Logo
YenetaTube
«ወደ ሥልጣን እንዲመለስ ከተባለዉ ዉሳኔ ጀርባ ያሉት ከ 100 የማይበልጡ ናቸዉ» ሳሞራ ዩኑስ

የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ ዩኑስ በትግራይ ክልል ህወሓትን ወደ ስልጣን ለመመለስ የተደረገዉን ውሳኔ አጥብቀዉ ተቃወሙ። በዚህ ሳምንት ከውጋሕት ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ "የቀድሞ አመራሮች እና ምክር ቤት (በትግራይ) ወደነበሩበት እንዲመለሱ መወሰኑ ህዝቡን ከልክ በላይ ጭንቀት ውስጥ ከቶታል „ብለዋል። ሳሞራ የህወሓት ነባር ታጋይና አባልም ነበሩ።

ሳሞራ አክለውም የትግራይ ህዝብ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የግል ንብረት ስላልሆነ በፓርቲው ታግቶ መቀመጥ የለበትም ሲሉም አክለዋል። ከጦርነቱ በፊት የነበረው የክልል ምክር ቤትና አስተዳደር «ወደ ሥልጣን እንዲመለስ ከተባለዉ ዉሳኔ ጀርባ ያሉት ከ 100 የማይበልጡ ናቸዉ፣ ውሳኔዉን ያሳለፉትም ከተጠያቂነት ለመዳን ያሰበ ዓላማን የያዘ ነዉ» ብለዉ እንደሚያስቡ ሳሞራ ዩንስ ተናግረዋል።

DW Amharic

17 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.