3 days ago
በኢትዮጵያ የአውሮጳ ኅብረት ልዑክ እና በአዲስ አበባ የሚገኙ የኅብረቱ አባል አገራት ኤምባሲዎች ስለ ሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ያወጡት መግለጫ
በኢትዮጵያ የአውሮጳ ኅብረት ልዑክ እና በአዲስ አበባ የሚገኙ የኅብረቱ አባል አገራት ኤምባሲዎች ግንቦት 24 ቀን 2018 ምርጫ ያልተካሔደባቸው የምርጫ ክልሎች ድምጽ የመስጠት “ዕድል ይሰጣቸዋል” የሚል ተስፋ እንዳላቸው አስታወቁ።
በኢትዮጵያ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ምርጫ መካሄዱን በበጎ እንደሚቀበሉ የኅብረቱ ተልዕኮ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ካደረጉ 25 ኤምባሲዎች ጋር በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ምርጫው በተካሔደ በሁለተኛው ቀን ዛሬ ረቡዕ መግለጫውን ከኅብረቱ ጋር ካወጡ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ኤምባሲዎች መካከል የጀርመን እና የፈረንሳይ የዲፕሎማሲ ተልዕኮዎች ይገኙበታል። የአውሮፓ ኅብረት አባል አገር ያልሆኑት ካናዳ፣ ኖርዌይ እና ስዊትዘርላንድም ምርጫን በተመለከተ በመግለጫው አቋማቸውን ካንጸባረቁ መካከል ናቸው።
በመግለጫው “የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ ሠራተኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዕጩዎች እና የሲቪል ማኅበራት ተዋናዮች ያበረከቱትን አስተዋጽዖ እናደንቃለን” ብለዋል።
የአፍሪካ ኅብረት እና የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እንደ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ያላቸውን ጠቃሚ ሚና እንገነዘባለን ያለው የጋራ መግለጫው ዘገባዎቻቸውን በጉጉት እንደሚጠብቅም አስታውቋል።
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ምርጫ ማካሄድ ያልቻሉ የምርጫ ክልሎች በሙሉ ይህን ለማድረግ እድሉ እንደሚሰጣቸው ተስፋ እናደርጋለን ሲል በኢትዮጵያ የኅብረቱ ልዑካንና የኅብረቱ አባል ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎች የጋራ መግለጫ አስታውቋል።
DW Amharic

16 days ago
በትግራይ ትምህርት ቤቶች በደመወዝ እና ሌሎች ጉዳዮች ምክንያት ግንቦት 30 ሊዘጉ ነዉ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የዘንድሮው የትምህርት ዘመን ከነዳጅ እጥረት፣ ከደመወዝ መዘግየት እና ከትምህርት መሠረተ ልማት መስተጓጎል ጋር በተያያዘ ምክንያት ከታቀደው አንድ ወር ቀደም ብሎ እንደሚያበቃ አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉሽ የፌደራል መንግሥት የበጀት ድልድል እና የነዳጅ አቅርቦቶችን መከልከሉ በክልሉ «የመምህራን ደሞዝ በወቅቱ እና በአግባቡ መክፈል» የማይቻል አድርጎታል ሲሉ መናገራቸው ተዘግቧል።
የክልሉ የትምህርት ቢሮ ፤ ለትግራይ ክልል መገናኛ ብዙኃን መግለጫ መስጠቱን ለዶቼ ቬለ የተናገረዉ በመቀሌ ነዋሪ የሆነዉ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አፅብሃ ፤ በትግራይ ክልል የሚገኙ የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች የ 2018 የትምህርት ዘመን ግንቦት 30 እንዲዘጋ ወስኗል። ትምህርት ቢሮዉ ለዚህ ምክንያት የሰጠዉ አንደኛ -የፌደራል መንግሥት በጀት እየላከ ባለመሆኑ ፤ ሁለተኛ ፤ መምህራን ደሞዝ እያገኙ ስላልሆነ ሥራቸዉን እየለቀቁ በመዉጣታቸዉ ትምህርት ቤቶች እየተዘጉ በመሆኑ ነዉ ሲል አክሏል። ወላጆች ልጆቻቸዉን ትምህርት ቤት የሚያደርሱበት ነዳጅ ባለማግኘታቸዉ የግል ትምህርት ቤቶች እንዲሁ ፤ ግንቦት 30 ቀን እንዲዘጉ ተወስኗል። ለ12 ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ግን እንደሌሎች ክልሎች ሁሉ በትግራይ ክልልም ተማሪዎች በተመሳሳይ ቀን ለፈተና ይቀመጣሉ።
ይሁን እና ይህን የትግራይ ክልል የትምህርት ቢሮ መግለጫ የሰሙ የክልሉ ነዋሪ፤ ተማሪዎቹ ትምህርታቸዉ ቀደም ብሎ እንዲዘጋ የተወሰነዉ፤ ምናልባት በትግራይ ክልል እና በፊደራል መንግሥት መካከል ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት ዉስጥ ገብቷል ሲል ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አፅብሃ ለዶቼ ቬለ DW ገልጿል።
ባለፈዉ ሳምንት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እና በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሃት) መካከል የነበረዉ ዉዝግብ ሰሞኑን ረገብ ያለ መስሏል። አዲስ የተሰማ ነገርም የለም ሲል ጋዜጠኛዉ አክሎ ለዶቼ ቬለ ተናግሯል።

18 days ago
«ወደ ሥልጣን እንዲመለስ ከተባለዉ ዉሳኔ ጀርባ ያሉት ከ 100 የማይበልጡ ናቸዉ» ሳሞራ ዩኑስ
የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ ዩኑስ በትግራይ ክልል ህወሓትን ወደ ስልጣን ለመመለስ የተደረገዉን ውሳኔ አጥብቀዉ ተቃወሙ። በዚህ ሳምንት ከውጋሕት ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ "የቀድሞ አመራሮች እና ምክር ቤት (በትግራይ) ወደነበሩበት እንዲመለሱ መወሰኑ ህዝቡን ከልክ በላይ ጭንቀት ውስጥ ከቶታል „ብለዋል። ሳሞራ የህወሓት ነባር ታጋይና አባልም ነበሩ።
ሳሞራ አክለውም የትግራይ ህዝብ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የግል ንብረት ስላልሆነ በፓርቲው ታግቶ መቀመጥ የለበትም ሲሉም አክለዋል። ከጦርነቱ በፊት የነበረው የክልል ምክር ቤትና አስተዳደር «ወደ ሥልጣን እንዲመለስ ከተባለዉ ዉሳኔ ጀርባ ያሉት ከ 100 የማይበልጡ ናቸዉ፣ ውሳኔዉን ያሳለፉትም ከተጠያቂነት ለመዳን ያሰበ ዓላማን የያዘ ነዉ» ብለዉ እንደሚያስቡ ሳሞራ ዩንስ ተናግረዋል።

የትግራይ የሰላም እና ለውጥ ምክር ቤት ተመሠረተ
«የትግራይ ሰላምና ለውጥ ምክር ቤት» የተባለ ስብስብ አዲስ አበባ ዉስጥ ተቋቋመ። የተለያዩ የሃገር ዉስጥ መገናኛዎች እንደዘገቡት፤ ከስምንት ወራት በፊት የትግራይ ለውጥ ፈላጊ ኃይሎች ንቅናቄ በሚል የተቋቋመው ማህበር ማኒፌስቶውን በማሻሻል «የትግራይ የሰላም ለውጥ ምክር ቤት» በሚል አዲስ አበባ ላይ የመጀመሪያ የምስረታ ጉባዔውን ትናንት ሰኞ አደርጓል።
በምክር ቤቱ ምስረታ ጉባዔ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተደራዳሪዎች መካከል የሆኑት ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ እና ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ጀነራል ጎዕሽ ገብረ ፣ ሰባት ማህበራዊ መሠረታቸውን ትግራይ ያደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣የቀድሞ የክልሉ አመራሮች፣ የቀድሞ ወታደራዊ አዛዦችና ታጋዮች እንዲሁም ማህበራት መገኘታቸዉን የአገር ዉስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል። አቶ ጌታቸዉ ረዳ እንደተናገሩት፤ ምክር ቤቱ በቅርቡ መቀሌ እንደሚገባ ተናግረዋል። የምክር ቤቱ ምስረታ ዋና አላማ በክልሉ የሚስተዋለውን ሕገ-መንግስታዊ ስርዓት እና የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት በመጣስ በጉልበት ስልጣን የተቆጣጠረውን የህወሓትን ቡድን በማስወገድ በክልሉ ምርጫ ተደርጎ ህጋዊ መንግስት እንዲመሠረት በተደራጀ መንገድ በመጓዝ ሰላማዊ አስቻይ ሁኔታን መፍጠር ነው መባሉም ተመልክቷል።
ከዚህ ሌላ ትግራይ ክልልን ከጦርነቱ ወደነበረችበት ሕገ መንግሥታዊ የግዛት ቅርጿ በመመለስ ተፈናቃዮች እንዲመለሱ በተደራጀ ሁኔታ መስራት ነዉ። ምክር ቤቱ አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም ስምረት፣ ባይቶና፣ ዓረና ትግራይ፣ ትንሳኤ 70 እንደርታ እና ቃንቺ ሀቂ እንዲሁም በአፋር ክልል የሚንቀሳቀሱትን የሀራ_መሬት ታጋዮችን ወታደራዊ ክንፍ ማሰባሰቡ ተገልጿል።

