2 months ago
ሰበር🚨🚨🚨
የዓለምን ጦርነት ስጋቶች፣ የኃያላን አገራትን ፍልሚያ እና ያልተሰሙ ሚስጥራዊ መረጃዎችን በቅጽበት የሚያቃብላችሁን ቻናል ተቀላቀሉት።
ተቀላቀል👇👇👇
https://t.me/Addis_Reporte...

ኢትዮጵያ የ2027ቱን የዓለም አቀፍ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር (AIPS) ጉባኤን ለማስተናገድ ተመረጠች
#ethiopia | የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር በ2027 የሚካሄደውን የዓለም አቀፍ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር (AIPS) ዓመታዊ ጉባኤን በዝግጅትነት ለመምራት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱ ተነገረ።
ታላቅ ዓለም አቀፍ መድረክ ኢትዮጵያ በስፖርቱ ዓለም ያላትን ስም የምታድስበትና "የስፖርት ቤተሰቡን" በአንድ ጣሪያ ሥር የምታገናኝበት ትልቅ ዕድል ተደርጎ ተወስዷል። በጉባኤው ላይ የሚከተሉት ዋና ዋና ክንውኖች እንደሚጠበቁ ታውቋል፦
ከ100 በላይ አገራ* የተውጣጡ ጋዜጠኞች ተሳትፎ፤ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የስፖርት ተቋማት መሪዎች መገኘት፤የዓለም "ምርጥ የስፖርት ጋዜጠኝነት ዓመታዊ የሽልማት ፕሮግራም"፤የወጣት ስፖርት ጋዜጠኞች (AIPS Young Reporters) ሥልጠና ይደረጋል።
ይህ ጉባኤ ከዘገባ ባለፈ ለኢትዮጵያ ስፖርት ዲፕሎማሲ፣ ለኢኮኖሚ መነቃቃትና ለአገራዊ ገጽታ ግንባታ የላቀ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል። የዓለም ስፖርት ባለሙያዎችና አመራሮች በ2027 በአዲስ አበባ እንደሚሰበሰቡ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #tikvah #ethiopia #aips #sportsjournalism #aips2027 #sportdiplomacy #ኢትዮጵያ #ስፖርትጋዜጠኝነት #አዲስአበባ

3 months ago
ኢዜማ ብርሃኑ ነጋን (ፕ/ር) በማሰናበት ኢዮብ መሳፍንትን የፓርቲው መሪ አድርጎ መረጠ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ፣ ፓርቲውን ላለፉት ሰባት ዓመታት ሲመሩ የነበሩትን ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አሰናብቶ እዮብ መሳፍንትን የፓርቲው መሪ አድርጎ መረጠ።
በአሁኑ ሰዓት ጠቅላላ ጉባዔውን በአድዋ መታሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ በሚገኘው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ከብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በተጨማሪ የፓርቲው ምክትል መሪ የነበሩትን አርክቴክት ዮሐንስ መኮንንም በተመሳሳይ አሰናብቷል። በምትካቸውም አቶ ንጋቱ ወልዴን ምክትል መሪ በማድረግ መርጧል።ፓርቲው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደርበትን ማኒፌስቶም ለአባላቱ ይፋ አድርጓል።
Via Reporter

