4 months ago
ኢትዮጵያ የ2027ቱን የዓለም አቀፍ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር (AIPS) ጉባኤን ለማስተናገድ ተመረጠች
#ethiopia | የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር በ2027 የሚካሄደውን የዓለም አቀፍ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር (AIPS) ዓመታዊ ጉባኤን በዝግጅትነት ለመምራት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱ ተነገረ።
ታላቅ ዓለም አቀፍ መድረክ ኢትዮጵያ በስፖርቱ ዓለም ያላትን ስም የምታድስበትና "የስፖርት ቤተሰቡን" በአንድ ጣሪያ ሥር የምታገናኝበት ትልቅ ዕድል ተደርጎ ተወስዷል። በጉባኤው ላይ የሚከተሉት ዋና ዋና ክንውኖች እንደሚጠበቁ ታውቋል፦
ከ100 በላይ አገራ* የተውጣጡ ጋዜጠኞች ተሳትፎ፤ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የስፖርት ተቋማት መሪዎች መገኘት፤የዓለም "ምርጥ የስፖርት ጋዜጠኝነት ዓመታዊ የሽልማት ፕሮግራም"፤የወጣት ስፖርት ጋዜጠኞች (AIPS Young Reporters) ሥልጠና ይደረጋል።
ይህ ጉባኤ ከዘገባ ባለፈ ለኢትዮጵያ ስፖርት ዲፕሎማሲ፣ ለኢኮኖሚ መነቃቃትና ለአገራዊ ገጽታ ግንባታ የላቀ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል። የዓለም ስፖርት ባለሙያዎችና አመራሮች በ2027 በአዲስ አበባ እንደሚሰበሰቡ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #tikvah #ethiopia #aips #sportsjournalism #aips2027 #sportdiplomacy #ኢትዮጵያ #ስፖርትጋዜጠኝነት #አዲስአበባ

5 months ago
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ
ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው ኮንቲኔንታል ቱር እና የዓለም ሻምፒዮናን የማስተናገድ ዕቅድ
#ethiopia | የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ዛሬ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በማግኖሊያ ሆቴል ለሚዲያ አካላት በሰጡት መግለጫ፣ በአገራችን አትሌቲክስ ታሪክ አዲስ ስኬት የሚመዘገብባቸው ታላላቅ ሥራዎች በቀጣይ ሳምንታት እንደሚከናወኑ አስታውቀዋል።
ታሪካዊው ኮንቲኔንታል ቱር፦
በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው የኮንቲኔንታል ቱር ውድድር የአገራችንን የስፖርት ዲፕሎማሲ አቅም የሚያሳድግና ዓለም አቀፍ ውድድሮችን የማዘጋጀት ብቃታችንን ለዓለም የሚያሳይ ይሆናል። ውድድሩን ከነሐስ (Bronze) ወደ ወርቅ (Gold) ደረጃ ለማሳደግ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው።
የዓለም ሻምፒዮናን የማስተናገድ ጥረት፦
ኢትዮጵያ በ2029 እና በ2031 የሚካሄዱትን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎችን ለማስተናገድ በጨረታ ሂደት ውስጥ በንቃት እየተሳተፈች ትገኛለች።
የ2028 ዓለም አቀፍ ውድድር፦
የ2028 የዓለም አትሌቲክስ አልትሜት ሻምፒዮንሺፕን ለማዘጋጀት የሚያስችሉ የጨረታና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገልጿል።
መደበኛ ስብሰባዎች፦
55ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እና 29ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በቀጣይ ሳምንታት የሚከናወኑ ሌሎች ዋና ዋና ተግባራት ናቸው።
ይህ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ውጤት ብቻ ሳይሆን፣ ትላልቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን በማዘጋጀትም የዓለም ትኩረት እንድትሆን የሚያስችላት ትልቅ እርምጃ ነው።
#getu #ethiopia #athletics #continentaltour #sileshisihine #worldathletics #sportdiplomacy #addisababa #አትሌቲክስ #ስለሺስህን #ኮንቲኔንታልቱር #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

ኢትዮጵያ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ አስመዘገበች
#ethiopia | የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባደረገው ከፍተኛ የስፖርት ዲፕሎማሲ ጥረት፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ውድድርን የማዘጋጀት ዕድል አገኘች።
ዛሬ ይፋ በሆነው መረጃ መሠረት፣ ውድድሩ በዓለም አትሌቲክስ (World Athletics) የውድድር ካላንደር ውስጥ በይፋ ተካቷል።
የውድድሩ ዝርዝር መረጃዎች
የውድድሩ ዓይነት፦
የአንድ ቀን ዓለም አቀፍ ስብሰባ (One Day Meeting)።
የሚካሄድበት ቀን፦
ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም (April 18, 2026 የቀን አቆጣጠር እንደ አውሮፓውያን)።
ቦታ፦ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ።
ተሳታፊዎች፦
ከተለያዩ የዓለም አገራት የተውጣጡ ዝነኛ አትሌቶች።
የልምድ ልውውጥ፦
ውድድሩ በዓለም አትሌቲክስ ከፍተኛ ባለሙያዎች የሚመራ በመሆኑ፣ ለሀገራችን አዘጋጆችና ሙያተኞች ትልቅ የልምድ መቅሰሚያ ይሆናል።
የአትሌቶች ተጠቃሚነት፦
በውድድሩ አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶች ከፍተኛ የገንዘብና የሜዳሊያ ሽልማት ይበረከትላቸዋል።
የስፖርት ቱሪዝም፦
በርካታ እንግዶችና ስፖርተኞች ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ በመሆኑ ለሀገሪቱ ገጽታ ግንባታና ለቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን በቅርቡ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ፣ ኢትዮጵያ እንዲህ ያለ ትልቅ ውድድር የማዘጋጀት ብቃት እንዳላት ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
ፌዴሬሽኑ ለዚህ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱት፦
ለዓለም አትሌቲክስ (World Athletics)
ለኢ.ፌ.ድ.ሪ. ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር
ለባለድርሻ አካላት በሙሉ ምስጋናውን አቅርቧል።
እንኳን ደስ አለን!
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ዝና በዓለም አቀፍ መድረክ ይበልጥ ደምቆ ይቀጥላል።
#ኢትዮጵያ #አትሌቲክስ #አዲስአበባ #worldathletics #ethiopia #addisababa2026 #sportdiplomacy #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

Sponsored by
Surafel
Comments