22 days ago
በኤራን ዩራንየም ጉዳይ ሩስያ ድጋፍ የማድረግ ሃሳብ ማቅረቧን ኢራን አረጋገጠች
ኢራን ከምዕራቡ ዓለም ጋር በሚያወዛግባት በኒዩክልየር ጉዳይ ላይ ሩስያ የበኩሏን ድጋፍ የማድረግ ሃሳብ እንዳቀረበች ኢራን አረጋገጠች። የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ፤ ዛሬ ኒውዴልሂ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በሩስያ ጉብኝታቸው ወቅት ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ስለ ዩራንየም ጉዳይ መነጋገራቸውን ገልጸው፤ ድጋፍ ለመስጠት ላቀረቡት ሀሳባቸውም አመሰግናቸዋለሁ ብለዋል።
ከብሪክስ አባል ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ ጎን ለጎን አራግቺ በሰጡት በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ፑቲን በቅርቡ ስለዚሁ ጉዳይ የተናገሩትን አረጋግጠዋል። ፑቲን ባለፈው ሳምንት ሀገራቸው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተጎናጸፈችው ድል በተዘከረበት የመታሰቢያ እለት ሩሲያ በከፍተኛ ደረጃ የበለፀገ ዩራኒየምን ከኢራን ወስዳ ለማከማቸት ዝግጁ መሆኗን አስታውቀው ነበር።
የኢራን የኒዩክልየር መርሀ ግብር ሲያወዛግብ ብዙ ዓመታት አስቆጥሯል። ዩናይትድ ስቴትስ እሥራኤል እና ምዕራባውያን ሀገራት ቴህራን የኒዩክልየር ጦር መሣሪያዎችን ለማምረት ትፈልጋለች ሲሉ ይከሷታል። ኢራን ግን ይህን ታስተባብላለች። ምዕራቡ ዓለም ኢራን አሁን ያላት የዩራንየም ክምችት ከለማ በርካታ የኒዩክልየር ጦር መሣሪያዎች ለመስራት በቂ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት አለው።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሚገኘው ዩራንየም ከሀገሪቱ እንዲወጣ ግፊት እያደረጉ ነው። ዩራንየሙ ከምድር በታች ከሚገኙ የኢራን የኒዩክልየር ተቋማት በአንዱ ውስጥ ተከማችቷል ተብሎ ይገመታል።

24 days ago
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ቻይና አቀኑ
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና በርካታ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ሥራ አስፈጻሚዎችን አስከትለው ወደ ቻይና አቀኑ። ትራምፕ እና የቻይና አቻቸው ሺ ዢንፒንግ ሐሙስ እና አርብ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ስብሰባ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሁለቱ መሪዎች ስብሰባ የሚካሔደው በኢራን ጦርነት የኢነርጂ ዋጋ በከተኛ መጠን ባሻቀበበት ወቅት ነው። የአሜሪካ እና የቻይና የንግድ ልውውጥ እና የአርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች ናቸው።
በአርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ቀዳሚ የሆኑ የአሜሪካ ኩባንያዎች ሥራ አስፈጻሚዎች ከዶናልድት ትራምፕ ጋር ወደ ቻይና አቅንተዋል። ለአርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ ቁልፍ ግብዓት የሆኑ ቺፖች በማምረት የሚታወቀው የንቪዲያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጀንሰን ሑዋንግ፣ የአፕል ሥራ አስፈጻሚ ቲም ኩክ እና የቴስላው ኤለን ሙስክ ከልዑካን ቡድኑ መካከል ይገኙበታል።
በቤጂንግ በሚደረገው የሁለቱ መሪዎች ስብሰባ አሜሪካ ለታይዋን የምትሸጠው የጦር መሣሪያ ጉዳይ ከሺ ዢንፒንግ እንደሚነጋገሩ ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ብለው አሳውቀዋል። የቻይና ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ግን ታይዋን የቻይና አንድ አካል በመሆኑ አሜሪካ የሚኖራትን ወታደራዊ ግንኙነትም ይሁን ከዚህ ቀደም የተስማማቸውን የጦር መሣሪያ ሽያጭ አጥብቀው ተቃውመዋል። ባለፈው ታኅሳስ የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር 11 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ የጦር መሣሪያዎች ለታይዋን እንደሚሸጥ ይፋ አድርጎ ነበር።

28 days ago
ኢራን በዓለም ዋንጫ እንደምትሳተፍ ገለጸች።
ኢራን በዓለም ዋንጫ እንደምትሳተፍ ገለጸች። ኢራን በትልቁ የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ ፍላጎቷን ስትገልጽ የውድድሩ አስተናጋጆች ቅድመ ሁኔታዎችን እንዲቀበሉ ጠይቃለች።
የኢራን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ቅዳሜ እንዳስታወቀው በ2026 የክረምት ወቅት በሚካሄደው የዘንድሮ የዓለም ዋንጫ የሀገሪቱ የወንዶች ብሔራዊ ቡድን ይሳተፋል። ነገር ግን የጋራ አስተናጋጆቹ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ ሁኔታዎችን ከመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ጋር እንዲያስማሙ ጠይቋል።
የኢራን ጥያቄ የተሰማው ካናዳ ባለፈው ወር ከፊፋ ጉባኤ በፊት የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሀላፊ ወደ ወደ ጉባኤው እንዳይገቡ መከልከሏን ተከትሎ ነው። ምክንያቱ ደግሞ በጎርጎሪያኑ 2024 እንደ ሽብርተኛ ቡድን ከተፈረጀው የኢራን ወታደራዊ ርዕዮተ ዓለም ክንድ ከሆነው ከኢራን አብዮታዊ ጥበቃ (IRGC) ጋር ግንኙነት አላቸው የሚል ነበር።
"በእርግጠኝነት በ2026 የዓለም ዋንጫ እንሳተፋለን፣ ነገር ግን አስተናጋጆቹ ስጋቶቻችንን ግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው" ሲል የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን በይፋዊ ድረ-ገጹ ላይ አስታውቋል።
ቅድመ ሁኔታዎቹ ቪዛ መስጠት እና ለብሔራዊ ቡድኑ ሰራተኞች አክብሮት መስጠት፣ የቡድኑ ባንዲራ እና ብሔራዊ መዝሙሩ በውድድሩ ወቅት እንዲሁም በአውሮፕላን ማረፊያዎች፣ ሆቴሎች እና ወደሚጫወቱባቸው ስታዲየሞች በሚወስዱ መንገዶች ላይ ከፍተኛ ጥበቃ እንዲደረግላቸው መጠየቅን ያካትታሉ።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የኢራን የእግር ኳስ ተጫዋቾች በውድድሩ ላይ መገኘታቸው መልካም መሆኑን ተናግረዋል።ነገር ግን አሜሪካ ከኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ጋር ግንኙነት ያላቸውን የኢራን ልዑካን ቡድን አባላትን እንደ ሽብርተኛ ድርጅትነት ቆጥሮ ፈቃድ ሊከለክል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
የኢራን የእግር ኳስ ኃላፊ ታጅ ግን «ሁሉም ተጫዋቾች እና የቴክኒክ ሰራተኞች፣ በተለይም እንደ መህዲ ታሬሚ እና ኢህሳን ሃጅሳፊ ያሉ በእስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ቡድን ወይም በIRGC ውስጥ ወታደራዊ አ አገልግሎት የሰጡ ያለምንም ችግር ቪዛ ሊሰጣቸው ይገባል» ሲሉ አጽንዖት ሰጥተዋል።
የዓለማቀፉ የእግር ኳስ ማሕበር ፊፋ ዋና ኃላፊ ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በበኩላቸው ኢራን በታቀደው መሰረት የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎቿን ዩናይትድ ስቴትስ እንደምታደርግ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

