3 months ago
“በኢትዮጵያ የመሰረተ ልማት ግንባታ በእጅጉ ተደንቂያለሁ”
#ethiopia | በኢትዮጵያ ያለውን የመሰረተ ልማት ግንባታና የሕንጻ ጥበብ በመመልከት በጣም መደነቁን ታዋቂው የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ አይሾው ስፒድ ገለጸ።
የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ አይሾው ስፒድ ለ30 ቀናት በአፍሪካ የነበረውን ቆይታ በተመለከተ በሰጠው ቃለ መጠይቅ፤ በኢትዮጵያ ያየው የመሰረተ ልማት ግንባታ እጅግ አስገራሚ መሆኑን ገልጿል።
በጉዞው ካያቸው ሀገራት ሁሉ የኢትዮጵያ የሕንጻ ጥበብ ምርጡ መሆኑን ጠቅሶ፤ የሕንጻዎቹ ጥበብ የወደፊቱን ጊዜ ቀድሞ የተነበየና የራሱ የሆነ አፍሪካዊ ወይም ኢትዮጵያዊ ቅኝት እንዳለው አስረድቷል።
አዲስ አበባ ከተማን ያደመቁት ዘመናዊ ሕንጻዎችና ግዙፍ የዲጂታል ስክሪኖች ከተማዋን ልዩ እንዳደረጓት የገለጸው አይሾው ስፒድ፤ የሕንጻዎቹ አወቃቀር ከሌላው ዓለም የተለየና የሀገሪቱን ማንነት የሚገልጽ መሆኑን ተናግሯል።
ይህ ልዩ የሕንጻ ጥበብና ፈጣን የመሰረተ ልማት ዕድገት ለሀገሪቱ ገጽታ ግንባታ ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም በንግግሩ አመልክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #epa #ኢትዮጵያ #አይሾው_ስፒድ #መሰረተ_ልማት #ሕንጻ_ጥበብ #አዲስ_አበባ #ishowspeed

4 months ago
የአይሾው ስፒድ የጋና ጉብኝትና የሺአ ቅቤ ሙዚየሙ ድንገተኛ ስኬት
#fastmereja I ታዋቂው ዩቲዩበር አይሾው ስፒድ (IShowSpeed) በቅርቡ በጋና ያደረገውን ጉብኝት ተከትሎ፣ የሃማማት ሞንቲያ የሺአ ቅቤ ሙዚየም (Hamamat Montia Shea Butter Museum) እስከ መጋቢት 16 ቀን 2026 ድረስ ሙሉ በሙሉ መያዙ (Sold Out) ተነገረ።
ሙዚየሙ በአይሾው ስፒድ የቀጥታ ስርጭት ላይ ከታየ በኃላ በ24 ሰዓታት ውስጥ እስከ መጋቢት ወር ድረስ ያሉት ቀጠሮዎች በሙሉ ተይዘዋል። ስርጭቱ ከ50 ሚሊዮን በላይ ተመልካቾችን ትኩረት የሳበ ሲሆን፣ ይህም ለሙዚየሙ ዓለም አቀፍ እውቅናን አትርፎለታል።
የሙዚየሙ ባለቤት ሃማማት ሞንቲያ እንደገለጸችው፣ የስፒድ ጉብኝት ሙዚየሙ ታስቦ የማይታወቅ ከፍተኛ ታዋቂነት እንዲያገኝ ረድቶታል።
ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ፣ ይህ ዓይነቱ በነፃ የተገኘ ማስታወቂያ በተለመደው የግብይት መንገድ ቢሆን ኖሮ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ሊያስወጣ ይችል ነበር።