4 months ago
#ቃለየሱስ በቀለ - የአቪየሽን ወርቃማው ጋዜጠኛ
#ethiopia | ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል።በተለይ ጉግል ላይ ታሪካቸው ሲፈለግ የማይገኝ ሰዎች አሁን የሙያ አበርክቷቸው በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ በግልፅ ተቀምጦ ይገኛልደ ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
#በዚህ የስነዳ ሥራችን ውስጥ በቅፅ 3 ከተካተቱት 20 ዘርፎች ውስጥ የሥራ ዘርፎች ውስጥ ሚድያ አንዱ ነው። በአሁኑ የሚድያ ሰዎችም፣ የቴአትር ባለሙያዎች እየተሰነዱ ይገኛሉ። አጠቃላይ 74 ከፍተኛ የሚድያ አመራሮች፣ሚኒስትሮች ፣ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የግል ሚድያ መሥራቾች፣ዋና አዘጋጆች እና መካከለኛ አመራሮች ተካተዋል። 35 ያህሉ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ያሉ ሲሆን የሁሉም ታሪክ በተሟላ ደረጃ ለመሰነድ ተችሏል። የእነዚህን ሰዎች ታሪክ ሰንዶ ለአንባቢ ተደራሽ ማድረግ ፈታኝ ቢሆንም አሳክተነዋል። በዚህ ተግባራችንም ተጠናክረን እንቀጥላለን።
#ዛሬን ሰንደን የምናስነብባችሁ የሚድያ ባለሙያ የቃለየሱስ በቀለን የሙያ ታሪክ ነው። በሚድያው ሥራ ሩብ ክፍለ- ዘመን የዘለቀው ቃለየሱስ በአቬሽን እና ማዕድን ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመዘገብ ትልቅ አሻራ አኑሯል። በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ በአገራችን በአንድ ርዕስ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ወይም ተክኖ መዘገብ ባልተለመደበት ሁኔታ ቃለየሱስ ችሎ አሳይቷል። ከባለታሪኩ የተገኘውን መረጃ በማግኘት፣ የቅርብ ሰዎቹን በማነጋገር የሙያ ታሪኩ ተሰንዷል። ዕዝራ እጅጉ እና ታደሠ ማሞ አጠናክረውታል።
፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#ትውልድና ዕድገት
‹‹የትኛውም አውሮፕላን ወደ አየር አኮብኩቦ መነሳቱ የተለመደ የጉዞው አማራጭ ቢሆንም አውሮፕላኑ ካሰበበት ደርሶ ማረፉ ደግሞ የግድ መሆን ያለበት ተግባር ነው፡፡››የሚል የአቪየሽን አባባል አለ፡፡በዚህ አባባል ተንደርድረን ወደ ውስጥ እንዝለቅ፡፡ሁሉም ዘርፍ የየራሱ አነፍናፊ ጋዜጠኞች እንዳሉት ሁሉ ቃለየሱስ በቀለ የተባለ ህልመኛና ደፋር ጋዜጠኛ በአቪየሽኑ ዘርፍ በተለየ መንገድ የራሱን የብዕር አሻራ ማኖር መቻሉ የዚህ ፅሁፋችን መነሻ ነው፡፡
#ቃለየሱስ በቀለ የውልደቱም ሆነ የእድገቱ መነሻ የምስራቅ ሸዋ አዳማ (ናዝሬት) ከተማ ናት፡፡ሀምሌ 18/1967 ዓ.ም በአዳማ ሀይለ ማሪያም ማሞ ሆስፒታል ቃለየሱስ የተባለ ብላቴና ከተፋፋመ ምጥ ውስጥ ወቅቱ አብዮታዊ ለውጥ ኢትዮጵያን በሚንጥበት በዚያ ጊዜ የለውጥ አየሩን እየማጉ ድምፃቸውን በማሰማት ይቺን ምድር ከተቀላቀሉት ጨቅላዎች አንዱ ሆኖ ተመዝግቦ በስሙ የልደት ካርድ ወጣለት፡፡
#ይህ ሰው ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ያለውን የትምህርት ጉዞውን ያሳለፈው በናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት ነው፡፡ትምህርት ቤቱ ከቀለም ትምህርት በተጨማሪ ተማሪዎችን በግብረ ገብና በመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት አንፆ በማብቃት ረገድ የተዋጣለት እንደነበር ቃለየሱስና አብረውት የተማሩት ሁሉ የሚመሰክሩት ሀቅ ነው፡፡
#በ1986 ዓ.ም ውጤታማ ሆኖ የአዲስ አበባ ንግድ ስራ ኮሌጅን ደጃፍ መርገጥ የቻለው ቃለየሱስ በኮሌጁ ሁለት ዓመታት በአካውንቲነግ ሙያ ተምሮ ቢያሳልፍም የሂሳብ ባለሙያ ሆኖ መቀጠሉ ስላልተዋጣልኝ ከልጅነቴ ጀምሮ አልመውና እፈልገው የነበረውን የጋዜጠኝነት ሙያ ለመቀላቀል መንከራተት የየዕለት ተግባሬ ሆነ ይላል፡፡ያኔምደፋር ብዕሩን ስሎ አሰሳውን የጀመረውና በእንግሊዝኛ ቋንቋ አርቲክሎችን እየዘጋጀ ለዴይሊ-ሞኒተር እና ዘ-ሪፖርተር ጋዜጦች ማቅረብ መጀመሩ የምኞት ጭላንጭሉን ወገግ አደረገለት፡፡
#ጋዜጠኝነት
እንደምኞትና ፍላጎቱም መንከራተቱ ፍሬ አፍርቶ ሳምንታዊ የቢዝነስ ጋዜጣ በሆነው ፎርቹን ጋዜጣ ላይ በሪፖርተርነት ተቀጥሮ ማገልገል ጀመረ፡፡ምኞትና ህልሙ መሬት እንዲረግጡ ቀዳሚውን ዕድል ያመቻቸለት የፎርቹን ጋዜጣ መስራችና ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው አቶ ታምራት ሀይለ ጊዮርጊስ በቃለየሱስ የህይወት ጉዞ ውስጥ ትልቅ ዋጋ አለው፡፡የጋዜጠኝነት ሀ ሁን ከማስቆጠር ጀምሮ ከዚያም ባሻገር አንደ ዓለም ባንክ፣የአሜሪካ ኤምባሲና ብሪቲሽ ካውንስል ያሉ ተቋማት በሚያዘጋጁት የሚዲያ ስልጠናዎች ላይ ተሳታፊ እንድሆን ዕድሉን ከማመቻቸት አልፎ ጠንካራ የጋዜጠኝነት ሰብዕናን እንድላበስ ያደረገኝ ባለውለታዬ ታምራት ነው ይላል ቃለየሱስ፡፡
#ወትሮም ለጋዜጠኝነት ታላቅ ጉጉት የነበረው ቃለየሱስ ዜና እንዴት ይፃፋል፣የዜና ግብዓቶች እንዴት ይሰበሰባሉ፣የዜና አስተማማኝ ምንጮችን እንዴት ማዳበር ይቻላል፣ፊቸር አርቲክል እንዴት ይፃፋል የሚሉና ሌሎችም ስልጠናዎችን አግኝቶ በብዕሩ መጠንከር የቻለው በፎርቹን ጋዜጣ ቆይታው እንደሆነ ያስታውሳል፡፡መች ይሄ ብቻ ከሀገር ውጪም በዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት በኤር ባስ አማካኝነት ከበረራና የበረራ ደህንነት መረጃ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ስልጠናዎችን በስፋት በመውሰድ የማረጋገጫ ሰርቲፊኬቶችን ተቀብሏል፡፡
#ቃለየሱስ ባለውለታዎቼ ብዙ ናቸው ይላል፡፡የፎርቹን ጋዜጣ ኤዲተር የነበሩት መላኩ ደምሴና ይበቃል ጌታሁን በጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ኮትኩተው ለውጤት አብቅተውኛል ካለ በኋላ በአጠቃላይ የፎርቹን ኤዲተሮች እኔን ጠፍጥፈው ሠርተውኛል ብል ማጋነን አይሆንም በሚል ያለፈበትን የጋዜጠኝነት ህይወት በአጭሩ ገልፆታል፡፡
#ከፎርቹን የሁለት ዓመታት ቆይታ በኋላ ሪፖርተር ጋዜጣን በመቀላቀል ለ18 ዓመታት ከከፍተኛ ሪፖርተርነት እስከ ኤዲተርነት ያገለገለው ቃለየሱስ ከሪፖርተር ጋዜጣ መሥራች አቶ አማረ አረጋዊ ጋር መሥራት መታደል ነው ይላል፡፡ከአቶ አማረ ጋዜጠኝነትን ብቻ ሳይሆን የአገር ፍቅርና ብሔራዊ ጥቅምን (National Interest)፣ደግነትንና ለሠራተኞቹ ያለውን ፍቅርና አክብሮት እንዲሁም ለጋዜጠኞች የሙያ ነፃነት ሰጥቶ ሠርቶ የሚያሠራበትን መልካም ትምህርት ቀስሜያለሁ ብሏል፡፡በሪፖርተር ሳለሁም በርካታ የሙያ ማሻሻያዎችንና የአጭር ጊዜ ሥልጠናዎችን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገሮች አግኝቻለሁ በማለት ትናንቱን ያመሰግናል፡፡
#በዘ -ሪፖርተር እንግሊዝኛ ጋዜጣ የማቀርባቸው ዘገባዎቼ በአብዛኛው ቢዝነስ ተኮር ነበሩ የሚለው ቃለየሱስ በተለይ በአቪዬሽንና በማዕድን ዘርፎች ላይ አተኩር ስለነበር፤በእነዚህ ዙሪያ በሚሠሩ የውጭ መጽሔቶች ለእኛም ጻፍልን የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበውልኝ እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ ኤርላይን ፍሊት ማኔጅመንት፣ወርልድ ኤር ኒውስ፣ኤርላይን ኢኮኖሚክስ፣አፍሪካን ኤሮስፔስና ዓረቢያን ኤሮስፔስ፣አቪዬሽን ኢንተርናሽናል ኒውስ፣አፍሪካን ቢዝነስ እና አፍሪካን ማይኒንግ ጆርናል ለተባሉ መጽሔቶች በፍሪላንስነት ለረዥም ዓመታት ሠርቻለሁ ይላል፡፡
እ.ኤ.አ.በ2008 በእንግሊዝ አገር በሚካሄድ “Best Aerospace Journalist of the Year” ሽልማት ታጭቼና ለንደን ተጋብዤ ዋናውን ሽልማት ባላሸንፍም፣"How Safe Are African Airlines?" በሚል ርዕስ በኤርላይን ፍሊት መጽሔት ላይ ያሳተምኩት ጽሑፍ ከ500 ለውድድር ከቀረቡ ጽሑፎች አምስቱ ምርጥ ውስጥ ለመግባት በመቻሉ፣ሰርተፊኬት ተበርክቶልኛል ብሏል፡፡
#በ2007 ዓ.ም. በትግራይ ሽመልባ የኤርትራ ስደተኞች መጠለያ ካምፕ ጉብኝት በማድረግ፣ ስለኤርትራዊያን ስደተኞች አሳዛኝ ሕይወት "The Woes of Eritrean Refugees” በሚል ርዕስ በዘ- ሪፖርተር ጋዜጣ ያሳተምኩት ሰፊ ጽሑፍ ጄኔቭ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) ዋና መሥሪያ ቤት ተመርጦ፣ለረዥም ጊዜ በድረ ገጻቸው ላይ ለንባብ ተቀምጦ ነበር፡፡በሻሸመኔ መልካ ኦዳ ስለሚገኙ የራስ ተፈሪያን ማኅበረሰቦች በቦታው ተገኝቼ የሠራሁት "The Plight of Rastafarians in Ethiopia" ዘገባ ከራስ ተፈሪያን ማኅረሰብ ምሥጋናና ዕውቅና አስገኝቶልኛል ይላል፡፡
ቃለየሱስን አንባቢያን የሚያውቁት ስለኢትዮጵያ አየር መንገድና በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ስለሚካሄዱ የማዕድንና የነዳጅ ፍለጋዎች ተከታታይ በርካታ ዜናዎችን በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በመሥራቱ ነው፡፡ ከዚያ ባለፈም ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና ጋዜጠኞች ጋር የመሥራት ዕድሉን አግኝቷል፡፡
#የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ለሥራ ወደ ኢትዮጵያ በሚመጡበት ወቅትም እነሱን በማገዝ የተለያዩ ሥራዎችን ከውኗል፡፡ከእነዚህም መካከል “CNN, Aljazeera, SKY News, The Economics, National Geographic, Los Angeles Times, News Week, New York Times, Christian Science Monitor, Chicago Tribune…” እና ሌሎችም ከተሳተፈባቸው ውስጥ ይገኙበታል፡፡
እ.ኤ.አ. በ2019 አደጋ የደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን በተመለከተ ሲኤንኤን (CNN) በሠራቸው ዘገባዎች ላይ በረዳት ፕሮዲዩሰርነት የሠራ ሲሆን፣በወቅቱ ላበረከተው አስተዋጽኦ ከሲኤንኤን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ምሥጋና ተችሮታል፡፡በዘገባዎቹ ላይም ሙሉ ስሙን በማስፈር ተገቢውን ዕውቅና ሰጥተውታል፡፡የአሜሪካው አልጄዚራ ኢንግሊሽ ቡድን ስለአውሮፕላን አደጋው ዶክመንተሪ ለማዘጋጀት አደጋው ከደረሰ ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመጣበት ወቅትም፣አብሮ የአገር ውስጥ ፕሮዲዩሰር (Local Producer) ሆኖ ሠርቷል፡፡
መቼ ይሄ ብቻ ቃለየሱስ የ”Fault Lines” ፕሮግራም አዘጋጅ ከሆነው ጆሽ ረሺንግ (Josh Rushing) እና ፕሮዲዩሰሯ ካቢታ ቺኩሩ ጋር የሠሩት ዶክመንተሪ የተለያዩ አህጉሮችን የሸፈነ ሲሆን፣ለኤሚ አዋርድ ዕጩ ሆኖ ቀርቦም ነበር፡፡
#ከ18 ዓመታት አገልግሎት በኃላ እ.ኤ.አ. በ2020 ሪፖርተር ጋዜጣን ተሰናብቶ ኦሪጅንስ ሚዲያን በማቌቋምና ከኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬዲዮ ጣቢያ የአየር ሰዓት በመውሰድ፣‹‹ኢትዮ የንግድና የኢንቨስትመንት መድረክ››የተሰኘ ፕሮግራም በሳምንት ለሁለት ቀናት እያዘጋጀ ለሦስት ዓመታት ያህል አቅርቧል፡፡ኦሪጅንስ የሚል የጉዞ (Travel Magazine) ለማሳተም እየንቀሳቀሰ የነበረ ቢሆንም፣በኮቪድ ወረርሽኝና በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ለፍሬ ሊበቃለት እንዳልቻለ በቁጭት ያስታውሳል፡፡
#ገጠመኞቹ
#ቃለየሱስ በጋዜጠኝነት ሙያ የገጠሙኝ ፈተናዎች ብዙ ናቸው ይላል፡፡ሙያው ራሱ የሚያስደስት ነገር እንዳለው ሁሉ ብዙ የሚያስጨንቁና የሚከብዱ ነገሮችም አሉት።ጋዜጠኛው ከህሊናው ጋር ተሟግቶና ሚዛኑን ጠብቆ የሚሰራው ነገር አንዱ ሲሆን።ዘገባን ወቅት ጠብቆ መስራትም የራሱ ፈተና አለው። ሚዛናዊነቱ ሳይጓደልም እንኳን ስለአንድ ነገር ሲፃፍ ወይም ሲዘገብ በዜናው ምከንያት የሚጠቀሙ ወገኖች ሊኖሩ ይችላሉ።
ወዲህ ደግሞ ጉዳቱም የዛን ያህል ነው።አንድ ሚዲያ በሚሰራው ዘገባ ባለስልጣንም ሆነ ካምፖኒ ሊሆን ይችላል የነበረውን አቅም ሊያጣ ይችላል።ይህ የሚዲያ ባህሪ ነው።ፈተናዎቹ የበዙ ቢሆኑም ጋዜጠኛው ሲፅፍ ሚዛናዊነት የተለበሰ መሆን አለበት ባይ ነው ቃለየሱስ።
#ቃለየሱስ ረጅም ዓመት የሠራው ህትመት ሚዲያ ላይ ነው።በአንድ ወቅት ከቺጋጎ ትሪቡን ጋዜጠኛ ጋር ወደ ትግራይ በማቅናት በኢትዮ ኤርትራ ስላለው ሁኔታ ለመዘገብ አመሩ፡፡ሽሬ አካባቢ ሽመልባ የሚባል የኤርትራ ስደተኞች ያሉበትን ስፍራ ጎብኝተውና አነጋግረዋቸው ወደ ሽራሮ ሄዱ፡፡የጦርነቱ ከተማ ወደነበረችው ባድመ ሄደውም ነዋሪዎችን፣አርሶ አደሮችና የከተማውን አስተዳደር ቃኝተውና ቃለመጠይቅ አድርገው ወደ ኤርትራ ድንበር ተጠጉ፡፡
#የኤርትራን መሬት ከወንዝ ባሻገር እያዩና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ሲያስጎበኟቸው የተቀበሩ ፈንጂዎች ስለነበሩ በተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሀይል አማካኝነት የፈንጂ ማስወገድ ስራው እየተሰራ ስለነበር የምንረግጠውን መንገድ ጠቆሙን ካለ በኋላ ቀይ ቀይ የተደረገባቸውን ድንጋዮች አሳይተውን ለእግር ፉካ የምትሆን ድንጋይ አሳዩን።ቀይ ምልክት የተደረገባቸውን ድንጋዮች ትተን ሌላ ከረገጥን ልንሞት እንደምንችል ነገሩን።በፈንጂ መሀከል በጭንቅና በዝግታ ያሳለፍንውን ምንጊዜም አልረሳውም ይላል ቃለየሱስ።
ሌላ ጊዜ ደግሞ በአቬየሽን፣በነዳጅ እና ማዕድን ፍለጋ ስራዎች ዙሪያ ለመዘገብ ወደ ሱማሌ ክልል ይሄዳል፡፡ከኦጋዴን ነፃ አውጪ ጋር የነበሩ ውጊያዎች ስለነበሩ አንድ ጊዜ አቦሌ ከሚባል በደቡብ ምዕራብ በሚገኝ ኩባንያ የነዳጅ ስራ ፍለጋ በሚያደረግ ካምፕ ላይ ታጣቂዎቹ ጥቃት ሰንዝረው 9 ቻይናውያን እና ወደ 65 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ህይወት ያልፋል።
ያንን ለመዘገብ ወደ አካባቢው የሄደው ቃለየሱስ ከቺጋጎ ትሪቡን ጋዜጠኛው ፖልስ አሎቤ ጋር ያለ እንቅልፍ ረጅም ቀናት በማሳለፋቸው በሀሩራማው ኦጋዴን ውስጥ ለረጅም ሰአታት ራሱን ስቶ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ በህክምና የነቃበትን ጊዜም ያስታውሳል።ቃለየሱስ ገጠመኞቹ የትየለሌ ናቸው፡፡በችሎት ዘገባ እንዲሁም ጋምቤላ ለዘገባ ሄዶ ያጋጠሙትንም ሁሌ እያስታወሰ ይገረምባቸዋል፡፡ በተለያዩ የአቪዬሽን ስብሰባዎችና እንዲሁም በአውሮፕላን አምራች ካምፓኒዎች በአካል እየተገኘም የሚያማልሉ ዘገባዎችን አስነብቧል፡፡
#ስለ ቃለየሱስ የታላላቅ ሰዎች ምስክርነቶች
"ቃለ ኢየሱስ በቀለ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በትጋት ከሠሩ ባለሙያዎች አንዱ ነው።" ይላል የሪፖርተር ጋዜጣ መስራች አማረ አረጋዊ። ምስክርነቱንም በመቀጠል፦
"... ቃለ ኢየሱስ በአቬሽን እና በማዕድን ዘገባዎች ላይ ያተኩር እንጁ የተሰጠውን ደስ ብሎት የሚሠራ ጋዜጠኛ ነው። የጋዜጠኝነት የሥነ ምግባር ደንብን አውቆ የሚተገብር ባለሙያ ነው። ፕሮፌሽናሊዝም እንዲሰፍን የሚታገል ጠንቃቃ ባለሙያ መሆኑን መመስከር እወዳለሁ።" በማለት ገልጿል
፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#የአቶ ግርማ ዋቄ ምስክርነት
#ቃለ ኢየሱስ በቀለን ረጅም ጊዜ አውቀዋለሁ። ለአቬሽን የተለየ ፍቅር አለው። አለምአቀፍ ኮንፈረንሶች ላይ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋል። ከዚያም በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ፅሁፍ ያቀርባል።ብስለቱ ይደንቃል። ከሌሎች የስሚ ስሚ ሰምቶ ሳይሆን አንድን ጉዳይ ከስር ከመሠረቱ አውቆ የመዘገብ ችሎታውን አደንቅለታለሁ። ስለ አፍሪካ አየር መንገድ ፣ ስለ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በወጉ ተረድቶ ስለሚፅፍም ፅሑፉ ተነባቢ ለመሆን ችሏል። ኢትዮጵያ ውስጥ አቬሽን ጋዜጠኝነት በጥልቀት ሲሠሪ የማውቀው እርሱን ነው።ሌሎችም አሉ። እርሱ ግን ከፍ አድርጎ በልህቀት የሚሠራ በመሆኑ ይለያል።
ገና አየር መንገድ ሲመጣ መረጃ ለማግኘት ፍላጎት ያሳያል። ዕውነትን ለማግኘት ይጎለጉላል። አፍሪካም ውስጥ ፈጠን ብሎ አቬሽን ጋዜጠኝነት ላይ የገባ በመሆኑ ይህም ግንባር ቀደም ያደርገዋል። ቃለኢየሱስ ካለበት ካናዳ ሆኖ የአቬሽን ጋዜጠኝነትን ሙያ እንዲያሳድግ ምክሬን እለግሰዋለሁ።
አቶ ግርማ ዋቄ
የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
‹‹እኔ ቃለየሱስ በቀለን የማውቀው ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ዓመታት ፎርቹን ጋዜጣ አብረን ስንሠራ ጀምሮ ነው›› የሚለው የሪፖርተር ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው መላኩ ደምሴ ነው፡፡‹‹ከዚያም በኌላ ለ18 ዓመታት አብረን በሪፖርተር ጋዜጣ ሠርተናል፡፡ከጀማሪ ሪፖርተርነት አንስቶ እስከ አርታኢነት በዘለቀው የሥራ ጉዞው በሚገባ አውቀዋለሁ፡፡በተለይ በአቪዬሽንና በማዕድናት ዘርፍ እጅግ በጣም በርካታ ዘገባዎችን የሠራ ሲሆን፣በሁሉም ሥራዎቹ አንጀት አርስ የሚባል ጋዜጠኛ ነው፡፡ጋዜጠኝነትን ከልቡ ከማፍቀሩ የተነሳ አብረው ለሚሠሩ ጋዜጠኞች ጭምር የሙያውን ፍቅር የማጋባት ችሎታ ያለው ነው፡፡ቃለየሱስ ዘገባዎችን ሲሠራ የሁሉንም ባለጉዳዮች ደምፅ ከማካተት በተጨማሪ፣አንባቢያን ለርዕሰ ጉዳዩ ቅርበት እንዲፈጥሩ የሚያስችል ስሜትን የተካነ ነው፡፡
‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በአቪዬሽን ዘገባ በግንባር ቀደምነትነት የሚጠቀስ ጋዜጠኛ ማነው ቢባል በመጀመሪያው ረድፍ ላይ የሚገኘው ቃለየሱስ ነው፡፡በዓለም ላይ አሉ የሚባሉ አውሮፕላን አምራች ኩባንያዎችን፣አየር መንገዶችን፣በአቪዬሽን ዘርፍ ውስጥ የተሰማሩ የሥራ ኃላፊዎችንና ባለሙያዎችን ሳይቀር በተለያዩ አገሮች በማግኘት በሪፖርቶቹ ውስጥ ድምፃቸውን ከማካተቱም በላይ በቃለ ምልልስ ጭምር ለአንባቢያን ተደራሽ በማድረግም ወደር የለውም፡፡የአውሮፕላን አደጋዎች ሲያጋጥሙም ሆነ የተለዩ ክስተቶች ሲኖሩ ከሚሠራቸው ዘገባዎች በተጨማሪ፣በተለያዩ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለማብራሪያ የሚፈለገው ቃለየሱስ ነው፡፡በውጭ ለሚዘጋጁና ቁጥራቸው ቀላል ለማይባል የአቪዬሽን መጽሔቶች በርካታ ዘገባዎችን በመሥራትም ታዋቂ ነው፡፡
‹‹በማዕድናት ዘርፍም ከካሉብ ነዳጅ የጀመረው የጋዜጠኝነት ህይወቱ በተለያዩ ክልሎች የሚደረጉ የነዳጅ፣የወርቅ፣የብረት፣የፖታሽ፣የታንታለም፣የኦፓልና ሌሎች የከበሩ ማዕድናት ፍለጋ ሥራዎችን በስፋት የዳሰሰ ነው፡፡በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታዎች፣በጂኦ ተርማል ፕሮጀክቶች፣ በፀሐይና በንፋስ ኃይል ማመንጫዎች፣በሲሚንቶና በሌሎች የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችም ሰፋፊ ዘገባዎችን በማበርከት ስመጥር ሆኖ ዘልቌል፡፡በፖለቲካው መስክ ደግሞ በተለያዩ አገራዊ ምርጫዎች ከአዲስ አበባ ውጪ በክልሎች ተሰማርቶ አመርቂ ሪፖርቶችን በማቅረብ ችሎታውን ማስመስከር የቻለ ነው፡፡ከሪፖርተር በገዛ ፈቃዱ ከተሰናበተ በኃላም በኤፍኤም 107.8 ሬዲዮ ጣቢያ የአየር ሰዓት ወስዶ ያቀርባቸው የነበሩ የቢዝነስ ፕሮግራሞቹ፣የቃለየሱስን ችሎታ ከጋዜጣ አንባቢያን ወደ ሬዲዮ አድማጮች በማዝለቅ ረገድ ትልቅ ግምት የሚሰጣቸው ነበሩ፡፡
‹‹ቃለየሱስ ግልጽ፣ ቅን፣ ሰብዓዊነትን የሚያስቀድም፣ኃላፊነት የሚሰማው፣ በአስገራሚ ትውስታው የረሳናቸውን ጉዳዮች የማስታወስ ችሎታ ያለው፣በቀልድም ሆነ በቁምነገር የሚታወቅ፣ ከማንኛውም ሰው ጋር ወዳጅነት ለመፍጠር ምንጊዜም ዝግጁ የሆነ፣በተለይ በሪፖርተር የሥራ ባልደረቦቹ ዘንድ በእጅጉ ተወዳጅና ምሥጉን ጋዜጠኛ ነው፡፡በተጨማሪም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በሚሰጣቸው ሰፊና ጥልቅ ትንተናዎቹ የሚታወቅ ሲሆን፣ብዙዎችም በዚህ መጠን ለነገሮች ትኩረት ሰጥቶ የማስረዳት ብቃቱን በአድናቆት የሚመሰክሩለት ነው፡፡እኔም ከሁለት አሠርት ዓመታት በላይ አብሬው ስለሠራሁ ችሎታውን በዚህ መጠን ስገልጽ በከፍተኛ ስሜት ሲሆን፣ይህንን ከመሰለ ብርቱና ታታሪ ጋዜጠኛ ጋር የመሥራት ዕድል በማግኘቴ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ›› በማለት መላኩ ምስክርነቱን አጠቃሏል፡፡
ካፒቴን ሰሎሞን ግዛው ስለ ቃለየሱስ በሰጡት ምሥክርነት ‹‹እኔ እሱን ለአየር መንገዱ ልዩ እንደ ሆነ ሰው አየዋለሁ።በጣም ትሁት፣አዳማጭ የሆነ ሰው ነው።ከየት እንዳመጣው ባላውቅም ልዩ የሆነ የኢንግሊዘኛ ፀሀፊ ነበር።በሁለት ምክንያት የሱን ፅሁፍ አነብ ነበር፡፡አንዱ በፅሁፉ ለመደሰትና እንደ ግጥም ስለምወደው ነው።ሌላው ከእውቀቱ ወይም አንብቦም ይሁን ባላውቅም የፅሁፎቹ ይዘት በሚያውቀው ነገር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ነው።በዚህም በጣም አበረታታዋለሁ።
‹‹ከተዋወቅን 15 ዓመታት ሆኖናል።በውጪ ህትመቶች ላይ የሚያወጣቸው ስራዎች ቃለየሱስ ብሎ ስሙ ይገለፅ ይሆናል እንጂ ማንም ነጭ የሚፅፈው አይነት ፅሁፍ ነው።የፅሁፉ ይዘትና አያያዝ ደረጃውን የጠበቀ ነው።የሚፅፍባቸው መፅሄቶች ደረጃቸውን የጠበቁና ትላልቅ ናቸው።ነገር ግን ደረጃቸውን ጠብቀዋል የሚባሉትም አንዳንዴ ትርኪምርኪ ሲፅፉም ይታያል።ግን የሱ ፅሁፍ በጣም የሚያኮራ ነው።ሌላው ዜግነቱን የሚወድ ሰው ነው።ተጨባጭ በሆነ መልኩ ለኢትዮጵያ አየርመንገድ በቦታው ካሉት ህዝብ ግንኙነቶች እሱ ብዙ የሰራ ይመስለኛል።እውቅናና ሽልማት ሊሰጠው በርታ ሊባል የሚገባው ልጅ ነው።ወገቡን ይዞ ነበር ለአየር መንገዱ ይሰራ የነበረው።አሁንም ቢሆን ባለበት ሆኖ ለአየርመንገዱ ነገሮችን መስመር የሚያሲዝ ሰው ነው››ብለዋል፡፡
፨፨፨፨፨፨፨
የቀድሞ የሲቪል አቬሽን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ወሰንየለህ ሁነኛው በበኩላቸው ‹‹ከተዋወቅን ከ7 ዓመት በላይ ይሆነናል።እኔ ከማቃቸው የሚዲያ ሰዎች በጋዜጠኝነት የሱን ያህል ብዙም አቬሽን ዘርፉ ላይ ገብቶ እያንዳንዱን ነገር አይቶ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይሁን የግል ኦፕሬተሮቹም ጋር እንደሱ የሚፅፍ አላየሁም።እሱ ነው የተሻለ ጠይቆ አንብቦ ተረድቶ አስተዋጽዖ ለማድረግ የሚጥረው።በዛ ወቅት ቃለ እየሱስ ጥሩ ዘጋቢ ነበር።ብዙ መፅሄቶች ላይ ይሳተፋል አንዳንድ አለም አቀፍ ስብሰባዎች ላይ ይሄዳል። በኢትዮጵያ አየርመንገድና በሲቪል አቬየሽን ላይ የተለየ እውቀት ያለው ነው።ምክንያቱም በየእለቱ ስለሚከታተል ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አቬየሽን ኢንዱስትሪ በደንብ ያውቀው ነበርና ነው።
‹‹አቬየሽን ኢንዱስትሪው በእነዚህ መፅሄቶች በብዙ መንገድ ይጠቀማል።ህብረተሰቡ አቬየሽኑም ሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራሱን ከማስተዋወቁ በላይ ምን ላይ እንዳለ እና በተለየ አካል እንዲሰራለት ትክክለኛነቱን ይረጋገጣል።እንዲሁም ምን ያህል የግል ኦፕሬተሮች ምን ያህል በኢኮኖሚው ይሳተፋሉ የሚለውንም ለህብረተሰቡም ለመንግስትም መረጃ ይሰጣል።ስራዎቹ ለብዙ ነገሮች የመረጃ ምንጮች ሆነው ያገለግላሉ ።
‹‹ቃለእየሱስ በዚያ ወቅት የሚያደርገው የኢትዮጵያን አቬየሽን ኢንዱስትሪ ከሌላው እያነፃፀረ በሚያውቀው ልክ ለህብረተሰቡ ሙሉ መረጃ ይሰጣል።ለግል ኦፕሬተሮችም ለኢትዮጵያ አየር መንገድም ግብዐት የሚሆኑ ብዙ ነገሮችን ያደርጋል።በተዘዋዋሪም ያስተዋውቃል።እውነተኛ መረጃ ሲያቀርብ ሰው ስለ አቬየሽን ኢንዱስትሪ ያለውን እውቀት ያዳብራል።አብዛኛው ሰው ስለ ግል ኦፕሬተር አያውቅም አውሮፕላን አላቸው ወይ ? ብሎ የሚጠይቅም ብዙ ሰው ነው።በዚህ ጉዳይ ላይ በብዛት የሚሰራው ቃለእየሱስ ነበር››ብለዋል፡፡
‹‹በኢትዮጵያ የጉዞና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ የቃለየሱስ አስተዋፅኦ ትልቅ ነው።››ብለው ምስክርነታቸውን መስጠት የጀመሩት አቶ ተወልደ ገብረማርያም የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ናቸው፡፡‹‹ቃለየሱስና እኔ ለረጅም ጊዜ እንተዋወቃለን በ«Reporter» ጋዜጣ ሲሰራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዜናዎችንና እድገቶችን ይዘግብ ነበር።በቀጣይ የአቪዬሽን ዘርፍ ላይ ጥልቅ ፍላጎት አሳየ፤እኛም ከIATA ጋር እንዲገናኝ አደረግነው፣በተለይም በየዓመቱ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚካሄዱ የIATA አመታዊ አጠቃላይ ጉባኤዎች (AGM) ላይ የፕሬስ ኮንፈረንሶች ላይ ይሳተፍ ነበር።
‹‹በአፍሪካ አየር እና አቪየሽን (African Aerospace and Aviation) መጽሔት እና በሌሎች ከአቪየሽን ጋር የተያያዙ መጽሔቶች ላይ ጽሁፎችን ይጽፍ ነበር።በአጋርነትም ብዙ ፕሮጀክቶችን አከናውነናል። እኔም የኢትዮጵያ ቱሪዝም ቦርድ ሊቀመንበር በነበርኩበት ሰዓት፣የራሱን የጉዞና ቱሪዝም መጽሔት እንዲጀምር ወይም እንዲያስብበት ሀሣብ አቀርብለት ነበር፤እርሱም ይህን ሀሳብ በአዎንታ ይመልከተው ነበር።
‹‹በአጠቃላይ፣ ይህ ዘርፍ እስከዛሬም በቂ የሚዲያ ሽፋንና የማስተዋወቂያ መድረክ ስላልነበረው፣ ቃለየሱስ ይህን ክፍተት ልብ ብሎ በማጤን በኢትዮጵያ የጉዞና ቱሪዝም ዘርፍ ልማት ላይ ከፍተኛ ስራ ሰርቷል።በእኔ አመለካከት፣ያበረከተው አስተዋፅኦ አስደናቂ ነው፣ለሥራውም እውቅናና ምስጋና ሊቀርብለት ይገባል››ብለዋል፡፡
ሲጠቃለል ከ15 አመት በላይ በአለም አቀፍ የአቪየሽን ስብሰባዎችን በአሜሪካ፣አውሮፓ፣አፍሪካ፣ መካከሉኛው ምስራቅ እና ኤሽያ ተሳትፌያለሁ 36 ሃገሮችንም የማየት እድል ገጥሞኛል የሚለው የአቪየሺን ባለወርቃማ ብዕሩ ቃለየሱስ በቀለ እ.ኤ.አ.ከ2023 መጨረሻ ጀምሮ ኑሮውን በካናዳ ያደረገ ሲሆን፤ለአፍሪካ ኤሮስፔስና አቪየሽን ኢንተርናሽናል ኒውስ በፍሪላንስነት በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