30 days ago
በናፍጣ እጥረት ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ ምርት ለገበያ ማቅረብ እያስቸገረ ነው
በሺህዎች የሚቆጠሩ የንግድ እና የነዳጅ ጫኝ መርከቦች በኢራን ፍኖተ-ሆርሙዝ እንዳያልፉ እገዳ ተጥሎባቸው መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው የነዳጅ እጥረቱ በየቦታው እየተስፋፋ ዋጋውም እየናረ መምጣቱ እየተገለጸ ነው ። በኢራን ክልከላ የተነሳ 22,500 መርከበኞች በ1,550 የንግድ መርከቦች ውስጥ በባሕረ መስመሩ ማለፍ ሳይችሉ መቅረታቸው ከሰሞኑ ተዘግቧል ። የነዳጅ እጥረት ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች እክሎችን እየፈጠረ መሆኑን የተለያዩ ሰዎች በምሬት እየተናገሩ ነው ።
በናፍጣ እጥረት ምክንያት እየናረ በመጣው የጭነት መጓጓዣ ዋጋ የተነሳ የሙዝ ምርታቸውን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ መቸገራቸውን ለዶይቸ ቬለ (DW) የተናገሩ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ ዞን ሙዝ አምራች አርሶአደሮችን መጥቀስ ይቻላል ። አርሶ አደሮቹ እንዳሉት፦ ቀደም ሲል ከ40 እስከ 50 ሺህ ብር ይጫን ነበረው አንድ አይሱዚ የጭነት ተሸርካሪ በአሁኑ ወቅት በአራት እጥፍ በመጨመሩ ምርታቸውን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ተቸግረዋል ። የአርባምንጭ ከተማ አስተዳዳር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ በበኩሉ በናፍጣ አቅርቦት ላይ የሚካሄደውን ማጭበርበር ለመከላከል የኩፖን አሠራር መጀመሩን ዐሳውቋል ።

1 month ago
በሆርሙዝ ሰርጥ የመርከቦች እጀባን ለጊዜው እንደደምታቋርጥ ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች
ዩናይትድ ስቴትስ በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል ማለፍ ላልቻሉ የንግድ መርከቦች የጀመረችውን አጀብ ለጊዜው እንደምታቆም አስታወቀች። የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመርከቦች እጀባው የቆመው ከኢራን ጋር የሰላም ስምምነት ላይ ለመድረስ ባለን ፍላጎት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ምንም እንኳን በቅርብ ቀናት በሰርጡ ግጭቶች የነበሩ ቢሆንም ትራምፕ ግን ወደ ስምምነት የሚያመራ ትልቅ ለውጥ ላይ ተደርሷል ብለዋል። መርከቦችን የማጀቡ ዘመቻ የሰላም ስምምነቱ ሊጠናቀቅና ሊፈረም ይችል እንደሆነ ለማየት ለአጭር ጊዜ ይቆማል ሲሉም ተናግረዋል።
ትራምፕ ይህን ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩብዮ ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ የምታካሂደውን የማጥቃት ዘመቻ ማጠናቀቋን ትናንት ከተናገሩ በኋላ ነው። ይሁንና ሩብዮ ኢራኖች በሰርጡ በሚተላለፉ መርከቦች ላይ ለሚሰነዝሩት ማንኛውም አዲስ ጥቃት ግን ከባድ ምላሽ እንደሚጠብቃቸው አስጠንቅቀዋል።
ኢራን በበኩልዋ የሰላም ስምምነቱን የምትቀበለው አድሏዊ ካልሆነ ብቻ ነው ስትል አስታውቃለች። ለጊዜው እንደሚቋረጥ ዛሬ የተነገረው እጀባ ለሦሶት ቀናት ብቻ ነበር የዘለቀው። «የነጻነት ፕሮጀክት» የሚል ስያሜ የተሰጠው ይኽው ዘመቻ በሆርሙዝ ሰርጥ የመርከቦች ጉዞ እንዲቀጥል የሚያደርግ ጉልህ ውጤት አለማስገኘቱን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

የኢራኑ ተደራዳሪ ለተጨማሪ ምክክር ወደ ፓኪስታን ተመለሱ
የኢራኑ ተደራዳሪ ለተጨማሪ ምክክር ወደ ፓኪስታን መመለሳቸው ተዘገበ።እንደ አሶሸትድ ፕሬስ ዘገባ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ዛሬ እሁድ ለተጨማሪ ምክክር ወደ ኢስላማባድ ተመልሰዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የልዑካናቸውን የፓኪስታን ጉዞ ቢሰርዙም ዓለም አቀፍ አስታራቂዎች የሰላም ድርድሩን በትክክለኛው መንገድ ለማስቀጠል እየጣሩ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።
እንደ ኢራን የዜና ወኪል አይ ኤስ ኤን ኤ /ISNA/ ዘገባ፣ አባስ አራግቺ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን "ጦርነቱን ሙሉ በሙሉ በማስቆም ላይ ኢራን ያላትን አቋም እና አመለካከት" ለማንፀባረቅ ከፓኪስታን ባለስልጣናት ጋር ለንግግር ተቀምጠው ነበር።ሚኒስትሩ እስከ ትናንት ቅዳሜ ኢስላማባድ የነበሩ ሲሆን ከዚያም ወደ ኦማን ተጉዘዋል። ሌሎች የኢራን ልዑኮች ደግሞ "ጦርነቱን ከማስቆም ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ አስፈላጊውን መመሪያ ለማግኘት" ወደ ቴህራን ተመልሰው ነበር ሲል የዜና አውታሩ ገልጿል።
አባስ አራግቺ ቅዳሜ ምሽት የፓኪስታን መዲና እስላማባድን ለቀው በመውጣታቸው በሁለተኛው ዙር በሚደረገው ውይይት ዙሪያ ግራ መጋባት ፈጥሮ ነበር። ነገር ግን ወደ ሞስኮ ከማምራታቸው በፊት ዛሬ ወደ ኢስላማባድ ተመልሰዋል ሲሉ የኢራን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ዋይት ሀውስ ዓርብ ዕለት ለሁለተኛ ዙር ውይይት ስቲቭ ዊትኮፍ እና ጃሬድ ኩሽነርን ያካተተ የልዑካን ቡድን ወደ ኢስላማባድ እንደሚልክ አስታውቋል። ነገር ግን የአራግቺ ፓኪስታንን ለቀው መውጣታቸው ከተዘገበ ብዙም ሳይቆይ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ያለው ውይይት መሻሻል አላሰየም በሚል ተልዕኮውን አቋርጠነዋል ብለዋል። ትራምፕ አያይዘውም "በፈለጉት ጊዜ ሊደውሉልን ይችላሉ" ሲሉ ገልፀዋል።

እስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለሦስት ሳምንት አራዘሙ
እስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን በሦስት ሳምንታት ለማራዘም ተስማምተዋል ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሳውቀዋል።ስምምነቱ የመጣው የእስራኤል እና የሊባኖስ ባለሥልጣናት ዋይት ሀውስ ውስጥ ያልተለመደ ስብሰባ ካደረጉ በኋላ ነው።
በጎርጎሪዮሱ የካቲት 28 ቀን፣ እስራኤል በኢራን ላይ የጋራ ጥቃት ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ እስራኤል በሊባኖስ፣ በተለይም በደቡብ እና በዋና ከተማዋ ቤሩት ላይ የአየር ድብደባ ስትፈጽም ቆይታለች።እስራኤል ጥቃቱ በሊባኖስ ውስጥ የሒዝቦላህ መቀመጫ ቦታዎችን እና ምሽጎችን ዒላማ ያደረገ መሆኑን ገልፃለች።
ሒዝቦላህ በዩናይትድ ስቴትስ፤ ጀርመን እና በርካታ የሱኒ ዐረብ ሃገራት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀ፤ በኢራን የሚደገፍ የሊባኖስ የሺዓ ፖለቲካ ፓርቲ እና ወታደራዊ ክንፍ ነው ። በጎርጎሪዮሱ 1982 በሊባኖስ የእርስ በርስ ጦርነት (1975-1990) እና በእስራኤል የደቡብ ሊባኖስ ወረራ ወቅት ብቅ ያለ ቡድን ነው። ሒዝቦላህ የፖለቲካ እና የትጥቅ ቡድን ሲሆን፤በ1979 በኢራን የእስልምና አብዮት መሰረት በነበረው የሺዓ እስላማዊ ርዕዮተ ዓለም ደጋፊ ነው። ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮም በኢራን የእስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ድጋፍ፣ ስልጠና እና መሣሪያ ያገኛል።
ቡድኑም ለትልቋ ለጋሽ ሀገር ለኢራን ወኪል ሆና ይሰራል። የአሜሪካ መንግስት በጎርጎሪያኑ 2023 መጨረሻ ባወጣው መረጃ ኢራን ለሒዝቦላህ በየዓመቱ ወደ 700 ሚሊዮን
ዶላር (661 ሚሊዮን ዩሮ) ትሰጣለች ተብሎ ይገመታል።

