ-ፈረንሳይ የማይበጠስ ወዳጅነት!
*********************

ከንጉሥ ሳህለ ሥላሴ የሸዋ ግዛት እስከ ዘመናዊቷ ኢትዮጵያ፣ ከታላቁ ገጣሚ አርተር ራምቦ የሐረር ቆይታ እስከ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የትላንትናው ታሪካዊ ጉብኝት... በቅኝ ግዛት ያልተበከለውና በእኩልነት ላይ የተመሠረተው የኢትዮጵያና የፈረንሳይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዴት ዛሬም ድረስ እንደጸና አለ!

በዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ የሀገራት ግንኙነት እንደየዘመኑ የፖለቲካ ንፋስ መዋዠቅ እና መለዋወጥ የተለመደ ክስተት ነው።

ነገር ግን፣ ከክፍለ ዘመናት መፈራረቅ፣ ከርዕዮተ ዓለም ለውጦች እና ከዓለም አቀፍ ቀውሶች ተርፈው በጽኑ መሠረት ላይ የሚቆሙ ጥቂት የማይበጠሱ የወዳጅነት ገመዶች አሉ።

ከእነዚህ ብርቅዬ ታሪካዊ ትሥሥሮች መካከል የኢትዮጵያ እና የፈረንሳይ የሁለትዮሽ ግንኙነት በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው።

ይህ ግንኙነት የተፀነሰው በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንደታየው በቅኝ ግዛት ጌታና ሎሌነት ሳይሆን፣ በሁለት ሉዓላዊ እና ገለልተኛ መንግስታት መካከል በነበረ ፍፁም የእኩልነት መርሕ ላይ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።

የዚህን መረጃ ሙሉ ሐሳብ አስተያየት መስጫው ውስጥ ካለው ሊንክ ያገኛሉ፦
#ebc #ethiopia #france #diplomacy #relations

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.