#ረመዷን
ታላቁ የረመዷን ጾም ጨረቃ ነገ ማክሰኞ ከታየች ረቡዕ ጨረቃ ካልታየች ደግሞ ሐሙስ የካቲት 12 ይጀምራል።
ታላቁን የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ምን አሉ ?
" ለመላው ሙስሊም ማሕበረሰብ እንኳን ለ1447ኛው የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ።
ረመዳን ከአምስቱ የእስልምና ማዕዘናት አንዱ በመሆኑ ሁሉም ሕዝበ ሙስሊም እንዲፆም በአላህ የታዘዘ ወር ነው።
ረመዳን የአንድነትና የመተሳሰብ ወር ነው።
የይቅርታ፣ የእዝነት እና የማህበራዊ ትስስር ጊዜ በመሆኑ ሙስሊሞች ሁሉ ከበጎ ስራዎች ጋር ሊገናኙ ይገባል።
አቅመ ደካሞችን በመርዳት፣ ማዕድን በማካፈል፣ በመተሳሰብና አላህን በመለመን ወሩን ማሳለፍ ይገባል።
ረመዷን የሰላም ወር በመሆኑ ሁሉም ከግጭት እና ከፀብ በመራቅ ሊያሳልፍ ይገባል።
መንፈሳዊ ልዕልና የሚኖረው ሰላም ሲኖር በመሆኑ ለሀገራችን ሰላም እና ለሕዝባችን ደኅንነት ዱዐ ልናደርግ ይገባል። "
Addis_Reporter

