በኢትዮጵያ ያለው የድህነት ምጣኔ በ2025 ወደ 43 በመቶ ከፍ ሊል እንደሚችል የዓለም ባንክ አስታወቀ
የዓለም ባንክ ድህነትንና የሀብት ፍትሐዊነትን በተመለከተ ከሰሞኑ ባወጣው መረጃ በኢትዮጵያ በተያዘው እ.ኤ.አ. 2025 የድህነት ምጣኔ ወደ 43 በመቶ ከፍ ሊል እንደሚችል አስታወቀ፡፡
የዓለም ባንክ የድህነት ምጣኔና የሀብት ፍትሐዊነት ሰነድ ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ድህነትን ለመቀነስ መሠረታዊ ስኬቶችን ብታሳይም የውጭና የውስጥ መሰናክሎች የዜጎች ኑሮ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማሳደራቸውን አስታውቋል፡፡
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና ከፍተኛ ድርቅ፣ የአገራዊ ጥቅል ምርት ዕድገቱን እንዳቀዘቀዘውና የዋጋ ንረቱን እንዳባባሰው አክሎ ገልጿል፡፡
የአገሪቱ የድህነት ምጣኔ እ.ኤ.አ. በ2016 ከነበረበት 33 በመቶ በ2021 ወደ 39 በመቶ ከፍ ማለቱን የገለጸው የዓለም ባንክ፣ ይህ መለኪያ በቀን ከሦስት ዶላር በታች የሚያገኙ ዜጎችን ግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡
ከኢትዮጵያውያን መካከል 37 በመቶ የሚሆነው ዜጋ ከሦስት ዶላር በታች ገቢ ያለው፣ 38 በመቶ ቢያንስ አንድ ለትምህርት የደረሰ ሕፃን ትምህርት ቤት ያልገባ የቤተሰብ አባል ያላቸውና 26 በመቶ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ያልጨረሱ ጎልማሶች እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡
Via Ethiopian reporter

8 months ago