Logo
YenetaTube
የገቢዎች ሠራተኞች በካሜራ የታገዘ ዩኒፎርም ሊለብሱ ነው!

የግልፅነትና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ወደ ሥራ አስገባ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከግብር ከፋዮች ጋር ግንኙነት የሚፈጥሩና ቁጥጥር የሚያደርጉ ሠራተኞች ላይ ትልቅ ለውጥ አመጣ።

ከዛሬ ረቡዕ፣ ኅዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ግብር ከፋዮችን የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፊነት የተሰጣቸው የቢሮው ሠራተኞች ቪዲዮ ካሜራ የተገጠመበት ዩኒፎርም ለብሰው ወደ ሥራ ይሠማራሉ።

ስሙ የቦዲ ዎርን ካሜራ ፕሮጀክት (Body Worn Camera Project) ሲሆን ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ወጥቶበታል::

ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት (ኢንሳ) ጋር በመተባበር።
የተሰራው ይህ አዲስ የካሜራ ቴክኖሎጂ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡-

1. ቀረጻ:
የቁጥጥር ባለሙያዎች የሚያደርጉትን ሥራ በሙሉ በድምፅና በምሥል ይመዘግባሉ።

2. ቀጥታ ስርጭት:
የተቀረጸው መረጃ ወዲያውኑ ለዋናው መሥሪያ ቤትና ለቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች በቀጥታ ይላካል።

3. ክትትል (Location Tracking):
የቢሮው ባለሙያዎች በዋና መሥሪያ ቤት እና በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ቁጥጥር የሚያደርጉ ሠራተኞች እያንዳንዱን እንቅስቃሴ እና የት አካባቢ እንደሚገኙ ይከታተላሉ።

4.ግልጽነት:
ከግብር ከፋዮች ጋር የሚደረጉ ንግግሮች በሙሉ ስለሚመዘገቡ ግልፅነትና ተጠያቂነትን ያረጋግጣል።

ይህ እርምጃ በግብር አስተዳደር ሥራዎች ላይ ያለውን ግልፅነትና ቅልጥፍና እንደሚያሳድግ ይጠበቃል።

©️Ethiopia Reporter

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.