Sponsored by
Surafel
4 months ago
የልዩ መለያ QR Code ደረሰኝ ኅትመት ችግር የተፈጠረው በሥርጭት ምክንያት መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታወቀ
#ethiopia :
ነጋዴዎች ደረሰኙን ለማግኘት ባለመቻላቸው ሥራ መሥራት እንዳልቻሉና ለኪሳራ እየተዳረጉ መሆኑን ተናግረዋል
ልዩ መለያ (QR Code) ያረፈበት ደረሰኝ ኅትመት በመዘግየቱ ነጋዴዎች እንዲማረሩ ምክንያት የሆነ ችግር የተፈጠረው በሥርጭት ምክንያት መሆኑን፣ የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ከዚህ ቀደም ጥቅም ላይ ይውል የነበረው ደረሰኝ ከጥር 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ጥቅም ላይ እንደማይውል ውሳኔ መተላለፉን ተከትሎ፣ ነጋዴዎች አዲሱን ልዩ መለያ (QR Code) ያረፈበት ደረሰኝ ለማግኘት የሚጠበቅባቸውን ክፍያ ቢፈጽሙም፣ በመዘግየቱ ምክንያት መቸገራቸውን በተደጋጋሚ ገልጸዋል፡፡
ደረሰኙን በማሳተም ለነጋዴዎች የማድረስ ኃላፊነት ወስዶ እየሠራ የሚገኘው የገቢዎች ሚኒስቴር፣ ችግሩ የተፈጠረው በሥርጭቱ ላይ በተፈጠረ መዘግየት ምክንያት መሆኑን የሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ በፍርዱ ተሰማ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
በተለይም በክልሎች ለሚገኙ ግብር ከፋዮች ደረሰኙን ለማድረስ በብቸኝነት እያተመ ከሚገኘው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ተቀብሎ እስከ ግብር ከፋዩ ለማድረስ ባለው ሒደት የጊዜ መራዘም መኖሩና ለችግሩ መፈጠር ምክንያት መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
ችግሩን ለመፍታት ሚኒስቴሩ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ድረስ በአካል በመገኘት የሚከታተል ቡድን ከአንድ ወር በፊት ማቋቋሙንና ቡድኑ ባደረገው ክትትል ችግሮቹ የሚፈጠሩት የታተሙትን ደረሰኞች ለግብር ከፋዩ በማድረስ ሒደት ላይ በሚያጋጥም የሥርጭት ችግር መሆኑን፣ ይህን ለመፍታትም በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በአካል በመገኘት ጭምር እየተቆጣጠረ ይገኛል።
ግብር ከፋዮች ደረሰኛቸውን ለመውሰድ ግብር በሚከፍሉበት ቅርጫፍ ጽሕፈት ቤት በመገኘት ሲጠይቁ እንዳልደረሰ እንደሚገለጽላቸውና በማተሚያ ድርጅቱ በኩል ደግሞ ታትሞ መላኩ እንደሚነገራቸው፣ በመሀል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታትም ከቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ በኩል አለመድረሱን የሚገልጽ ደብዳቤና ደረሰኙን እየተጠቀሙ ሲያዙ የከፈሉበትን ማስረጃ እንዲያቀርቡ በማድረግ ችግሩን ለመፍታት እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ አክለውም በቅርጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ተከማችቶ የሚገኝ ደረሰኝ መኖሩንና አንዳንድ ግብር ከፋዮች እየወሰዱ እንዳልሆነ ጠቁመዋል፡፡Via:- Reporter
seledadotio

