3 months ago
የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በጎግል 'AI' የፍለጋ አገልግሎት ተካተቱ!
#ethiopia | ግዙፍ ኩባንያ ጎግል የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የፍለጋ አገልግሎቱን በማዘመን፣ አማርኛንና አፋን ኦሮሞን ጨምሮ 13 የአፍሪካ ቋንቋዎችን ማካተቱን አስታወቀ። ይህ እርምጃ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ መረጃን በላቀ ጥራት እንዲያገኙ መንገድ የሚከፍት ነው።
በአዲሱ ዝመና ተጠቃሚዎች የሚከተሉትን አገልግሎቶች ማግኘት ይችላሉ፦
* AI Overviews፦ ስለፈለጉት ርዕሰ ጉዳይ አጭር፣ ግልጽ እና በማስረጃ የተደገፈ ማጠቃለያ በገዛ ቋንቋቸው ያገኛሉ።
* AI Mode፦ በጽሑፍ፣ በድምፅ ወይም በምስል ጥያቄዎችን በማቅረብ ጥልቅና ዝርዝር ምላሾችን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል።
የጎግል ደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ካቤሎ ማክዋኔ እንደገለጹት፣ ይህ ዝመና ቴክኖሎጂ በጥቂት ቋንቋዎች ብቻ ተወስኖ የሚፈጥረውን መገለል ለማስቀረትና አፍሪካውያን የዲጂታሉ ዓለም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ ነው።
ይህ በ 'ዋክሳል' (Vaxsal) ፕሮጀክት አማካኝነት የተገኘው ስኬት፤ ከአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ እና ሱማልኛ በተጨማሪ እንደ ስዋሂሊ፣ ዮሩባ እና ሃውሳ ያሉ ታዋቂ የአፍሪካ ቋንቋዎችንም ያካተተ ነው። ይህም የ AI ቴክኖሎጂን ለማኅበረሰባዊ ችግር መፍቻና ለፈጠራ ሥራዎች ለማዋል ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #viacapitalnews #googleai #amharic #afanoromo #technology #africatech #aioverviews #ethiopia #digitalinnovation

Comments