አይሾው ስፒድ (IShowSpeed) የጋና ፓስፖርት ሊሰጠው ነው
#fastmereja I ታዋቂው አሜሪካዊ የኢንተርኔት ሰው Darren Watkins Jr. (በተለዋጭ ስሙ አይሾው ስፒድ) በቅርቡ በጋና ባደረገው ጉብኝት ወቅት እናቱ ጋናዊት መሆኗን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ፣ የሀገሪቱ መንግስት የጋና ፓስፖርት እንዲሰጠው ወስኗል።
ስፒድ በጋና በነበረው ቆይታ እናቱ የጋና ተወላጅ መሆኗን ለተከታዮቹ ገልጿል። ይህም "ወደ ቤቴ ተመልሻለሁ" በማለት ደስታውን እንዲገልጽ አድርጎታል።
የጋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ሳሙኤል ኦኩዴቶ አብላክዋ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ስፒድ ለጋና በጎ ገጽታን በመገንባት ረገድ ያሳየው ተነሳሽነት የሚደነቅ በመሆኑ የጋና ፓስፖርት እንዲሰጠው ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ማጽደቁን አስታውቀዋል።
ሚኒስትሩ ስፒድን ለጋና "ተገቢ አምባሳደር" ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ በዲጂታል ሚዲያ ያለውን ግዙፍ ተፅዕኖ ለሀገሪቱ ገጽታ ግንባታ እንደሚጠቅም ገልጸዋል።
ስፒድ ይህንን ውሳኔ ያገኘው ኢትዮጵያን ጨምሮ 20 የአፍሪካ ሀገራትን ለ28 ቀናት በጎበኘበት "Speed Does Africa" በተሰኘው ታሪካዊ ጉዞው ማጠቃለያ ላይ ነው።
ይህ እርምጃ ጋና በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ትውልደ ጋናውያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የምታደርገው ጥረት አካል ተደርጎ ተወስዷል። ስፒድ በአሁኑ ወቅት በዩቲዩብ (YouTube) ብቻ ከ50 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት ሲሆን፣ የአፍሪካ ጉዞው በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት አግኝቶ ነበር።

5 months ago
iShowSpeed በአልጄሪያ ጥቃት ደረሰበት!
ታዋቂው የዩቲዩብ ስተሪመር iShowSpeed በአልጄሪያ ስታዲየም ውስጥ ባልተጠበቀ ሁኔታ የደጋፊዎች ቁጣ ሰለባ ሆኗል።
ደጋፊዎቹ በስፒድ ላይ የፕላስቲክ ጠርሙሶችን በመወርወር ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።
ምክንያቱ፦ በስታዲየሙ የነበሩ ደጋፊዎች መቀረጽ እንደማይፈልጉና በጉዳዩ ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ጥላቻ በመግለጻቸው ስፒድ ግራ መጋባቱን ተናግሯል።
ውሳኔው፦ ሁኔታው እየተባባሰ በመምጣቱ ስፒድ የቀጥታ ስርጭቱን (Stream) ወዲያውኑ ለማቋረጥ ተገዷል።
የስፒድ አስተያየት፦ ምንም እንኳን ስታዲየም ውስጥ ያጋጠመው ነገር ቢያሳዝነውም፣ በአልጄሪያ የነበረው አጠቃላይ ቆይታ ግን በጣም አስደሳችና የማይረሳ እንደነበር ገልጿል።

