የልዩ መለያ QR Code ደረሰኝ ኅትመት ችግር የተፈጠረው በሥርጭት ምክንያት መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታወቀ
#ethiopia :
ነጋዴዎች ደረሰኙን ለማግኘት ባለመቻላቸው ሥራ መሥራት እንዳልቻሉና ለኪሳራ እየተዳረጉ መሆኑን ተናግረዋል
ልዩ መለያ (QR Code) ያረፈበት ደረሰኝ ኅትመት በመዘግየቱ ነጋዴዎች እንዲማረሩ ምክንያት የሆነ ችግር የተፈጠረው በሥርጭት ምክንያት መሆኑን፣ የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ከዚህ ቀደም ጥቅም ላይ ይውል የነበረው ደረሰኝ ከጥር 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ጥቅም ላይ እንደማይውል ውሳኔ መተላለፉን ተከትሎ፣ ነጋዴዎች አዲሱን ልዩ መለያ (QR Code) ያረፈበት ደረሰኝ ለማግኘት የሚጠበቅባቸውን ክፍያ ቢፈጽሙም፣ በመዘግየቱ ምክንያት መቸገራቸውን በተደጋጋሚ ገልጸዋል፡፡
ደረሰኙን በማሳተም ለነጋዴዎች የማድረስ ኃላፊነት ወስዶ እየሠራ የሚገኘው የገቢዎች ሚኒስቴር፣ ችግሩ የተፈጠረው በሥርጭቱ ላይ በተፈጠረ መዘግየት ምክንያት መሆኑን የሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ በፍርዱ ተሰማ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
በተለይም በክልሎች ለሚገኙ ግብር ከፋዮች ደረሰኙን ለማድረስ በብቸኝነት እያተመ ከሚገኘው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ተቀብሎ እስከ ግብር ከፋዩ ለማድረስ ባለው ሒደት የጊዜ መራዘም መኖሩና ለችግሩ መፈጠር ምክንያት መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
ችግሩን ለመፍታት ሚኒስቴሩ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ድረስ በአካል በመገኘት የሚከታተል ቡድን ከአንድ ወር በፊት ማቋቋሙንና ቡድኑ ባደረገው ክትትል ችግሮቹ የሚፈጠሩት የታተሙትን ደረሰኞች ለግብር ከፋዩ በማድረስ ሒደት ላይ በሚያጋጥም የሥርጭት ችግር መሆኑን፣ ይህን ለመፍታትም በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በአካል በመገኘት ጭምር እየተቆጣጠረ ይገኛል።
ግብር ከፋዮች ደረሰኛቸውን ለመውሰድ ግብር በሚከፍሉበት ቅርጫፍ ጽሕፈት ቤት በመገኘት ሲጠይቁ እንዳልደረሰ እንደሚገለጽላቸውና በማተሚያ ድርጅቱ በኩል ደግሞ ታትሞ መላኩ እንደሚነገራቸው፣ በመሀል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታትም ከቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ በኩል አለመድረሱን የሚገልጽ ደብዳቤና ደረሰኙን እየተጠቀሙ ሲያዙ የከፈሉበትን ማስረጃ እንዲያቀርቡ በማድረግ ችግሩን ለመፍታት እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ አክለውም በቅርጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ተከማችቶ የሚገኝ ደረሰኝ መኖሩንና አንዳንድ ግብር ከፋዮች እየወሰዱ እንዳልሆነ ጠቁመዋል፡፡Via:- Reporter
seledadotio

4 months ago