2 months ago
ትራምፕ በፍኖተ ሆርሙዝ የመርከቦች ጉዞን ከኢራን ጋር መቆጣጠር ይሻሉ
ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን የፍኖተ ሆርሙዝ ለመርከቦች ክፍት መሆን የተኩስ አቁሙ ስምምነት ቁልፍ ቅድመ ሁኔታ እንደነበር ገለጠች ።
እንደ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ገለጻ፦ ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ደሕንነት በማስጠበቅ አብረው ሊሠሩ ይችላሉ ። ይህን በተመለከተም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሲናገሩ፦ በባሕረ ሆርሙዝ የሚያልፉ መርከቦች ደሕንነት በኢራን እና በአሜሪካ ጥበቃ እንደሚደረግላቸው ተናግረዋል ።
ፕሬዚደንቱ ለኤቢሲ ኒውስ እንደተናገሩት ከሆነ፦ የመርከቦች ደሕንነትን ለማስጠበቅ በዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን መካከል የጋራ ፕሮጄክትን ለመተግበር እያሰቡበት መሆኑንም ገልጠዋል ።
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ሲል ኢራን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የነዳጅ እና የጋዝ ንግድ ወሳኝ መተላለፊያ የሆነውን ፍኖተ ሆርሙዝ ከከፈተች ለሁለት ሳምንታት የቦምብ ድብደባ እና ጥቃት ከመሰንዘር እንደሚቆጠቡ ገልጠው ነበር ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን፦ ኢራን አሁንም በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ የመርከብ ጭነቶችን መቆጣጠርዋን እንደቀጠለች መሆኑ ተዘግቧል ። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በሰጡት መግለጫ መሠረት፣ የመርከቦች ትራፊክ ፍሰት እንደቀድሞው ሁሉ «በኢራን የጦር ኃይሎች ፈቃድ» ተገዢ ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል ።
እንደ የባህር ትራንስፖርት አገልግሎት ገለጻ ደግሞ፦ በሆርሙዝ ወሽመጥ ውስጥ የሚተላለፉ መርከቦች የትራፊክ ፍሰት ዳግም እየጨመረ ነው ።

Sponsored by
Surafel
2 months ago
ኢራን በዛሬው ዕለት በኬዌትና በባህሬን የሀይል መሰረተ ልማቶች ላይ ብርቱ ጥቃት መፈጸሟን የየሐገራቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።
ኢራን በኩዌት ላይ በፈጸመችው ጥቃት በአንድ የነዳጅ ማጣያ መሰረተ ልማት ላይ ብርቱ ጉዳት ማድረሷን የኩዌት የፔትሮልየም ኮርፖሬሽን ገልጿል።
መንግስታዊው የነዳጅ ኮርፖሬሽን እንዳለው «ኢራን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም በኩዌት የሃይል መሰረተ ልማት ላይ አሰቃቂ ጥቃት ፈጽማለች።» ኮርፖሬሽኑ አክሎም «ጥቃቱ በእነዚህ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ቃጠሎ አድርሷል፤ ከፍተኛ ቁሳዊ ጉዳትም አድርሷል።» ነው ያለው።
በተመሳሳይ ዜና ኢራን በባሕሬይን 2 የሃይል መሰረተ ልማቶች ላይም ጥቃት ሰንዝራለች።
በጥቃቱ በሁለቱም የነዳጅ ማጣሪያ መሰረተ ልማቶች ከፍተኛ ቃጠሎ ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን በእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ለማወቅ ተችሏል። በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ግን ባሕሬን አስታውቃለች። የዜናዎቹ ምንጭ አዣንስ ፍራንስ ፕረስና የጀርመን ዜና አገልግሎት ናቸው።

ዘጠኝ ስደተኞች በጅቡቲ የባህርዳርቻ ሞቱ
በጁቡቲ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ከትናንት በስተያ የሰመጠች ጀልባ ውስጥ ከነበሩት ስደተኞች ዘጠኙ መሞታቸውን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) አስታወቀ። ድርጅቱ እንዳለው ሌሎች 45 ስደተኞች ደግሞ ይኑሩ ይሙቱ አልታወቀም።
አደጋው የደረሰው ከትናንት በስተያ መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም. ለሊት ጅቡቲ ከምትገኘው ኦቦክ ከተባለችው ትንሽ ከተማ በስተሰሜን ባለ የባህር ዳርቻ መሆኑን IOM አስታውቋል። ጀልባዋ 320 ሰዎችን አሳፍራ ነበር ።
በፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ መሠረት የምሥራቅ መስመር በሚባለው በዚህ የፍልሰት መንገድ ከሚሰደዱት አብዛኛዎቹ ከኢትዮጵያ የሚመጡ ናቸው። በዚህ መስመር በጎርጎሮሳዊው 2024 ዓ.ም. የ922 ስደተኞች ሕይወት አልፏል። ይህም እስከዛሬ ከተመዘገበው ሞት ከፍተኛው ተብሏል።

አሜሪካ ለኢራን ባለ 15 ነጥብ የተኩስ አቁም የስምምነት ሃሳብ በፓኪስታን በኩል ማቅረቧ ተዘገበ።
አሜሪካ የተኩስ አቁም ሃሳቡን በፓኪስታን አምባሳደሮች በኩል ለኢራን ማቅረቧን የኢስላማባድ ባለስልጣናት ዛሬ አረጋግጠዋል። አሜሪካ የሰላም የስምምነት ሃሳብ ማቅረቧ የተሰማው ተጨማሪ የአየር ወለድ ወታደሮቿን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሃገራት እያሰማራች ባለችበት ወቅት ነው።
በፓኪስታን በኩል ለኢራን ቀረበ የተባለው የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ "የሰላም ዕቅድ" 15 ነጥቦች ያካተተ ሲሆን አብዛኞቹ ሐሳቦች ኢራንን የሚያስገድዱ ናቸው ተብሏል።
ከእነዚህ መካከል በኢራን የሚሳይል ፕሮግራም ላይ ገደብ መጣል እና በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል መርከቦች በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ መፍቀድ ፣ የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ ፣ የኢራንን የኑክሌር መርሃ ግብር መቀነስ ፣ በሲቪል የኑክሌር መስክ ላይ መተባበር እና በኢራን ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን ማንሳት እንደሚገኙበት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የፓኪስታን ባለስጣናት ተናግረዋል።
አሜሪካ የተኩስ አቁም ሃሳብ አቀረበች ይባል እንጂ ተጨማሪ ወታደሮችን ወደ ቀጣናው ከመላክ ግን አላቀባትም። አሜሪካ በትንሹ 1,000 የሚሆኑ የ82ኛው የአየር ወለድ ክፍለ ጦር አባላት ወደ ቀጠናው እንደሚላኩ ተገልጿል። ይህም ቀደም ብለው ከተሰማሩት 5,000 የባህር ኃይል ወታደሮች በተጨማሪ ነው።
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ዩናይትድ ስቴትስ "ትክክለኛ ሰዎች" ካሏቸው ጋር የኢራን ጦርነትን ለማብቃት እየተነጋገረች እንደምትገኝ በዋይት ሐውስ ለጋዜጠኞች ተናግረው ነበር። ፕሬዝደንቱ ኢራን ሥምምነት ላይ የመድረስ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።
አንድ የኢራን ወታደራዊ ቃል አቀባይ ግን ዩናይትድ ስቴትስ ከራሷ ጋር እየተደራደረች እንደሆነ በመግለጽ የተባለውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አጣጥለዋል።
ኢራን በእስራኤል እና በሌሎች የባህረ ሰላጤው ሃገራት ላይ የምትፈጽማቸውን ጥቃቶች አጠናክራ መቀጠሏን አሶሽየትድ ፕረስ ዘግቧል። በዚህም በኩዌት ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በደረሰ ጥቃት ከፍተኛ እሳት መነሳቱና ከፍተኛ ጭስ ሲወጣ መታየቱ ተነግሯል።
የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በሰሜን ምዕራብ ኢራን በሚገኘው ቃዝቪን ከተማ ላይ ሰፊ የአየር ድብደባ መጀመሩን አስታውቋል።
የኢራን ጤና ሚኒስቴር በአሜሪካ እና እስራኤል ጥምር ጥቃት የሟቾች ቁጥር ከ1,500 በላይ መድረሱን ገልጿል።
እስራኤል በተናጥል ባደረሰችው ጥቃት ሊባኖስ ውስጥ ከ1,000 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።
ኢራን በበኩሏ ባደረሰችው የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃት እስራኤል ውስጥ 16 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል። በተጨማሪም 13 የአሜሪካ ወታደራዊ አባላት ሕይወታቸውን አጥተዋል።
በጦርነቱ ለጊዜው በቁጥር ያልተገለጸ በሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።
በጦርነቱ ምክንያት የጨመረው የነዳጅ ዋጋ አሁንም መቀነስ አላሳየም ። በአሁኑ ወቅት አንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ በ100 ዶላር አካባቢ እየተሸጠ ይገኛል። ይህም ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ከነበረው ዋጋ የ40 በመቶ ጭማሪ አለው።

