ቀይ ባሕር ፡ የኢትዮጵያ ቁልፍ ስትራቴጂያዊ…?
የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ስትራቴጂካዊ ፋይዳ
በስላባት ማናዬ
#ethiopia | ኢትዮጵያ የምትገኝበት የአፍሪካ ቀንድ መልከዓ ምድራዊ አቀማጥ ለመካከለኛው ምሥራቅ፣ለአወሮፓ እና ኤስያ ትልቅ ጂኦ ስትራቴጂካዊ ቦታ ነው። ይህ ቀጣና ከቀይ ባሕር እና ከሕንድ ውቅያኖስ ጋር የሚተሳሰር ነው።
ቀጣናው በወሣኛ የዓለማችን የንግድ መሥመሮች መተላለፊያ ፡በሦስቱ አብርሃማዊ ሐይማኖቶች መነሻ ቅርብ የሆነውን ያህል በታሪክ እና በገቢር በርካታ የደኀንነት ስጋቶችን በየጊዜው ደቅኖ የሚገኝ ነው።
ሽብርተኝነት፣ የባሕር ላይ ዘራፊዎች፣ ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች፣ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች እና አደገኛ ዕጽ አዘዋዋሪዎች በቀጣናው ከተደቀኑ አደጋዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
በዚህ ቀጣና ከሚገኙ አገራት መካከል ሁነኛዋ መልሕቅ አገር ኢትዮጵያ ነች። ኢትዮጵያ በቀጣናው የተደቀኑ የደኀንነት ስጋቶች በራሷ እና በዓለም አቀፍ የደሕንነት ስርዓት ውስጥ ከባድ መሰናክል እንዳይፈጥር ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ ሥራ ስታከናውን ቆይታለች።
በተለይ በአካባቢው የሽብርተኞች አደጋን በመዋጋት ረገድ ከኃያላንም ከመካከለኛ ኃይላት ጋር በጋር ተንቀሳቅሳለች፡እየተንቀሳቀሰችም ትገኛለች።
ይህ እንቅስቃሴዋ በተለይ ላለፉት 30 ዓመታት በየብስ እና በአየር ኃይል ብቻ ተወስኖ ቆይቷል። አሁን ኢትዮጵያ አላግባብ የተወሰደብኝን የባሕር በር መልሼ ማግኘት ይገባኛል የሚል ጥያቄ አንስታ እየተጓዘች ነው።
በቀጣናው እና በቀይ ባሕር አካባቢ ያለውን የደህንነት ሥጋት በጥሞና ለተከታተለው ኢትዮጵያ አሁን ላይ በየብስ እና በአየር ክልሉ ከምታደርገው የደህንንት ሥራ አኳያ የባሕር በሯን መልሳ ማግኘት እና የቀይ ባሕር አባል ወደ መሆን የመመለስ ጉዞዋ ጠቀሜታው ከራሷ ያለፈ በዓለም አቀፍ የደህንነት እና ጸጥታ መዋቅር ውስጥም የጎላ ሚና ይኖረዋል።
ከዚህ አኳያ የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ ዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ መደገፍ ብቻ ሳይሆን ለተግባራዊነቱ በንቃት ሊሳተፍ ይገባል።
በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የራሴን ምልከታ አቅርቢያለሁ፡ የግላችሁን ደግሞ በአስተያየት መስጫው ሥር አስፍሩ
https://www.thereportereth...

6 months ago