Logo
FIDEL POST NEWS
ኢዜማ ብርሃኑ ነጋን (ፕ/ር) በማሰናበት ኢዮብ መሳፍንትን የፓርቲው መሪ አድርጎ መረጠ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ፣ ፓርቲውን ላለፉት ሰባት ዓመታት ሲመሩ የነበሩትን ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አሰናብቶ እዮብ መሳፍንትን  የፓርቲው መሪ አድርጎ መረጠ።

በአሁኑ ሰዓት ጠቅላላ ጉባዔውን በአድዋ መታሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ በሚገኘው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ከብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በተጨማሪ የፓርቲው ምክትል መሪ የነበሩትን አርክቴክት ዮሐንስ መኮንንም በተመሳሳይ አሰናብቷል። በምትካቸውም አቶ ንጋቱ ወልዴን ምክትል መሪ በማድረግ መርጧል።ፓርቲው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደርበትን ማኒፌስቶም ለአባላቱ ይፋ አድርጓል።

Via Reporter
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.