የውጭ ምንዛሬ ተመን ማሻሻያው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ላይ የ445 ቢሊዮን ብር የሒሳብ ኪሳራ ማስከተሉ ተገለፀ
በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ እንዲወሰን መደረጉ፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሒሳብ መዛግብት ላይ የ445 ቢሊዮን ብር ያልተመዘገበ (unrealized) የሒሳብ ኪሳራ ማስከተሉን በዚህ ሳምንት የወጣው የባንኩ ኦዲት ሪፖርት አመለከተ።
በአዲሱ የባንኩ ገዢ ዶ/ር እዮብ ተካሊኝ የተፈረመውና የ2024/25 በጀት ዓመትን የሚሸፍነው ይህ ሪፖርት፣ ባንኩ በበጀት ዓመቱ 428 ቢሊዮን ብር የተጣራ የሥራ ኪሳራ እንዳጋጠመው ያሳያል። ይህ ከፍተኛ የሒሳብ ቀውስ የተከሰተው ባንኩ ያለበት የውጭ ምንዛሬ ዕዳ እና ግዴታዎች፣ የብር ዋጋ ዝቅ ማለቱን ተከትሎ በብር ሲመነዘሩ በከፍተኛ ሁኔታ በማሻቀባቸው መሆኑ ተገልጿል።
የባንኩን የሒሳብ መዝገብ የመረመረው 'MSE Audit Service LLP' ባወጣው መግለጫ፣ ይህ የኪሳራ መጠን ከባንኩ ካፒታልና አጠቃላይ መጠባበቂያ ፈንድ በላይ ሊሆን እንደሚችል በመጠቆም፣ ባንኩ እንደ ተቋም የመቀጠል አቅሙ (Going Concern) ላይ አደጋ እንዳይጋርጥ ስትራቴጂካዊ የፖሊሲ ጣልቃ ገብነት እንደሚያስፈልግ አስጠንቅቋል።
እንደ ኦዲተሮቹ ገለጻ፣ ባንኩ ያለበትን የውጭ ምንዛሬ ዕዳዎች የሚከፍልበት ጊዜ ሲደርስ ለከፍተኛ የገንዘብ ጫና ሊጋለጥ ይችላል። በተለይም ባንኩ ከአቡ ዳቢ ፈንድ እና ከሳዑዲ አረቢያ የተቀበላቸው የቢሊዮን ዶላሮች ተቀማጭ ዕዳዎች፣ ብር ዋጋውን ማጣቱን ተከትሎ ለመክፈል የሚጠይቁት የብር መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ለኪሳራው ዋነኛ ምክንያት ሆኗል።
በተጨማሪም ሪፖርቱ በባንኩ የወርቅ ግብይት ላይ የታየውን ለውጥ የዳሰሰ ሲሆን፣ ለወርቅ ግዢ የወጣው ወጪ ካለፈው ዓመት ከነበረበት 7 ቢሊዮን ብር ወደ 421 ቢሊዮን ብር አሻቅቧል። ባንኩ ሕገ-ወጥ የወርቅ ዝውውርን ለመከላከል ለሀገር ውስጥ አቅራቢዎች የ15 በመቶ ተጨማሪ ክፍያ (Premium) በመስጠቱ ምክንያት ብቻ 57 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ኪሳራ መመዝገቡም ተመልክቷል። የኢኮኖሚ ባለሙያው ዶ/ር አብዱልመነን መሐመድ እንደገለጹት፣ ይህ ኪሳራ የሚጠበቅ ቢሆንም መጠኑ ግን እጅግ አስደንጋጭ ነው።
ባለሙያው አክለውም ብሔራዊ ባንኩ ይህንን ኪሳራ ለመሸፈን ያለው ብቸኛ አማራጭ መንግሥት ቦንድ እንዲያወጣለት ማድረግ እንደሆነና ይህም ውሎ አድሮ የኢትዮጵያ ግብር ከፋይ ሕዝብ ዕዳ ሆኖ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።
Reporter English

5 months ago