5 months ago
የቶንሲል ህመምን በቤት ውስጥ ለማከም
የቶንሲል እጢዎች በጉሮሮ ግራና ቀኝ የሚገኙ ሁለት እጢዎች ሲሆኑ፥ የተለያዩ ባክቴሪያዎችና ቫይረሶች ወደ ሰውነታችን ዘልቀው እንዳይገቡ ይከላከላሉ።
የሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅም የሚያሳድጉ ነጭ የደም ህዋሳትንም ያመርታሉ።
እነዚህ እጢዎች ራሳቸው ሲመረዙ ቶንሲሊቲስ የተሰኘ በተለምዶ ቶንሲል ብለን የምንጠራው ህመም ይከሰታል።
በባክቴሪያ አልያም ቫይረስ ኢንፌክሽን የሚከሰተው የቶንሲል ህመም፥ የቶንሲል እጢዎችን የማሳበጥና ጉሮሮን የመከርከ ምልክቶች አለው።
ህመሙ አንዳንድ ጊዜም መተንፈስ አለማስቻልን ሊያስከትል ሁሉ ይችላል።
ቶንሲል በየትኛውም የእድሜ ክልል የሚከሰት ስሆን፥ በህፃናት እና ታዳጊዎች ላይ በጣም የተለመደ ነው።
የቶንሲል ህመም ምልክቶች
- የጉሮሮ ህመም፣
- ምግብ የመዋጥ ችግር፣
- የድምፅ ለውጥ፣
- መጥፎ አተነፋፈስ፣
- ትኩሳት፣
- የጆሮ ህመም፣
- ራስ ምታት፣ ወዘተ..
የቶንሲል ህመምን የተለያዩ መድሃኒቶችን በመውሰድ መከላከል የሚቻል ሲሆን፥ ብዙ ጊዜ በቤት ውስጥ በሚዘጋጁ ነገሮች በቀላሉ ማከም እንደሚቻል ይታወቃል።
ውሃ ውስጥ ጨው ጨምሮ አፍን መጉመጥመጥ፣ አፍ እና ጉሮሮን ከጎጂ ተህዋስያን ለማፅዳት እና በቶንሲል እጢዎች አካባቢ ሌላ ኢንፌክሽን እንዳይከሰት ያግዛል።
የፍራፍሬ ጭማቂዎችን ከሶስት እስከ አምስት ቀናት መውሰድ በሽታ የመከላከል አቅምን በማሳደግ የትኛውንም መመረዝ (ኢንፌክሽን) ለመዋጋት ያግዛል።
ከሚጎመዝዙና ቅመማ ቅመም ከበዛባቸው ምግቦችና መጠጦች ግን መራቅ ተገቢ ነው ተብሏል።
የቶንሲል ህመምን በቤት ውስጥ ለማከም የሚረዱ ዘዴዎች
1.ማር
አንድ ብርጭቆ ውሃ ውስጥ አራት ማንኪያ ማር፣ ሩብ ማንኪያ ጨው እና የሎሚ ጭማቂ ጨምረን በማዋሃድ በቀን ከ2 እስከ 3 ጊዜ መጠጣት ጥሩ ወጤት ያስገኛል።
2.በርበሬ እና እርድ
አንድ ብርጭቆ የፈላ ወተት ላይ የእርድ ብናኝ እና ጥቂት በርበሬ ጨምሮ በማዋሃድ ከመኝታ በፊት መጠጣት ህመሙን ያስታግሳል።
3.ካሮት፣ ቀይ ስር እና ኩከምበር 300 ግራም ካሮት፣ 100 ግራም ቀይ ስር እና 100 ግራም ኩከምበር በአንድ ላይ በመፍጨት ጭማቂ በማዘጋጀት መጠቀምም ሌላኛው ለህመሙ መፍትሄ ነው ተብሎ የተጠቀሰ ነው።
4. ሎሚ
አንድ ሎሚ ለሁለት በመክፈል ጨው መነስነስ፤ ከዚያም በመጭመቅ መጠጣትም ጥሩ መፍትሄ ያስገኛል ተብሏል።
5. በረዶ
ብዙዎቻችን በረዶ እንዴት የቶንሲል ህመምን ለመቅረፍ ይረዳል የሚለው ጉዳይ ሊያስገርመን ይችላል። ነገር ግን በረዶ ችግሩን በማስወገድ ረገድ ውጤታማ መሆኑ ነው የሚነገረው።
የተወሰኑ የበረዶ ጡቦችን በጨርቅ ጠቅልሎ ወደ ቶንሲል እጢዎች በመላክ ከ10 እስከ 15 ደቂቃ መቆየት፤ ይህንኑ በቀን ለአራት ጊዜ ማከናወን ህመሙን በአጭር ጊዜ ለማስወገድ ይረዳል።
6. ዝንጅብል
ዝንጅብል ጨምቀን ሞቅ ካለ ውሃ ጋር ማዋሃድ (ካስፈለገም አንድ ማንኪያ ማር መጨመር ይቻላል)፤ ከዚያም በቀን ለአንድ ወይም ሁለት ጊዜ መጉመጥመጥ።
ዝንጅብልን ሻይ ውስጥ ጨምሮ መጠጣትም ሌላኛው አማራጭ ነው።
7. ቀይ ሽንኩርት
ቀይ ሽንኩርት በመፍጨትና ከሞቀ ውሃ ጋር በማዋሃድ አፍን መጉመጥመጥ ህመሙን ለማስታገስ እንደሚያግዝም ተነግሯል።
በአጠቃላይ ከላይ የተጠቀሱትን ዘዴዎች በመጠቀም ህመሙ ሊታገስልን ካልቻለ ወደ ህክምና ተቋማት በመሄድ አስፈላጊውን ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው።

የiPhone 18 Pro እና የApple የመጀመሪያው ተጣጣፊ ስልክ (iPhone Fold) መረጃዎች ይፋ ሆኑ!
የአፕል ደንበኞችን ለረጅም ጊዜ ሲያስጠብቅ የነበረው ተጣጣፊው ስልክ እና የiPhone 18 Pro ዝርዝር መረጃዎች በኢንተርኔት ተለቀቁ።
📱 iPhone 18 Pro እና Pro Max
አዲስ ዲዛይን፡ Face ID ከስክሪን በታች (Under-screen) በመሆኑ ስክሪኑ ሙሉ ለሙሉ ክፍት ይሆናል።
ካሜራ፡ ለፊት ካሜራ (Selfie) በጣም ትንሽ ቀዳዳ (Notch) ብቻ ይኖረዋል።
Hardware: እጅግ የረቀቀ አዲስ ፕሮሰሰር እና የሃርድዌር ማሻሻያ ይኖረዋል።
🌀 iPhone Fold (ተጣጣፊው ስልክ)
ካሜራ፡ በጀርባው ሁለት ካሜራዎች፣ በፊት ለፊቱ ደግሞ ሁለት የፊት ካሜራዎች ይኖሩታል።
ደህንነት፡ ከፊት Face ID ይልቅ በጎን በኩል የሚሰራ የጣት አሻራ (Touch ID) ይጠቀማል።
ዲዛይን፡ ሲዘረጋ ታብሌት የሚመስል ሰፊ ስክሪን ይኖረዋል።
📅 የመውጫ ጊዜ
iPhone 18 Pro እና Fold: መጪው መስከረም ላይ ለገበያ ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
iPhone 18 እና 18e: መደበኛዎቹ ስልኮች ግን እስከ 2027 የጸደይ ወቅት (Spring) ሊዘገዩ እንደሚችሉ ተገልጿል።

የውጭ ምንዛሬ ተመን ማሻሻያው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ላይ የ445 ቢሊዮን ብር የሒሳብ ኪሳራ ማስከተሉ ተገለፀ
በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ እንዲወሰን መደረጉ፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሒሳብ መዛግብት ላይ የ445 ቢሊዮን ብር ያልተመዘገበ (unrealized) የሒሳብ ኪሳራ ማስከተሉን በዚህ ሳምንት የወጣው የባንኩ ኦዲት ሪፖርት አመለከተ።
በአዲሱ የባንኩ ገዢ ዶ/ር እዮብ ተካሊኝ የተፈረመውና የ2024/25 በጀት ዓመትን የሚሸፍነው ይህ ሪፖርት፣ ባንኩ በበጀት ዓመቱ 428 ቢሊዮን ብር የተጣራ የሥራ ኪሳራ እንዳጋጠመው ያሳያል። ይህ ከፍተኛ የሒሳብ ቀውስ የተከሰተው ባንኩ ያለበት የውጭ ምንዛሬ ዕዳ እና ግዴታዎች፣ የብር ዋጋ ዝቅ ማለቱን ተከትሎ በብር ሲመነዘሩ በከፍተኛ ሁኔታ በማሻቀባቸው መሆኑ ተገልጿል።
የባንኩን የሒሳብ መዝገብ የመረመረው 'MSE Audit Service LLP' ባወጣው መግለጫ፣ ይህ የኪሳራ መጠን ከባንኩ ካፒታልና አጠቃላይ መጠባበቂያ ፈንድ በላይ ሊሆን እንደሚችል በመጠቆም፣ ባንኩ እንደ ተቋም የመቀጠል አቅሙ (Going Concern) ላይ አደጋ እንዳይጋርጥ ስትራቴጂካዊ የፖሊሲ ጣልቃ ገብነት እንደሚያስፈልግ አስጠንቅቋል።
እንደ ኦዲተሮቹ ገለጻ፣ ባንኩ ያለበትን የውጭ ምንዛሬ ዕዳዎች የሚከፍልበት ጊዜ ሲደርስ ለከፍተኛ የገንዘብ ጫና ሊጋለጥ ይችላል። በተለይም ባንኩ ከአቡ ዳቢ ፈንድ እና ከሳዑዲ አረቢያ የተቀበላቸው የቢሊዮን ዶላሮች ተቀማጭ ዕዳዎች፣ ብር ዋጋውን ማጣቱን ተከትሎ ለመክፈል የሚጠይቁት የብር መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ለኪሳራው ዋነኛ ምክንያት ሆኗል።
በተጨማሪም ሪፖርቱ በባንኩ የወርቅ ግብይት ላይ የታየውን ለውጥ የዳሰሰ ሲሆን፣ ለወርቅ ግዢ የወጣው ወጪ ካለፈው ዓመት ከነበረበት 7 ቢሊዮን ብር ወደ 421 ቢሊዮን ብር አሻቅቧል። ባንኩ ሕገ-ወጥ የወርቅ ዝውውርን ለመከላከል ለሀገር ውስጥ አቅራቢዎች የ15 በመቶ ተጨማሪ ክፍያ (Premium) በመስጠቱ ምክንያት ብቻ 57 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ኪሳራ መመዝገቡም ተመልክቷል። የኢኮኖሚ ባለሙያው ዶ/ር አብዱልመነን መሐመድ እንደገለጹት፣ ይህ ኪሳራ የሚጠበቅ ቢሆንም መጠኑ ግን እጅግ አስደንጋጭ ነው።
ባለሙያው አክለውም ብሔራዊ ባንኩ ይህንን ኪሳራ ለመሸፈን ያለው ብቸኛ አማራጭ መንግሥት ቦንድ እንዲያወጣለት ማድረግ እንደሆነና ይህም ውሎ አድሮ የኢትዮጵያ ግብር ከፋይ ሕዝብ ዕዳ ሆኖ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።
Reporter English

"አስደንጋጭ ነው!!"
- 470,000 የንግድ ድርጅቶች ከፌደራል መዝገብ ተሰርዘዋል!
#ethiopia | የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ኤክስፐርቶች ጥናትን ዋቢ አድርጎ ሪፖርተር ጋዜጣ ባወጣው መረጃ መሰረት፤ በፌደራል ደረጃ ከተመዘገቡት 570,000 የንግድና አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ውስጥ 470,000 (80%) የሚሆኑት በ2024 ብቻ ከስራ ውጪ ሆነዋል/ተዘግተዋል።
አቶ ሙሼ ሰሙ ይህንን ክስተት "ከዜናነት ባሻገር በጥልቅ ሊመረመር የሚገባው አደጋ" ሲሉ ገልጸውታል።
የዚህ አደገኛ ክስተት እንድምታዎች (በአቶ ሙሼ እይታ)፡
የሥራ አጥነት መጨመር፡ የ470 ሺህ ድርጅቶች መዘጋት በዚያው ልክ ለሚቀነሱ ሠራተኞች እና ቤተሰቦች መርዶ ነው።
የገቢ መቀነስ እና የግብር ጫና፡ መንግስት ከነዚህ ድርጅቶች ያገኝ የነበረው ገቢ ይቋረጣል። ይህን ክፍተት ለመሙላት በቀሩት 100 ሺህ ድርጅቶች ላይ "የታክስ ጫና" ሊያይል ይችላል፤ ይህም ቀሪዎቹን ከገበያ የማስወጣት ዕድሉ ሰፊ ነው።
የገበያ መዛባት፡ የአቅርቦት እና ስርጭት ሰንሰለቱ ስለሚበጠስ፣ የምርት እጥረት እና የዋጋ ንረት ሊባባስ ይችላል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #business #economy #reporter #mushesemu #trade

🛑 ጥያቄ፡
የንግድ ድርጅቶች በዚህ ፍጥነት ከገበያ መውጣታቸው ዋነኛ ምክንያቱ ምን ይመስላችኋል? መንግስትስ ይህንን "የደም መፍሰስ" ለማቆም ምን ማድረግ አለበት?