3 months ago
የሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲን የኢራን ታማኝ ወዳጅ ሆነው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ። ፑቲን ይህን ያስታወቁት ዛሬ የሚከበረውን የኢራን የአዲስ አመት መለወጫ (ኑሩዝ) አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው።
የሩስያ ፕረዚደንት ፅሕፈት ቤት እንዳለው ፑቲን የመልካም ምኞት መግለጫቸውን ያስተላለፉት ለኢራኑ ከፍተኛ መሪ አያቶላሕ ሙጂታባ ካመኒና ለኢራኑ ፕረዚደንት መሱድ ፔዢሽኪያን ነው።
ፕረዚደንት ፑቲን ለኢራን ሕዝብ ባስተላለፉት መልዕክት ደግሞ «ይህን አስቸጋሪ ሁኔታ በፅናት ታልፉታላችሁ ብዬ አምናለሁ፤ ሩስያ የኢራን ታማኝ ወዳጅ ሆና እንደምትቀጥልም እገልጻለሁ» ማለታቸውን የዘገበው ሮይተርስ የዜና ወኪል ነው።

አሜሪካ ለመግባት 15 ሺሕ ዶላር፤-ኢትዮጵያም ተጨመረች
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት የዶናልድ ትራምፕ መስተዳድር አሜሪካ መግባት በሚፈልጉ የተለያዩ ሐገራት ዜጎች ላይ የጣለዉ የገንዘብ ማስያዢያ ከመጪዉ መጋቢት 24 ጀምሮ ተግባራዊ ሊሆን ነዉ።
የትራምፕ መስተዳድር ከዚሕ ቀደም ባወጣዉ ደንብ የ38 ሐገራት ዜጎች የአሜሪካ ቪዛ ለማግኘት ከሌሎች ነባር መመዘኛዎች በተጨማሪ 15ሺሕ ዶላር እንዲያስዙ ወስኗል።ትናንት ደግሞ የኢትዮጵያን ጨምሮ የሌሎች 12 ሐገራት ዜጎች ከዝርዝሩ ዉስጥ መካተታቸዉን የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት አስታዉቀዋል።
አብዛኞቹ የአፍሪቃ ሐገራት ናቸዉ
ከመጋቢት 24 ጀምሮ ገቢር ይሆናል በተባለዉ ደንብ መሠረት የ50ዎቹ ሐገራት ዜጎች ለሥራና ሐገር ለመጎብኘት የሚያገለግለዉን B1 እና B2 የተባለዉን ቪዛ ለማግኘት 15 000 ዶላር ማስያዝ አለባቸዉ።ተጓዞቹ ወደየሐገራቸዉ ሲመለሱ ማስያዢያዉ ይመለሳል ተብሏል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በተከሰተው የመሬት መንሸራተት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ለ3 ቀናት የሚቆይ ክልላዊ የሐዘን ቀን መታወጁን የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ገለጹ ፡፡
የአገልግሎቱ ሃላፊ አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በአደጋው ህይታቸውን ያጡ ወገኖችን ለማሰብ ክልሉ ከመጋቢት 05/2018 ቀን ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሀዘን ቀን እንዲሆን መወሰኑን አስታውቀዋል ፡፡
በናዳ ተቀብረው ከሚገኙት መካከል 4 ተጨማሪ አስክሬን መገኘቱንና የዛሬውን ጨምሮ በአጠቃላይ እስከአሁን 74 አስከሬን ለማግኘት መቻሉን ነው የአገልግሎቱ ሃላፊ በመግለጫቸው የጠቀሱት ፡፡
በአደጋው የ125 ሰዎች ህይወት መጥፋቱን የጠቀሱት የአገልግሎቱ ኃላፊ “ ቀሪ አስክሬኖችን የማፈላለጉ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል “ ብለዋል ፡፡ አደጋው በደረሰበት አካባቢ የሚገኘው የመንገድ መሠረተ ልማት ምቹ አለመሆን ለተጎጂዎች ሰብዓዊና ቁሳዊ ድጋፍ የማድረስ ሂደቱን ፈታኝ ቢያደርገውም የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝም አቶ ኃይለማሪያ አብራርተዋል ፡፡
በአደጋው ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ ለሚገኙ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፁት የአገልግሎቱ ኃላፊ በዘላቂነት የሟቋቋሙ ሥራ ጎን ለጎን እንደሚሰራም ተናግረዋል። በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ፣ ካምባ ዙሪያ ፣ ቦንኬ እና አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳዎች ባለፈው ማክሰኞ በተከሰተው የመሬት ናዳ እና የጎርፍ አደጋ ህይወታቸው ካለፉት በተጨማሪ 3 ሺህ 480 የቤተሰብ አባላት ያሏቸው 575 አባወራና እማወራዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል።

የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በጎግል 'AI' የፍለጋ አገልግሎት ተካተቱ!
#ethiopia | ግዙፍ ኩባንያ ጎግል የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የፍለጋ አገልግሎቱን በማዘመን፣ አማርኛንና አፋን ኦሮሞን ጨምሮ 13 የአፍሪካ ቋንቋዎችን ማካተቱን አስታወቀ። ይህ እርምጃ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ መረጃን በላቀ ጥራት እንዲያገኙ መንገድ የሚከፍት ነው።
በአዲሱ ዝመና ተጠቃሚዎች የሚከተሉትን አገልግሎቶች ማግኘት ይችላሉ፦
* AI Overviews፦ ስለፈለጉት ርዕሰ ጉዳይ አጭር፣ ግልጽ እና በማስረጃ የተደገፈ ማጠቃለያ በገዛ ቋንቋቸው ያገኛሉ።
* AI Mode፦ በጽሑፍ፣ በድምፅ ወይም በምስል ጥያቄዎችን በማቅረብ ጥልቅና ዝርዝር ምላሾችን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል።
የጎግል ደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ካቤሎ ማክዋኔ እንደገለጹት፣ ይህ ዝመና ቴክኖሎጂ በጥቂት ቋንቋዎች ብቻ ተወስኖ የሚፈጥረውን መገለል ለማስቀረትና አፍሪካውያን የዲጂታሉ ዓለም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ ነው።
ይህ በ 'ዋክሳል' (Vaxsal) ፕሮጀክት አማካኝነት የተገኘው ስኬት፤ ከአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ እና ሱማልኛ በተጨማሪ እንደ ስዋሂሊ፣ ዮሩባ እና ሃውሳ ያሉ ታዋቂ የአፍሪካ ቋንቋዎችንም ያካተተ ነው። ይህም የ AI ቴክኖሎጂን ለማኅበረሰባዊ ችግር መፍቻና ለፈጠራ ሥራዎች ለማዋል ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #viacapitalnews #googleai #amharic #afanoromo #technology #africatech #aioverviews #ethiopia #digitalinnovation

የኢራን ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዤሺኪያን የትራንፕን ''እጅ ስጡ '' ውድቅ አደረጉ
የኢራን ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዤሺኪያን ሀገራቸው “ያለ አንዳች ቅድመ-ሁኔታ እጅ እንድትሰጥ” የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የሰጡትን ማሳሰቢያ ውድቅ አደረጉ። ፔዢሽኪያን የዶናልድ ትራምፕን ማሳሰቢያ “ሕልም” ብለውታል።
በቪዲዮ ተቀርጾ በተላለፈ ንግግራቸው “ወደ መቃብራቸው ሊወስዱት ይገባል” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን “ያለ አንዳች ቅድመ-ሁኔታ እጅ እንድትሰጥ” ያሳሰቡት ትናንት አርብ ነበር።
ለዓለም አቀፍ ሕግ፣ የሰብአዊነት ማዕቀፍ እና ለመርሆዎቻቸው ኢራን ቁርጠኛ እንደሆነች የገለጹት ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዤሺኪያን “ለነዚያ መርሆዎች ቁርጠኛ መሆን አለባቸው። የኢራንን ጨምሮ የማንኛውንም ሀገር መብቶች ችላ ማለት አይችሉም” ሲሉ ተናግረዋል።
እስራኤል እና ዩናይትድ ስቴትስ ከኢራን የገጠሙት ጦርነት ስምንተኛ ቀኑን ሲያስቆጥር ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዤሺኪያን ሀገራቸው በአጎራባች ሃገራት ላይ ለተፈጸሙ የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃቶች በራሳቸው ስም ይቅርታ ጠይቀዋል።
የኢራን ወታደራዊ አዛዦች እና የሀገሪቱ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ፕሬዝዳንቱ “አረመኔያዊ” ባሉት ጥቃት በመገደላቸው የሀገሪቱ ጦር “አዛዦቻቸው ባለመኖራቸው ምክንያት በፍላጎታቸው ተኮሱ፤ አስፈላጊ የሆነውን ሁሉ አደረጉ” ሲሉ ተናግረዋል። “በክብር እና በኃይል” ሀገራቸውን እንደተከላከሉም አሞግሰዋል።
ካሁን በኋላ ጎረቤት ሀገራት ጥቃት ካልፈጸሙ በስተቀር የኢራን ጦር ጥቃት እንዳይፈጽም ወይም ሚሳይል እንዳይተኩስ ጊዜያዊ የመሪዎች ምክር ቤት ውሳኔ ማስተላለፉን ፕሬዝደንቱ ገልጸዋል። “ይህንን በዲፕሎማሲ መፍታት አለብን ብዬ አስባለሁ” ብለዋል። ፕሬዝዳንት ፔዜክሽያን በጥቃቶቹ ሳቢያ እየጨመረ የመጣውን የባሕረ ሰላጤው አረብ ሃገራት ቁጣ ለማርገብ ቢሞክሩም፣ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ግን የሚሳኤልና የድሮን ጥቃቶች በዱባይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መፈጸማቸውን ተከትሎ በረራዎችን አስተጓጉለዋል።
የኤሜሬትስ አየር መንገድም በረራ መጀመሩን ከገለጸ ከአንድ ቀን በኋላ በድጋሚ በረራዉ መቋረጡን አስታውቋል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተባለ ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ በኩል በጻፉት መልክዕት ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዤሺኪያን ይቅርታ የጠየቁት በኢራን ላይ “ዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል በፈጸሙት የማያቋርጥ ጥቃት” ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል።

