"አፍሪካን ያገለለ የዓለም ሥርዓት ጊዜው አልፎበታል!" ሲሉ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ተናገሩ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በአዲስ አበባው የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ አህጉሪቱ በዓለም አቀፍ መድረክ የሚገባትን የክብር ቦታ እንድታገኝ ጠንከር ያለ ጥሪ አቀረቡ።
ዋና ፀሐፊው አሁን ያለው ዓለም አቀፍ አወቃቀር "ፍትህ የጎደለውና አፍሪካን የረሳ" መሆኑን በግልጽ ተችተዋል።
ሆኖም "ምክር ቤቱ የተዋቀረው አፍሪካ በቅኝ ግዛት ቀንበር ስር በነበረችበት ዘመን ነው" ያሉት ጉተሬዝ፣ አህጉሪቱ ቢያንስ ሁለት ቋሚ መቀመጫዎችን ማግኘት እንዳለባት አሳስበዋል።
የዓለም የፋይናንስ ሥርዓት ለሀብታም አገራት ብቻ የተመቸ መሆኑንና አፍሪካን ለከፍተኛ የብድር ወለድና ለኢኮኖሚ ቀውስ እየዳረጋት መሆኑን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ማዕድናትና ሀብቶች የሚበዘበዙበት ታሪክ አብቅቶ፣ አህጉሪቱ ያላትን የታዳሽ ኃይል አቅም ለመጠቀም የረጅም ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ ሊደረግላት ይገባል ብለዋል።
በአፍሪካ ሕብረት ለሚመሩ የሰላም ማስከበር ስራዎች የተባበሩት መንግሥታት የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግ የሚፈቅደው ውሳኔ 2719 መጽደቁን እንደ ትልቅ ድል ጠቅሰውታል።
"የአፍሪካ ጉዳይ እስከ መጨረሻው የሥራ ዘመኔ ድረስ የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባሬ ነው!" ሲሉም አንቶኒዮ ጉተሬዝ በማጠቃላያ ሃሳባቸው ላይ አንስተዋል።
ይህ መግለጫ ተራ ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ብቻ አይደለም። አፍሪካ በዓለም ፖለቲካና ኢኮኖሚ ላይ ያላት ተፅዕኖ እያደገ በመጣበት በዚህ ወቅት፣ የተባበሩት መንግሥታት ቁንጮ መሪ እንዲህ ያለ ግልጽ ወገንተኝነት ማሳየታቸው ለለውጥ ትልቅ ግፊት ይፈጥራል ተብሏል ።
Ethio Fm

6 months ago