6 months ago
ቀይ ባሕር ፡ የኢትዮጵያ ቁልፍ ስትራቴጂያዊ…?
የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ስትራቴጂካዊ ፋይዳ
በስላባት ማናዬ
#ethiopia | ኢትዮጵያ የምትገኝበት የአፍሪካ ቀንድ መልከዓ ምድራዊ አቀማጥ ለመካከለኛው ምሥራቅ፣ለአወሮፓ እና ኤስያ ትልቅ ጂኦ ስትራቴጂካዊ ቦታ ነው። ይህ ቀጣና ከቀይ ባሕር እና ከሕንድ ውቅያኖስ ጋር የሚተሳሰር ነው።
ቀጣናው በወሣኛ የዓለማችን የንግድ መሥመሮች መተላለፊያ ፡በሦስቱ አብርሃማዊ ሐይማኖቶች መነሻ ቅርብ የሆነውን ያህል በታሪክ እና በገቢር በርካታ የደኀንነት ስጋቶችን በየጊዜው ደቅኖ የሚገኝ ነው።
ሽብርተኝነት፣ የባሕር ላይ ዘራፊዎች፣ ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች፣ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች እና አደገኛ ዕጽ አዘዋዋሪዎች በቀጣናው ከተደቀኑ አደጋዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
በዚህ ቀጣና ከሚገኙ አገራት መካከል ሁነኛዋ መልሕቅ አገር ኢትዮጵያ ነች። ኢትዮጵያ በቀጣናው የተደቀኑ የደኀንነት ስጋቶች በራሷ እና በዓለም አቀፍ የደሕንነት ስርዓት ውስጥ ከባድ መሰናክል እንዳይፈጥር ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ ሥራ ስታከናውን ቆይታለች።
በተለይ በአካባቢው የሽብርተኞች አደጋን በመዋጋት ረገድ ከኃያላንም ከመካከለኛ ኃይላት ጋር በጋር ተንቀሳቅሳለች፡እየተንቀሳቀሰችም ትገኛለች።
ይህ እንቅስቃሴዋ በተለይ ላለፉት 30 ዓመታት በየብስ እና በአየር ኃይል ብቻ ተወስኖ ቆይቷል። አሁን ኢትዮጵያ አላግባብ የተወሰደብኝን የባሕር በር መልሼ ማግኘት ይገባኛል የሚል ጥያቄ አንስታ እየተጓዘች ነው።
በቀጣናው እና በቀይ ባሕር አካባቢ ያለውን የደህንነት ሥጋት በጥሞና ለተከታተለው ኢትዮጵያ አሁን ላይ በየብስ እና በአየር ክልሉ ከምታደርገው የደህንንት ሥራ አኳያ የባሕር በሯን መልሳ ማግኘት እና የቀይ ባሕር አባል ወደ መሆን የመመለስ ጉዞዋ ጠቀሜታው ከራሷ ያለፈ በዓለም አቀፍ የደህንነት እና ጸጥታ መዋቅር ውስጥም የጎላ ሚና ይኖረዋል።
ከዚህ አኳያ የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ ዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ መደገፍ ብቻ ሳይሆን ለተግባራዊነቱ በንቃት ሊሳተፍ ይገባል።
በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የራሴን ምልከታ አቅርቢያለሁ፡ የግላችሁን ደግሞ በአስተያየት መስጫው ሥር አስፍሩ
https://www.thereportereth...

በኢትዮጵያ ከጥር ወር ጀምሮ የፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም፣ ማምረት ወይም ማስገባት በገንዘብ ቅጣት እና በእስራት የሚያስቀጣ አዋጅ በይፋ ተፈጻሚ ሊሆን ነው።
የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የሽግግር ጊዜው መጠናቀቁን ተከትሎ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር አስታውቋል።
የፕላስቲክ ከረጢት አምራቾች ለስድስት ወራት የተሰጠው የመሸጋገሪያ ጊዜ በቂ አለመሆኑን ቢገልጹም፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የሽግግሩ ጊዜ ጥር 23 እንደሚያበቃ በመጥቀስ ወደ ተግባራዊ እርምጃ እንደሚገባ አሳውቋል።
* መጠቀም ይዞ መገኘት:- ከ5,000 እስከ 10,000 ብር
* ማምረት/ ማስገባት/ መሸጥ :- ከ50,000 እስከ 100,000 ብር እና እስከ 5 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት
አዋጁ የወንጀል ድርጊቶችን የፈጸመው ሕጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት (አምራች ወይም አስመጪ) ከሆነ፣ የተጣለው የገንዘብ ቅጣት ሦስት እጥፍ እንደሚሆን በግልጽ አስቀምጧል።
አዋጁ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ሥራ ላይ መዋሉን አስመልክቶ፣ ማንኛውም ግለሰብ እና ድርጅት ይህን አዲስ ደንብ ተከትሎ ራሱን እንዲያስተካክል ጥሪ ቀርቧል።
Via Ethiopia Reporter

የገቢዎች ሠራተኞች በካሜራ የታገዘ ዩኒፎርም ሊለብሱ ነው!
የግልፅነትና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ወደ ሥራ አስገባ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከግብር ከፋዮች ጋር ግንኙነት የሚፈጥሩና ቁጥጥር የሚያደርጉ ሠራተኞች ላይ ትልቅ ለውጥ አመጣ።
ከዛሬ ረቡዕ፣ ኅዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ግብር ከፋዮችን የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፊነት የተሰጣቸው የቢሮው ሠራተኞች ቪዲዮ ካሜራ የተገጠመበት ዩኒፎርም ለብሰው ወደ ሥራ ይሠማራሉ።
ስሙ የቦዲ ዎርን ካሜራ ፕሮጀክት (Body Worn Camera Project) ሲሆን ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ወጥቶበታል::
ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት (ኢንሳ) ጋር በመተባበር።
የተሰራው ይህ አዲስ የካሜራ ቴክኖሎጂ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡-
1. ቀረጻ:
የቁጥጥር ባለሙያዎች የሚያደርጉትን ሥራ በሙሉ በድምፅና በምሥል ይመዘግባሉ።
2. ቀጥታ ስርጭት:
የተቀረጸው መረጃ ወዲያውኑ ለዋናው መሥሪያ ቤትና ለቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች በቀጥታ ይላካል።
3. ክትትል (Location Tracking):
የቢሮው ባለሙያዎች በዋና መሥሪያ ቤት እና በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ቁጥጥር የሚያደርጉ ሠራተኞች እያንዳንዱን እንቅስቃሴ እና የት አካባቢ እንደሚገኙ ይከታተላሉ።
4.ግልጽነት:
ከግብር ከፋዮች ጋር የሚደረጉ ንግግሮች በሙሉ ስለሚመዘገቡ ግልፅነትና ተጠያቂነትን ያረጋግጣል።
ይህ እርምጃ በግብር አስተዳደር ሥራዎች ላይ ያለውን ግልፅነትና ቅልጥፍና እንደሚያሳድግ ይጠበቃል።
©️Ethiopia Reporter

በአዲስ አበባ የገቢዎች ሠራተኞች በካሜራ የታገዘ ዩኒፎርም ሊለብሱ ነው ተባለ
ከዛሬ ረቡዕ፣ ኅዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ግብር ከፋዮችን የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፊነት የተሰጣቸው የቢሮው ሠራተኞች ቪዲዮ ካሜራ የተገጠመበት ዩኒፎርም ለብሰው ወደ ሥራ ይሠማራሉ ተብሏል።
ስሙ የቦዲ ዎርን ካሜራ ፕሮጀክት (Body Worn Camera Project) ሲሆን ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ወጥቶበታል::
ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት (ኢንሳ) ጋር በመተባበር የተሰራው ይህ አዲስ የካሜራ፡-
1. ቀረጻ:
የቁጥጥር ባለሙያዎች የሚያደርጉትን ሥራ በሙሉ በድምፅና በምሥል ይመዘግባሉ።
2. ቀጥታ ስርጭት:
የተቀረጸው መረጃ ወዲያውኑ ለዋናው መሥሪያ ቤትና ለቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች በቀጥታ ይላካል።
3. ክትትል (Location Tracking):
የቢሮው ባለሙያዎች በዋና መሥሪያ ቤት እና በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ቁጥጥር የሚያደርጉ ሠራተኞች እያንዳንዱን እንቅስቃሴ እና የት አካባቢ እንደሚገኙ ይከታተላሉ።
4.ግልጽነት:
ከግብር ከፋዮች ጋር የሚደረጉ ንግግሮች በሙሉ ስለሚመዘገቡ ግልፅነትና ተጠያቂነትን ያረጋግጣል።
ይህ እርምጃ በግብር አስተዳደር ሥራዎች ላይ ያለውን ግልፅነትና ቅልጥፍና እንደሚያሳድግ ይጠበቃል።
Reporter

7 months ago
ሰይፉ ፋንታሁን ባለውለታው አገኛቸው
#ethiopia | ዝነኛው የመዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጅ ሰይፉ ፋንታሁን የ30ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ለማክበር በዝግጅት ላይ የሚገኘው ሪፖርተር ጋዜጣ ቢሮ በድንገት በመገኘት ለሪፖርተር መስራችና ባለቤት አቶ አማረ አረጋዊ የእንኳን አደረሰዎ መልካም ምኞቱን ገልጿል።
በኢትዮጵያ የመዝናኛ ኢንደስትሪ ውስጥ ስመ ጥር የሆነው ሰይፉ ፋንታሁን ፣ ወደዚህ ከፍታ ከመድረሱ በፊት አቶ አማረ አረጋዊ ላደረጉለት ድጋፍም ልባዊ ምስጋናውን አቅርቧል።
#reporter

ወንድማማቾች በአንድ ቀን በተለያዩ የመኪና አደጋዎች ህይወታቸው አለፈ
የሁለት ወንድማማቾች ዕለታዊ ድርብ ሐዘን
1. ታላቁ ወንድም - ይስሐቅ አብርሃም
በአርባ ምንጭ ሃይላንድ ሙሉ ወንጌል አባልና አገልጋይ የነበረ። ከአዲስ አበባ ወደ አርባ ምንጭ በሚያደርገው ጉዞ ላይ እያለ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ሕይወቱ አልፏል።
2. ታናሹ ወንድም - አቤኔዘር አብርሃም
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪ የነበረ። የታላቅ ወንድሙን (ይስሐቅን) መርዶ እንደሰማ፣ ቀብር ለመድረስ ከሆሳዕና ወደ ወላይታ ሶዶ ሲጓዝ ነበር። በትላንትናው ዕለት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በከምባታ ዞን በደረሰ ሌላ የመኪና አደጋ ሕይወቱ አልፏል።

የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ለምን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደጣሰ እንዲያስረዳ ጥብቅ ትዕዛዝ ተሰጠ
#ethiopia : የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እየተጠቀመባቸው ያሉ ቢሮዎችን በሚመለከት የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በኃይል (በጉልበት) አስወጥቶ ለራሱ መጠቀሚያ እንዳያደርግ ፍርድ ቤት ዕግድ ጥሎ ቀጠሮ የሰጠ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ግን በኃይል ሰብሮ በመግባት ያደረገው የመንጠቅ ሒደት አግባብ አለመሆኑን፣ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ አንደኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ቀርቦ እንዲያስረዳ ዛሬ ኅዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
ፍርድ ቤቱ ኅዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ያቀረበውን አቤቱታ መርምሮ፣...
ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter....