Sponsored by
Surafel
5 months ago
🇪🇬 የግብፅ ሃውልቶች አፍንጫ ምስጢር የታሪክ ሴራ ወይስ እምነት?
ታዋቂው ዩቲዩበር I Show Speed ግብፅን በጎበኘበት ወቅት የጠየቀው ጥያቄ አሁንም መነጋገሪያነቱ አልበረደም
ለምንድነው አብዛኞቹ የግብፅ ሃውልቶች አፍንጫቸው የተቆረጠው?
ለዚህ ጥያቄ የሚሰጡት መልሶች ከታሪክ፣ ከፖለቲካና ከዘር ማንነት ጋር የተያያዙ ናቸው።
1️⃣ "ጥቁርነታቸውን ለመደበቅ የተደረገ ሴራ"
ብዙ የታሪክ ተመራማሪዎችና የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ አጥኚዎች (Afrocentrists) እንደሚከራከሩት የሃውልቶቹ አፍንጫ እንዲሰበር የተደረገው የጥንት ግብፃውያን ጥቁር አፍሪካውያን መሆናቸውን ለመደበቅ ነው።
* የአፍንጫ ቅርጽ ምስክርነት፦
የአፍሪካውያን መለያ የሆነው ሰፋ ያለ አፍንጫ (Afroid features) በሃውልቶቹ ላይ በግልጽ ይታይ ነበር ይህንን የዘር ምልክት በማጥፋት ስልጣኔው የጥቁሮች አለመሆኑን ለማሳየት ሆን ተብሎ የተደረገ የጥፋት ስራ ነው ይላሉ።
* የፈርኦኖች የፀጉር አሠራር፦
የጥንት ፈርኦኖችና ንግሥቶች ምስል ሲታይ ፀጉራቸው ዛሬ በአፍሪካውያን ዘንድ እንደሚታየው ሹሩባ (Braids)፣ ቁንጮ (Locs) እና አፍሮ (Afro) ስታይል ነው ይህ የፀጉር አሠራር ከዛሬዎቹ ነጭ ግብፃውያን ይልቅ ከጥቁር አፍሪካውያን ባህል ጋር ቀጥታ ይገናኛል።
2️⃣ "አሁንም ድረስ ያሉት ጥቁር ግብፃውያን" 🇪🇬
የጥንት ግብፃውያን የዘር ግንድ ዛሬም አልጠፋም በደቡባዊ ግብፅ (በአስዋንና አካባቢው) የሚኖሩት ኑቢያውያን (Nubians) የጥንቶቹ ፈርኦኖች ቀጥተኛ ወራሾችና ጥቁር ቆዳ ያላቸው ግብፃውያን ናቸው ዛሬም ድረስ በግብፅ ውስጥ ጥቁር ቆዳ ያላቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኑቢያውያን መኖራቸው "ጥንታዊቷ ግብፅ የጥቁሮች አልነበረችም" የሚለውን የተሳሳተ ትርክት ውድቅ ያደርገዋል።
3️⃣ "የመንፈሳዊ ኃይል መግደያ"
(የምዕራባውያን ምሁራን እይታ)
በሌላ በኩል ደግሞ አርኪኦሎጂስቶች የሚከተለውን ምክንያት ያቀርባሉ
* ትንፋሽ መከልከል - ጥንታውያን ግብፃውያን ሃውልቶች "ካ" (Ka) የተባለ መንፈስ አላቸው ብለው ያምኑ ነበር።
የአንድን ሃውልት አፍንጫ መስበር ማለት መንፈሱ እንዳይተነፍስና ኃይል እንዳይኖረው ማድረግ እንደሆነ ይታመን ነበር።
* የፖለቲካ በቀል - አዳዲስ ነገሥታት የቀደሙትን ዝና ለማጥፋትና መንፈሳቸውን ለመግደል አፍንጫቸውን ያስሰብሩ ነበር።
የ"I Show Speed" ጥያቄ አለም በግብፅ ታሪክ ላይ የነበረውን የተዛባ አመለካከት እንዲመረምር በር ከፍቷል የፈርኦኖቹ የፀጉር አሠራር፣ የፊታቸው ቅርጽና ዛሬም ድረስ ያሉት ጥቁር ኑቢያውያን ምስክሮች ናቸው።
የግብፅ ስልጣኔ የአፍሪካውያን ስልጣኔ መሆኑንና አፍንጫዎቹ የተሰበሩትም ይህን እውነት ለመሸፈን ሊሆን እንደሚችል ብዙዎች ያምናሉ።
የእናንተስ አስተያየት ምንድነው?
ታሪኩን ለመቀየር የታቀደ የዘር ጥቃት ነው? ወይስ የጥንቶቹ ግብፃውያን መንፈሳዊ እምነት ውጤት?
አስተያየታችሁን በኮሜንት አጋሩን! 👇🏾🇪🇬 #egypt #blackhistory #nubia #ancientegypt #kemet #ishowspeed #africanhistory #ethiopia #amharic #ታሪክ #ጥቁር_ታሪክ #ኑቢያ

ስለ አይሾ ስፒድ (iShowSpeed) ታዋቂ የጥበቃ አባላት፣ ሄንሪ እና ሩዲገር መረጃዎች እነሆ፦
1. ሄንሪ (Henry) - "የዝምታው ጥንካሬ"
ሄንሪ በስፒድ ተከታታዮች ዘንድ እንደ "አለት" የሚታይ ጠባቂ ነው።
ባህሪው እጅግ ቁጥብ፣ ትኩረቱን የማይሰርቅና ሁልጊዜም በንቃት አካባቢውን የሚቃኝ ነው። ስፒድ በቪዲዮዎቹ ላይ ሊያሾፍበት ቢሞክርም ሄንሪ ከሙያዊ ስነ-ምግባሩ ዝንፍ አይልም። በኢትዮጵያ ቆይታው ስፒድ በገበያ ቦታዎችና በሰው መሃል ሲገባ፣ ሄንሪ የሰውን ማዕበል የመከላከልና ስፒድ ሳይገፋ መንገድ የማስከፈት ዋናውን ኃላፊነት ይወስዳል። ምንም እንኳን ዝምተኛ ቢሆንም፣ የራሱ የሆነ ትልቅ የደጋፊ ቁጥር በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አፍርቷል።
2. ሩዲገር (Rudiger) - "ተወዳጁ ግዙፍ"
ሩዲገር ከጥበቃነቱ ባለፈ የቪዲዮዎቹ አካል እስከመሆን ደርሷል።
ስሙ "ሩዲገር" የሚለው ስም የወጣለት ታዋቂውን የእግር ኳስ ተጫዋች አንቶኒዮ ሩዲገርን ስለሚመስል በስፒድ አማካኝነት የተሰጠው ቅጽል ስም ነው። ከሄንሪ በተለየ መልኩ ሩዲገር አልፎ አልፎ በቪዲዮዎች ላይ ፈገግ ሲል፣ ሲሳቅ ወይም ስፒድ የሚያደርጋቸውን አስገራሚ ነገሮች ሲታዘብ ይታያል። ይህም በተመልካቾች ዘንድ በጣም ተወዳጅ እንዲሆን አድርጎታል። እጅግ ግዙፍና አስፈሪ ቁመና ያለው ቢሆንም፣ ውስጡ ግን በጣም ደግና አስተዋይ እንደሆነ ይነገራል።

