በኢትዮጵያ ከጥር ወር ጀምሮ የፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም፣ ማምረት ወይም ማስገባት በገንዘብ ቅጣት እና በእስራት የሚያስቀጣ አዋጅ በይፋ ተፈጻሚ ሊሆን ነው።
የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የሽግግር ጊዜው መጠናቀቁን ተከትሎ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር አስታውቋል።
የፕላስቲክ ከረጢት አምራቾች ለስድስት ወራት የተሰጠው የመሸጋገሪያ ጊዜ በቂ አለመሆኑን ቢገልጹም፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የሽግግሩ ጊዜ ጥር 23 እንደሚያበቃ በመጥቀስ ወደ ተግባራዊ እርምጃ እንደሚገባ አሳውቋል።
* መጠቀም ይዞ መገኘት:- ከ5,000 እስከ 10,000 ብር
* ማምረት/ ማስገባት/ መሸጥ :- ከ50,000 እስከ 100,000 ብር እና እስከ 5 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት
አዋጁ የወንጀል ድርጊቶችን የፈጸመው ሕጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት (አምራች ወይም አስመጪ) ከሆነ፣ የተጣለው የገንዘብ ቅጣት ሦስት እጥፍ እንደሚሆን በግልጽ አስቀምጧል።
አዋጁ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ሥራ ላይ መዋሉን አስመልክቶ፣ ማንኛውም ግለሰብ እና ድርጅት ይህን አዲስ ደንብ ተከትሎ ራሱን እንዲያስተካክል ጥሪ ቀርቧል።
Via Ethiopia Reporter

8 months ago