የጎዳና ላይ ስብከት‼️
የመንገድ ላይ ስብከትን የሚያስቀር የሕግ መሻሻልና ማስፈጸሚያ መመርያ ሊዘጋጅ እንደሚገባ ተገለጸ ‼️
የትኛውንም የሃይማኖት ተቋም በማይወክልና ይልቁንም ማኅበረሰቡን በሚረብሽና በሚያማርር ሁኔታ በመንገድ ላይ የሚደረግን ስብከት የሚያስቀር ሕግ ሊሻሻልና መመርያ ሊዘጋጅ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ገለጸ፡፡
ቢሮው ይህንን የገለጸው ከአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ጋር በጋራ በመተባበር፣ የሃይማኖት ተቋማት ሚዲያዎች ለሰላም እሴት ግንባታ ያላቸውን ሚና በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደበት ወቅት ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ፣ የጎዳና ላይና በንግድ ቦታዎች ላይ የሚደረግ የሃይማኖት ስብከትን በተመለከተ ሲናገሩ "በንግድ እና በመንገድ ላይ እየተጎተትን እየተሰበክን ነው"በማለት ማህበረሰቡ በተደጋጋሚ ቅሬታ ያቀርባል ብለዋል።
ድርጊቱ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ በመለየቱ፣ የሕግ ማሻሻያ ከሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አንዱ እንደሆነ ተናግረዋል። ይህን በተመለከተም በቅርቡ ከሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት እንደሚኖር ጠቁመዋል።
የሃይማኖት ተቋማት አስተምህሮን እንዴት ማካሄድ ይገባል? በሚለው ላይ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባላት ጋር በጋራ የተለዩና እነሱም መክረውበት አቋም ሊይዙባቸው የሚገቡ ሌሎች የሕግ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች መኖራቸውንም ጠቁመው፣ በጋራ ጉዳዮች ላይ ግብዓት የመስጠት ልምድ ሊዳብር እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

በክልሎች የደመወዝ ጭማሪ በጀት ጉድለት ያጋጠመው ኮሚሽኑ በፈጠረው የቀመር ሥሌት አረዳድ ችግር ነው ተባለ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ያጋጠመው የደመወዝ ጭማሪ በጀት ጉድለት፣ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በሠራው የቀመር ሥሌት ላይ በተፈጠረ የአረዳድ ችግር ምክንያት መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በገንዘብ ሚኒስቴር የበጀት ዝግጅትና አስተዳደር መምርያ ኃላፊ አቶ ፍሬው ኃይሌ፣ አምስቱ ክልሎች የበጀት ጉድለት እንዳጋጠማቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኃላፊዎችና የክልሎቹ ተወካዮች በተገኙበት በተደረገ ውይይት፣ ችግሩ የተፈጠረው ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የሠራው የደመወዝ ጭማሪ ወይም ማስተካከያ ቀመር ሥሌትን በአግባቡ ካለመረዳት በመነጨ
ምክንያት እንጂ፣ ባጋጠመ የበጀት እጥረት ወይም በሌላ ምክንያት አለመሆኑንና መግባባት ላይ መደረሱን አስረድተዋል፡፡
በውይይቱም ክልሎች በአማካይ፣ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ደግሞ በእርከን ሒሳቡን መሥራታቸውን መናገራቸውን ያወሱት ኃላፊው፣ በዚህም ሒሳብ የሠሩበት መንገድ አንድ ዓይነት እንዳልሆነ መተማመናቸውንም ጭምር ጠቅሰው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ኮሚሽኑ ባቀረበው ሥሌት መሠረት የበጀት ምደባ ማድረጉን ገልጸዋል።
ጉዳዩን በምሳሌ ሲያስረዱ፣ ‹‹የበጀት ጉድለት ያጋጠመባቸው ክልሎች ደመወዛቸው 4,6ዐዐ ብር የነበሩ ሠራተኞች በቀጥታ 6,9ዐዐ ብር ይሆንላቸዋል›› ተብሎ በሰው ቁጥር እንደተባዛ ጠቁመው፣ ይህ ግን መሀል ላይ ያሉትን ወደ ዘጠኝ የሚደርሱ ደረጃዎች ወይም እርከኖች መሠረት ያደረገ አይደለም ብለዋል፡፡ ሆኖም በእርከኑ መሠረት የተሠራው ሒሳብና የሠራተኛው ቁጥር አንድ እንደሚሆን አቶ ኤፍሬም አስረድተዋል፡፡
ሦስት ሚሊዮን ብር፣ አሥር ሚሊዮን ብር፣ እንዲሁም እስከ አሥር ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት አጋጥሞናል ብለው ጥያቄ ያቀረቡ ክልሎች መኖራቸውን የጠቀሱት ኃላፊው፣ ሆኖም ሲቪል ሰርቪስ የሰጠው ምላሽ የአንድ ወይም የሁለት ሚሊዮን ብር የበጀት ልዩነት ሊፈጠር ይችላል እንጂ ይኼን ያህል አይሆንም የሚል መሆኑን፣ ይህም ከሆነ ደግሞ ክልሎች በራሳቸው ገቢ መሙላት የሚችሉ መሆኑን እንደተነገራቸው አስታውሰዋል፡፡
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ቀመሩን የሠራው እስከ 2016 ዓ.ም. ሰኔ ወር ባለው የመንግሥት ሠራተኛ ቁጥር መሠረት መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው፣ ከዚያ በኋላ ቅጥር የፈጸሙ ክልሎች ላይ የሠራተኛ ቁጥር ልዩነት መምጣቱንና ይህንንም በጥያቄ መልክ ቀርቦ ነበር ብለዋል፡፡ ነገር ግን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ቅጥር በማድረጉ ለእነዚህ ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ በጀት ከፌዴራል መንግሥት ሊደለድል እንደማይችል፣ ራሳቸው ክልሎች ኃላፊነቱን እንዲወስዱ እንደተነገራቸው አስረድተዋል።
ለ12 ክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የሚለቀቀው በጀት በየሦስት ወራት ለሦስት ጊዜያት ያህል ተከፋፍሎ ከግምጃ ቤት እንዲደርሳቸው እንደሚደረግ፣ በዚህም የመጀመሪያው ሦስት ወራት ማለትም የመስከረም፣ የጥቅምትና የኅዳር ወራት ደመወዝ መሠራጨት መጀመሩን ጠቁመዋል።
በኅዳር አጋማሽ፣ የታኅሳስ፣ የጥርና እንዲሁም የየካቲት፣ በየካቲት አጋማሽ ደግሞ፣ የመጋቢት፣ የሚያዝያ፣የግንቦትና የሰኔ ወራት እንደሚለቀቅ ተናግረዋል።Reporter

8 months ago
ሰሜን ኢትዮጵያን ከታጁራ፣ አሰብ እና ምጽዋ የወደብ ከተሞች ጋር ለማገናኘት የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የ1.58 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር መደበኛ-መስመር ባቡር ዝርጋታ ዕቅድ ይፋ አደረገ።
Reporter English
Reporter English
8 months ago
በኢትዮጵያ ያለው የድህነት ምጣኔ በ2025 ወደ 43 በመቶ ከፍ ሊል እንደሚችል የዓለም ባንክ አስታወቀ
የዓለም ባንክ ድህነትንና የሀብት ፍትሐዊነትን በተመለከተ ከሰሞኑ ባወጣው መረጃ በኢትዮጵያ በተያዘው እ.ኤ.አ. 2025 የድህነት ምጣኔ ወደ 43 በመቶ ከፍ ሊል እንደሚችል አስታወቀ፡፡
የዓለም ባንክ የድህነት ምጣኔና የሀብት ፍትሐዊነት ሰነድ ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ድህነትን ለመቀነስ መሠረታዊ ስኬቶችን ብታሳይም የውጭና የውስጥ መሰናክሎች የዜጎች ኑሮ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማሳደራቸውን አስታውቋል፡፡
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና ከፍተኛ ድርቅ፣ የአገራዊ ጥቅል ምርት ዕድገቱን እንዳቀዘቀዘውና የዋጋ ንረቱን እንዳባባሰው አክሎ ገልጿል፡፡
የአገሪቱ የድህነት ምጣኔ እ.ኤ.አ. በ2016 ከነበረበት 33 በመቶ በ2021 ወደ 39 በመቶ ከፍ ማለቱን የገለጸው የዓለም ባንክ፣ ይህ መለኪያ በቀን ከሦስት ዶላር በታች የሚያገኙ ዜጎችን ግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡
ከኢትዮጵያውያን መካከል 37 በመቶ የሚሆነው ዜጋ ከሦስት ዶላር በታች ገቢ ያለው፣ 38 በመቶ ቢያንስ አንድ ለትምህርት የደረሰ ሕፃን ትምህርት ቤት ያልገባ የቤተሰብ አባል ያላቸውና 26 በመቶ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ያልጨረሱ ጎልማሶች እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡
Via Ethiopian reporter