አይሾ ስፒድ በአዲስ አበባ ከዓለማችን "ፈጣኑ" ቤተሰብ ጋር የተደረገ ድንቅ ቆይታ
የአለማችንን ትኩረት በቪዲዮዎቹ መሳብ የቻለው አሜሪካዊው አይሾ ስፒድ (iShowSpeed) በኢትዮጵያ እያደረገ ባለው ጉብኝት፣ በታሪክ የማይረሳ አጋጣሚን አስተናግዷል። ስፒድ በተለያዩ አገራት በሚያደርጋቸው ጉዞዎች አስገራሚ ነገሮችን ማየትና ከታዋቂ ሰዎች ጋር መገናኘት ልማዱ ቢሆንም፣ በአዲስ አበባ ግን "ከፍጥነቱ" ጋር የሚመጥኑትን የዲባባ ቤተሰቦችን በማግኘቱ እጅግ እድለኛ ሆኗል።
አይሾ ስፒድ በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና በሩጫ ባለው ፍላጎት ይታወቃል። በኢትዮጵያ ቆይታው ደግሞ በኦሎምፒክና በዓለም አትሌቲክስ መድረኮች የወርቅ ታሪክ የጻፉትንና የዓለማችንን የፍጥነት ክብረ ወሰኖች በእጃቸው ያስገቡትን እነ ጥሩነሽ ዲባባንና እህቶቿን ማግኘቱ ልዩ ትርጉም ሰጥቶታል።
📌 "እድለኛው" ስፒድ
ብዙዎች ስፒድን "እድለኛ" የሚሉበት ምክንያት፣ የዲባባ ቤተሰቦች በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው ክብርና ዝና እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ነው። እነዚህ የሩጫ ንግሥቶች በውጭው ዓለም እንደ ታላቅ ተምሳሌት የሚታዩ በመሆናቸው፣ ስፒድ ከእነሱ ጋር ጊዜ ማሳለፉ ለተከታዮቹ ትልቅ አስገራሚ ክስተት ሆኗል።

ታዋቂው ዩቲዩበር ስፒድ (IShowSpeed) በአዲስ አበባ ከፍተኛ ትኩረት አገኘ!
ከ263,000 በላይ ሰዎች ጉብኝቱን በቀጥታ እየተከታተሉት ነው! 🇪🇹🎥
#ethiopia | ታዋቂው አሜሪካዊ ዩቲዩበር IShowSpeed (አይ ሾው ስፒድ) በአዲስ አበባ እያደረገ ያለው ጉብኝት በዓለም አቀፍ ደረጃ ትኩረትን ስቧል። በዩቲዩብ ቻናሉ እያስተላለፈ የሚገኘውን የቀጥታ ስርጭት (Live Stream) በዚህ ደቂቃ ከ263 ሺህ በላይ ዓለም አቀፍ ተመልካቾች እየተከታተሉት ይገኛሉ።
የ21 ዓመቱ ወጣት ዩቲዩበር በአጠቃላይ 20 የአፍሪካ ሀገራትን በመጎብኘት የአፍሪካን ባህል፣ ታሪክ እና መልካም ገጽታ ለዓለም ህዝብ ለማስተዋወቅ እየሰራ ይገኛል።
ተደራሽነት፡ ስፒድ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ከ150 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት በመሆኑ፣ የአዲስ አበባ ጉብኝቱ ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ትልቅ ማስተዋወቂያ እንደሚሆን ታምኖበታል።
አሁን በመስቀል አደባባይ አየተጠበቀ ነው።

