Logo
FIDEL POST NEWS
​የእቴጌ ጣይቱ ህይወት የመጨረሻው ምዕራፍ የካቲት 4 ቀን 1910 ዓ.ም ተፈጸመ። ስጋቸው በእንጦጦ ማርያምና በኋላም በበዓታ ለማረፍ ቢበቃም፣ ስማቸውና ዝናቸው ግን ለዘላለም በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ታትሞ ይኖራል። የእሳቸው ታሪክ የሞት ታሪክ ሳይሆን፣ የህያውነትና የድል ታሪክ ነው። በዛሬው ትውልድ ውስጥ የጣይቱ መንፈስ ዳግም ሊቀሰቀስ ይገባል። ሀገራችን በፈተና ውስጥ ባለችበት በዚህ ወቅት፣ እንደ ጣይቱ ያለ ቆራጥነትና ሀገራዊ ፍቅር ካልተላበስን የአድዋን ድል መዘከር ብቻውን ትርጉም አይኖረውም።

"ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ" የሚለው ቅጽል ስም በትክክል ይገልፃቸዋል። ሀገሪቱ በጨለማና በቅኝ አገዛዝ ስጋት ውስጥ በነበረችበት ወቅት፣ እርሳቸው ብርሃን ሆነው መርተዋል። ዛሬም ቢሆን የሀገራችንን ችግሮች ለመሻገር እንደ ጣይቱ አይነት አርቆ አሳቢነት፣ እንደ ጣይቱ አይነት "ለሀገሬ አልደራደርም" የሚል ፅናትና እንደ ጣይቱ አይነት ፍፁም ኢትዮጵያዊነት ያስፈልገናል። ትውልዱ ከጣይቱ ሊማር የሚገባው ትልቁ ቁምነገር፣ ታሪክ የሚሰራው በንግግር ሳይሆን በተግባር መሆኑን ነው።

የእቴጌ ጣይቱ ብጡል ክብርና ዝና ለዘላለም በኢትዮጵያ ምድር ላይ ይኑር!!
8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.