9 months ago
ታዋቂው ዩቲዩበር I Show Speed ግብፅን በጎበኘበት ወቅት የጠየቀው ጥያቄ አሁንም መነጋገሪያነቱ አልበረደም
ለምንድነው አብዛኞቹ የግብፅ ሃውልቶች አፍንጫቸው የተቆረጠው?
ለዚህ ጥያቄ የሚሰጡት መልሶች ከታሪክ፣ ከፖለቲካና ከዘር ማንነት ጋር የተያያዙ ናቸው።
1️⃣ "ጥቁርነታቸውን ለመደበቅ የተደረገ ሴራ"
ብዙ የታሪክ ተመራማሪዎችና የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ አጥኚዎች (Afrocentrists) እንደሚከራከሩት የሃውልቶቹ አፍንጫ እንዲሰበር የተደረገው የጥንት ግብፃውያን ጥቁር አፍሪካውያን መሆናቸውን ለመደበቅ ነው።
* የአፍንጫ ቅርጽ ምስክርነት፦
የአፍሪካውያን መለያ የሆነው ሰፋ ያለ አፍንጫ (Afroid features) በሃውልቶቹ ላይ በግልጽ ይታይ ነበር ይህንን የዘር ምልክት በማጥፋት ስልጣኔው የጥቁሮች አለመሆኑን ለማሳየት ሆን ተብሎ የተደረገ የጥፋት ስራ ነው ይላሉ።
* የፈርኦኖች የፀጉር አሠራር፦
የጥንት ፈርኦኖችና ንግሥቶች ምስል ሲታይ ፀጉራቸው ዛሬ በአፍሪካውያን ዘንድ እንደሚታየው ሹሩባ (Braids)፣ ቁንጮ (Locs) እና አፍሮ (Afro) ስታይል ነው ይህ የፀጉር አሠራር ከዛሬዎቹ ነጭ ግብፃውያን ይልቅ ከጥቁር አፍሪካውያን ባህል ጋር ቀጥታ ይገናኛል።
2️⃣ "አሁንም ድረስ ያሉት ጥቁር ግብፃውያን"
የጥንት ግብፃውያን የዘር ግንድ ዛሬም አልጠፋም በደቡባዊ ግብፅ (በአስዋንና አካባቢው) የሚኖሩት ኑቢያውያን (Nubians) የጥንቶቹ ፈርኦኖች ቀጥተኛ ወራሾችና ጥቁር ቆዳ ያላቸው ግብፃውያን ናቸው ዛሬም ድረስ በግብፅ ውስጥ ጥቁር ቆዳ ያላቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኑቢያውያን መኖራቸው "ጥንታዊቷ ግብፅ የጥቁሮች አልነበረችም" የሚለውን የተሳሳተ ትርክት ውድቅ ያደርገዋል።
3️⃣ "የመንፈሳዊ ኃይል መግደያ"
(የምዕራባውያን ምሁራን እይታ)
በሌላ በኩል ደግሞ አርኪኦሎጂስቶች የሚከተለውን ምክንያት ያቀርባሉ
* ትንፋሽ መከልከል - ጥንታውያን ግብፃውያን ሃውልቶች "ካ" (Ka) የተባለ መንፈስ አላቸው ብለው ያምኑ ነበር።
የአንድን ሃውልት አፍንጫ መስበር ማለት መንፈሱ እንዳይተነፍስና ኃይል እንዳይኖረው ማድረግ እንደሆነ ይታመን ነበር።
* የፖለቲካ በቀል - አዳዲስ ነገሥታት የቀደሙትን ዝና ለማጥፋትና መንፈሳቸውን ለመግደል አፍንጫቸውን ያስሰብሩ ነበር።
የ"I Show Speed" ጥያቄ አለም በግብፅ ታሪክ ላይ የነበረውን የተዛባ አመለካከት እንዲመረምር በር ከፍቷል የፈርኦኖቹ የፀጉር አሠራር፣ የፊታቸው ቅርጽና ዛሬም ድረስ ያሉት ጥቁር ኑቢያውያን ምስክሮች ናቸው።
የግብፅ ስልጣኔ የአፍሪካውያን ስልጣኔ መሆኑንና አፍንጫዎቹ የተሰበሩትም ይህን እውነት ለመሸፈን ሊሆን እንደሚችል ብዙዎች ያምናሉ።
የእናንተስ አስተያየት ምንድነው?
ታሪኩን ለመቀየር የታቀደ የዘር ጥቃት ነው? ወይስ የጥንቶቹ ግብፃውያን መንፈሳዊ እምነት ውጤት?
አስተያየታችሁን በኮሜንት አጋሩን! 👇🏾
9 months ago
ገናን በቅዱስ ላሊበላ፦ የታሪክ እና የመንፈሳዊነት ጥምረት
#ethiopia | ዘንድሮ የገና በዓልን በደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ለማክበር ዝግጅቱ ተጠናቋል። ይህ ታሪካዊ እና መንፈሳዊ ክስተት፣ የዓለምን ዓይን በሳቡት ድንቅ ውቅያዊ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል።
🌟 ለምእመናን እና ለጎብኝዎች የቀረበ ዝግጅት፦
ዝግጁነት፦ የከተማዋ ሆቴሎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎቶች እና የአየር በረራ አማራጮች እንግዶችን ለመቀበል በተሟላ ሁኔታ ዝግጁ ናቸው።
የአስጎብኝዎች ዝግጅት፦ አስጎብኝ ድርጅቶች ልዩ ልዩ የጉብኝት ፓኬጆችን በመቅረፅ ቱሪስቶችን በተጠንቀቅ በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።
ባህልና እውቀት፦ ውብ የሆኑ የባህል አልባሳት እንዲሁም በሊቃውንት የተዘጋጁ የታሪክ መጻሕፍት ለሽያጭ ቀርበዋል።
የነዋሪዎች አቀባበል፦ የላሊበላ ነዋሪዎች እንደተለመደው "እግር አጥበው" እንግዳ ለመቀበል በከፍተኛ ጉጉት ይጠባበቃሉ።
🗿 ላሊበላ፦ የጥቁር ህዝቦች ኩራት
ቤዛ ኩሉ እና ሌሎቹም አብያተ ክርስቲያናት አንዱ ከሌላው የማይመሳሰሉ፣ በዘመናዊ ኢንጂነሪንግ እንኳን ለመስራት ቀርቶ ለማሰብ የሚከብዱ ድንቆች ናቸው። ላሊበላ የኢትዮጵያ መመኪያ፣ የጥቁር ህዝቦች ኩራት እና ዘመን አይሽሬ አሻራችን ነው።
"እያንዳንዱ ድንጋይ የራሱ ዜማ፣ እያንዳንዱ ህንፃ የራሱ ታሪክ አለው።"
ኢትዮጵያዊውን እና ዓለም አቀፋዊውን ወንድማማችነት የምናጠናክርበት፣ በመንፈሳዊ በረከት የምንታደስበት ልዩ አጋጣሚ እንዳያመልጥዎ።
ላሊበላ እንገናኝ!
Let’s meet in Lalibela for Christmas. A must-see place that stays forever new in our hearts.
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #landoforigins #lalibelachristmas #visitethiopia #gennainlalibela #tourismethiopia #blackhistory #heritage

Comments