የጎዳና ላይ ስብከት‼️
የመንገድ ላይ ስብከትን የሚያስቀር የሕግ መሻሻልና ማስፈጸሚያ መመርያ ሊዘጋጅ እንደሚገባ ተገለጸ ‼️
የትኛውንም የሃይማኖት ተቋም በማይወክልና ይልቁንም ማኅበረሰቡን በሚረብሽና በሚያማርር ሁኔታ በመንገድ ላይ የሚደረግን ስብከት የሚያስቀር ሕግ ሊሻሻልና መመርያ ሊዘጋጅ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ገለጸ፡፡
ቢሮው ይህንን የገለጸው ከአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ጋር በጋራ በመተባበር፣ የሃይማኖት ተቋማት ሚዲያዎች ለሰላም እሴት ግንባታ ያላቸውን ሚና በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደበት ወቅት ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ፣ የጎዳና ላይና በንግድ ቦታዎች ላይ የሚደረግ የሃይማኖት ስብከትን በተመለከተ ሲናገሩ "በንግድ እና በመንገድ ላይ እየተጎተትን እየተሰበክን ነው"በማለት ማህበረሰቡ በተደጋጋሚ ቅሬታ ያቀርባል ብለዋል።
ድርጊቱ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ በመለየቱ፣ የሕግ ማሻሻያ ከሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አንዱ እንደሆነ ተናግረዋል። ይህን በተመለከተም በቅርቡ ከሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት እንደሚኖር ጠቁመዋል።
የሃይማኖት ተቋማት አስተምህሮን እንዴት ማካሄድ ይገባል? በሚለው ላይ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባላት ጋር በጋራ የተለዩና እነሱም መክረውበት አቋም ሊይዙባቸው የሚገቡ ሌሎች የሕግ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች መኖራቸውንም ጠቁመው፣ በጋራ ጉዳዮች ላይ ግብዓት የመስጠት ልምድ ሊዳብር እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡
#reporter
seledadotio

9 months ago