ኢትዮጵያ የ2027ቱን የዓለም አቀፍ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር (AIPS) ጉባኤን ለማስተናገድ ተመረጠች
#ethiopia | የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር በ2027 የሚካሄደውን የዓለም አቀፍ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር (AIPS) ዓመታዊ ጉባኤን በዝግጅትነት ለመምራት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱ ተነገረ።
ታላቅ ዓለም አቀፍ መድረክ ኢትዮጵያ በስፖርቱ ዓለም ያላትን ስም የምታድስበትና "የስፖርት ቤተሰቡን" በአንድ ጣሪያ ሥር የምታገናኝበት ትልቅ ዕድል ተደርጎ ተወስዷል። በጉባኤው ላይ የሚከተሉት ዋና ዋና ክንውኖች እንደሚጠበቁ ታውቋል፦
ከ100 በላይ አገራ* የተውጣጡ ጋዜጠኞች ተሳትፎ፤ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የስፖርት ተቋማት መሪዎች መገኘት፤የዓለም "ምርጥ የስፖርት ጋዜጠኝነት ዓመታዊ የሽልማት ፕሮግራም"፤የወጣት ስፖርት ጋዜጠኞች (AIPS Young Reporters) ሥልጠና ይደረጋል።
ይህ ጉባኤ ከዘገባ ባለፈ ለኢትዮጵያ ስፖርት ዲፕሎማሲ፣ ለኢኮኖሚ መነቃቃትና ለአገራዊ ገጽታ ግንባታ የላቀ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል። የዓለም ስፖርት ባለሙያዎችና አመራሮች በ2027 በአዲስ አበባ እንደሚሰበሰቡ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #tikvah #ethiopia #aips #sportsjournalism #aips2027 #sportdiplomacy #ኢትዮጵያ #ስፖርትጋዜጠኝነት #አዲስአበባ

4 months ago