ዓለም አቀፉ የዩቲዩብ ኮከብ አይሾው ስፒድ (IShowSpeed) በአዲስ አበባ፡ የዓድዋ መታሰቢያን በባዶ እግሩ ጎብኝቷል
ታዋቂው አሜሪካዊ የዩቲዩብ ኮከብ እና የቀጥታ ስርጭት አቅራቢ ዳረን ዋትኪንስ ጁኒየር (በቅፅል ስሙ አይሾው ስፒድ) በኢትዮጵያ እያደረገ ባለው ጉብኝት መላውን የኢንተርኔት ዓለም ትኩረት ስቧል።
ወጣቱ ኮከብ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችን እየጎበኘ የሚገኝ ሲሆን፣ የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ ለሚሊዮን ተከታዮቹ እያስተዋወቀ ይገኛል።
የ21 ዓመቱ አይሾው ስፒድ ወደ አዲስ አበባ ሲደርስ በቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
ይህ ጉብኝት "Speed Does Africa" በሚል መጠሪያ በ20 የአፍሪካ ሀገራት እያደረገ ያለው ሰፊ ጉዞ አካል ነው። ስፒድ በኬንያ በነበረው ቆይታ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ 300 ሺህ አዲስ ተከታዮችን ማግኘቱ የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን ላይ የዩቲዩብ ተከታዮቹ ቁጥር 48 ሚሊዮን ደርሷል።
ከጉብኝቱ እጅግ አስገራሚ ትዕይንቶች አንዱ ስፒድ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የዓድዋ ድል መታሰቢያን በባዶ እግሩ መጎብኘቱ ነው።
ለኢትዮጵያ ታሪክ ያለውን አክብሮት በገለጸበት በዚህ ቆይታው፣ በመታሰቢያው ውስጥ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶችን ሲመለከት የነበረውን ስሜት በቀጥታ ስርጭት (Live Stream) ለተከታዮቹ አጋርቷል። ስርጭቱን በአንድ ጊዜ ከ 191 ሺህ በላይ ሰዎች ሲከታተሉት ተመልክተናል።
በአትሌቲክስ ስሟ በገነነችው ኢትዮጵያ ከታዋቂ አትሌቶች ጋር ጊዜውን ያሳለፈው ስፒድ፣ "ኢትዮጵያ የፈጣን ሰዎች ሀገር መሆኗን አውቃለሁ" በማለት አድናቆቱን ገልጿል።
በቆይታውም፦
👉የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ ፍቅሩን ገልጿል፤
👉ባህላዊ ልብሶችን በመልበስና እስክስታ በመለማመድ ተሳታፊ ሆኗል፤
👉የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግቦች በተለይም 👉👉እንጀራን በመቅመስ ምስክርነቱን ሰጥቷል።
በማህበራዊ ሚዲያ ከ60 ሚሊዮን በላይ አጠቃላይ ተከታዮች ያሉት የዚህ ወጣት ጉብኝት ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ትልቅ ዕድል ተደርጎ ተወስዷል። የሀገሪቱን ገጽታ፣ እንግዳ ተቀባይነት እና ዘመናዊ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም ለወጣቱ ትውልድ በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
አይሾው ስፒድ በቀጣይ ቀናትም ሌሎች ታሪካዊ ቦታዎችንና የቱሪስት መስህቦችን እንደሚጎበኝ ይጠበቃል።

አሜሪካዊው ታዋቂ ዩቲዩበር አዲስ አበባ ገባ!
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ከ150 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያለው አሜሪካዊው ታዋቂ ዩቲዩበር አይ ሾው ስፒድ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡
የ21 ዓመቱ አሜሪካዊ ዳረን ጄሰን ዋትኪንስ ጁኒየር በ20 የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እያደረገ ሲሆን የአፍሪካን ባህል ታሪክ ለዓለም እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውሮ እየጎበኘ ይገኛል፡፡
ዩቲዩበሩ በአሁን ሰዓት በአዲስ አበባ እያደረገ ያለውን ጉብኝት IShowSpeed በተሰኘው የዩቲዩብ ገፁ በቀጥታ ስርጭት እያስተላለፈ የሚገኝ ሲሆን፤ ከ159 ሺህ በላይ ሰዎች የቀጥታ ስርጭቱን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡
በዩቲዩብ ስሙ አይ ሾው ስፒድ (IShowSpeed) በሚል የሚታወቀው ዳረን ጄሰን ዋትኪንስ ጁኒየር፤ በዓለም ላይ ታዋቂ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪ ሲሆን ከ150 ሚሊዮን በላይ ተከታዮችን ማፍራት ችሏል፡፡
seledadotio

Comments