ጅቡቲ ውስጥ ህጻናት በፍንዳታ ተገደሉ
ደቡባዊ ጂቡቲ ውስጥ አራት ህጻናት በፍንዳታ ተገድለዋል ሲሉ ባለሥልጣናት አስታወቁ። አንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን ግን ህጻናቱ የተገደሉት በድሮን ጥቃት ነው ማለቱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
የጅቡቲ አቃቤ ሕግ ሀሰን መሐመድ ሀሰን ትናንት ማምሻውን ባወጡት መግለጫ ህጻናቱ አፋር ድሂኪል በተባለው ክልል ውስጥ በደረሰ ፍንዳታ መገደላቸውን አስታውቀዋል።
የጅቡቲ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ የተባለው ድርጅት በምህጻሩ LDDH ደግሞ አንዲት የስድስት ዓመት እና አንድ የሰባት ዓመት ህጻናት ወዲያውኑ ሲሞቱ በአደጋው የቆሰሉ ሌሎች ሁለት ህጻናት ደግሞ የሕክምና እርዳታ ባለማግኘታቸው ማክሰኞ መሞታቸውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ሌሎች 6 ህጻናትም መቁሰላቸውንና ከመካከላቸው አንዱ ከባድ ጉዳት እንደረሰበትም ገልጿል። ድርጅቱ እንዳለው ህጻናቱ የተገደሉት ከብቶች በመጠበቅ ላይ ሳሉ ነበር።
ህጻናቱ በድሮን ጥቃት ነው የተገደሉት የሚለው ድርጅቱ የአሁኑ ጥቃትም በአካባቢው ለስድስተኛ ጊዜ የተፈጸመ ነው ብሏል። አቃቤ ሕግ ሀሰን የፍንዳታውን መንስኤ የሚያጣራ አንድ ቡድን በስፍራው እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ሱዳን በኢትዮጵያ ላይ ያቀረበችው ክስ
በጄነራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን የሚመራው የሱዳን መንግስት ከኢትዮጵያ ግዛት የተነሳ ድንበር ተሻጋሪ የድሮን ጥቃቶች ተፈጽሞብኛል ሲል ከሰሰ። የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ሰኞ ባወጣው መግለጫ ድርጊቱን "ግልጽ ወረራ" ሲል ገልጾታል። በጎረቤት ሀገራት በኩል የሚደረግ የውጭ ጣልቃ ገብነት ጦርነቱን እያባባሰው ነው ሲልም አስጠንቅቋል።
ሚኒስቴሩ በመግለጫው ባለፉት ሁለት ወራት በሱዳን የተለያዩ ስፍራዎች የተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች መነሻቸው "የኢትዮጵያ ግዛት" መሆኑ ይታወቅልኝ ብሏል። ሚኒስቴሩ ለዚህ "የጠብ አጫሪነት " ላለው ድርጊት አዲስ አበባን ያስጠነቀቀ ቢሆንም፣ ጥቃቱ በማን እንደተፈጸመና ያደረሰውን ጉዳት ግን በዝርዝር አለመገለጹን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
ሦስት ዓመት ሊሞላው በተቃረበው የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ኢትዮጵያ እጇን አስገብታለች ተብላ በይፋ ስትወቀስ ይህ የመጀመሪያው ነው።
በሌላ በኩል፣ ግጭቱ በውጭ ኃይሎች ድጋፍ እየተቀጣጠለ መሆኑ በዓለም አቀፍ መድረክ ስጋት ፈጥሯል። የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢቬት ኩፐር በቅርቡ በተካሄደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባ ላይ እንዳሉት፣ በሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ዘንድ "ድል እንቀዳጃለን" በሚል የተሳሳተ እምነት በመኖሩና ከውጭ ሀገራት ዘመናዊ መሣሪያዎች እየቀረቡላቸው በመሆኑ የተኩስ አቁም ላይ መድረስ አልተቻለም።
የግብፅ አምባሳደር ኢሃብ አዋድ በበኩላቸው፣ ስሟ ያልተጠቀሰ የሱዳን ጎረቤት ሀገር ታጣቂዎችን የምታሰለጥንበትና የምታስታጥቅበት ካምፕ መኖሩን የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ ብለዋል። በተያያዘም የዓለም አቀፉ የቀውስ ጥናት ቡድን ባወጣው መረጃ፣ የሱዳን ባለስልጣናት ፣የተባበሩት አረብ ኤምሬትቶች በኢትዮጵያ በኩል ለፈጥኖ ደራሹ ቡድን (RSF) መሣሪያዎችን እያቀረበች ነው ብለው መክሰሳቸውን ጠቁሟል።
እንደዚያም ሆኖ ግን ጄነራል አብዱል ፈታህ አል-ቡርሃን የሚመሩት የብሔራዊ ጦሩ በጎረቤት ሃገራት ላይ ጣቷን የምትቀስረውን ግብጽን ጨምሮ ከሳዑዲ አረቢያ እና የቱርክ ድጋፍ እንደሚያገኙ ዘገባው አመልክቷል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ቱርክ ጦርነቱን "አስከፊና ትርጉም የለሽ" ሲሉ ገልጸውታል። በጎርጎርሳዉያኑ 2025 ብቻ በርስ በርስ ግጭቱ የሚሞቱ ንጹሃን ቁጥር ከእጥፍ በላይ መጨመሩንም አስጠንቅቀዋል። ግጭቱ ወደ ጎረቤት ሀገራት ሊዛመት ይችላል በሚል ስጋትም ቻድ ከሱዳን ጋር ያለውን ድንበር መዝጋቷ ታውቋል።
ኢትዮጵያ ለቀረበባት ይፋዊ ክስ መልስ ስለመስጠቷ ዘገባው ያለው ነገር የለም። ከሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙኃንም ሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ የተሰጠ ምላሽ የለም።

በፍሎሪዳ ወደሚገኘው የትራምፕ መኖሪያ ቤት መሳሪያ ይዞ የገባ ግለሰብ መገደሉን የደህንነት መሥሪያ ቤቱ አስታወቀ
የአሜሪካ የደህንነት አገልግሎት ፍሎሪዳ ውስጥ በሚገኘው የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ቤት «ሊገባ ሞክሯል» ያለውን አንድ መሣሪያ የታጠቀ ግለሰብ ተኩሶ መግደሉን አስታወቀ። ሟች በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኝ ነው ተብሏል።
ግለሰቡ ወደ ዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት በሕገ ወጥ መንገድ ለመግባት በሞከረበት በዛሬው ዕለት ትራምፕና ባለቤታቸው በዋሽንግተን ዲሲ እንደነበሩ የደህንነት መሥሪያ ቤቱ አክሏል። የግለሰቡ ማንነትም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ይፋ አለመደረጉን የዘገበው አሶሽየትድ ፕረስ ነው። ይሁንና የሟች ቤተሰቦች ልጃቸው ከ2 ቀናት በፊት መሰወሩን ሪፖርት አድርገው እንደነበረ ዜናው አክሏል።
ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ ቀደም እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በሐምሌ13 ቀን 2024 በምረጡኝ ዘመቻ ላይ እያሉ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ነበረ። በዚያው ዓመት በመስከረም 15 ደግሞ በዌስትፓልም የባሕር ዳርቻ የጎልፍ ስፖርት በሚጫወቱበት ጊዜ ተመሳሳይ ሙከራ እንደተካሄደባቸውም ይታወቃል። የግድያ ሙከራ አድራጊው በዚህ ወር መጀመሪያ የዕድሜ ይፍታህ እስር ተፈርዶበታል።