9 months ago
በአማራ ክልል ውጊያ ባለባቸው አካባቢዎች ታዳጊዎች ለሴተኛ አዳሪነት መጋለጣቸውን ጥናት አመላከተ
በአማራ ክልል ላለፉት ሁለት ዓመታት ውጊያ ባለባቸው አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው፣ ዕድሜያቸው ለጋብቻ ያልደረሱ ታዳጊዎች ወደ አዲስ አበባና ወደ ሌሎች የክልል ከተሞች በመሄድ በሴተኛ አዳሪነት እንደሚሰማሩ፣ ጀንደር ኤንድ አዶለስንስ ግሎባል ኤቪደንስ (Gender and Adolescence Global Evidence) የተሰኘ ዓለም አቀፍ የጥናት ቡድን አስታወቀ፡፡
የተቋሙ ጥናት አማራ ክልልን ጨምሮ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በሶማሌና በአፋር ክልሎች ግጭትና ድርቅ ባሉባቸው አካባቢዎች በሚኖሩ 20 ሺሕ ሴቶች ላይ የተደረገ መሆኑንና የልጅነት ጋብቻን ጨምሮ ፆታዊ ጥቃት በከፍተኛ መጠን እንደጨመረ መረጋገጡ ተመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያ የሴቶችን ማኅበራዊ ቅንጅት ‹‹ትመራለች›› በሚል መሪ ቃል ላለፉት አምስት ዓመታት በወጣት ሴቶች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ሲሠራ የነበረው ፕሮጀክት የመዝጊያ ፕሮግራም ላይ ጥናቱን ያቀረቡት፣ የምርምር ተቋሙ የኢትዮጵያ ተወካይ ወርቅነህ አበበ (ዶ/ር) ናቸው፡፡
በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን አምስት ወረዳዎች ውስጥ ካሉ 67 ቀበሌዎች ናሙና መወሰዱን የተናገሩት ወርቅነህ (ዶ/ር)፣ በቀበሌዎቹ ላለፉት ሁለት ዓመታት ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተዘግተው መቆየታቸውንና ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ውጪ ለመሆን መገደዳቸውን ገልፀዋል።via.reporter

10 months ago
መረጃ የማይሰጡ ኃላፊዎችን ከደመወዛቸው የሚቀጣ የመረጃ ነፃነት ማሻሻያ አዋጅ መዘጋጀቱ ተነገረ!
-ከመንግሥት ጋር የሚሠሩ የግል ተቋማት መረጃ እንዲሰጡ ይገደዳሉ
መረጃ የማይሰጡ የመንግሥት ኃላፊዎች የደመወዛቸውን አንድ-ሦስተኛ እንዲቀጡ የሚያደርግ የመረጃ ነፃነት ማሻሻያ አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑ ታወቀ፡፡የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ ቁጥር 590/2000 እየተሻሻለ ያለው የመረጃ ነፃነት ረቂቅ አዋጅ ተብሎ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
በማሻሻያው መሠረት መረጃ ሲጠየቁ አልሰጥም የሚሉ ኃላፊዎች እንደ በፊቱ በተቋም ደረጃ ሳይሆን፣ በግለሰብ ደረጃ በሕግ ተጠያቂ እንዲደረጉ የሚያስገድድ አንቀጽ በማሻሻያ ረቂቁ መካተቱ ታውቋል።
ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter....
-ከመንግሥት ጋር የሚሠሩ የግል ተቋማት መረጃ እንዲሰጡ ይገደዳሉ
መረጃ የማይሰጡ የመንግሥት ኃላፊዎች የደመወዛቸውን አንድ-ሦስተኛ እንዲቀጡ የሚያደርግ የመረጃ ነፃነት ማሻሻያ አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑ ታወቀ፡፡የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ ቁጥር 590/2000 እየተሻሻለ ያለው የመረጃ ነፃነት ረቂቅ አዋጅ ተብሎ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
በማሻሻያው መሠረት መረጃ ሲጠየቁ አልሰጥም የሚሉ ኃላፊዎች እንደ በፊቱ በተቋም ደረጃ ሳይሆን፣ በግለሰብ ደረጃ በሕግ ተጠያቂ እንዲደረጉ የሚያስገድድ አንቀጽ በማሻሻያ ረቂቁ መካተቱ ታውቋል።
ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter....
10 months ago
በሕንፃዎችና በቤቶች ውስጥ የፀሐይ ኃይል መጠቀም አስገዳጅ ሊሆን ነው
ኢትዮጵያ ያላትን የፀሐይ ኃይል ለመጠቀም በሁሉም ሕንፃዎችና ቤቶች ውስጥ የፀሐይ ኃይል መጠቀም በሒደት አስገዳጅ እንደሚሆን ተገለጸ፡፡ይህ የተገለጸው የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኢንተርናሽናል ሶላር አሊያንስ (International Solar Alliance) ጋር የፀሐይ ኃይል በጋራ ለማልማት የሚያስችል ስምምነት ነሐሴ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ሲፈራረሙ ነው፡፡
‹‹ኢትዮጵያ ከፍተኛ የፀሐይ ኃይል አላት›› ያሉት የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ደኤታ ሡልጣን ወሊ (ኢንጂነር)፣ ይህን አቅም ጥቅም ላይ ለማዋል ከዚህ ቀደም አለመሠራቱን፣ ለዚህም ሲባል በሒደት በእያንዳንዱ ቤትና ሕንፃ ጣሪያ የፀሐይ ኃይል ቴክኖሎጂ እንደሚገጠም አስታውቀዋል፡፡
ተጨማሪ : https://ethiopianreporter....

ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ ማንነታቸው ባልታወቁና ጭምብል ባደረጉ ሰዎች መወሰዱ ተጠቆመ
#ethiopia | ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ ላለፉት አራት ቀናት ማለትም ከነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓም ጀምሮ ሥራ ባለመግባቱ በእጅ ስልኩ ላይ ቢደወልለትም ሆነ ከቤተሰቦቹ ለማጣራት ቢሞከርም ማግኘት አልተቻለም።
በሥራ ላይ እያለ የገባበት በመጥፋቱ የሥራ ባልደረቦቹም ሆኑ የሚቀርቡት ጓደኞቹ በእጅ ስልኩ ላይ ቢደውሉም ማግኘት አልተቻለም።
ጋዜጠኛ ዮናስ በሚኖርበት በሸገር ከተማ ኮዬ ፌጬ ኮንዶሚኒዬም በመሄድ በተደረገ ማጣራት፣ ጋዜጠኛው የተወሰደው ረቡዕ ምሽት ፊታቸውን በጭምብል በሸፈኑ ሰዎች መሆኑን ባካባቢው ካሉ የጥበቃ ሠራተኞች ለማወቅ ተችሏል።
የጥበቃ ሠራተኞቹ ተጨማሪ መረጃ መስጠት ባለመቻላቸው፣ ጋዜጠኛ ዮናስ፣ እነማን እንደወሰዱትና የት እንደተወሰደ ማወቅ አልተቻለም። #ሪፖርተር
Ethiopian Reporter’s Yonas Amare Abducted by Masked Men
Yonas Amare, a senior editor at the Ethiopian Reporter and The Reporter, remains missing after being abducted by a group of masked individuals several days ago.
Individuals wearing what appeared to be military uniforms and face masks took Yonas from his residence in Koye Fiche, Addis Ababa, at around 9:30PM on the night of Wednesday, August 13, 2025, according to eyewitnesses.
These individuals confiscated the mobile phones of residents in the area before detaining Yonas to prevent videos of his abduction being recorded. Residents were instructed to remain inside their homes while it was taking place, and warned not to talk about it afterwards.
Yonas’s whereabouts remain unknown. The Addis Ababa Police Commission has stated it does not have Yonas in custody. No formal charges have been instituted against Yonas, nor has he been brought before a court of law.
Attempts to locate Yonas have so far been unsuccessful.

ኢትዮጵያ የተቀበሩ ፀረ ሰው ፈንጂዎችን ለማስወገድ የጊዜ ገደቡ ለአራተኛ ጊዜ እንዲራዘምላት ጥያቄ አቀረበች!
በጄኔቫ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤት፣ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በጦርነት ወቅት ተቀብረው የቀሩ የፀረ ሰው ፈንጂ ቅሪቶችን ለማስወገድ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ለአራተኛ ጊዜ እንዲራዘም ጥያቄ አቀረበ፡፡
እ.ኤ.አ. በ2004 ኢትዮጵያ ያፀደቀችውና የኦታዋ ስምምነት በመባል የሚታወቀውን እ.ኤ.አ. በ1997 የፀደቀውን የፀረ ሰው ፈንጂዎች ጥቅም፣ ምርት፣ ግብይትና ክምችትን ለማስወገድና ለማገድ የወጣ ስምምነት መፈረሟ ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያ በስምምነቱ አንቀጽ 5 መሠረት በየትኛውም የአገሪቱ አካባቢዎች ያሉ ፀረ ሰው ፈንጂዎችን ማስወገድ፣ ወይም መወገዳቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ዕርምጃዎችን የመውሰድ ግዴታ እንዳለባት ተደንግጓል፡፡
https://ethiopianreporter....

11 months ago
ኢትዮጵያ እና ቻይና የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመርን ለማሻሻል ውይይት እያደረጉ ተባለ
ኢትዮጵያ ለዚህ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ቤጂንግን ተስፋ አድርጋለች።
አዲስ አበባን ከጅቡቲ ጋር የሚያገናኘው የ760 ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር ሰፊ መሠረተ ልማት ማሻሻያ ተጨማሪ ድልድዮች፣ አጥሮች፣ ለእንስሳት መሻገሪያ የሚሆኑ መንገዶች፣ የባቡር ጣቢያዎች እና ሌሎች መገልገያዎች መገንባት እንዲሁም ተጨማሪ ባቡሮች (ሎኮሞቲቭ) መግዛትን እንደሚያካትት ተገልጿል።
Reporter English
ኢትዮጵያ ለዚህ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ቤጂንግን ተስፋ አድርጋለች።
አዲስ አበባን ከጅቡቲ ጋር የሚያገናኘው የ760 ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር ሰፊ መሠረተ ልማት ማሻሻያ ተጨማሪ ድልድዮች፣ አጥሮች፣ ለእንስሳት መሻገሪያ የሚሆኑ መንገዶች፣ የባቡር ጣቢያዎች እና ሌሎች መገልገያዎች መገንባት እንዲሁም ተጨማሪ ባቡሮች (ሎኮሞቲቭ) መግዛትን እንደሚያካትት ተገልጿል።
Reporter English
11 months ago
የተከፈለ ካፒታላቸውን አምስት ቢሊዮን ብር ማድረስ ያልቻሉ የግል ባንኮችን በአስገዳጅነት እንዲዋሃዱ የሚያደርግ በመሆኑ ባንኮች እንዲዘጋጁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክምክትል ገዥ አሳሰቡ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ደስታ ሰሞኑን በተካሄደው የኢትዮጵያ ፋይናንስ ሪፎርም ላይ በግልጽ እንደተናገሩት፣ ባንኮች በተቀመጠላቸው ጊዜ የተከፈለ ካፒታላቸውን አምስት ቢሊዮን ብር ካላደረሱ፣ ብሔራዊ ባንክበቀጥታ እንዲዋሃዱ አስገዳጅ ዕርምርጃ ይወስዳል፡፡
የሚጠበቀውን ካፒታል እንዲያሟሉ እ.ኤ.አ. 2026 ድረስ ቀነ ገድብ የተቀመጠ መሆኑን ያመለከቱት ምክትል ገዥው፣ ‹‹ባንኮችን እባካችሁ ብለን አንለምንም፣ ይህንን ታሳቢ በማድረግ ሊዘጋጁ ይገባል፤›› ብለዋል፡፡
ወደ ውህደት እንዲገቡ የሚገደዱት ባንኮች ማን ከማን ጋርይዋሃዳሉ? የሚለውም ውሳኔ የሚሰጠው ከብሔራዊ ባንክእንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡
Via Reporter Newspaper

Comments