2 months ago
የመድፈኞቹ የ22 ዓመት ትጋትና ፅናት ያስገኘው የድል ደስታ በአዲስ አበባ
******
የለንደኑ መድፈኞች የ22 ዓመታት ረጅም የዋንጫ ጥበቃን በስኬት አጠናቀው የዘንድሮውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነታቸውን ማረጋገጣቸውን ተከትሎ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ልዩ የደስታ ማዕበል ተፈጥሯል።
የዚህን ታሪካዊ የታሪክ ምዕራፍ ወሳኝ ጨዋታ በትልቅ ስክሪን ለመታደም በርካታ ቁጥር ያላቸው የአርሰናል ደጋፊዎች በጊዮን ሆቴል አዳራሽ በጋራ የተሰበሰቡ ሲሆን ምሽቱም ስታዲየምን በሚያስንቅ የደጋፊዎች ጩኸት፣ መዝሙርና በከፍተኛ ስፖርታዊ ስሜት የታጀበ ነበር።
ይህንን ልዩ ምሽት ይበልጥ ማራኪ ያደረገው ደግሞ የተለያዩ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የስፖርት ባለሙያዎችና የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ከደጋፊው ጋር አብረው በመገኘት ደስታውን መጋራታቸው ነው፡፡
በተለይም ሰሞኑን ወደ አዲስ አበባ የመጣው ታዋቂው ዓለም አቀፍ የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪ "ዴላን ፔጅ" በቦታው ተገኝቶ ይህንን አስደናቂ የኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ፍቅርና ስሜት አብሮ ተካፍሏል።
በጊዮን ሆቴል የነበረውን ደማቅ ትዕይንት የታደሙት ደጋፊዎች ማራኪ ምስሎችንና ተንቀሳቃሽ ቪዲዮዎችን ወደ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው በቀጥታ በማጋራት የአዲስ አበባን የአርሰናል ደጋፊነት ስሜት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስተላልፈዋል።
መድፈኞቹ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን በበላይነት አጠናቅቀው ዋንጫውን ከ22 ዓመታት በኋላ በክብር ተረክበዋል።
በብሌን ደምበሎ
#arsenalmustvisitethiopia #arsenal #premierleaguechampions #addisababa #dylanpage #ethiopianbroadcastingcorporation

ኢትዮጵያ እንዴት የዓለም ተጽዕኖ ፈጣሪዎችና የሀያላን ሀገራት ማዕከል ሆነች? #ethiopia #dylanpage #visitethiopia #ishowspeedethiopia #ethiopiantourism #landoforigins #addisababacorridor
2 months ago
ከአይሾ ስፒድ እስከ ዲላን ፔጅ
***
ኢትዮጵያ እንዴት የዓለም ተጽዕኖ ፈጣሪዎችና የሀያላን ሀገራት ማዕከል ሆነች?
#ethiopia #dylanpage #addisababa #visitethiopia #gerd #ishowspeedethiopia #ethiopiantourism #landoforigins #addisababacorridor
3 months ago
የዓድዋ ድል መታሰቢያን የጎበኘው ‘ዲላን ፔጅ’ ኢትዮጵያ በቅኝ ያልተገዛችበትን ታሪካዊ ዳራ በአድናቆት ተመልክቶታል
**********************
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮችን ያፈራው እንግሊዛዊው የቲክቶክ ተፅዕኖ ፈጣሪ ‘ዲላን ፔጅ’ በኢትዮጵያ እያደረገው ባለው ጉብኝት የሀገራችንን ገጽታ ለዓለም በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል።
ዲላን በአዲስ አበባ ቆይታው የወንዝ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በመዲናዋ የተከናወኑ ቁልፍ የልማት ሥራዎችን እና የቱሪስት መዳረሻዎችን ተዟዙሮ ተመልክቷል።
በጉብኝቱ መሃል በአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት መስክ አረንጓዴ ዐሻራውን በማሳረፍ የልማት ተሳትፎውን በማኅበራዊ ሚዲያ ለተከታዮቹ አጋርቷል።
ዝነኛው ቲክቶከር በፒያሳ የሚገኘውን የዓድዋ ድል መታሰቢያም የጎበኘ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ያልተገዛችበትን ታሪካዊ ፋና በአድናቆት ተመልክቷል።
በስፍራው ሲደርስ ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን፤ በባህላዊ የአፈላል ሥነ-ሥርዓት የተዘጋጀለትን የኢትዮጵያ ቡና ከመቅመስ በተጨማሪ የመታሰቢያ ስጦታዎች ተበርክተውለታል።
ዲላን ስለኢትዮጵያ ጉብኝቱ በሰጠው አስተያየት፣ ጉብኝቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስለ አፍሪካ ያለውን የተዛባ አመለካከት ለመቀየር የሚያግዝ እንደሆነም ተናግሯል።
ተፅዕኖ ፈጣሪው ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ወደፊት ሐረር እና አፋርን ጨምሮ የተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎችን ለመጎብኘት ያለውን ፍላጎት ገልጿል።
በቢታኒያ ሲሳይ
#dylanpage #ethiopia #addisababa #adwa #adwavictorymemorial #corridordevelopment #riversidedevelopment #greenlegacy #ebc

ታዋቂው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ዲላን አዲስ አበባ ገባ
#ethiopia | በማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተሰሚነትን ያተረፈው ዲላን (ዲላን ፔጅ ) አዲስ አበባ ገብቷል።
ዲላን በቲክቶክ ብቻ ከ19 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት ሲሆን፣ አዲስ አበባ መግባቱን አስመልክቶ ባስተላለፈዉ መልእክት በርካታ ቀናትን የሚወስደውን ታላቁን ጉዞዬን፣ በቅኝ ግዛት ባልተገዛችዉ ሀገር ኢትዮጵያ ጀምሬያለሁ ብሏል።
ግርማ ሞገስ ያለው መልክዓ ምድር፣ በርካታ የታሪክ እና የሃይማኖት እሴቶች ያሏት ኢትዮጵያ የሰው ልጅ እና የቡና መገኛ መሆኗን ተናግሯል፡፡
ተፅዕኖ ፈጣሪዉ ዲላን ለተከታዮቹ፤ “ከምነግራችሁ ይልቅ ባሳያችሁ ይሻላል” በማለት ቀጠሮ ይዟል።
ኢትዮጵያ በርካታ የአርሰናል ደጋፊዎች ያሏት ሀገር መሆኗን እንደሰማ ጠቅሶ፣ ከእነሱ ጋርም ልዩ ጊዜ ለማሳለፍ ቀጠሮ መያዙን ገልጿል።
የዓለም አቀፍ ቱሪስቶች የስበት ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባም ዲላንን እንኳን ደህና መጣህ ብላ ተቀብላዋለች፡፡
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #addismedianetwork #voiceofgeneration #dylanpage #addisababa #ethiopia

Comments