4 months ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር መውጫ መንገድ ለመፈለግ የምታደርገውን ጥረት ቱርክ እንድትደግፍ ጠየቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጥያቄውን ያቀረቡት የቱርኩ ፕሬዚዳንት ራሲፕ ታይፕ ኤርዶኻን ለአንድ ቀን ጉብኝት ትናንት ማክሰኞ ወደ አዲስ አበባ በተጓዙበት ወቅት ነው።
ፕሬዝዳንት ኤርዶኻን በአዲስ አበባ በነበራቸው ቆይታ በዚሁ ጉዳይ ላይ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር መምከራቸው ተገልጿል። ፕሬዝደንት ኤርዶኻን በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር ሀገራቸው ኢትዮጵያ በምትገኝበት ክፍለ ዓለም «አዲስ ግጭቶች እና አዲስ ህመም እንዲጨምር እንደማትፈልግ» ገልጸዋል። ኤርዶኻን «የአፍሪካ ቀንድ የውጭ ኃይሎች መፋለሚያ» መሆን እንደሌለበትም በጋራ መግለጫ ንግግራቸው አሳስበዋል። የቱርኩ ፕሬዝደን የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው «ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት» ተናግረዋል።
ሁለቱ መሪዎች በቆይታቸው በአፍሪቃው ቀንድ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የተስማሙ ሲሆን በኃይል ዘርፍም ለመተባበር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ተገልጿል። ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት በሚል ከሶማሊላንድ ጋር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሟን ተከትሎ ከሶማሊያ ጋር የተፈጠረውን ውጥረት ቱርክ በጎርጎሪዮሳዊው 2024 ታኅሣስ ወር አሸማግላ ማርገቧ ይታወሳል። በሶማሊያ እና ኢትዮጵያ መካከል የተደረሰው ስምምነትም አዲስ አበባ አስተማማኝ የባሕር በርን በሶማሊያ በኩል የመጠቀምን እድል የሚያመቻች እንደሚሆን በወቅቱ ተገልጿል። በዚህ ጉዳይ ላይ የሚደረገው ውይይት እንደቀጠለ ነው።
ቱርክ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በአምራች እና ግንባታ ዘርፎች ላይ በመሰማራት ቀዳሚ ከሆኑ አራት የውጭ ሃገራት ተርታ ትሰለፋለች። ከኢኮኖሚ ትብብሩ ባለፈ አንካራ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ሚና በማስፋፋትም ስሟ ይነሳል።
ቱርክ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ተፈጥሮ የነበረውን እሰጥ አገባ ከማለዘብ ባሻገር በአባይ ወንዝ እና የባሕር በርን በተመለከቱ ቁልፍ ጉዳዮች ለአዲስ አበባ ድጋፏን ስትቸር ቆይታለች።

በጋሞ ዞን በተከሰተ ግጭት 15 ሰዎች ተገደሉ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በተቀሰቀሰ ግጭት 15 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎችና አካባቢውን የወከሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ገለጹ፡፡ ነዋሪዎቹና የምክር ቤት አባሉ እንዳሉት ሰዎቹ የተገደሉት ከትናንት በስቲያ እሑድ እና ትናንት ሰኞ በወረዳው ዛይሴ ወዘቃ እና ዛይሴ ደንብሌ በተባሉ ቀበሌያት በተቀሰቀሰ ግጭት ነው ፡፡
አንድ ለደኅንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የዛይሴ ደንብሌ ቀበሌ ነዋሪ ግጭቱ ከትናንት በስቲያ አሑድ 10 ሰዓት ላይ ተከስቶ እስከ ትናንት ሰኞ ቀትር ድረስ መቀጠሉን ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ በፖሊስ አጀብ ተሽከርካሪ ተጭነው በቀበሌው በማለፍ ላይ የነበሩ የጋሞ ዞን የፀጥታ አባላት «ድንጋይ ተወርውሮብናል» በሚል የወረወረውን ሰው ለመያዝ ወደ መንደሮች መግባታቸውን የጠቀሱት እኝሁ የቀበሌው ነዋሪ «የፀጥታ አባላቱ በየቤቱ መግባት መጀመራቸውን ተከትሎ ነው ግጭቱ የተነሳው። የፀጥታ አባላቱ በመንደሩ ላይ በከፈቱት ተኩስ ወላጅ አባታችንን ጨምሮ የአምስት ሰዎች ሕይወት አልፏል» ብለዋል፡፡
የዛይሴ የምርጫ ክልልን በመወከል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አብረሃም አሞሼ የፀጥታ አባላቱ በቀበሌያቱ ከፈቱት ባሉት ተኩስ በዛይሴ ወዘቃ ቀበሌ ሰባት እና በዛይሴ ደንብሌ ቀበሌ ደግሞ ስምንት ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።
ዶይቸ ቬለ ተከስቷል የተባለውን ግጭት አስመልክቶ ምላሽ ለማግኘት የጋሞ ዞን አስተዳደርንም ሆነ የዞኑን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊዎች ለማነጋገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ ይሁን እንጂ ከቀናት በፊት በተካሄደው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 5ተኛ ዓመት 6ተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ የሥራ ሪፖርት ያቀረቡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፤ የክልሉን የፀጥታ ጉዳይ በሪፖርታቸው ጠቅሰዋል። ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን በስም ባልጠቀሷቸው ነገር ግን በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች ባሏቸው ሥፍራዎች ላይ ከአደረጃጀት ጥያቄ፣ ከማንነት፣ ከሃይማኖት ጽንፈኛነት እና ከመሬት ወረራ ጋር በተያያዘ ግጭቶች መከሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
በግጭቶቹ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ «የተወሰኑ ግጭቶች በዕርቅ እንዲፈቱ ተደርጓል። በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ተዘርፈው የነበሩ ንብረቶችም ለባለቤቶቹ የመመለስ ሥራዎች የተከናወኑ ሲሆን ግጭት ጨማቂዎችም ለሕግ እንዲቀርቡ ተደርጓል» ብለዋል።

ዕውቁ ኤርትራዊ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር አስምሮም ለገሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
ፕሮፌሰር አስምሮም በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሞ የገዳ ስረዓት ላይ ባደረጉት ምርምር እና ለዓለም በማስተዋወቅ እንደሚታወቁ የሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ፕሮፌሰሩ በተለይ በ1960ዎቹ አጋማሽ የዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ስረዓት የሆነውን የኦሮሞ የገዳ ስረዓት ፣ ታሪክ ባህል እና ወግ በማጥናት ቀጥለው ለመጡ ተመራማሪዎች በር መክፈታቸው ይነገርላቸዋል።
በምርምራቸውም በርካታ መጽሃፍት እና ጥናታዊ ዘገባዎችን ማቅረባቸው የሚነገርላቸውን ፕሮፌሰር አስምሮም ለገሰ በ2010 ዓ/ም ለረዥም ዓመታት ካገለገሉት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተበርክቶላቸዋል።
ፕሮፌሰር አስምሮን ለገሰ ባለትዳር እና የሶስት ልጆች አባት ነበሩ ።

5 months ago
🇪🇬 የግብፅ ሃውልቶች አፍንጫ ምስጢር የታሪክ ሴራ ወይስ እምነት?
ታዋቂው ዩቲዩበር I Show Speed ግብፅን በጎበኘበት ወቅት የጠየቀው ጥያቄ አሁንም መነጋገሪያነቱ አልበረደም
ለምንድነው አብዛኞቹ የግብፅ ሃውልቶች አፍንጫቸው የተቆረጠው?
ለዚህ ጥያቄ የሚሰጡት መልሶች ከታሪክ፣ ከፖለቲካና ከዘር ማንነት ጋር የተያያዙ ናቸው።
1️⃣ "ጥቁርነታቸውን ለመደበቅ የተደረገ ሴራ"
ብዙ የታሪክ ተመራማሪዎችና የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ አጥኚዎች (Afrocentrists) እንደሚከራከሩት የሃውልቶቹ አፍንጫ እንዲሰበር የተደረገው የጥንት ግብፃውያን ጥቁር አፍሪካውያን መሆናቸውን ለመደበቅ ነው።
* የአፍንጫ ቅርጽ ምስክርነት፦
የአፍሪካውያን መለያ የሆነው ሰፋ ያለ አፍንጫ (Afroid features) በሃውልቶቹ ላይ በግልጽ ይታይ ነበር ይህንን የዘር ምልክት በማጥፋት ስልጣኔው የጥቁሮች አለመሆኑን ለማሳየት ሆን ተብሎ የተደረገ የጥፋት ስራ ነው ይላሉ።
* የፈርኦኖች የፀጉር አሠራር፦
የጥንት ፈርኦኖችና ንግሥቶች ምስል ሲታይ ፀጉራቸው ዛሬ በአፍሪካውያን ዘንድ እንደሚታየው ሹሩባ (Braids)፣ ቁንጮ (Locs) እና አፍሮ (Afro) ስታይል ነው ይህ የፀጉር አሠራር ከዛሬዎቹ ነጭ ግብፃውያን ይልቅ ከጥቁር አፍሪካውያን ባህል ጋር ቀጥታ ይገናኛል።
2️⃣ "አሁንም ድረስ ያሉት ጥቁር ግብፃውያን" 🇪🇬
የጥንት ግብፃውያን የዘር ግንድ ዛሬም አልጠፋም በደቡባዊ ግብፅ (በአስዋንና አካባቢው) የሚኖሩት ኑቢያውያን (Nubians) የጥንቶቹ ፈርኦኖች ቀጥተኛ ወራሾችና ጥቁር ቆዳ ያላቸው ግብፃውያን ናቸው ዛሬም ድረስ በግብፅ ውስጥ ጥቁር ቆዳ ያላቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኑቢያውያን መኖራቸው "ጥንታዊቷ ግብፅ የጥቁሮች አልነበረችም" የሚለውን የተሳሳተ ትርክት ውድቅ ያደርገዋል።
3️⃣ "የመንፈሳዊ ኃይል መግደያ"
(የምዕራባውያን ምሁራን እይታ)
በሌላ በኩል ደግሞ አርኪኦሎጂስቶች የሚከተለውን ምክንያት ያቀርባሉ
* ትንፋሽ መከልከል - ጥንታውያን ግብፃውያን ሃውልቶች "ካ" (Ka) የተባለ መንፈስ አላቸው ብለው ያምኑ ነበር።
የአንድን ሃውልት አፍንጫ መስበር ማለት መንፈሱ እንዳይተነፍስና ኃይል እንዳይኖረው ማድረግ እንደሆነ ይታመን ነበር።
* የፖለቲካ በቀል - አዳዲስ ነገሥታት የቀደሙትን ዝና ለማጥፋትና መንፈሳቸውን ለመግደል አፍንጫቸውን ያስሰብሩ ነበር።
የ"I Show Speed" ጥያቄ አለም በግብፅ ታሪክ ላይ የነበረውን የተዛባ አመለካከት እንዲመረምር በር ከፍቷል የፈርኦኖቹ የፀጉር አሠራር፣ የፊታቸው ቅርጽና ዛሬም ድረስ ያሉት ጥቁር ኑቢያውያን ምስክሮች ናቸው።
የግብፅ ስልጣኔ የአፍሪካውያን ስልጣኔ መሆኑንና አፍንጫዎቹ የተሰበሩትም ይህን እውነት ለመሸፈን ሊሆን እንደሚችል ብዙዎች ያምናሉ።
የእናንተስ አስተያየት ምንድነው?
ታሪኩን ለመቀየር የታቀደ የዘር ጥቃት ነው? ወይስ የጥንቶቹ ግብፃውያን መንፈሳዊ እምነት ውጤት?
አስተያየታችሁን በኮሜንት አጋሩን! 👇🏾🇪🇬 #egypt #blackhistory #nubia #ancientegypt #kemet #ishowspeed #africanhistory #ethiopia #amharic #ታሪክ #ጥቁር_ታሪክ #ኑቢያ

በዓመት ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያገኙ ቲክቶከር እና ዩቲዩበሮች "የንግድ ሥራ ገቢ ግብር" ሊከፍሉ ነው!
እንደ ቲክቶክ እና ዩቲዩብ ካሉ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች በዓመት ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ የሚያገኙ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች፤ እንቅስቃሴያቸው "በንግድ ሥራነት" ተቆጥሮ ግብር እንዲከፍሉ የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ ተዘጋጀ።
የገንዘብ ሚኒስቴር ያዘጋጀው ረቂቅ ደንብ፤ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች "ማስታወቂያዎች እና ስፖንሰርሺፖችን" ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች ያገኙትን "ሁሉንም የገቢ መጠን" የሚያሳይ "የሂሳብ መዝገብ" እንዲይዙ ያስገድዳል።ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂት ለማይባሉ ወጣቶች የገቢ ምንጭ በሆነው የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ ታክስ የሚጣልበት ሁኔታ በዝርዝር የተቀመጠው የገንዘብ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የገቢ ግብር ረቂቅ ደንብ ነው።
የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የገቢ ግብር ከፋይ ዝርዝር ውስጥ የገቡት ባለፈው ዓመት ሐምሌ 2017 ዓ.ም. በጸደቀው "የገቢ ግብር አዋጅ" ነው።አዲሱ ረቂቅ ሕግ፤ በአዋጁ ላይ የተቀመጡ ድንጋጌዎችን የተመለከቱ ዝርዝር ጉዳዮችን የያዘ ነው።ከአምስት ወራት በፊት የጸደቀው አዋጅ፤ ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ ገቢ የሚያገኝ "አንድ ግለሰብ ወይም ድርጅቶች" ግብር መክፈል እንዳለባቸው ደንግጓል።
'የዲጂታል ይዘት ፈጣሪ' በሚባለው ዝርዝር ውስጥ እንደ ዩትዩብ እና ቲክቶክ ያሉ "የቪዲዮ ማጋሪያ አገልግሎቶችን" እንዲሁም እንደ ፌስቡክ ያሉ "የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮችን" ተጠቅመው ገቢ የሚያገኙ ግለሰቦች ተጠቅሰዋል።
https://www.bbc.com/amhari... ቲክቶክ እና ዩቲዩብ ካሉ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች በዓመት ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ የሚያገኙ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች፤ እንቅስቃሴያቸው "በንግድ ሥራነት" ተቆጥሮ ግብር እንዲከፍሉ የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ ተዘጋጀ። የገንዘብ ሚኒስቴር ያዘጋጀው ረቂቅ ደንብ፤ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች "ማስታወቂያዎች እና ስፖንሰርሺፖችን" ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች ያገኙትን "ሁሉንም የገቢ መጠን" የሚያሳይ "የሂሳብ…

በደሴ ከተማ የቆሻሻ ማከማቻ ስፍራ ላይ በተከሰተ የመደርመስ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ፤ ሁለት ሰዎች ላይም ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የደሴ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ፅዳትና ዉበት ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀዉ ትናንት እኩለ ቀን ላይ የደረሰዉ የቆሻሻ ክምር መደርመስ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።
ከ20አመት በላይ በደሴ ከተማ ለሚወገድ ቆሻሻ የማቃጠያ ስፍራ ሆኖ የሚያገለግለዉ ደምበልቄ በዚህ መልኩ የመደርመስ አደጋ ሲያጋጥመዉ የመጀመሪያ ባይሆንም የሰዉ ህይወት ግን ከዚህ ቀደም እንዳልጠፋበት የገለፁት የአካባቢዉ ኖሪ አቶ ሀብታሙ ታደሰ ትናንት እኩለ ቀን ላይ የቆሻሻ ናዳዉ የተጫናቸዉን ሰዎች አስከሬን ለማዉጣት እስከ ዛሬ ድረስ ጥረት ብናደርግም አስከሬኑን ማዉጣት አልቻልንም ይላሉ።
የደሴ ከተማ አካባባ ጥበቃ ፅዳትና ዉበት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮናስ ሰይድ በበኩላቸዉ አስከሬን የመፈለግ ስራዉ ከአካባቢዉ መንግስት አቅም በላይ ሆኖል ማለታቸውን የደሴው ወኪላችን ኢሳያስ ገላው ዘግቧል።

6 months ago
አንቶንዮ ጉተረዥ ኢትዮጵያና ኤርትራ በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት አንዱ የሌላኛው የግዛት አንድነት እንዲያከብሩ አሳሰቡ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ጉተረዥ ኢትዮጵያና ኤርትራ በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት አንዱ የሌላኛው የግዛት አንድነት ለማክበር ቁርጠኝነታቸውን ዳግም እንዲያረጋግጡ አሳሰቡ። የዋና ጸሐፊው ቃል አቀባይ ስቲፋን ዱጃሪክ የስምምነቱን 25ኛ ዓመት አስመልክተው ባስተላለፉት የዋና ጸሐፊው መልዕክት ሁለቱም ሐገራት ዘላቂ ሰላምን በማምጣት ላይ ተግተው እንዲሰሩ ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች ከ7 አመታት በፊት ያደሱት ሰላማዊ ግንኙት ያወደሰው የጉተረዥ መልዕክት ይህም የውይይትና የትብብር ዋጋ የሚያሳይ ነው ብሏል። አያይዘውም በአልጀርስ ስምምነት ላይ የተካተተውን የዘላቂ ሰላም፣ ሉአላዊነት እና የግዛት አንድነትን ለማክበር ቁርጠኝነታቸውን ዳግም እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርበዋል

Comments